ይድረስ ለቲክቶከኛው ትውልድ!! እንደውቅያኖስ ጥልቅ ከሆነ የጥበብ ሰው ጸጋዬ ገብረ መድኅን


 ” ቃል አይሞትም ይሏል እንጂ፥
እስትንፋስ ይሞታል ቅሉ
ቃሌ በፅንሱ በነነ፥
እፍ አልሺውና በሽሉ።”
  ቃል ቃተተ ፲፱፻፶፮
ጸጋዬ ገብረ መድኅን

***

እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ የሆነውን ሰው በሕይወት ከማለፉ ጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ቃለ መጠይቅ አድርገው ከነምሥሉ ላስተላለፉልን ካሉበት ክብርና ምሥጋና ይድረሳቸው ። ትልቅ ሥራ ሠርተዋል። ትንሹ ሥራ ደግሞ ይኸው – ጥድፊያና ወከባ በበዛበት በዚህ  የዲጂታል ዘመን ከጊዜ አንፃር ይህንኑ ሁለት ሰዓት ያህል የሚረዝመውን ቪድዮ በአንዴ ለማየት ለአብዛኛው የቲክቶክ ትውልድ አያመችም። ስለዚህ የመረጡትን ክፍል ለማየት እንዲችሉ ለማነሳሳት በማሰብ ቀስቃሽ ይሆናሉ በሚል እሳቤ ከዛው ውስጥ የተወሰኑት ከዚህ በታች ተቀነጫጭበው በፅሁፍ ቀርበዋል። ኾኖም ቁርጥራጩ ጥቅስ ከምንም ይሻላል እንጂ ሙሉውን አይቶና ሰምቶ ከነአውዱ ማገናዘብን አይተካም። የምንጩ ርዕስ ከላይ ማያያዣው (ሊንኩ) የተቀመጠው Interview  with Legendary Poet Laureate Tsegaye G/ Medhin ሲሆን የየተጠቃሾቹ የጊዜ አመላካቾች በየቅንፉ ያሉት ናቸው። ከድምፅ ወደ ፅሁፍ ሲገለበጥ ሊኖር ለሚችለው ግድፈት ይቅርታ። 
(ጌ.ማ.ፍ. ፳፻፲፭)

ባለቅኔው ጸጋዬ እንዲህም ብሎ ነበር።

” … ከኢትዮጵያ ከጥንቱ ከባህሉ ጋር ተያይዞ የመጣ ሥርዓት ደግሞ አለ። የሴት ልጅ  የነበራት ሥፍራ ከፍተኛ ነው። …የአሜሪካ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን ብዙ ጊዜ ይፈጅባታል ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ንግሥታት ሴቶች ከነገሡ ብዙ ዘመን ነው። … ለወንዴነት የሚባለው አባባል ጀግንነትን ከሴትነት ነጥሎ ነው የሚያየው። እኛ ግን ጣይቱን ተከትለን ነው አድዋ የሄድነው፡፡… ”

(8:58) ጸ.ገ.መ.
” … ጠመንጃ ነፃነት አይሰጥም። ሰጥቶም አያቅም።…
ተኩሶ የያዘ ተተኩሶበት ይወርዳል። … “
(18:23) ጸ.ገ.መ.
” … ወሳኙ ሕዝብ የተቀበለው ነው። … “
(26:55) ጸ.ገ.መ.
 “ሰው ወደ ማርስ የሚሄደው መሬት ፍለጋ ነው፡፡ … መሬት በጣም ጠቧል። … ወልቃይት የመሬት ነገር ነው፡፡ ገና እሳት ሆኖ ይወጣል። … የቴዎድሮስ አገር ነው። … እንደዚህ ቀላል ነገር የለም። …”
(31:55) ጸ.ገ.መ.

“ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ጥሩ አርአያ አልሆነችላቸውም። ለኮለኒያሊዝም ጥሩ አርአያ አልሆነችላቸውም። ምኒሊክን አይወዱም። ቴዎድሮስን አይወዱም።…
ና ውጣ ብሎ ጠርጎ ያስወጣ የለም። በጥቁር ዓለም ውስጥ በታሪካቸው የለም።”
(33:05) ጸ.ገ.መ.

” … የሥነጥበብ ሰው በቁና አይሰፈርም። … “

(45:50) ጸ.ገ.መ.

” … ሕዝብ አውቋል። …ሕዝብ ቀድሞ መንግሥት ጭራ ሆኖ ኋላ ይጎትተዋል። … reverse ነው ሲትዌሽኑ … ብዙ ችግር አለ በኢትዮጵያ … ግን የዓለም ሕዝብ ያልተቸገረውን ተቸግረን አናውቅም። … ስለቻልነውም ነው የምንቸገር ይመስለኛል። … ላይችል አይሰጥም። እና ይችላል። ግን እኔ እንደሚያሸንፍ አልጠራጠርም።”
(50:57) ጸ.ገ.መ.

” … ጴጥሮስ … ወቅት የፈጠረው ሰው ማለት ነው። … ያ ዓይነት ሰው ለዛሬም መድኅኒት ነው። … በድንጋይ ሐውልት አስሮ ቁጭ ማለት ሌላ ጉዳይ ነው። … አንደበቱን ግን መድረክ ላይ አውጥቶ ማንቀሳቀስ መስማት የትውልዱ መብት ነው። … በተለይ ቤተ ክህነት በእንዲህ ዓይነት ጣር ውስጥ ባለችበት ጊዜ  የፖለቲካ ካድሬዎች መጫወቻ ስትሆን እንደ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ ናቸው ያባቴን ቤት የንግድ የቁማር ቤት አታድርጉ ብለው ጅራፋቸውን የሚያነሱት። … ”
(53:50) ጸ.ገ.መ.

” … ኩሽ ነው ምድሩ። እሳት ነው አርማው። … ካም ሰላም ማለት ነው። … ካም ጥቁር ሆኖ ግን የውጭ ደም አለበት። እንደኛ ዓይነት ማለት ነው። … ኢትዮጵያዊ በሙሉ ጥቁር ሆኖ የውጭ ደም አለበት። … ኩሽ ጥቁር አፍሪካዊ አባት ነው መሠረቱ። ስለዚህ ከኩሽ ሥልጣኔ ተነስቶ ከሌላ ደም ጋር ፊዩዝድ የሆነው ካም ተደምሮበት ነው የግብፅ ሥልጣኔ  ሰማይ የደረሰው። የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ የኑብያ ሥልጣኔ፣ የሜሮን ሥልጣኔ፣ … በመሠረት ምድሩ ላይ የነበረው የምድሩ ባለቤት ኩሽ ነው። … የሰው ዘር መጀመሪያ ሲፈጠር የተፈጠረበት ቦታ ያ ነው። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ አካባቢ። … አውሮፓውያን … ግንዳቸው እኛ መሆናችንን ፈልፍለው አግኝተው ያሳወቁን እነሱ ናቸው። … የዓለም ግንድ እኛ መሆናችንን…”
(56:20) ጸ.ገ.መ.

“… ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል። እኔ ወሎዬ ይግደለኝ እላለሁ ብዙ ጊዜ። … ወሎ እስላሙ ያርዳል። አንድ በግ አርዶ ያ በስመአብ ወልድ ይላል። ያ ቢስሚላኢ ይላል።  … አንድ ቃል እኮ ነው። … ብሎ አንዱን በግ ቆርጠው … በሰላም አብረው … ይሄ ብስለት ነው። ርቀት ነው።…”
(1:05:05) ጸ.ገ.መ.

” …ኦሮሞ ነኝ ማለትህ አማራ አይደለሁም ማለት አይደለም። አማራ ነኝ ማለትህ ትግሬ አይደለሁም ማለት አይደለም። አማራ ሲል ሀም ሀራ አዲስ ሀም … ለምን አዲስ ጨመርክበት? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ተቀበልኩኝ ሀዲስ ኪዳንን … ሀም ነኝ ግን አዲስ ሀም ነኝ ። … አማራን አማራ የሚያደርገው አዲስ ካም መሆኑ ነው። ሀይማኖተ አበውን ክርስትናን መቀበሉ ነው።… ሦስተኛ በአማርኛ መናገሩ ነው። … ”
(1:06:40) ጸ.ገ.መ.

” … ሬቮሊሽን ነው አማርኛን የፈጠረው። … ፊደሉ የግዕዝ ፊደል ነው። ከሳባውያን ነው የመጣው። ሳባውያን ደሞ የኢትዮጵያ ናቸው።… ሳውዲ አረቢያ ትላንትና ነው የወሰደው። …”
(1:09:55) ጸ.ገ.መ.

” … ኢትዮጵያን ማዳን ማለት መሠረቱን ማወቅ እውነቱን ማወቅ … እውነትንም ታውቃላችሁ ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል ነው ያለው። … “
(1:11:05) ጸ.ገ.መ.
” … እኛ ማንነታችንን ማወቅ ያስፈልገናል። …ኦሮሞ የትግሬ ወንድም ፣ ትግሬ የአማራ ወንድም ፣ አማራ የጉራጌ ወንድም ፣ ጉራጌ የሶማሌ ወንድም ፣ … የኩሽ ልጅ – የካም ልጅ አንድ መሆኑን መጀመሪያ ማረጋገጥ … ችግር የሚፈጥሩት ጎሰኞች ጠባቦች ለሥልጣናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አፈር ድሜ ቢበላ ግድ የላቸውም። …”
(1:11:40) ጸ.ገ.መ.
” … የኢትዮጵያ ጉዳይ አሻሚ እስከሆነ ድረስ የአንተም ስም አሻሚ ይሆናል። … “
(1:18:10) ጸ.ገ.መ.
” … ብዙ ዓይነት ስሞች ከጀርባህ ይፈጠራሉ። አንተ ግን ጉዞህን – መንገድህን መቀጠል ነው። … “

(1:18:55) ጸ.ገ.መ.

“… አባቶቻችን አብሮ መኖር ስለሚያውቁ ነው የስምንት ሺህ ዓመት ሥልጣኔ ያቆዩን። … ስለዚህ ይኼ የኔ ዘር ካንተ ይበልጣል የሚል የሰይጣን ጨዋታ ቢቀር ይሻላል። … ማንም ከማንም አይበልጥም። … ”
(1:25:55) ጸ.ገ.መ.

“… የጎሳ የበላይነት የባርነት አገዛዝ ነው። … የአንድ ጎሳ ፈላጭ ቆራጭነት ነው ባርነት። … አንተ አትበላም አንተ ከበላህ እኔ አፈር እበላለሁ ማለት ሰይጣናዊ ነው። የሰው አይደለም። አመራርም አይደለም። ጭለማ ነው።… ”
(1:27:40) ጸ.ገ.መ.

” … እንዴት ሰው ሕዝቡን ጠልቶ የጠላውን ሕዝብ እገዛሀለው ይላል? … “

(1:30:10) ጸ.ገ.መ.

“… ሆሞ ሳፒያን ሰው ቃላት መፍጠር የጀመረው በአንደበቱ አፍሪካ ውስጥ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የመጀመሪያው  ሰው። … ”
(1:31:30) ጸ.ገ.መ.

” …የበላበትን እጅ መብላት መካድ መካካድ … ኢትዮጵያን የሚገል ይኼ ነው። አገር የሚያጠፋ። … ይዋሻል። ይቀጥፋል። ተንሰራፍቶ ቁጭ ብሎ አፉን እየው ተመልከተው ገፁን ቅጥፍ እያደረገ እግዚአብሔርን አይፈራም። …”
(1:40:45) ጸ.ገ.መ.

” … ዓለምን አታክቷል የእኛ አበሳ ። አበሳ ፋብሪኬት በማድረግ በጭራሽ የሚችለን ጠፋ። … ”
(1:44:50) ጸ.ገ.መ.

” … ትላንት መጥቶ መስመር ያሰመረው ኮሎኒያሊስት አንዱ ዘረኛ … አታልፍም በዚህ ይለዋል ። … ስለዚህ እገሌ መስመር አሰመረ ብለህ ሕዝቡን አታሰቃይ። … የአንተ ሥራ መጠበቅ ነው። … የሕዝብ አሽከር ነህ። … ትበላለህ ደሞዝ ጠብቅ። … ልትነግስበት አይደለም የቀጠረህ። … ሕዝቡ የት እንደሚሄድ መቼ እንደሚሄድ ለምን እንደሚሄድ ያውቃል ። … ስለዚህ  … የሕዝቡን ፈቃድ ተግባር ላይ ማዋል ነው እንጂ እገሌ ባሰመረው … ያውም በማይታይ መስመር … ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች ሕዝቡን ይከተሉ። … “

(1:48:09) ጸ.ገ.መ.

” … የአሁን የጥቁር የአፍሪካ መሪ ጭንቅላቱ ሌላ ነው። ጭንቅላቱ ወይ የአረብ ነው። ወይ የአይሁድ ነው። ወይ ጣልያን ነው። አፍሪካዊ እኮ አይደለም።  እና የእዚያኛውን ፍላጎት ነው እዚህ እሚያሟለበት ።… እና የሕዝቡ መከራ ነው የኾንነው ። … መሪ ማለት ገደል እሚያገባ ማለት አይደለም ። እኛ አገር ሕዝቡን ገደል ነው የምናገባው። ስለዚህ የሕዝቡን ፈቃድ ሙሉ። ትልቁ ፈተናችሁ ያ ነው። አንድ ሕዝብ ፈቃዱ ተሟልቶለት በሰላም ካደረ  በቃ። … ሲከለክሉት ነው ጦር የሚነክሰው። ድንጋዩን ማሾል ይጀምራል።…”
(1:50:40) ጸ.ገ.መ.

” … እኔ ምን አደረገኝ የሱዳን ኩሽ? ለምን መጥቶ አዲስ አበባ ተንቀባሮ ብሩ ካለው … ምንድነው ችግሩ? ምንድነው ጣጣው? ወንድሜ እኮ ነው። …”
(1:52:16) ጸ.ገ.መ

” … ክርስቶስ ሄደ አይደለም እንዴ? ግብፅ መጣ አይደል? ግብፅ መጥቶ ተምሮ ሄደ። እየው ሕፃናት ያርዳሉ። ሥርዓት ነው ብለው።  ሄሮዶስ የአይሁድ ንጉሥ እረድልኝ ሕፃናቱን አለ።  ሕፃናት የሚያርድ ከልቸር ነው ያለው። ሸሸ። ይኼ ልጅ እናቱ እንዲታረድባት አልፈለገችም። የት ሸሸ? አውሮፓ ሸሸ? No they were barbarians … civilization የላቸውም። እዛ ቢሄድ ይገሉታል። የሠለጠነ ቦታ የት ልሂድ ሲል ጥቁር ግብፅ  ነው የመጣው። … ሰላም አገኘ አይደለም? ተምሮ ተመለሰ። ሲመለስ አልተቻለም። … ሲመለስ የራሱን ካህናት ባንዴ ዜሮ አደረጋቸው በአሥራሁለት ዓመቱ ። መቅደሳችን እንዳትደርስ አሉት። መቅደስ ባባቴ አትነግዱ ብሎ በጅራፍ። … So he travelled independently … አይምሮ ያለው እዚህ ነው። … ያደገው ከጥቁር ጋር ነው። … They can’t stand his smartness. He is too much for them. They hanged him. These are barbarians. … ሥልጣኔ የሚሰጠው ኩሽ ነው። መጀመሪያ ሰው የተፈጠረው እዛ ነው። ጥበብ የተቀናጀው እዛ ነው። መርከብ የተሠራው እዛ ነው። … ብዙ ተዓምር ሠርተዋል። … እኛጋ … ይታያል። የቤተክህነቱ ሥርዓት ግልጥ ብሎ ይታያል። … ቁልቢ ሂድ ታየዋለህ ሥርዓታቸውን ። … የቅኔ ምሽት ሂድ።… ሼህ ሁሴን … ሌሊቱን ቁጭ ብለው ነው የሚያድሩት ሲቀኙ። ጭንቅላት የሚያዞር fantastic የሆነ ቅኔ ነው የሚቀኙት። …That is why the black mind still exists. … ”
(1:52:35) ጸ.ገ.መ

***

F37EPAOXYAA vqk 1 1 1
Previous Story

ፋኖ ታላቋን ከተማ መልሶ ያዘ | የአመራሮች የባህር ዳር የጭንቅ ውሎ መረጃ ወጣ

185447
Next Story

ፋኖ በአራቱም ግዛት ድል ተቀዳጀ | ደብረታቦር፣ እብናት፣ አዲስ ዘመን! “ከተማው በፋኖ ተጥለቀለቀ”| የአማራ ድምጽ ዜና |

Go toTop