December 27, 2024
3 mins read

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

471299790 1615423966014723 5000438086577621437 n
ምነው አምላክ ሆይ ይህን ያህል ጠላኸን፤ ተጠየፍከን፡፡ የሠራሃትን አገር፣ የፈጠርከውን ሕዝብ ለሠራዊተ አጋንንት አጋልጠህ መሠወርህ ለምን ይሆን? ምን እስክንሆን ነው ለኦነግሸኔ የመከራ ውርጅብኝ አጋልጠህ የተውከን?

GfRcG4BXUAAGf0W

አዲስ አበባ እየጠፋች ነው፡፡ ሕዝቧ ብቻ ሣይሆን ታሪኳም ቅርሷም ቅርጿም ወዳልነበርነት እየተቀየሩ ነው፡፡ አንበሣ አውቶቡስ መልኩንም ስሙንም ቀየሩት፡፡ አመልካች ሥራ ፈላጊዎችን በአማርኛና ኦሮምኛ ፈትነው የኦርምኞቹን ሲያሣልፉ ያማርኞቹን ጣሏቸው፡፡ አቤት ግፍ! የኑሮ ውድነቱን ከጣራ በላይ ሰቀሉት፡፡ ቤቱን የሚያፈርሱበትን የአዲስ አበባ ኗሪ ለማፍረሻ ገንዘብ ያስከፍሉታል፡፡ ካልከፈለ ዕቃውን ይቀሙታል ፤ አፈናቅለውም የትም ይጥሉታል፡፡

470473581 1615420859348367 8355758726016504320 n

እነዚህ ወፍዘራሾች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየከመሩበት ያለው ከፍሎ የማይዘልቀው የታሪክ ዕዳ ከአሁኑ ያሣስበኛል፡፡ አይነጋ መስሏቸው በተለዬ እሽቅንድር አድርጓቸዋል፡፡ ጥጋብ ትቢታቸው ይሠሩት አሳጥቷቸዋል፡፡ የዕብሪተኞችን መጨረሻ ከደርግና ከወያኔ ሊማሩ አልቻሉም፡፡ የሁሉም ነገር መፍትሔ ጥይት ብቻ መስሏቸው ሕዝብን በጥይት አረር እየቆሉ አገር ማፍረሳቸውንና በተለይ አማራን መጨፍጨፋቸውን፣ ማፈናቀላቸውን፣ ማሳደዳቸውን፣ አግቶ ብዙ ገንዘብ ማስከፈላቸውን … በስፋት ቀጥለዋል፡፡ ያቺ ቀጭን የፍርድ ጊዜም አትቀርም፤ እየመጣችላቸው ነው፡፡ ያኔ ነው ጉዱ፡፡ ትልቁ ችግር የዐረመኔ አምባገነኖች ዳፋ ወይም ጦስጥምቡስ ለየዋሁ ዜጋ መትረፉ ነው፡፡

GfkEHLgbYAAhnOM

ኦነግሸኔ አቢይና ሽመልስ ሆይ! ሌላ የምላችሁ የለም፡፡ መልካም የግድያና የውድመት ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ወደአባታችሁ ቤት ወደ ሲዖል እስክትሸኙ አባታችሁ ሣጥናኤልን ቶሎ ቶሎ አስደስቱ፡፡ ከምታፈሱት የአማራ ደም ጅረት ደግሞ እያንደቀደቃችሁ ጠጡ፤ ሥጋውንም ብሉ፡፡ የቀረቻችሁን አጭር ጊዜ በደምብ ተጠቀሙባት፡፡ ግን ይብላኝ ለልጆቻችሁና ለቀሪው ምሥኪን ኦሮሞ፡፡

470499944 1145987473755918 1132103333508863737 n

 

Ynegal Belachew

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop