በአማራ ክልል ውስጥ በተካሄዱት ሰልፎች ላይ ለምን “በኦህዴድ” በተለይ በዶ/ር አብይ ክህደት ተፈፅሞብናል –

ሰሞኑን አማራ ክልል ውስጥ በተካሄዱት ሰልፎች ላይ ለምን “በኦህዴድ”  በተለይ በዶ/ር አብይ ክህደት ተፈፅሞብናል የሚሉ ድምፆች ተሰሙ??? ለዚህ ጥያቄ እርካብና መንበር”  የሚል ርዕስ ያለው የዶ/ር አብይ  መፅሃፍ መልስ ይኖረው ይሆን? አብረን እንከታተል…

መሰረት ተስፉ (Meserettefu4@gmail.com)

የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በተለይም ከትግራይ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ተሰልፎ በመታገል የደርግ ስርዓት ከስልጣን እንዲወገድ የበኩሉን ድርሻ እንደተወጣ ይታወቃል። እኔም ከተራ አባልነት እስከ አመራርነት በትግሉ ውስጥ ስለቆየሁ የአማራን ህዝብ የትግል ተሳትፎ በሚገባ እመሰክራለሁ።  የአማራ ህዝብ የትግሉ ተሳታፊ የነበረው እኩልነት የሰፈነባት፣ ከአፈናና ከአድሎ ነፃ የሆነች፣ ፍትሃዊነት የተሞላባት፣ ሰላም የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያን ገንብቶ የተረጋጋ ህይወት መምራት ይቻላል ከሚል ፍላጎት ነበር። እንዳለመታደል ሆነና ግን ከደርግ ውድቀት ማግስት ጀምሮ የህወሃቶች እኩይ ፍላጎት በተግባር እውን ሆነ።  የህወሓቶች እኩይ ተግባር የጀመረው የአማራ የሆኑ መሬቶችን እየሸነሸኑ የ’ኛ ነው ወደሚሉት ክልልና ወደሌሎች አከባቢዎች እንዲካተቱ በማድረግ ነበር። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ለረጅም ጊዜ በስትራቴጅክ ጠላትነት ፈርጀውት የነበረውን የአማራ ህዝብ የተለያዩ ስሞችን በመለጠፍ ማሳደድ፣ ማሰርና መግደል ቀጠሉ። በአጠቃላይ ከፋፍሎ የመግዛት መርሆዎች ላይ ተመስርተው አማራን የማዳከም ፕሮጀክታቸውን ለማስፈፀም ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ይህን ያደረጉት ደግሞ  ዋና ዋና የሚባሉ የፌዴራል የፀጥታ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ  ተቋማትን በመቆጣጠር እንደነበር ሁላችንም የምንዘነጋው አይመስለኝም። እንዲህ አይነቱን በ’ኛ ዘመን በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ደባ “ክህደት ቁጥር አንድ” ብላችሁ ልትሰይሙት ትችላላችሁ።

ከላይ የተገለፀው የህወሓቶች ክህደት ያስከተለው ግፍ ሲበዛ መሸከም ያልቻለው የአማራ ህዝብ አሁንም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በተለይም ከኦሮሞ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ የተበላሸውን የህወሃት/ኢህአዴግ ስርዓት ገፍቶ በመጣል የለውጥ ተስፋ መሰነቁ ይታወቃል። በተለይ ከለውጡ በኋላ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን መንበር ላይ የወጣው ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ስለ እኩልነት፣ ስለእኩል ተጠቃሚነት፣ ስለፍትሃዊነት፣ ስለየህግ የበላይነት፣ ስለእድገት፣ በአጠቃላይም ስለኢትዮጵያ ብልፅግና ድምፁን ከፍ አድርጎ በመዘመሩ ምክንያት ልክ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የአማራ ህዝብ ደስታም ቀላል አልነበረም። በወቅቱ ብአዴኖችና ኦህዴዶች የነበራቸውን ሽር ብትን ያለ ግንኙነትም ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው።

