May 25, 2023
6 mins read

ልባም የጥበብ ሰዎችን አደንቃለሁ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Tina Turner 1 1
#image_title
Tina Turner 1 1
#image_title

ልባም የጥበብ ሰዎች ከሆኑት የዓለማችን ምርጥ አርቲሥቶች አንዷ ቲና ተርነር ናት ። እጅግ ተመሥጠው ሙዚቃን ከሚጫወቱና ለሙዚቃ ከተሰጡ አርቲስቶች መካከልም አንዷ ናት ።

( በእኛም አገር  ነፍስ ሄር ፣ ሽሽግ ቸኮል ፣  ሜሪ አርምዴ   ኢዮኤል ዮሐንሥ ፣  አሰፋ አባተ ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ አሊ ቢራ ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ምኒሊክ ወስናቸውን ፣ ታምራትና ማዲንጎን በቅርብ ያረፈችውን ሂሩትን ደሞ ከብዙዬ እኩል ማሥታወስ እንችላለን ። … “በጥቂቱ መጥቀስ በብዙ መታማት ቢሆንም ቅሉ ። “)

 

ቲና ተርነር ደግሞ እጅግ ትለያለች ። አንድም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደናቂ በመሆኗ ሁለትም ወጣ ባለ የመድረክ አቀራረቧ ። በአንደ ወቅት በ1980 ዎቹ ( እኣአ) የመቶ ምርጥ አርቲስቶች ቁንጮ የተባለችም ነበረች ።

ቲና ተርነር የሙዚቃ ሥራዋን የጀመረችው ” ትንሾ አን ” በመባል እኤአ በ1957 ነው ።

1958 እና 1960 ዓ/ም ( GC) ላይ ደግሞ    ሙዚቃን  በቅጂ መልክ በማውጣት ተዋቂነቷን ሀ ብላ ጀምራለች ።

በመጀመሪያ ለዓለም ያሳወቃት የመድረክ ሥራዋ ” A Fool in Love ” የተሰኘው ነው ። ” የሞኝ ፍቅር ” በሉት ። ወይም ሞኝ ፍቅር ሲይዘው ። (  ሞኝ በፍቅር ሲያዝ ይታያችሁ ¡¡ )

ቲና ፣ እስከ 1976 እኤአ  “It’s Gonna Work Out Fine”, “River Deep – Mountain High”, “Proud Mary”, and “Nutbush City Limits የተሰኙ ዜማዎችን ለአድናቂዎቿ አበርክታለች ።

ቲና ፣  በአሥራዘጠኝ ሰማኒያዎቹ ፣   በከፍተኛ ግርማ  ወደ ሙዚቃ ዓለም  ብቅ ያለችበት ወቅት ነው ። በ 1984 ዓ/ም እኣአ የግራሚ አዋርድ ተሸላሚ የሆነውን ዜማዋን ,what’s love got to do  ጨምሮ ሌሎች ቁንጮ የሶሎ ፤ የሮክ ና ሮል  ንግሥት የተባለችባቸውን ሙዚቃዎችን ያበረከተችሁ በ 1980 ዎቹ ነው ። በከፍተኛ ደረጃ በዓለም ላይ ዝነኛና ታዋቂ  ለመሆን የቻለችው በእነዚህ አሥርት  ዓመታት ነው ።

ቲና ተርነር በሥራዎቿ ፣ አያሌ ሽልማት ያገኘች ሲሆን  ፣ ከተለያዩ ተዋቂ እና ሥመ ጥር ሸላሚ ድርጅቶች  ልዩ ፣ ልዩ  ሽልማቶችና የክብር ማአረጎችንም አግኝታለች ።

ቲና ተርነር በ83 ዓመቷ ግንቦት 16 / 2015 ዓ/ም (  እኣአ ) ፣ ከረዢም ጊዜ ህመሟ አርፋለች ። ዝነኛዋና ድምፀ መረዋዋ ቲና ተርነር   ከዚህ ዓለም በሥጋ ከነገ አፈረ ሰው  ብትለይም  በሥራዋ ግን እሥከዓለም ፍፃሚ በመጪው ትውልድ ሁሉ ሥሞ መጠራቱና ሙዚቃዋ መሠማቱ አይቀርም   ።

በእኛ አገር እንኳ ከ1997  ዓ/ም ምርጫ ጋር ተያይዞ በአና ጎሜዝ ( የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ኃላፊ ) እና   በቅንጅት አመራር በነበሩት በፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ ዙሪያ ፣ ይኽ ዘፈን በሥም ማጠልሸት ተነሥቶ ነበር ።  አቶ መለሥ ፖለቲካዊ ትርፍ   ለማግኘት ( በቅንጅት ላይ ነጥብ ለማስቆጠር ) ” የቲና ተርነርን ,what’s love got to do ? … ” ዘፈንን ፣ እንደ ምሳሌ በንግግራቸው ጣልቃ በማስገባት  በፕሮፊሰሩ ላይ   በአደባባይ የሥም ማጥፋት ንግግር አድርገው እንደነበር ይታወሳል    ። …

ቀፅሑፊ መጨረሻ  ግጥሙን ለእናንተ  ለአንባቢያን ሳቀርብ የግጥሙን ጥንካሬ እና ከፍቅር እና ከመውደድ አንፃር ፣  ግልፅ  የሆነ   ጠንካራ መልዕክቱን እንድትረዱ በማለት ነው ።

” በግልፅ እኔ ና አንቺ … አልተወያየንም …ፍቅር ባሥተርጓሚ … በመልዕክት አይሆንም ። ..” የሚል ዘፈን እኛም አለን  ።  ምኒልክ ወስናቸው  የተጫወተው ። ምኒልክ በአጃቢ ታግዞ  በደመቀ መልኩ በመድረክ ላይ አዚሞታል ። የግጥምና የዜማ ደራሲው (…) ይደነቃሉ (…)   ። …

እንካችሁ የቲና ተርነርን

WHAT’S LOVE GOT TO DO ?

you must understand though

the touch of your hand

makes my pulse react

what’s love got to do ?

that it’sonly the thrill of boy        meeting girl opposite attract

It’s physical

Only logical

You must tray to ignore

That it means more than that .

Ooh,what’s love got to do

Got to do with it ?

What’s love but a second – hand emotion .

Who needs a heart

When a  heart can be broken ?

It may seem to you

That I am acting confused

When you’re close to me .

If I Tend to look dazed

I have read it someplace

I’ve got cause to be

There’s name for it

There’s a phrase that fits

But whatever the reason

You do it for me .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182911
Previous Story

የቦንብ ፍንዳታ በባህር ዳር /የርስ በርስ ግጭት የየደረሰው ገዳት /ብሄርተኝነታቸው ወደ አምልኮነት(አሻራ ዜና

balezemenu 1 1
Next Story

ግማሽ ጎፈሬ ግማሽ ልጬ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር ፕሮጀክት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop