June 4, 2022
2 mins read

የ ኢዜማ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ውጤት ማሳወቅ – ስመራጭ ኮሚቴ

ፓርቲያችን በሰኔ ወር በሚያካሄደው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ፤ ለፓርቲው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ አመልካቾችን ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም መቀበላችን ይታወቃል።  በዚሁ መሰረት ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ግንቦት 17 ቀን 2014ዓ.ም ውጤታቸው በየግላቸው ተገልጾላቸዋል፡፡ በምርጫ ተግባራት የግዜ ሰሌዳ መሰረት የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ስለተጠናቀቀ፤ የዕጩዎቻችንን አጠቃላይ ውጤት ከዚህ በታች አያይዘናል፡፡
በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮች ይህ ምርጫ የፓርቲያችንን ገፅታ በሚገነባ መንገድ፤ የመተዳደሪያ እና የፓርቲያችንን የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ፤ እንዲሁም የፓርቲውን እሴት ባከበረ መንገድ እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡
በአስመራጭ ኮሚቴ የግዜ ሰሌዳ መሰረት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ይፋዊ የምረጡኝ ቅስቀሳ ይጀምራል፡፡ ቅስቀሳው ፓርቲውን በሚያጠናክር መልኩ በምክንያት እና በሀሳብ ላይ ሊመሰረት ይገባል፡ ፡ በቅስቀሳ ተግባራት የስነ-ምግባር ደንብ እና በሌሎች መመሪያዎች ከተደነገገው ውጪ ለመንቀሳቀስ የሚሞክር ዕጩ፣ አመራር እና አባል ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ስራ ላይ እንዲውል በብ/ስ/አ/ኮ በተፈቀደው የጉባኤ እና የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ መሰረት ተጠያቂ እነደሚሆን ለማስገንዘብ እንፈልጋለን፡፡
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትገኙ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ይህ ምርጫ በኢትዮጵያ የፓርቲዎች የውስጥ አመራር አመራረጥ ታሪክ ላይ አስተማሪ ሆኖ እንዲያልፍ የናንተም ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሕግ እና ስርዓት እንዲከበር የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታበረክቱ በአክብሮት እንጠይቃለ፡፡
ስመራጭ ኮሚቴ283591262 569472834543473 7408786985079034966 n
284122882 569472887876801 316385330156098153 n
283607986 569472931210130 5246059399258725843 n

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop