December 18, 2021
50 mins read

በአሜሪካ ሕግ አጽዳቂዎች ምክርቤት (ሰኔት) 17ኛ ኮንግረስ ተርጓሚ – ጥበቡ ሞላ

US Senate

1ኛ ስብሰባ   ኤስ.____ሰላምና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅና ለሌሎችም ዓላማ
Mr. MENEDEZ (አቶ መነንዴዝ) (በግሉ፣ Mr. RISCH (አቶ ሪሽ) እና Mr.COONS (አቶ ኩንስ)) የሚከተለው ሰነድ ሁለት ግዜ ተነብቦና ተጣቅሶ ወደ ኮሚቴ ስለ

ሰነዱ

ሰላምና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅና ለሌሎችም ዓላማዎች

  1. በሕግ አጽዳቂና በሕግ አውጭ ምክር ቤቶች ስብሰባ እንዲተገበር
  2. ክፍል 1. አጭር ርዕስ
  3. ይህ አድራጎት “የ 2021 ኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲ ማስተዋወቅያ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
  4. ክፍል 2. ትርጓሜዎች
  5. በዚህ አድራጎት ውስጥ፣
  • አግባብነት ያለው የኮንግረስ ኮሚቴ አባላት– አግባብነት ያለው ማለት የሕግ አጽዳቂና የሕግ አውጭ ምክር ቤት ተወካዮች የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቲዎችን ማለት ነው።
  • ጸሃፊ—“ጸሃፊ” የሚለው ቃል የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ዋና ሃላፊ

ክፍል 3. ግኝቶች

ምክር ቤቱ የሚከተሉትን ግኝቶች ተመልክቷል

  • አሜሪካና የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጠቃሚ የሆኑ ግንኙነቶችን የሚጋሩና ከመቶ ዓመት በላይ ዲፕሎማሲያዋ ግንኙነቶች ያላቸው መሆኑ
  • ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛ የሕዝብ ብዛት ያላት እንደመሆኗ በመካከለኛው ሰሃራ ቀጠና ሰላም መረጋጋት  የተባበሩት መንግስታትን መለያ በመልበስ ጨምሮ ቁልፍ ሚና የምትጫወት ሲሆን የአፍሪካ ሕብረትን አስተናጋጅም ናት።
  • የሕዝባዊ ተቃውሞ ተስፋፍቶ በ2018 ለአስርታት አመቶች በማን አለብኝ አገዛዝ የመራውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር( ኢፒ አር ዲ ኤፍ)  አብይ አሕመድን ጠቅላይ ሚንስትር አድርጎ መረጠ፣ ከተመረጠ በኋላም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጦችን በሰፊው በመቀስቀሱ የእርስ በርስ ግጭቶች ተከስተው የፖለቲካ ግድያዎችና ዲሞክራሲም ወደ ኋላ መንሸራተቱ፣
  • በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሀመድና  በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ቲ ፒ ኤል ኢፍ) አመራርሮች  እስከ 2019 ከ ኢ ፒ አር ዲ ኤፍ ጥምር ተጓዳኝ የነበሩ መካከል ውጥረቶች ተከስተው  በ2019 እና በ2020ዎቹ በመባባሳቸው የፌድራል ኢትዮጵያ መንግሥት የ2020ን ምርጫዎች  በማስተላለፉና ቲፒ ኤል ኤፍም ምርጫዎች  የፌደራል መንግሥት ተቃውሞም አድርጎ በትግራይ ውስጥ ማደረጉ ሁሉ ለውጥረቶቹ አበርክተዋል።
  • በኖቨምበር 2020 ጥዋት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቲ ፒ ኤል ኤፍ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን እዝ (ኢ ኤን ዲ ኤፍ) ላይ ጥቃት የ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ባለስልጣኖች እራስን ለመከላከል ብለው የገለጹትን በመፈጸሙ የፌደራል የጦር ሃይል ጥቃት እንዲያደርግ ትእዛዝ ሰጠ።
  • በ2020ዎቹ በኢ ኤን ዲ ኤፍ እና በታማኝ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ሃይሎች መካከል ያሉ ውጥረቶች ተባብሰው የኤርትራንም መከላከያ ሃይል (ኢ ዲ ኤፍ)፣የአማራ ክፍል ሃይሎችና ሚሊሻዎች የፌደራል መንግሥቱን በመደገፍ ከፍተኛ የጦር ግጭት መካሄድ ጀመሮ ቀጠለ።
  • በአሜሪካና አለም አቀፍ ተባባሪዎቿ በተደጋጋሚከ2020 ጀምሮ  የኤርትራን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ መውጣት ማረጋገጫ ቢጠየቅም የኤርትራ ጦር ሃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ቆይታቸውን ቀጠሉ።
  • በቲ ፒ ኤል ኤፍ አምሳል ሃይሎችና በኢ ኤን ዲ ኤፍ አጋሮች መካከል ጦርነቶች በትግራይ እየተካሄደ ወደ አማራና ወደ አፋር ክፍሎችም በመስፋፋቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ግለሰቦች ለሞት ዳርጓል፣ከ 61,000 (ስድሳ አንድ ሺህ) ኢትዮጵያውያን በሱዳን ጥገኝነት እንዲጠይቁና ከ 2,000,000 ( ሁለት ሚልዮን) ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል።
  • ጦርነቱ ምርት እንዳይሰበሰብ፣አኗኗርን፣ግብይትን፣ባንክ አገልግሎትን አስተጓጉሏል፤ መሰረታዊ ልማቶች በረቀቀ መንገድ ተዘርፈዋል፣ከጥቅም ውጭም ተደርገዋል፤ ግጭቱ በሚካሄድበት ወቅት የጤና ተቋማትን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ውድመቶች የተፈጸሙት በ ኢ ኤን ዲ ኤፍ ፣ በ ኢ ዲ ኤፍ  እና በ አጋር ሚላሻዎች መሆናቸውን መረጃዎቻችን ያመላክታሉ። የአቅርቦት ሰንሰለቶችና ምግቦች የተዘረፉት በ ኢ ኤን ዲ ኤፍ ፣ ኢ ዲ ኤፍና በአጋር ሚሊሻዎች ጥምረት ሲሆን ከ 400,000 (አራት መቶ ሺህ) እስከ 900,000 (ዘጠኝ መቶ ሺህ) ኢትዮጵያውያን ለረሃብ ኑሮ እንዲጋለጡ አስተውጽዖ ከማድረጉም በላይ ወደ 1,800,000 (አንድ ሚልዮን ስምንት መቶ ሺህ) የሚጠጉ ይሆናል የሚል የጁን 2021 ትንታኔ ያሳያል።
  • በ ኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የኤሌክትሪክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች እንዲስትጓገሉ ማድረግ ለሰበዓዊ ድጋፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማደናቀፍ አስተዋጽዖ ሲያደርግ በሁሉም ወገን ውግያ ተዋናዮች አበረታትቶ ስለ አካባቢዎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚሰራጩ መረጃዎችን ውስን እንዲሆኑም አድርጓል።
  • የፊደራል ኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ወደ ትግራይ ያልተገደበ የሰብዓዊ አቅርቦት የተረጋገጠ ፈቃድ ቢሰጥም ዘርፈ ብዙ የሆኑ የአሰራር እንቅፋቶችን በመጫን የአለም አቀፍ ሰብዓዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን በጠላትነት በማየት በስፍራው ለተሰማሩ ሰራትኞቻቸው ደህንነት ስጋትን ፈጥሯል።
  • በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ 23 (ሃያ ሦስት) የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ፣ አንድ በአሜሪካ አለም አቀፍ አድገት ድርጅት ወኪል ሰራተኛ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃይሎች በ ሜይ 2021 የተገደለውንና ሦስት ዶክተሮች ያለ ድንበር ሰራተኞች ባልታወቁ ታጣቂዎች የተገደሉትን ጭምሮ ተገድለዋል።
  • የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ተዋናዮች በተጨማሪ ሕጋዊ ግድያዎች፣በአስገድዶ መድፈር፣ በዘር ማጽዳት፣ በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል፣በሰብዓዊ ጥቃት ወንጀልና በዘር ማጥፋት ወንጀሎች እየተከሰሱ ይገኛሉ።
  • በትግራይ ውስጥ ሁለት የኤርትራ ሰደተኛ ጣብያዎች ሺመልባና ሂትሳትስ ከ ኖቨምበር 2020  እስከ ጃንዋሪ 2021 በታጣቂ ተዋናዮች ጥቃት ተደርጎባቸው ሲደመሰሱ ስደተኞቹ ግድያና አፍኖ በማስገደድ ተመላሾች እንዲሆኑ ተደርገዋል።
  • እስከ ኦክቶበር 31, 2021 ድረስ የአሜሪካ መንግሥት በ2020ና በ2021 በጀት አመቶች ውስጥ ለሰሜን ኢትዮጵያ በድምሩ $617,387,662 (ሥድስት መቶ አስራሰባት ሚልዮን ሦስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ሁልት ዶላር) የሰብዓዊ እርዳታ በማድረግ ብችኛና ዋነኛው በመሆን የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ቀውስ ከተጀምረ ጀምሮ ለግሷል።
  • በጁላይ 2021 የቲ ፒ ኤል ኤፍ ተጓዳኝ ሃይሎች የጦር ማጥቃት በማድረግ አጎራባች የአማራና የአፋር ክፍሎችን በመያዝ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራና የአፋር ተራ ስዎች ከስፍራዎቻቸው ተፈናቀሉ፤ በመሆኑም የትግራይ ሃይሎች የአካባቢውን ተራ ሰዎች አፈናቀሉ  በማይ አይኒ እና በአዲ ሃሩሽ ካምፖች ይኖሩ የነበር ኤርትራውያንን አጠቁ የሚባል ስሞታን አስነስቷል።
  • የቲ ፒ ኤል ኤፍ ጁላይ 2021 ማጥቃት እርምጃ የተነሳ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሁመራ ውስጥ ግድያዎች ሲፈጸምባቸው ቀስቃሽ ዘር ተኮር ጥላቻ የተሞላባቸው መግለጫዎች በመንግሥት መድረኮችና በሚዲያዎችም ተስተጋብተዋል።
  • የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ለቲ ፒ ኤል ኤፍ ጁላይ እስከ ኦገስት 2021 ጥቃት ምላሽ የሰጠው አጠቃላይ ጦር ክተት በመጥራት፣ የአካባቢዎች ልዩ ሃይሎችና ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ሚሊሻዎችን በማቀናጀት የቲ ፒ ኤል ኤፍን ጥቃት መመክትና መግታት ሆነ።
  • በኦገስት 2021 የቲ ፒ ኤል ኤፍና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ጦር ( ኦ ኤል ኤ) ሃላፊዎች ታጣቂ ቡድን በቅድሚያ በኦሮሞ ክፍሎች የጦር ፍልሚያ በመግጠም በገሃድ ተጣምረው የኢትዮጵያን ፌደራል መንግሥት እንደሚዋጉ አረጋገጡ፣ ይህም የሆነው ቲ ፒ ኤል ኤፍ በአማራ ክፍል እያጠቃ ባለበትና ኦ ኢል ኤ ደግሞ በኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ግዜ ነው።
  • በሰብተምበር 2021 የፌደራል ኢትዮጵያ መንግሥት ሰባት ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ሃላፊዎችን እንደሚያባርር አስታውቆ በኦክቶበር 2021 በትግራይ ዋና ከተማ  መቀሌ ላይ የአየር ሀይል ጥቃት ማድረግ ጀመረ፣ ይህም የዓለም እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን የበለጠ የምግብ እርዳታ እንዳያቀርቡ አደረጋቸው።
  • በኦክቶበር የመንግሥት ንብረት የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ “ይህ ስንዴ (ምግብ እርዳታ) የተባለ ነገር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ እርግጠኛ ብንሆን፣ 70 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ችግር እናቃልላለን” ያለውን ንግግር አስደምጧል፣ ስለሆነም የዓለም አቀፍ ምግብ እርዳታም በአጠቃላይ አንዳይሰጥ ሊያግድ ይችላል የሚል ግምት አለ።
  • በኦክቶበር 2021 የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ እርዳታ የኣየር አገልግሎቶች ወደ መቀሌ በመሄድ ምግብ እርዳታ እንዲሰጥ በፌደራል ባለስልጣኖች ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ በረራውን በአየር ሀይል ጥቃት ምክንያት እንዲያጨናግፍ ተገድዷል፣ በዚህም የ 11 ( ኣሥራ አንድ) የተባበሩት መንግሥታትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሰራተኞች ህይወት ለአደጋ ተጋልጧል።
  • የትግራይ መከላከያ ሃይሎች የወታደር እንቅስቃሴዎች በገሰገሰበት ኦክቶበር 2021 መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዜጎች መሳሪያ በማንሳት እንዲከላከሉ በማበረታት በ ኖቨምበር 2, 2021 ኢትዮጵያ የ 6 ወር (ሥድስት ወር) አስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጀች።
  • በኖቨምበር 3, 2021 የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ስለተባሉት ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ሰብዓዊና የስደተኛ መብት ሕግ  በሁሉም የግጭቱ ተዋናዮች በትግራይ የፌደራል ኢትዮጵያ ክፍል የተፈጸሙ ጥሰቶች ላይ ያደርጋችውን የጋራ ምርመራ  ይፋ አደረገ፤ ምርመራውም “ በተራ ሰዎችና ቁሶች እንዲሁም ያልነጠሉ ጥቃቶች በ ኢ ኤን ዲ ኤፍ፣ ኢ ዲ ኤፍ፣ እና ቲ ኤስ ኤፍ ቲግራይ ልዩ ሃይሎች የዓለምን ሰበዓዊ መብት በመጣስ ስለተፈጸሙ ምናልባትም በጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ ይሆናል፤ እነዚህና ተባባሪ ሚሊሻዎች የዓለም ሰብዓዊ መብቶችንና የዓለም ሰብዓዊ መብት ሕግ ጥሰቶችን ፈጽመዋል”።
  • በፌደራል የኢትዮጵያ መንግሥትና ተጓዳኞቹ መካከልና በ ቲ ፒ ኤል ኤፍ እና ኦ ኤል ኤ ያለው ግጭት መዛመት የድንበር ፖለቲካ ሁኔታዎች በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ብልሽት እየከፉ መምጣት፣ የማያቋርጥ የጎሳ ውስጥ ግጭቶችን ጨምሮ፣ እየተስፋፋ ያለው ጋዜጠኞችን መጨቆን፣ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ተቃዋሚ ድምጾችንና ከፍተኛ ፉክክር ያስከተለው በጁን 2021 የተካሄደው ብሄራዊ ምርጫን ጨምሮ በዓለም ተቀባይነት ያላቸውን ሚዛናዊነት መስፈርቶች አያሟሉም።
  • የኢትዮጵያ ቀውጥ በተወሳሰቡ የአካባቢ ሁኔታዎች የተከበበ ነው፤ ከነዚህም በጣም አስፈላጊ ሁኔታዊ ጎኖች ዋነኞቹ ሦስቱ በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል  በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያለው አለመረጋጋት፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ ኣል ፋሽጋ ድንበር በተመለከተ  የአካባቢው ጉልበት ማሳየት ውጥረት እና እየጨመረ ያለው የገልፍን ሀይሎች ቱርክ፣ ኢራን፣ ሩስያና ሕዝባዊ የቻይናን ሪፐብሊክን ጭምር  ለአፍሪካ ቀንድ ጂኦግራፊያዊ በላይነት ፊክክሮች የተከበበ ነው።
  • አሜሪካ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በተደጋጋሚ ውጥረቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ በማቅረብ፤ ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ ለተፈጸሙ ጭካኔያዊ ድርጊቶች በፈጸሙ ማናቸውም ተፋላሚዎች ሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ሁሉን ድንበር ያካተተ ብሄራዊ ውይይት እንዲደረግ መበረታቻዎች ተጠቁመዋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት በሰላማዋዊ መንገድ ባለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎች ፣ የእድገት እርዳታ፣ የጸጥታ እርዳት ቅነሳ፣ ቪዛ ዕቀባ ከፍተኛ ደረጃ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ተደረገዋል።
  • በሰብተምበር 17, 2021, ፕሬዘዳንት ጆ ብይድን ቁጥር 14046  “ ሰብዓዊና የሰበዓዊ መብት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ ቀውስ  በተወሰኑ ሰዎች ላይ የተደረገ ማዕቀብ” ልዩ ትዕዛዝ ፈረመ፤ ይህ ትዕዛዝ አሜሪካ ተጠያቂ የተባሉትን ኢላማ የማድረግ ወይም እርምጃ ለመውሰድ ችላ የሚሉትን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማራዘም መመርያዎች በሚያወጡ፣ ወይም ሰብዓዊ መብቶችን በሚጥሱ፣ ወይም የሰብዓዊ ተደራሽነትና ከግጭቱ ጋር የተያያዘ የተኩስ ማቆም በሚያግዱ ላይ ትዕዛዙ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ይሰጣል።
  • የፌደራል ኢትዮጵያ መንግሥት ለግጭቱ የቀረበለትን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ሁሉ አልተቀበለም፤ የአፍሪካ አንድነት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ በኖቨምበር 2020, እና ዓለም አቀፍ ባለስልጣኖች ለእድገት (ኢ ጋ ድ) ሊቀመንበር አብዳላ ሃምዶክ በ ኦገስት 2021 ከ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ጋር የዕርቅ ውይይት እንዲያካሂዱ የቀረቡለትን ጨምሮ አልትቀበለም።

ክፍል 4. የፖሊሲ መግለጫ

ሰላማዊ፣ዲሞክራሲያዊ አንድ ኢትዮጵያ ለመደገፍ የአሜሪካ ፖሊሲ ነው፤ ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ፣ ዕድገትና ሌሎች ህጋዊ መንገዶች በመጠቀም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመጨረስ፣ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጸቦችን ለማቆም፣ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት እንዲካሄድ፣ ሰብዓዊንት እንዲሰፍን፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ መብቶች እንዲጠበቁ መርዳት የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ መርሆ ነው።

ክፍል 5. ድጋፍ ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ

(ሀ) በአጠቃላይ፣– ሰክረታሪው ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ እድገት ወኪል አስተዳደር ጋር በመመካከር በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን ለመደገፍ  ስትራተጂ በመንደፍ ሲተገበር ማብራርያና ለመተግበሩም እርግጠኛንት የሚከተሉትን–

  • ተራው ማህበረ ሰብ ዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ ለማስፈት የሚደረጉ  ጥረቶችን ለመርዳት ያሉ ዕቅዶችን መደገፍ፣
  • ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደግፉ ዕቅዶች፣
  • በግጭቱ ሳብያ ግፍና ጭካኔዎችን የፈጸሙ ለፍትህ ተጠያቂነት የታቀዱ ዘዴዎችን መደገፍ፣
  • በኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ንግግሮችና ስም ማጥፋትን የመታገል ዕቅዶች፣
  • አዲስና የታቀደ ዲሞክራሲና ተገዢ የኢትዮጵያን ገዢ ድርጅቶቶች መርዳትና
  • (ሀ) የእነዚህን የቅርብ ግዜ ግምገማ ውጤቶችና

(ለ) ከተደረጉ ግምገማዎች  የተገኙ ተመክሮ ውጤቶች ለመተግበር  ዕቅዶችን

 

ለምክር ቤት ሪፖርት ማድረግ—ይህ ድርጊት (አክት) በስራ ላይ በዋለ ከ180 (መቶ ሰማንያ) ቀን ባላነሰ ግዜ ውስጥ ሰክረታሪው በንኡስ አንቀጽ (ሀ) በተጠቀሰው መሰረት ለሚመለከታቸው የምክር ቤት ኮሚቴዎች ሪፖርት ይሰጣል፣

ክፍል 6. ድጋፍ ለግጭት መፍቻ፣መግቺያና በአግባብ መያዝ፣ ማስማማት

(ሀ) ግጭት መፍታት– ፕሬዚደንቱ ገንዘብ፣ባለ  ሙያና ዲፕሎማሲያዊ  እርዳታ የማድረግ ስልጣን ለመደገፍ–

  • በአፍሪካ አንድነትና ሌሎች ዕውቅና ባላቸው ተቋሞች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ  ለሚሳተፉና፣
  • በተራው ማህበረሰብ፣ በተለይም የተጉላሉ ህበረትሰቦች፣ ሴቶችና ወጣቶች ለሰላም ግንባታ ተሳትፎ፣ እርቅና ህብረተሰብ ስምምነት ለማምጣት ለሚጥሩ፣

(ለ) ግጭትን መከላከልና ዕርቅን ማስፈን፣–

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ እድገት ወኪል አስተዳዳሪ እንደ ኣስፈላጊነቱ ከስክረታሪ ጋር

በመቀናጀት ስትራተጂ ነድፎ በመተግበር ግጭት ማስወገድና ከቁጥጥር ውጭ

እንዳይሆን መርዳት፣ በግጭት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ኣዕምሮ መረበሽ    ለደረሰባቸው የሚከተሉትን የሚያካትት፣–

  • በኢትዮጵያ ውስጥ ግጭቱን የመሩትን መገምገም፣
  • ጠለቅ ያለ ግጭት መከላከልና ከቁጥጥር እንዳይወጣ ማቀድ፣
  • በህብረተሰብ የሚመራ ዕርቅ ላይ ማተኮር፣
  • ድርጅቱ በዘልማድ የተጉላሉ ህብረተሰቦችና የጎሳ ክፍሎች፣ ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ እንዲኖራቸው ወኪሉ ልዩ ትኩረቶች ይሰጣል፣
  • ዕቅዶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም አቅምን ለማዳበር ማናቸውም ዕርዳታዎች በተገቢው መድረሳችውን ለማረጋገጥ፣ ለማደረግ እስከተቻለ ድረስ በህብረተሰብ መሰረት ግጭት መከላከልና ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ማድረግ፣ ብጥብጥ መከላከል፣ ሰላም ግንባታ፣ ዕርቅ ልምምዶች፣ ኣዕምሮ ደህንነት ድጋፍ መስጠትና  በኣዕምሮ መረበሽ የተጎዱትን መፈወስ፣
  • ግልጽ መግለጫ ስለ–

