ይህ ፎቶግራፍ ብዙ ይናገራል (መሳይ መኮነን)

217546604 4192523210793289 8875349646090261988 n
217546604 4192523210793289 8875349646090261988 n

ከክምር ቃላት በላይ ጠለቅ ያለ መልዕክት አዝሏል። አንዳንድ ፎቶግራፎች ታሪክን ይቀይራሉ። የአሜሪካ ቬትናም ጦርነት ላይ የአንዲት የዘጠኝ ዓመት ልጅ ፎቶግራፍ ዓለምን አስደንግጧል። በአሜሪካን ትላልቅ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሶ ጦርነቱ እንዲቆም የዚያች ልጅ ፎቶግራፍ ሚናው ከፍተኛ እንደነበረ ይነገራል። ራቁቷን ከጦርነት መሀል እያለቀሰች የምትታየው ቬትናማዊት ልጅ ፎቶግራፍ ዓለም ዓቀፉን የፑልቲዘር ሽልማትን ተቀዳጅቷል። ፎቶግራፉ ከሺህ መጻህፍት፡ ከአያሌ ፊልሞች በላይ ስለቬትናሙ ጦርነት ታሪክን እየነገረ በታሪክ ወደፊትም ይኖራል።

ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሰኞ ዕትሙ ህወሀትን ለማጀገን በሚል ይዞ የወጣው ፎግራፍም እንደቬትናማዊቷ ህጻን ፎቶግራፍ ታሪክ መቀየር የሚችል መሆን አለበት። ፎቶግራፉ የህወሀትን የክፋት ጥግ በማሳየት ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ምድር ምን እየተደረገ እንዳለ እንዲያውቀው የማድረግ ግዙፍ ሃይል አለው ብዬ አምናለሁ። በእርግጥ ኒውዮርክ ታይምስ የህወሀትን ‘አይበገሬነት’፡ ‘ህዝባዊነት’ ያሳያል ያለው ፎቶግራፍ ከታሰበለት መልዕክት ይልቅ የህወሀትን ጉድ ያጋለጠ ሆኖ ለዓለም ቀርቧል። ዕድሜአቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናት ለጦርነት እየተማገዱ መሆኑን ፎቶግራፉ ምስክር ሆኖ ይታያል። ህወሀት አከርካሪው ተሰብሮ ወደ ቆላ ተምቤን ከመውረዱ በፊት ጀምሮ ህጻናት ወታደሮች በከፍተኛ ቁጥር መልምሎ በለብለብ ስልጠና ለጦርነት ሲማግድ ቆይቷል። ይህ ዓለም ዓቀፍ ወንጀል በመሆኑ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም።
እንደህወሀት የትግራይን ህዝብ ስቃይ መከራ የጋተ አገዛዝ የለም። ከፍጥረቱ ጀምሮ የትግራይን ህዝብ ለእኩይና ሴጣናዊ ዓላማው ሲገድል፣ ሲያስገድል ኖሯል። አሁንም እያንቋረረ፣ ሞቱን በቅርብ እያየ የትግራይ ህዝብ ላይ ታላቁን እልቂት አውጆ እየተንቀሳቀሰ ነው። በረሃ እያለ ህዝቡን እንደአልቂት ተጣብቆት በረሃብና በጦርነት ሲቆላው እንደነበር ቅን የትግራይ ልጆች የሚመሰክሩት ሀቅ ነው። ስልጣን ላይ ወጥቶ በቆየባቸው 27ዓመታት በስሙ እየማለ፣ ጥቂቶችን የሀብት ጋራ ላይ እንዲወጡና የአንድ መንደር ስረወ መንግስት እንዲተከል አድርጓል። በእነዚህ ዓመታት የትግራይን ህዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ወገኑ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ በማድረግ የጥላቻ ግድግዳ ሲያቆም ነው የከረመው። ይኸው ያ ጦስ ሁለቱንም ወገኖች ዋጋ ማስከፈል ጀምሯል። በፎቶግራፉ ላይ የሚይታየው ትዕይንት የሚያረጋግጥልን ህወሀት በመጪው ትውልድ ላይ ቂምና ጥላቻ ለማቆየት እየሄደ ያለበትን ርቀት ነው።
ይህ ፎግራፍ ከወጣ በኋላ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፡ የህጻናት መብት ላይ የሚሰሩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት፡ ለሰው ልጅ እንቆረቆራለን የሚሉ እጅ ጠምዛዥ መንግስታት አንድ ነገር ይላሉ ብዬ ጠብቄ ነበር። ልብ ያላቸው፡ ትንሹ ፈጣሪ ለሆነው ህሊናቸው የተገዙ ጥቂት የትግራይ ምሁራን ከፎቶግራፉ በኋላ እንኳን የህወሀትን የእብደት አካሄድ በግልጽ ለማውገዝ ወደ አደባባይ ይወጣሉ የሚል ግምት ነበረኝ።
>በእርግጥ ፎቶግራፉ ከወጣ 24 ሰዓት ስላልሞላው ቸኩዬ ሊሆን ይችላል። ዓለም ይህን ድርጊት ካላወገዘው፡ እንደእርጎ ዝንብ በሰው ሀገር ጥልቅ እያሉ የሚፈተፍቱ ሀገራት ህወሀትን ተው ካላሉት ስለሰው ልጅ መብት ለመከራከር ሞራል ሊኖራቸው አይገባም። ከዚህ በላይ ወንጀል ምን አለ?
የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ፎቶግራፍ ይዞ የዲፕሎማሲ ዘመቻ መክፈት አለበት። ሳይታሰብ ድንገት የተገኘ ማስረጃ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ጩኸቱ ለምን እንደነበረ ይህ ፎቶግራፍ የሚነግረን ነገር አለ። ይህን መጠቀም ይገባል። በገዛ እጃቸው ትልቅ ዶክመንት ሰጥተዋልና

2 Comments

  1. ለስብሀት ነጋ ህይወት ብሎ የትግሬን ህጻን የሚይስፈጅ ሀይል አጋንንት ካልሆነ ምን ይባላል? የነሱ ልጆች ምርጥ የሆነ ትምህርት ቤት ይማራሉ ምርጥ በሆነ መኪና ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ እንደሚመስለኝ ትግሬ ማለት አድዋ ነው ማለት ነው።

  2. Evidence also reveals that Amhara militias raped the sisters, mothers, aunties and 90-year-old grandmas in front these children. Evidence also reveals that Amhara militias killed all male Tigrayans over the age of six in front of these children. These children luckily survived Amhara massacre and fled to the mountains to save their lives. For these children, even if it is true that they carry guns, it is a matter of survival, do or die situation.

    ያንተዉ አማራ ሚሊሻ የአራት ዓመት እህቱን፤ እናቱን፤ አክስቱንና የዘጠና ዓመት ሴት አያቱን ዐይኑ እያየ ስደፍሩ ምን ያድርግ የትግሬ ወንድን ለማጥፋት የተሰማራዉ ያንተዉ አማራ ሚሊሻ ከስምንት እስከ ዘጠና ስምንት ዓመት የሆነዉን ወንድ ሁሉ ሰፈጅ አይቶ ቢያመልጥና ተገዶ ራሱን ለማዳን ጠመንጃ ይዞ ጫካ ቢገባ ራስን መከላከል ይባላል እንጂ ህፃን ን በጦርነት መማግድ አይባልም። ለዚህ ሁሉ ነገር ዋና ተጠያቂዉ አማራ ነዉ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.