የሕወሃት ወደ አፋር የመሄድ ሚስጥር #ግርማካሳ

የሕወሃት ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል ዞን አራት በመግባት ወረራ አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ወገኖች የጅቡቲን መስመር በመያዝ አዲስ አበባ ያለውን የአብይ አህመድ አስተዳደር በማናቅ የሚፈልጉትን ለማግኘት ትልቅ የመደራደሪያ ጉልበት እንዲኖራቸው ነው ያንን ያደረጉት የሚል ግምት ያላቸው አሉ፡፡
በዚህ አስተያየት አልስማማም። ሕወሃቶች ወደ አፋር ዞን 4 የዘለቁት ከጅቡቲ የሚመጣውን መስመር ለመዝጋት ሳይሆን በሌላ ምክ ያት ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡a

219211655 10225577363891692 1787175553970656311 n

የሕወሃት ጦር እየተመራ ያለው ረጅም የሚሊተሪ ሳይንስ እውቀት ባለቸው የቀድሞ የኤታ ማጆር ሹም በነበሩት ሚሊተሪ ስትራቲጁስት፣ ጀነራል ጻድቃን ገብረ እግዚባሄር ነው፡፡ ጀነራል ጻድቃን እብድ አይደሉም። የጅቡቱን መስመር ለመያዝ ታጣቂዎችን የሚያሰማሩት፡፡ ለዚህም አምስት ምክንያቶች ላስቀምጥ፡
አንደኛ ከጅቡቱ የሚወጣውና የሚገባው በዋናነት በባቡር ነው። በባቡር ጅቡቲ እስከ ድሬዳው፣ ከዚያ አዋሽ እያለ ወደ መሐል አገር ይመጣል። የጭነት መኪናዎች ከጅቡቲ፣ በዮቦኪና ገላፊ አድርገው የቀድሞዉ አሰብን ከአዋሽ ያገናኝ የነበረውን መንገድ በመያዝ በሃዩ፣ ሰመራ፣ ሚሌ ፣ ገዋኔ አድርገው ወደ አዋሽ፣ የተወሰኑትን ደግሞ በባቲ አድርገው ወደ ደሴ ይጓዛሉ። ወያኔዎች መንገድ ከዘጉ ሊዘጉ የሚችሉት ይሄንን መስመር ነው።

219267362 10225576985362229 1017329274679709235 n
ይሄ መንገድ ቢዘጋ የባቡር አገልግሎት በተጨማሪ የጭነት መኪናዎች በሶማሌ ላንድ በሉል በሳይላክ፣ ካቡልቀድር፣ ቦራማ፣ ቶጎ ቻሌን ጅጂጋ አድርገው ወደ ድሬዳዋ፣ አዋሽ መሰማራት ይችላሉ። ችግር ቢፈጥርም ያንን ያህል የሚያንቅ እርምጃአ አይሆንም፡፡
ሁለተኛ ከላይ የተጠቀሰውን በሰመራ በኩል የጅቡቲ አዋሽ መስመር ወያኔ ለመዝጋት ከፈለገች፣ የሚቀርባት ሰመራን መያዝ ነው። አሁን የወያኔ ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀሱበት ከራያ አካባቢ ሰመራ በመንገድ ለመሄድ ቆቦን፣ ወልዲያን አልፎ ወደ ደቡብ ምስራቅ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል። እነ ወልዲያን የመቆጣጠር እድሉ ደግሞ በጣም የመነመነ ነው። እንደዚያም ሆኖ ወልዲያን መያዛ ቻሉ ብንል እንኳ፣ ከወልዲያም በኋላ ለመሄድ ብዝ ረቀት ነው ያለው። ቀጥታ አቋራጭ ይዞ ለመንቀሳቀስ ደግሞ ቢያንስ ወደ 100 ኪሎሜተር የሕወሃት ታጣቂዎች መጓዝ ይኖርባቸዋል። በከፍተኛ ሙቀት፣ ዉሃ በቀላሉ በማይገኝበት፣ እንኳን ኪሎሜትሮች ለቀናት ሊጓዙ ለሰዓታት እንደ እሳት የሚቃጥለውን የአፍር መሬት ተቋቁመው ሰመራ መድረስ የመቻላቸው እድል እጅግ በጣም የመነመነ ነው።
ሶስተኛ ሕወሃቶች ሽንፈት ገጥሟቸው ወደ ኋላ ማፈግፈግ ከሞከሩ ፣ ከቤዛቸው ከትግራይ እጅግ በጣም ስለራቁ ከማለቅ ወይንም እጅ ከመስጠት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ግምገማ

አራተኛ ከአላማጣ ወደ ደቡብ ምስራቅ ሲኬድ፣ ከደጋውና ወይናደጋው ወደ ቆላው ነው የሚኬደው። ሜዳ ነው። የሕወሃት ታጣቂዎች ለአየርና ለሂሌኮፕተር ጥቃት የተጋለጡ ነው የሚሆኑት።

አምስተኛ እነ ሰመራን ለመያዝ ሕወሃቶች ከተንቀሳቀሱ ዶር አብይ አህመድ በርሱ ላይ፣ በስልጣኑ ላይ እንደመጡ ስለሚቆጥር አስፈላጊም ከሆነ የቤተ መንግስት ሬፓብሊካን ጋርዶችን እስከማሰማራት ነው የሚደርሰው። ኮረም፣ አላምጣ ወዘተ ሲወረሩና ጥቃት ሲፈጸምባቸው ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጎ ቁጭ እንዳለው፣ አሁን ቁጭ አይልም። ቸኩሎ በራሱ ውሳኔ ያወጀውን የተናጥል ተኩስ አቁሞና ሰርዞ ለመከላከያ ትእዛዝ ይሰጣል። የአይሮፕላን ጥቃቶች ይደረጋሉ። ይሄን ለሕወሃቶች አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።
በኔ ግምት ሕወሃቶች ወደ አፋር ክልል ዞን 4 የዘለቁት ለአፋር ክልል ዞን 2 ፈር ወይም ሽፋን እንዲሆናቸው ነው። በዞን 2 በኩል ፣ በቀይ ባህር ዳር ባሉ የአፋር ደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን እንደ ጢዎ ያሉትን እንደኮሪዶር በመጠቀም፣ እንደ ፈለጉ በነጻነት መውጣት መግባት ስለፈለጉ ነው የሚል ግምት ነው ያለኝ።
የዉጭ ኮሪዶር ማግኘት ለህልውናችን አስፈላጊ ነው የሚል እምነት ስላላቸው፣ በራያ መስመር ከመንቀሳቸው በፊት ሕወሃቶች በርካታ ጊዜ ወልቃይትን ለመቆጣጠር ሞክረው አልቻሉም። አዲ ጎሹ አካባቢ ብዙ የሕወሃት ታጣቂዎች ረግፈዋል። ከብዙ ሙከራ በኋላ ወልቃትን እንደ ኮሪዶር የማግኘቱ ጉዳይ አስችጋሪ ስለሆነባቸው፣ በምስራቅ በኩል እነ ጢዎን እንደ ሚስጥራዊ ኮሪዶር መጠቀሙን እንደ አማራጭ የወሰዱ ነው የሚመስለኝ።
እንደዚያም ሆኖ ግን ሕወሃቶች ይሳካላቸዋል ብዬ አላስብም። በቀይ ባህር ሚስጥራዊ ኮሪዶሮች ቢከፍቱም፣ ምን አልባት የነርሱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲወጡና እንዲገቡ ለማድረግና መጠነኛ የሆነ በጀልባዎች የሚደረግ ቁሳቁሶችና መሳሪያዎች ከማስገባት ያለፈ ብዙም የሚያደረጉት ነእግር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡
ያ ብቻ አይደለም የኤርትራ መንግስት ጥበቃዉን ካጠናከረ ሚስጥራዊ ኮሪደሮቻቸውን በቀላሉ ሊዘጋባቸውም ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ፣ አቶ ሬድዋን ሁሴን የታንዛኒያው የሰላም ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም” ብለዋል

ያ ብቻ አይደለም ለረጅም ጊዜ በአዋሽ ዞን 4 መቆየት ያስቸግራቸዋል፡፡ ከአፋር ዞን 4 ነቅለው ወይንም ተሸንፈው የመውጣታቸውን እድል በጣም ሰፊ ነው፡፡ በተለይም መከላከያ እንዲቀሳቀስ ከተደረገ፡፡
ብቻ ምን አለፋችሁ ትግራይ ያሉ ወገኖች በጦርነት ለማሳካት እየሞከሩት ያለው ነገር በኔ ግምት እብደት ነው፡፡ አሁን ረጋ ብለው፣ ከስሜት ወጥተው ሰክን እንዲሉና እንዲያስቡ እመክራቸዋለሁ፡፡ ከራያ በቶሎ ወጥተው፣ ጠመንጃቸውን ደፍተው፣ በተለይም ከአማራ ማህበረሰብ ጋር ሰላምና ስምምነት እንዲኖር ማድረግ ካልቻሉ፣ ብዙም ረቀው መሄድ አይችሉም።
ለመስማማት፣ ለመወያየት መዘጋጀት ትልቅነት ነው፡፡ ቅንነት ካለ ሁሉንም አሸናፊ ያደረገ ስምምነት ማድረግ ይችላል፡፡ ትግሬው ከአማራው ጋር አንድ ሕዝብ ነው፡፡ የወያኔ የዘር ፖለቲካ መከፋፈል አመጣ እንጂ፡፡

1 Comment

  1. እንደው ግርማ ካሳ ነገር አታጣም ያ ዮሀንስ አብረሀም የሚባለው ሰው እነ ባይደንን የሚያሳስትብን እሱ ይሆን እስቲ ጆሮህን ወደዛ ጣል አድርግ ግለሰቡ እዚሁ እኛ ዘንድ የተወለደ ትግሬ ነው ይባላል። መጥፋትህ አሳስቦኝ ነበር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share