(ሀ) ስትራተጂው ግቦችና የሚጠበቁ ውጤቶች፣ እና

(ለ) ወደ ተፈለጉ ግቦች ለመድርስ የሚያገልግሉ መጠቀሚያዎችን በጥልቅ በማጤን የትኞቹ ውጤት እንዳመጡ መገንዘብ፣ እና

  • የአሁን ሀገር እድገት ትብብር ስትራተጂ ዕቅዶች እንደ ግዜው በማሻሻልና በመከለስ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ያሉትን አንኳሮች እንዲያካትት፣

(ሐ) ኣቅርቦት— በነዑስ አንቀጽ (ለ) ስር እንዲፈጸም የተጠየቀው ስትራተጂ ለሚመለከታቸው የኮንግረስ ኮሚቴ አባሎች 90 (ዘጠና) ቀናት ባልበለጠ ግዜ ይህ ድርጊት በተግባር ከዋለበት ቀን በኋላ ይቀርባል።

 

ፍል 7. በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለመደገፍ የሚወሰዱ እርምጃዎች

(ሀ) ዕቀባዎች  ወደ ዲሞክራሲ የሚደረግ ሽግግርን ዝቅ በማድረግ

  • በአጠቃላይ–ፕሬዝደንቱ በአንቀጽ (2) በተጠቀሰው መሰረት በማንኛውም የውጭ አገር ሰው አግባብ ነው ብሎ ከወሰነ ማዕቀብ ሊጥል ይችላል–

(ሀ) በሰላም በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ጠላትነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን ዝቅ በማድረግ፣

(ለ) ከፍተኛ የአመራር አባሎች በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በኤርትራ መንግሥት ወይም በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ወይም ሌሎች በሰሜን ኢትዮጵያና አካባቢዎች ግጭቶች ተሳታፊዎች የፋይናንስ ተጠቃሚነት በሚያሳድዱ፣ በሙስና፣ምርጫ በማጭበርበር የፖለቲካ ስልጣን በመወስድ ወደ ዲሞክራሲ የሚደረግ ሽግግርን በሚያግዱ፣

(ሐ) በኢትዮጵይ ጠላትነቶች ተካፋይ ለሆኑ  እርዳታዎች ለሚሰጡ በማናቸውም ወገኖች፣–

  • የጦር መሳርያዎች፣ ጦር መሳርያ የታጠቁ ድሮኖች፣ሄሊኮፕተሮች፣ተዋጊ አውሮፕላኖች፣

የጦር ታንኮች፣ለታንኮች የሚሆኑ መሳርያዎች፣

ሚሳዪሎች ወይም የሚሳዪል ሲስተሞች ወይም፣

(ii)እንደነዚህ ያሉ ሲስተሞችን፣ጥይቶችን፣መለዋወጫ

እቃዎችን፣ጠጋኞችን፣ፓይለቶችን በመስጠት በሚረዱ፣ወይም፣

(መ)  በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ጠላትንቶች ተሳታፊ ለሆኑ ማናቸውም ወገኖች በማወቅ  የጦር መሳርያ ሽያጭን ወይም ልውውጥን በሚያመቻች፣

  • ዕቀባዎች ሲገለጹ–በአንቀጽ (1) መሰረት ዕቀባዎች የሚደረግባቸው የውጭ ሰዎች የሚከተሉት ናቸው፣

(ሀ) ንብረት እገዳ– ፕሬዚደንቱ በዓለም አቀፍ አስችኳይ ግዜ የኢኮኖሚ ስልጣን ድርጊት (50 ዪ ኤስ ሲ 1701 ኢቲ ኤስ ኢኪው) በተሰጠው ስልጣን መሰረት እንደ አስፈላጊነታቸው የውጭ አገር ሰውነት ያላቸው ጠቅላላ በአሜሪካ ውስጥ ወይም በአሜሪካ ቁጥጥር ያሉ ንብረቶችን ማገድ፣እንዳይዘዋወሩ መገደብ ይችላል።

(ለ) ቪዛዎችን ማግኘት የማይፈቀድላቸው፣ በይቅርታ የማይታለፉ ባእዳን፣–

  • ቪዛዎች፣መፍቀድ፣ ወይም በይቅርታ መታለፍ —

አንድ ባዕድ በአንቀጽ (1) እንደተገለጸው —

  • አሜሪካ ለመግባት የማይችል፣
  • አሜሪካ ለመግባት ቪዛ ወይም ሌላ ሰነድ ለማግኘት የማይበቃና
  • በስድተኛና ብሄር ድርጊት አንቀጽ (8 ዩ ኤስ ሲ 1101 ኢቲ ኤስኪው) መሰረት ቪዛ ወይም ሌሎች ጥቅሞችን ለማግኘት የማይፈቀድለት

(ii)  በግዜው የተገኘ ቪዛን አገልግሎት እንዳይሰጥ  መሰረዝ

  • በአጠቃላይ—ለባእዳን የተሰጡቪዛ ወይም ሌሎች መግቢያ ሰነዶች በአንቀጽ(1) እንደተጠቀሰው ይሰረዛሉ፣
  • አስቸኳይ ተፈጻሚነት–በን ኡስ አንቀጽ(I)የተጠቀሰው

(ሀሀ) ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል

(ለለ)ያለምንም ማስጠንቀቂያ በባዕዳን ሰዎች እጅ ያለ ቪዛ ወይም መግቢያ ሰነድ ወድያውኑ ይሰራዛል

 

  • በዕቀባው የማይካተቱ—

(ሀ) ወደ ውስጥ የሚገቡ እቃዎችን በተመለከተ የማይካተቱ–

  • በአጠቃላይ–ዕቀባ ስለሚደረግባቸው ወይም ሊያሳቅቡ የሚያስችሉ መስፈርቶች በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰው ወደ አገር የሚገቡ እቃዎችን አያካትትም።
  • እቃ ምንነት ገለጻ—በዚህ ን ኡስ አንቀጽ “እቃ” የሚለው

ቃል ማንኛውንም ቁስ፣ የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ የሆነ

ነገር፣የመመርመርያ መሳርያ ሙያዊ መረጃን ሳይጨምር

ማለት ነው።

(ለ) የአሜሪካን ዋና መስርያ ቤቶች ስምምነትን ህግ ማስከበር ኣላማዎች ማሟያ መስፈርት—ዕቀባዎች አንቀጽ (2)(ለ) ወደ አሜሪካ የሚገባ ለአሜሪካ ባዕድ ከሆነ ዕቀባው ተፈጻሚነት አይኖረውም–

  • አሜሪካ ከተባበሩት ዋና መስሪያ ቤቶች በሌክ ስክሰስ ጁን 26, 1947 እና በኖቨምበር 21, 1947 ተፈጻሚ ሆኖ የገባችውን ስምምነት

በስራ ላይ እንድታውል መፍቀድ ግድ ነው፣ ወይም

  • ጠቀሜታ ያላችውን ዓላማዎች ተፈጻሚነት ሊያጎለብት ይችላል።
  • በስራ ላይማዋል፣ቅጣቶች–

(ሀ) አፈጻጸም—ፕሬዘዳንቱ በአንቀጾች 203 እና 205 ዓለም አቀፍ ኢኮኖምያዊ አስችኳይ ስልጣኖች ድርጊት (50 ዩኤስሲ 1702 እና 1704) የተሰጠውን ስልጣን በመተቀም በዚህ ን ኡስ አንቀጽ የተጠቀሰውን ሊያደርግ ይችላል።

(ለ) ንብረትን በማገድ የሚደረግ ቅጣትን በተመለከተ–በን ኡስ አንቀጽ (ሀ) አንቀጽ(2) ወይም ሌላ ማንኛውንም ህግ የጣሰ፣ ሊጥስ የሞከረ፣ለመጣስ ያደመ ሰው በን ኡስ አንቀጽ (ለ)ና(ሐ) ክፍል 206 የዓለም አቀፍ አስቸኳይ ኢኮኖምያዊ ስልጣኖች ተግባር (50 ዩኤስሲ 1705) መሰረት ህጎችን በጣሰ ሰው ላይ ቅጣት በን ኡስ አንቀጽ (ሀ) መሰረት ይቀጣል።

  • ትርጉሞች–በዚህ ን ኡስ አንቀጽ፣

(ሀ) መፍቀድ፣ተፈቀደ፣ባዕድ–“መፍቀድ”፣”ተፈቀደ”፣ና “ባዕድ” የተባሉት ቃላት በስደተኛና ብሄሮች ተግባር ክፍል 101 (8 ዩኤስሲ 1101) ውስጥ የተሰጡ ትርጉሞችን ያመላክታል፣

(ለ) የውጭ ሰው–“የውጭ ሰው” የሚለው ቃል አሜሪካዊ ያልሆነ ሰው ማለት ነው፣

(ሐ)በማወቅ—“በማወቅ” የሚለው ቃል ከጸባይ፣ከሁኔታ ወይም ከውጤት ጋር በተመለከተ ሆኖ የተሰራው ስህተት በፈቃደኝነት፣ሁኔታን ተረድቶ የተፈለገ ውጤት ለማግኘት የተደረገ ማለት ነው፣

(መ)አሜሪካዊ ሰው—“አሚሪካዊ ሰው” የሚለው ቃል ማለት–

  • የአሜሪካ ዜግነት ያለው፣ ወይም በሕጋዊ መንግድ አሜሪካ ውስጥ የሚኖር ባዕድ ወይም ማንኛውም ግለሰብ በአሜሪካ አስተዳደር ያለ፣ ወይም
  • ማንኛውም በአሜሪካ ህግ ስር ያለ ተቋም ወይም በአሜሪካ አስተዳደር ስር የሚገኝ በውጭ ያለ ቅርንጫፍ ተቋምን ጨምሮ ማለት ነው።

ለ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚሸጡ ጥምር አገልግሎት ያላቸው መከላከያ ነክ ነገሮችን በተመለከተ ውስንነቶች–

  • የጥምር አገልግሎት ቁሶች–በአንቀጽ 1754(c)(1)(A) ወደ ውጭ መላክ ቁጥጥር መሻሻል ተግባር 2018 (50 ዩኤስሲ 4813(c)(1)(A) ወደ ውጭ መላክ፣እንደገና መላክ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ኤርትራ እቃዎችን ማስተላለፍ በዚያ አንቀጽ(ii) እንደተገለጸው፣
  • መከላከያ ቁሶች–ከአሜሪካ ምንም ኣይንት መከላከያ ቁሶች ወደ ኢትዮጵያና ኤርትራ ለመላክ ፈቃድ በአሚሪካ የጦር መሳርያዎች ወደ ውጭ መላክ ቁጥጥር ተግባር (22 ዩኤስሲ 2778 (ሀ)(1) ጃንዋሪ 1, 2016 መሰረት መስጠት ሊከለከል ይችላል፣

ለኢትዮጵያ እንዳይሰጡና ለመሰረዝ የተለየ እርዳታ፣

(1)በአሜሪካ ዓለም እድገት ገንዘብ ተቋም ኮርፖሬሽን ድጋፍ–

የአሜሪካ ዓለም እድገት ገንዘብ ተቋም በአርእስት II ለተሻለ እድገት ወጪ አጠቃቀም ተግባር 2018 (22 ዩኤስሲ 9621 ኢቲ ኤስ ኢ ኪው) መሰረተ ለኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ላያደርግ ይችላል።

