ኢትዮጵያ ታሸነፍላች ፤ ህዝቧም ነፃነትን ይጎናፀፋሉ – ማላጂ

ኢትዮጵያ እንደአገር ራሷን ችላ ሉዓላዊነት በማስጠበቅ እና የህዝቧን ነጻነት (ተፈጥሯዊ እና ሠባዊነት) ለማስጠበቅ በሚደረግ ትንቅንቅ ከአንድ ክ/ዘመን ጀምሮ ደንቀራ እና ግርዶሽ በመሆን ከታሪካዊ የሩቅ ጠላቶች በላቀ ሁኔታ የዉስጥ ጥገኞች እና ምንደኞች ከጥንት አስከ ዛሬ ከፍተኛዉን አፍራሽ ሚና ይጫወታሉ ፡፡

ኢትዮጵያን ቅንቅን እንደበላዉ ዕንጨት ከዉስጥ እና ከዉጭ እየቦረቦሩ ዛሬም ተደላድለዉ በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላይ አዛዥ ናዛዥ መሆናቸዉን ሳንዘነጋ የታላቁን የኪነጥበብ ሠዉ ዮፍታሄ ንጉሴን “ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝነሽ ተላላ ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የሞተልሽ በላ ” ዞትር ስለ እኛም ሆነ ስለ አገር ስናስብ ማስታወስ አለብን ፡፡

ኢትዮጵያ ፣ አገር ፣ ኢትዮጵያዉያን ….. ስንል ታሪክን ወደ ኋላ ማወቅ ግድ ይላል ፡፡ ታሪክን የማያዉቅ ወደ ዉጊያ አይግባ እንዲሉ የድል ባለቤት እና የራስ መተማመን የሚያስገኘዉ በራስ እና ታሪክ መግባባት ሲኖር እና ሲኖር ብቻ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ የምታሸንፈዉም ሆነ ህዝቧ / ዜጎች መብታቸዉ ፣ ማንነታቸዉ እና የማይገሰስ ሙሉ ነፃነታቸዉ የሚረጋገጠዉ ስለነጻነት እየደጋገሙ እንደበቀቀን በሚያስተጋቡት ሳይሆን የኋላ በጎ ማንነት እና ታሪክ የተረዱ እና የሚረዱ በንቃት እና በህብረት ለራሳቸዉ ሲቆሙ ነዉ ፡፡

ለዘመናት ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማዳከም እና ለማክሰም ሌት ተቀን ሲሰራ ከነበር ኢትዮጵያን ለመታደግ መጠበቅ የዘመናችን የክፍለ ዘመኑ ድንቁርና ጫፍ እንደሆነ ሁላችንም ልንረዳ ይገባል ፡፡

በዘመኑ ቋንቋ ርግጥ ይህ ቅጭ ገዥዎች እና ለነርሱ ያደሩ ምንዱባን የሚጠቀሙበትን “ዓማራ” በማለት የሚጠሩትን ህዝብ ለዘመናት በማሳደድ እና በማስወገድ የሚጠቀሙበት አግላይ የበታችነት የወለደዉ ጥላቻ ጥላቻ በመዉለድ እና በማዋለድ ለዘመናት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከስሩ ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ዛሬም ያልገባን ዕልፍ ዐዕላፍ መሆናችንን መርሳት የለብንም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትህዴን በለቀቀው የጦር ኃይሉን የሚያሳይ ቪድዮ ዙሪያ አስተያየትዎ ምንድን ነው?

በዋናነት ትህነግ በ1968 .ም በትግል መመሪያ ጠላት ብሎ በግንባር ቀደም የፈረጀዉ ዓማራ ፣ ፅዮናዉያን እና ከበርቴ( ኢምፔራሊዝም) መሆኑን እያወቅን ከዚህ ኃይል ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚተሻሽ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን ለማስቀጠል በሚደረግ ተጋድሎ በጎ ነገር መሻት “ጅብን ስጋ እንዲያደርስ ”ከመላክ አይለይም ፡፡

ለዓመታት በኢትዮጵያዊነት ላይ በተለይም ዓማራ ላይ በተደረገ ስፍር ቁጥር የለሽ ግፍ እና ሰቆቃ በእያንዳንዱ ሠባዊ ፍጡር ፣ ኢትዮጵያዊ እና አገር ላይ የተገመደ አገር የማጥፋት ሴራ መሆኑን እያወቀ ለግል ዉዳሴ እና ጥቅም ምንቸገረኝ ካለ እና ዛሬም በዚህ ንግድ ትርፉን ከሚያሰላ ምንም ነገር ከመጠበቅ ወጥተን ለራስ እና ለአገር ዘብ መቆምን ወደድንም ጠላንም መቀበል ያለብን አሁን ነዉ ፡፡

ዛሬም ለዘመናት የተካሄደዉ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን የማዳከም እና የማክሰም ሴራ በሰም ካልሆነ በግብር ወደር የማይገኝለት የክፍለ ዘመናችን የክፋት እና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸዉ “ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸዉ የነበሩ ፍርደ ገምድል አድርባዮች ” ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስተምር ሲዳዳቸዉ መስማት በራሱ ምን ያህል በኢትዮጵያ ላይ ያላቸዉን ንቀት እና ጥላቻ አመላካች ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያን የሰጠን ዓምላክ ሆኖ ኢትዮጵያን የመሰረቷት ጀግኖች ቅድመ አያቶቻችን ሆኖ እያለ ለምን ፮ኛዉ ኢህዴግም ሆነ ስደተኛዉ ኢህአዴግ( ህወሀት እና ተባባሪዎች) ወይም ምዕራባዉያን እኛንም ሆነ ኢትዮጵያን አልሰሩም ፣አልሰጡንም ይልቅ አገር ለማፍረስ እና ህዝብ ከማስለቀስ በቀር ፡፡ አገር ሲፈርስ ሰፍቶ እና ተንሰራፍቶ ለመኖር ከሚመኝ የወዳጅ ጠላት እና አስመሳይነት አድርባይነት ልንጠበቅ ፣ልንጠበቅ እና በንቃት ልንቆም ይገባል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ ኢትዮጵያውያን ማህበረስብ በቤልጅግ በአምስተርዳም ከተማ ሕዝባዊ ስበስባ ጠራ

ዛሬ ኢትዮጵያ እና ዜጎች የከፈሉት እና እየከፈሉ ያሉት የዘመናችን ዉድቀት እና ሞት ዋጋ ትናንት እና በፊት በነበሩ ዘመናት በምንቸገረኝነት እና ምንአለበት የመጣ ስቃይ እና መከራ ነዉ “አበዉ ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ቆሞ ለማዉረድ ያስቸግራል እንዲሉ ” ይህ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚደረግ ሴራ ሲጎነጎን ነግ በእኔ አለማለት ኢትዮጵያዊነት ሊሆን አይችልም ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ እና ኅዝቧ ”

ማላጂ

1 Comment

  1. ወያኔ እንደ ዱቄት ብትበተንም፤ ግብአተ መሬትዋ ቢፈፅምም፣ ወያኔዊነት ግን ህገ መንግስቱ እስካለ የሚቀጥል ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share