ሚያዝያ 2013 ከፈንታሁን ጥሩነህ ዋሺንግተን ዲ ሲ ዐፄ ኢዛና ሃሌን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ አሥር ዓመት ከገዛ በኋላ ከልጆቹ መሃል የአክሱም መኳንንት ካሌብን አነገሡ፤ ስመ ንግሡም ዳግማዊ ዐፄ እለ አጽብሃ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ መሲሃ እግዚአብሔር ተብሎ በ483 ዓም ነገሠ። ሠላሳ አምስት ዘመን ከገዛ በኋላ ሃይማኖቱ ኦሪታዊ የሆነ ዱኖባስ ፊንሐስ በናግራን [አሁን የመን ተብሎ በሚታወቀው] የክርስቲያኖች ቁጥር መብዛቱን አይቶ በግዛቱ ውስጥ የነበሩትን ከአራት ሺ በላይ ክርስቲያኖችን የገደለውን ንጉሥ በማስወገዱ ይታወቃል። ፊንሐስ** ትውልዱ ኑባ፣ እድገቱ ኢትዮጵያ ነበረ። ፊንሐስ ከመርዌ ወደ አክሱም ሂዶ የቤተመንግሥት ሥርዓት እና የኦሪትን መጻሕፍትንና ቅዱስ ወንጌልን