mengesha syum
1ኛ ) ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም ሲሉ የሰጡት ቃለ መጠይቅ
2ኛ ) ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ ታህሳስ 5 ቀን 2018ዓም ወልቃይት በትግራይ ስር ነበረ ሲሉ የሰጡት ቃለ መጠይቅ
ማሳሰቢያ፦
እነዚህን ሁለት የሚቃረኑ ቃለ መጠይቆችን አዳምጦና ለምን ብሎ መርምሮ መንስኤውን ማንም በቀላሉ ሊረዳ ይችላል፡፡
ቃለ መጠይቅ ቁጥር 1፦
ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም የሰጡት የመጀመሪያው ቃለ መጠይቅ
Online ምንጭ ፦ https://www.youtube.com/watch?v=N4jPUj_3FYI&t=1489s
በዚህ ቪኦኤ ባቀረበው ቃለ መጠይቅ ውስጥ በ23ኛው ደቂቃ ላይ ራስ መንገሻ ስዩም “”እኔ ልጅ ሆኜ ሳድግም ሆነ በኋላ ትግራይን ሳስተዳድር ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም’’ ብለ እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም የሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው፡፡
ቃለ መጠይቅ ቁጥር 2፦
ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እኤአ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓም የሰጡት ሁለተኛው ቃለ መጠይቅ
Online ምንጭ ፦ https://www.youtube.com/watch?v=Ueh8YnWvFF4
እኔ ልጅ ሆኜ ሳድግም ሆነ በኋላ ትግራይን ሳስተዳድር ወልቃይት በትግራይ ስር አልነበረም ብለው እኤአ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ ላይ መስማት ይቻላል፡፡
ወያኔ ቃላቸውን አጥፈው አዲስ ቃለ መጠይቅ እንዲሰጡ ባሳደረባቸው ተጽእኖ ይመስላል በነጻ ህሊናቸው በፊት የሰጡትን ቃል ሸምጥጠው ወልቃይት በትግራይ ስር ነበረ ያሉበትን ይህንን የ2018ቱን ቃለ መጠይቅ ሰጡ፡፡ ይህ የ4 ደቂቃ አጭር የቃለ መጠይቅ ዘገባ በድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ጋር ካድረጉት ቆይታ ተቀነባብሮ የቀረበ መሆኑን ከቪድዮው ማወቅ ይቻላል፡፡
ማስታወሻ፦ ሁለቱም ቪድዮወች በእጃችን ይገኛሉ ፡፡