አሜሪካን እየወጋችን ነዉ! (መኮንን ብሩ)

blinken
blinken

ለእናት ኢትዮጵያም ሆነ በዉስጧ ለሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች አሰቃቂ መጨረሻ ሊሆን የሚችል አርማጌዶናዊ ጉዞና የጉዞ መጨረሻ አልያም የጭሰኝነት ዘመን በርቀት መኖሩን በርካታዎች ያምናሉ። ይህ ጉዞ የሚጀመረዉ ከመቀሌ አልያም ከአክሱም ሳይሆን ከወልቃይት ነዉ። በአጭሩ የኢትዮጵያ አርማጌዶን ወይም የጭሰኝነት ዘመን የሚቀጣጠል ከሆነ መቀጣጠል የሚጀምረዉ በቀደሞዉ በጌምድር ግዛት በአሁኑ መጠሪያ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና ሑመራ የሚባለዉ የኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥ ነዉ። ለዚህም ነዉ የአረብ እና የምህራብ ሀገራት ጠላቶቻችን ይህን ግዛት ከአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ነጥቆ ሁሌም የእነሱን ጥቅም ሊያስጠብቅ ለቆመ ካልሆነም በኢትዮጵያ ምድር ፈንጂ ሊቀብርላቸዉ ለሚችል ትህነግ ለማስረከብ ያለ የሌለ ኃይላቸዉን እየተጠቀሙ ያሉት። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ትቀጥል ዘንድ የምንሻ ሁሉ ይህን ተረድተን የትግሉ አካል ለመሆን የመወሰኛዉ ጊዜ አሁን ነዉ።

ሀገር በዉቅያኖስ ላይ እንዳለች መርከብ በብዙ ማዕበል በየዘመኑ ትፈተናለች። እንደቸነፈርና ነዉጡም ክብደትና ቅለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሰምጣ ትጠፋለች፣ አልያም ተሰባብር ርዝራዥ ብቻ ትሆናለች፣ አልያም ሁሉን ተቋቁማ የዘመናት ጉዞዋን ትቀጥላለች። ስለዚህ ጥያቄዉ ከአባቶቻችን የተረከብናት ኢትዮጵያ የምትባል መርከባችንን ዓይናችን እያየ ትስመጥ ወይስ በደምና በአጥንታችንም መስዋዕትነትም ቢሆን አስቀጥለን ለልጆቻችን እናዉርስ ነዉ። ይህ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ሊሆን ይገባል።

ሳዉዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር በመወገን የየመንን ሁቲ ንቅናቄ ድምጥማጡን እያጠፋች ትገኛለች። ‘ሞት ለእስራኤል’ እና ‘ሞት ለአሜሪካ’ ብሎ  የተነሳዉ የየመን ሁቲ ንቅናቄ የቀድሞዉን የየመን መሪ ዓሊ አብደላ ሳለን መንግስት  አስወግዶ ወደ ስልጣን ሲቃረብ ወባ እንደያዘዉ የተንቀጠቀጡት አሜሪካኖች ነበሩ። ምክንያቱም አብደላ ሳላ በአሜሪካ በጭሰኝነት ያሽመደመዳት ሀገርን ነጥቆ ወደ ሂራን እና ራሺያ በመዞር ነፃነቱን እንደ ፍልስጥኤም የሚጠይቅን የየመን ሕዝብ የሚታገስ አሜሪካ የለምና የየመንን ሁቲ ንቅናቄ ዓመድ በማድረግ ሰበብ የመንን እያፈራረሰች ትገኛለች። በዚህ የየመን መፍረስና በዉቅያኖሱ ዉስጥ እየሰጠመች መሄድ ዋንኛዋ ማዕበል ፈጣሪ ሳዉዲ ዓረቢያ ብትመስልም የሁሉ አድራጊና ፈጣሪ ግን አሜሪካን ነች። አብይም እንደ ሁቲ ንቅናቄ አልተፈለገም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቾክ እጥረት ትምህርት ቤቶች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ

አሜሪካን ሂራንን ለማሽመድመድና እስራኤል ላይ ሊመጣ የሚችለዉን አርማጌዶናዊ የኒኩለር ቁጣ ለማኮላሸት በያዘችዉ የመቶ ዓመታት ዕቅድ ላይ በሂራን ጎን ሊቆሙ የሚችሉትን ሀገራት መበታተን ወይም ማስጠም ሲሆን ከእነዚህም ሀገራት መካከል የመን፣ ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ ራሺያ፣ እና ቱርክ ይገኙበታል። የኢትዮጵያ እና የትህነግ ጉዳይም እየተቃኘ ያለዉ በዚህ የእስራኤልንና የአሜሪካንን ጭሰኞች እና ጉዳይ አስፈፃሚዎች በመጠበቅ የራስን ዕልዉና የማረጋገጥ መርህ ዜማ ዉስጥ ነዉ። የጂዉሽ ወይም የእስራኤል ደም ያለዉም አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያት መንግስትን የቁም ስቃይ እያሳየ ያለዉም ለዚህ ነዉ።

አሜሪካን ከግብፅ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ለማንበርከክና ለማድቀቅ የበኩሏን ሚና የምትጫወትበት ዋናዉ ምክንያት የተዳከመች ኢትዮጵያ ለሂራን ለቱርክ እና ለራሺያ አጋር መሆን ቀርቶ ከመቶ ሚሊዮን በላይ የሚሆነዉን ሕዝቧን ባለመመገብ ተሽመድምዳ ትቀር ዘንድ ለመግታት ነዉ። ከተቻለም እንደ ሳዉዲ ዓረቢያ መንግስት በኢትዮጵያም የአሜሪካን ተላላኪ ሊሆን የሚችልን የትህነግ መንግስት አንግሶ ዘላለሟን የአሜሪካን እና እስራኤል ጭሰኛ አድርጎ ማስቀረት ነዉ።  ስለዚህ የአብይም መንግስት ይሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዓረብ እና ከምህራብ ሀገራት የተጋረጠበት አንድ እና አንድ አማራጭ  በግልፅ ሊያዉቀዉ ይገባል። ይህ አማራጭ ለአሜሪካም ይሁን ለእስራኤል ሕልዉና ወሳኝ በመሆኑ ሊመለስ የሚችለዉም በድርድር ሳይሆን በደም እና አጥንት ብቻ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያዉቀዉ ያስፈልጋል።

ዛሬ የመን እየነደደች ያለችዉ፣ ሊቢያ ያለመንግስት የቀረችዉ፣ ሱማሊያ የተሰነጣጠቀችዉ፣ ሶሪያ የተበተነችዉ፣ ኢራን በኢኮኖሚ ማዕቀብ እየተሰቃየች ያለችዉ፣ ቱርክ የአዉሮፓ ሕብረት አባልም ብትሆን እንደ ባይታዋር ማስጠንቀቂያ እና ፉከራ እያስተናገደች ያለችዉ ለዚሁ የአሜሪካና እስራኤል ዕልዉና እና የበላይነት አስጊ በመሆናቸዉ ነዉ። የአብይም መንግስት እንደነዚህ ሀገራት የጭሰኝነቱን ጥያቄ አልቀበል በማለቱ ጥርስ መነከስ ሳይሆን ጦር ተመዞበታል። ወያኔ ያቀናበረዉን እና ኢሕአዴግ መቶ በመቶ ያሸነፈበትን አምስተኛዉን ሀገራዊ  ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነበር በማለት አላግጠዉ በመሳለቅ መከራችንን ላለማየት የጨፈኑት አሜሪካኖች የሰሞኑን ምርጫ ሲያጣጥሉት ለሚሰማ ሁሉ ማንነታቸዉን ሊረዳ ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ

ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያዊያንም ምርጫችንን ልንወስን ይገባል። ሕዝብ የማይደግፈዉ መንግስት ተልፈስፍሶ የሌሎች ጭሰኛ መሆኑ አይቀርምና የተጋረጠብንን የሀገር ክብርና ነፃነት ማጣት አደጋ እጅ ለእጅ በመያያዝ ልናስጠብቀዉ ግድ ይላል።

ከዉጪ ጠላቶቻችን ጎን ለጎን በስመ አማራ ወይም አፍቃሪ አማራ ሽፋን ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚሰራጩት የኢትዮጵያ አንድነት ተዉሳክ ድምፆችም ኢትዮጵያን ቀን በቀን እየገዘገዙ ለአርማጌዶኑ አልያም ጭሰኝነት እያቀረቡን ቢሆንም በትግላችን ልናመክናቸዉ እንችላለን። አማራ የሚሉትን ኃይል ኦሮሙማ ከሚሉት የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ቢቻላቸዉ ለማፋለም ካልሆነም ለመለያየት በትጋት እየጣሩ ነዉ። የኦሮሞ ልዩ ኃይል ትህነግን ለመፋለም ራያ መግባቱን ከማድነቅ ይልቅ ‘ይህ ሕዝብ ኬኛ ልማዱ ነዉና አልወጣም እንዳይል’ ብሎ በዚህ ወቅት በሕዝብ ላይ ማላገጥ ታዳሚዉን ሊያስቅ የሚችል ትርኪምርኪ ሳይሆን ሀገር ላይ ከተጋረጠዉ የስዉር ደባ አካል መሆኑን በመረዳት ልናሸንፋቸዉ ግድ ይላል።

ወገን ሆይ …. አሜሪካኖች ካልተንበረከክንላቸዉ በቀር ፈፅሞ ፋታ ሊሰጡን አይችሉም። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ምክንያት የአፍሪካ ቀንድ ከጭሰኝነት በመላቀቅ የአሜሪካንን እና የእስራኤልን የጭሰኛ አሳዳሪነት ህልዉና ፈተና ዉስጥ ይገባ ዘንድ አይታገሱም። ይህ ማለት ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ነፃነት የሚወስድ አማራጭ መንገድ የለንም ማለት አይደለም። እንደ ሕዝብ የጀግኖች አባቶቻችን ልጆች መሆን ከወሰንን ኤርዶጋናዊ አልያም ፑቲናዊ የነፃነት መንገድ አሁንም አለን። ይህ መንገድ ትህነግን ከማንበርከክ ይጀምራል። ይህ መንገድ ከወልቃይት፣ ከጠገዴ፣ ከራያ እና ሑመራ ትህነግ አልባነት ይጀምራል። ለአሜሪካ እና አዉሮፓዊያን ዛቻና ኢኮኖነማዊ ማዕቀብ ሳይንበረከኩ በጋራ በመቆም ግድቡን ተባብሮ ከመጨረስ ይጀምራል።

አሜሪካ ከእኛ ይልቅ ትህነግን የመረጠችዉ ለራሷ ዕልዉና ስትል ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዊያንም ስለ ሀገር ክብርና ነፃነታችን ስንል የጊዚያዊ ልዩነቶቻችንን ወደጎን በመተዉ ከመንግስት፣ ከመከላከያ ሰራዊታችን ከአማራ ኃይሎች እና ከተለያዩ የክልል ኃይሎች ጋር በመተባበር ለክብራችን እንተባበር። አለበለዚያ ዕጣችን እንደ የመን መፈራረስ ወይም የአሜሪካ ጭሰኛ መሆን ነዉ። ይህን ደግሞ እኛ በፍፁም አንቀበልም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግራጫ አተያይ - ዶ/ር መኮንን ብሩ

ኢትዮጵያ ትቅደም።

ዶ/ር መኮንን ብሩ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share