August 6, 2024
4 mins read

አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አስገኘች

አትሌት ፅጌ ዱጉማ
454309311 886587770167778 1682362902833604793 nፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በ800 ሜትር በታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አስገኘች
በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
የፅጌ ታሪክ በጥቂቱ
454314211 893623252812777 7820976665916689492 n” አባቷን አታውቃቸውም፤ ገና በአንድ ዓመቷ ነው ያረፉት ከቤተሰቦቿ ሰባት ልጆች የመጨረሻዋ እሷ ነች አንድ ወንድም ብቻ ነው ያላት፤ ስድስቱ ሴቶች ናቸው በልጅነቷ አትሌቲክስ፣ እግር ኳስና ሌሎች ስፖርቶችን ታዘወትር ነበር በባዶ እግሯ መሮጥ ጀመረች፤ ትምህርት ቤት ስትሄድም በሩጫ ሆነ ወደደችው።
ብቸኛ ወንድሟ በሩጫው እንድትገፋ ያበረታታት ነበር ለትምህርት ቤት፣ ለወረዳ፣ ለዞንና ለክልል በአጭር ርቀቶች መሳተፍ ጀመረች ሁሉም እህቶቿ ትዳር መስርተው ከቤት ስለወጡ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር ወንድሟ አቅሟን ተመልክቶ አካዳሚ እንድትገባ ገፋፋት፤ እሷ ግን እናቴን ትቼ አልሄድም አለች ካልሄድሽማ እንጣላለን ብሎ አስጠነቀቃት በመጨረሻ ተስማማችና የትውልድ ቀዬዋን ለቀቀች።
አሰላ ጥሩነሽ ዲባባ ማዕከል የመግባት እድል አገኘች፤ የ100 እና 200 ሜትር ሯጭ ሆና አካዳሚውን ተቀላቀለች። ከሰባት አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገርን የመወከል እድል አገኘች በአፍሪካ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና በ200 ሜትር አልጄሪያ ላይ ተወዳደረች፤ የብር ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች ለአምስት አመት ያህል ከ100 እስከ 400 ሜትር ሮጠች ከባለፈው አንድ አመት ጀምሮ 800 ሜትር ላይ አተኮረች የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ሆነች አምና ቤልጂየም ላይ ለአለም ሻምፒዮና የሚያበቃት ሚኒማ አመጣች የዶፒንግ ምርመራ ወቅት በማለፉ ግን በቡዳፔስቱ የአለም ሻምፒዮና ሳትሳተፍ ቀረች በዚህ አመት በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ800 ሜትር አሸነፈች በአፍሪካ ሻምፒዮናም በተመሳሳይ ወርቅ አጠለቀች በኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሯን ወከለች ሁለቱን ማጣሪያዎች በብቃት አልፋ ለፍፃሜው በቃች።
እናም ዛሬ ምሽት…!
\የአቶ ዱጉማ ገመቹና የወይዘሮ ሜታ ሙለታ የመጨረሻ ልጅ የሆነችው፥ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሽ ተነስታ ፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ የተገኘችው፥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቷ፥ የ23 አመቷ ፅጌ ዱጉማ አዲስ ታሪክ ፅፋለች፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የሴቶች 800 ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ሀገሯን ከፍ አድርጋለች፤ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ርቀት ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ውስጥ ገብታለች፤ የራሷን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች፤ 1:57:15፥
(አበባየሁ ተመስገን)
192876
Previous Story

” የዐቢይ አህመድ ተሿሚ ሆኜ ሕዝቡን በመበደሌ ከልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ::”ገዱ አንዳርጋቸው

192896
Next Story

የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ | የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

192896

የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ | የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

https://youtu.be/GMjaXoaAvho?si=JHLNavMjxMse3KFg https://youtu.be/zsnYsJHwmfg?si=MZnzCl3JpShe5ByK የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | የአማራ
Economic Consequences of Ethiopian Birr Devaluation in Foreign Markets

የምን መነሻ! የምን መድረሻ!

አንዱ ዓለም ተፈራ አርብ፣ ሐምሌ ፳ ፮ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ፮ ዓ. ም. (8/2/2024) በማንኛውም