* የአልኮል መጠጥ ማቆም
ምክንያቱም አልኮል የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ
* ሲጋራን ማጤስ ማቆም
ምክንያቱም ሲጋራ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ
* ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር
* በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፣ ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን
* የጠዋት ፀሐይን መሞቅ ይህም ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም በሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል
* የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ ምክንያቱም ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ነው
* ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ይህም ሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል
* ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል
ለተጨማሪ የጤና ምክሮች የሚከተሉትን ማህበራዊ ገጾች ይከታተሉ