  • መቋረጥ–በአንቀጽ (1)ስር ክልከላው ከ30 (ሠላሳ) ቀናት በኋላ ወይም ሰክረተሪ ኦፍ ስቴት( የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊ)  ለተገቢ የኮንግረስ ኮሚቴዎች በየኢትዮጵያ መንግሥትና አጋሮቹ የሚወሰድ እርምጃን ካጸደቀ በኋላ ላይሆን የሚችለው፣

(ሀ) በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ሁሉም የጦር ማጥቃት ሲቆም፣

(ለ) ግጭቱን ለማቆም እውነተኛ የፖለቲካ ውይይት ለማድረግ እርምጃ ከተወሰደ፣

(ሐ) ሰብዓዊ መብቶች፣ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ለመጠበቅ እርምጃዎች ሲወሰዱ፣

(መ) ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሲፈቀድ፣

(መ) በጠላትነቶች የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን፣ሰብዓዊ መብትና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከሚመረምሩ ገለልተኛ መርማሪዎች ጋር ትብብር ሲደረግ፣

ዘርፈ ብዙ ዕቀባዎች—ሰክረተሪው ከትሬዠሪ ሰክረተሪና ኮመርስ፣ እንዳስፈላጊነቱም የተባበሩት መንግሥታት ጸጥታው ክፍል፣ የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅትን፣የአውሮፓን ህብረት፣የአፍሪካ ህብረትንና ሌሎች ተዋናዮችን በማሳተፍ የተቀነባበረ የውጭ ንግድ ቁጥጥር ዕቀባዎች በን ኡስ ከፍል (ሀ)(1) መሰረት የተፈለገውን ውጤት እንዲያስከትሉ ያደርጋል።

ክፍል 8. ደህንነት እርዳታ

(ሀ) የደህንነት እርዳታ መቋረጥ–የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ይሰጡ የነበሩ የደህንነት እርዳታዎች ሰክርታሪው አስፈላጊ ነው በሚልበት ግዜ በሙሉ በአስቸኳይ ይቋረጣሉ፤ ሰክርታሪው የኢትዮጵያ መንግሥት የግጭቱ ተሳታፊዎች ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ የሚያሳዩትን ፈቃደኝነት በመገምገም የዕርዳታ ማቋረጥን ውሳኔ ያስፈጽማል፣

(ለ) ሪፖርት–ሰክረታሪው  ይህ ድርጊት በስራ ላይ በዋለ 15 (አሥራ አምስት) ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ አግባብ ለሆኑ የኮንግረስ አባላት የተቋረጡ እርዳታዎች በመዘርዘር ን ኡስ አንቀጽ (ሀ) በሚጠይቀው መሰረት ያቀርባል።

ክፍል 9. ለፌደራል ኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት  የሚደረጉ እርዳታዎች፤

(ሀ) ውስንነቶች–የገንዘብ ሚንስትር (ሰክረተሪ ኦፍ ትሬዠሪ) ለአሜሪካ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ተቋማት ዳይረክተሮች ዋና አስፈጻሚ መመራያ በማስተላለፍ፣

  • ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለኤርትራ የብድር መክፈያ ግዜ መራዘም ወይም ለሙያዊ እርዳታ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች በመቃወም ድምጽ እንዲሰጡ፣
  • ከሌሎች አበዳሪ አገሮች ጋር የፖሊሲ ቅንብር በማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥትና ኤርትራ ሰብዓዊ መብት መሻሻልን በተመለከተ የማበደር ፖሊሲ እንዲያቀነባብሩ፣

(ለ) ለሰብዓዊነት ዓላማዎች የተለየ ፖሊሲ—

አንቀጽ (1) እና  (2) ን ኡስ ክፍል (ሀ) ላይ ሰብዓዊ መብትን በተመለከተ የሚሰጡ የገንዘብና ሙያዊ እርዳታዎች ግድቦች ኮቪድ-19 ወረሽን ለመከላከል፣ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚጠየቁ ብድርና እርዳታዎችን አያካትትም፤ ከዕቀባው ገደብ ነጻ ናቸው።

(ሐ) ለሰብዓዊ መሰረተ ፍላጎቶች በቀጥታ የሚደግፉ ፕሮጅክቶች ከዕቀባ ውጭ ስለማድረግ፣

የገንዘብ ሚንስትር (ሰክረታሪ ኦፍ ትሬዠሪ) በን ኡስ ክፍል (ሀ)(1) የተመለከተውን ለሚመለከታቸው የኮንግረስ ኮሚቴ አባላት ካሳወቀ በኋላ ከዕቀባ ሊያወጣቸው ይቻለዋል፣ለማድረጉም የወሰነበትን ምክንያት በጽሁፍ ለውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ(ሰክረተሪ ኦፍ ስቴት) ዕቀባው የማይመለከትበት ምክንያት መሰረታዊ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ፕሮጀክት መሆኑን ይገልጻል።

(ሠ) መቋረጥ— ን ኡስ ክፍል (ሀ)(1) የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ(ሰክረተሪ ኦፍ ስቴት)በ 30 (ሠላሳ) ቀናት ለተገቢ የኮንግረስ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ መንግስትና አበሮቹ የሚጠበቅባቸውን–

  • በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የጦር ማጥቃት መቆሙን፣
  • ግጭቱን ለማቆም የሚወሰዱ ከልብ የመነጨ ጥረት መደረጉን ሲያረጋግጥ፣
  • ሰብዓዊ መብት፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች መከበራቸውን ካረጋገጠ፣
  • ዘላቂና ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት መፈቀዱን ሲያረጋግጥ፣
  • ከሚታመኑ ገለልተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪዎች ጋር በመተባበር በግጭቱ የደረሱ በደሎች ምርመራ እንዲደረግ ሲደረግ፣ ዕቀባዎች ይቋረጣሉ።

(ረ) አጭር መግለጫ—ይህ ድርጊት በስራ ላይ እንደዋለ ከ 60 (ሥልሳ) ቀናት ባልበለጠ ግዜና በየ 120 (መቶ ሃያ) ቀኖች ከዚያ በኋላ በን ኡስ ክፍል (ሀ)(1) በ ን ኡስ ክፍል (መ) መሰርት ይወገዳሉ፣ የገንዘብ ሚንስትር(ሰክረተሪ ኦፍ ትሬዠሪ) ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ወኪል አስተዳዳሪ ጋር በመቀናጀት ወይም በተወካዮቻቸው ለተገቢ ኮንግረስ ኮሚቴ አባሎች ስለ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዲሬክተሮች በን ኡስ ክፍል (ሀ) መሰረት አጭር መግልጫ ያደርጋሉ።

ክፍል 10. ተጠያቂነትን መደገፍ—

(ሀ) በአጠቃላይ—ፕሬዘዳንቱ ለጦር ወንጀል፣በሰብዓዊንት ላይ ለተፈጸሙ ወንጅሎች፣ በኢትዮጵያ ሰሜን ክፍሎችና ሌሎችም አካባቢዎች ስለ ተፈጸሙ ወንጀሎች መረጃ መጠበቅና ለጦር ወንጀሎች ተጣያቂነት እንዲውሉ የገንዘብ፣የሙያ፣ የዲፕሎማሲ እርዳታ የመስጠት ስልጣን ተሰጥቶታል።

(ለ) መረጃ አቅርቦት—ፕሬዘዳንቱ በአሜርካ መንግሥት ከሌሎች ተቀባይነት ካላቸው መርማሪዎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በተባሉ ወይም ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ህግ ጥሰት በተመለከተ መረጃዎችን ለማካፈል ስልጣን ተሰጥቶታል።

ክፍል 11. ከጦር መሳርያ በተያያዘ፣ የፋይናንስና ሌሎች ሪፖርት ማቅረብ አስፈላጊነቶች፣

(ሀ) ሪፖርት ስለ ከፍተኛ የኢትጵያ መንግሥት፣ ኤርትራና ተቃዊሚ ታጣቂ ክፍሎች እንቅስቃሴዎች— ይህ ተግባር በሥራ ላይ በዋለ ከ 180 (መቶ ሰማንያ) ቀናት ባልበለጠ ግዜና ከዚያም በየዓመቱ ለሁለት ዓመታት ያህል የትግራይ ክፍል ጠላትነቶች እስከሚያልቅ ሰክረተሪው ለተገቢ ኮንግረስ ኮሚቴ አባላት በሚያቀርበው ሪፖርት፣

  • የከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ኢርትራና ሌሎች ታጣቂ ክፍሎች አመራር አባላት ስለ ግጭቱ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችን ያብራራል፣

(ሀ) የመሳርያ ሽያጭ ልውውጦችን፣ ገንዘብ አቅርቦትና ልውውጥ በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በኤርትራ መንግሥት በታጠቁ ተቃዋሚ  ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት ተሳታፊ ክፍሎች እንቅስቃሴዎች፣

(ለ) ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ አስገድዶ መድፈሮች እንዲፈጸም የመሩ፣ የተሳተፉ፣

(ሐ) ሕጻናትን በመመልመል ጦር መሳርያ ያስታጠቁ ታጣቂ ክፍሎች ወይም ጦር ሃይሎች፣ እና

(ሠ) ከፍተኛ ሙስናን የመሩና የተሳተፉትን የሰክረተሪው ሪፖርት በመዘርዘር ያቀርባል።

  • ኢትዮጵያዊን፣ኤርትራዊንና ሌሎች የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያ መንግሥት፣የኤርትራ ከፍተኛ አመራሮችን በመለየት በአንቀጽ (1) እንደተገለጸው ከሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስልጣንና አመራሮች ያላቸው ተሳትፎና እንቅስቃሴ በአንቀጽ (1) እንደተገለጸው፣ መጠነኛ ንብረቶችና ዋጋቸውን መተመንና፣
  • ኢትዮጵያዊ፣ ኤርትራዊና የውጭ ገንዘብ ተቋማት በማወቅ መሳርያዎች፣ጦሮች፣ገዳይ ያልሆኑ መገልገያ ሆነው በሶስተኛ ፓርቲ ለጦር አገልግሎት እንዲውሉ ለኢትዮጵያ ጠላትነቶች ያስተላለፉ ነጥሎ በማውጣት በሪፖርት መግለጽ፣

(ለ) ፎርም–በን ኡስ ክፍል (ሀ)  የተጠቀሰውን ሪፖርት የሚቀርበው በሚስጥር ሳይሆን እንደማንኛውም ለሁሉም ክፍት ሲሆን ምስጢራዊ መረጃዎች የያዘ ሊሆን ይችላል፣

(ሐ) በኢትዮጵያ ስለ ተጠያቂነት እድገት ሪፖርት—

180 (መቶ ሰማንያ) ቀናት ይህ ተግባር እንደተፈጸመ 180 (መቶ ሰማንያ) ቀኖች ከዚያ በኋላ የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት (ሰክረተሪ ኦፍ ስቴት) በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰብዓዊ መብቶች፣ በስብዓዊነት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ተጠያቂነት ሪፖርት እድገት ለኮንግረስ ያቀርባል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop