1ኛ ) ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም ሲሉ የሰጡት ቃለ መጠይቅ 2ኛ ) ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ ታህሳስ 5 ቀን 2018ዓም ወልቃይት በትግራይ ስር ነበረ ሲሉ የሰጡት ቃለ መጠይቅ ማሳሰቢያ፦ እነዚህን ሁለት የሚቃረኑ ቃለ መጠይቆችን አዳምጦና ለምን ብሎ መርምሮ መንስኤውን ማንም በቀላሉ ሊረዳ ይችላል፡፡ ቃለ መጠይቅ ቁጥር 1፦ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም የሰጡት የመጀመሪያው ቃለ መጠይቅ Online ምንጭ ፦ https://www.youtube.com/watch?v=N4jPUj_3FYI&t=1489s በዚህ ቪኦኤ ባቀረበው ቃለ መጠይቅ ውስጥ በ23ኛው ደቂቃ ላይ ራስ መንገሻ ስዩም “”እኔ ልጅ ሆኜ ሳድግም ሆነ በኋላ ትግራይን ሳስተዳድር ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም’’ ብለ እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም የሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው፡፡