ቀናት በወራት እየተተኩ በሄዱ ቁጥር ግን “ኦህዴዶችም” እንደ ህወሃቶች  ሁሉ ድብቅ አጀዳ እንዳላቸው የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ከነዚህ አመላካች ሁኔታዎች ውስጥ ያልታሰቡ ወታደሮች ቤተመንግስት ገብተው በነበረበት ወቅት / አብይ አዲስ አበባ መሃል ላይ ተቀምጦ የሱሉልታ፣ የቡራዩና የሰበታ ህዝብ መንግስታችን ተነካ ብሎ ግልብጥ ብሎ ሊመጣ ነበር ያለው ተጠቃሽ ነው። ይህ ንግግር አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የኦሮሞ ብቻ እንደሆነ ተንደርጎ እንዲቆጠር የታለመ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ የሆነ ውስጠ ወይራ ንግግር ነው በሚል የተረዱት ሰዎች ቁጥር ቀላል አልነበረም። በነገራችን ላይ አነአቶ ሌንጮ ለታ ሳይቀሩ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ኦሮሞ “እነሱም” እያስተዳደሩት እንደሆነ ሲናገሩ የተሰሙት ከዚህ ተነስተው ነው ቢባል መሳሳት አይሆንም። በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ጦርነት እንከፍታለን ከሚለው የዶ/ አብይ ማስፈራሪያ ጀምሮ የዴሞግራፊ ለውጥና ሌሎች መሰል ጉዳዮችም የኦህዴዶችን” ድብቅ አጀንዳ ከሚያሳብቁት ሁነቶች ሊመደቡ ይችላሉ። ኦሮሚያ ክልል በተከታታይ ዙሮች በአስር ሽህዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል እያሰለጥነ ባለበት ሁኔታ ዶ/ር አብይ ደሴ ሄዶ በነበረበት ወቅት የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ማሰልጠኑ ትክክል እንዳልሆነ የተናገረውም ሌላው የድብቁ አጀና ማሳያ ነው ተብሎ ይጠቀሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምሥራቅ ወለጋ ዞን የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት የንጹሃን ህይወት አለፈ

ከሁሉ በላይ ግን ከላይ የተዘረዘሩት ክስተቶች የፈለቁበትና በብዙ ሰዎች ዘንድ የዶ/ር አብይ እሳቤ ነው ተብሎ የተወሰደው ታላቅ የሆነ ፕሮጀክት ሳይታሰብ ወደ አደባባይ መውጣቱ ኦህዴዶች ድብቅ አጀንዳ እንዳላቸው አጉልቶ ሳያወጣው አልቀረም። ይህ ድብቅ ፕሮጀክት ሳይታሰብ ወደ አደባባይ የወጣው የኦሮሞ ልሂቃንና ከፍተኛ የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮች በተገኙበት ሰፊ አዳራሽ ውስጥ አቶ ሽመልስ  በድብቅ ያደረገው ንግግር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ወደ ህዝብ ከተሰራጨበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚል እምነት አለኝ። አቶ ሽመልስ ያደረገው ንግግር  በርካታ ጉዳዮችን ያዘለ ቢሆንም ለዛሬ የተወሰኑትን ብቻ በሚከተለው መልኩ ለማብራራት እሞክራለሁ። በአቶ ሽመልስ ንግግር ውስጥ ያሉትን ነጥቦች በየፈርጃቸው ለይቸ ለማስቀመጥ ስሞክር ዶ/ር አብይን ጨምሮ “ኦህዴዶች” በአደባባይ ለህዝቡ ከሚናገሩት ጋር እያነፃርኩ እንደማቀርባቸው ይታወቅልኝ።

ስለብልፅግና ፓርቲ አላማ፡

“ኦህዴዶች” ለህዝቡ የሚነግሩት ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች የሚያካትት፣ በእኩልነት የሚያይና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚተጋ ፓርቲ እንደሆነ አድርገው ነው።

ድብቁ ፕሮጀክታቸው ግን  ህወሓቶች ኢህአዴግ የሚባለውን ግንባር የፈጠሩት ሌሎች ክልሎችን ለማሾር እንዲያመቻቸው እንደነበረው ሁሉ ኦህዴድም ብልፅግናን የፈጠረው በተመሳሳይ መንገድ ሌሎች ክልሎችን ለመቆጣጠር እንዲችል ነው በሚል ያሰቀምጠዋል።

ስለሃገር መሪ፡

“ኦህዴዶች” ለህዝቡ የሚነግሩት ብልፅግና ፓርቲ በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እስከሆነ ድረስ ቢሸነፍ ስልጣኑን ለአሸናፊው ፓርቲ በደስታ የሚሰጥ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ ነው።

ድብቁ ፕሮጀክታቸው ግን ከዚህ በኋላ ሃገር መምራት ያለበት በዋነኛነት ኦሮሞ፤  እሱ ካልሆነ ደግሞ ኦሮሞ የፈቀደለት አካል ብቻ ነው የሚል ፍፁም ፀረዴሞክራሲያዊ፣ አምባገነናዊ እና አመክኗዊ የሆነ እሳቤን አንግቧል።

የፌዴራል የስራ ቋንቋዎች፡

“ኦህዴዶች” በአደባባይ ለህዝቡ የሚነግሩት ብዙ የስራ ቋንቋዎች መኖራቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያዳብራሉ፤ እዛው ሳሉም አንድነትን ያጠናክራሉ እያሉ ነው።

ድብቁ ፕሮጀክታቸው ግን አፋርኛ፣ ሶማልኛና ትግርኛ የፌዴራል መንግስቱ ተጨማሪ ቋንቋዎች እንዲሆኑ የተደረገው አማርኛን ለማዳከም ነው የሚል እንደሆነ ተረድተናል። አማርኛ መዳከም ያለበት ደግሞ አፋን ኦሮሞ ከፍ እንዲልና ከአማርኛ ብልጫ እንዲኖረው ያለመ ፍላጎት ስላላቸው እንደሆነም ድብቁ ፕሮጀክት ያስቀምጣል። ይህን እቅዳቸውን  በተግባር እንደጀመሩትም ከአንዳንድ ክልሎች ጋር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማየት መረዳት ይቻላል።

የአዲስ አበባን ጉዳይ፡

አንዳንድ አመርሮችና አባላት  በግልፅ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት የሚሉባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንደ “ኦህዴድ” ለህዝቡ የሚነግሩት አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት እያሉ ነው።

“ድብቁ ፕሮጀክታቸው ግን ሌሎች ፌዴራላዊ የሆኑ ዋና ከተሞችን በማቋቋም አዲስ አበባን ዋጋ አሳጥቶ ቀስ በቀስ ወደ ኦሮሚያ መጠቅለል ነው። ይህ እቅዳቸው በተግባርም ሰዎች በማስፈር፣  መታወቂያ በማደልና በመሳሰሉ መልኮች እየተገለፀ እንደሆነ እያየን ነው።

እቅድ ማፈፀሚያ መንገዶች፡

ኦህዴዶች ለህዝቡ ፊት ለፊት የሚናገሩት እቅዶቻቸውን ሲያስፈፅሙ ግልፅነት የተሞላበት፣ ተጠያቂነት የሰፈነበትና በመርህ ላይ የተመሰረተ አሰራር በሚያሰፍን አኳኋን እንደሆነ አድርገው ነው። እንዲያውም መጀመሪያ አከባቢስ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሳይቀር ህዝቡ በቀጥታ ሊያየው በሚችል መንገድ ይሆናልም ተብለን ነበር። ከዚህ አልፎም የሽኩቻ፣ የቡድነኝነት፣ የመጠቃቃት በአጠቃላይም መርህ አልባ የሆነ አሰራር እንደማይኖር ቃል እንደተገባም አስታውሳለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች የስር ተላላኪዎቻቸውን ሕዝቡ ኢሕአዴግን እንዲመርጥ አልቀሰቀሳችሁም በሚል ከሃላፊነታቸው ማውረዳቸው ተዘገበ

በድብቁ ፕሮጀክት ግን የእቅድ ማስፈፀሚያ ተብሎ የቀረበው ዘዴ ማሳመንና ማደናገር (Convince & Confuse)  እንደሆነ ተገልጿል። ምናልባትም ከሚታየው ተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው በመነሳት መሸንገል፣ ማታለልና ማስገደድም እንደ አላማ ማስፈፀሚያ ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆነ ለመገመት አይከብድም።  

ከላይ የተገለፁትና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው ሲታዩ ቁጥሩ ቀላል ነው የማይባል የኢትዮጵያ በተለይ የአማራ ህዝብ “በኦህዴድ” በዋናነት  ደግሞ በዶ/ር አብይ ተከድቻለሁ የሚል ቅሬታ እንዳሳደረ መረዳት ይቻላል። እዚህ ላይ በተለይ ዶ/ር አብይ ከድቶናል የሚለው ቅሬታ ለምን በረታ የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው ብየ አምናለሁ። በዚህ ረገድ ብዙ ምክንያቶችን መዘርዘር ቢቻልም አንባቢን ላለማሰለቸት ስል የተወሰኑ ጉዳዮችን ብቻ በመጥቀስ ለማሳየት እሞክራለሁ።

የቅሬታው አጠቃላይ መነሻ ዶ/ር አብይ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች በ’ኩልነት ያያል ሲባል እንዴት ለአንድ ብሄር ያደላል የሚል አረዳድ ይመስለኛል። ይህን ለማለት እየቀረቡ ካሉት ማረጃዎች ውስጥ ደግሞ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

  • ዶ/ር አብይ ኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የደህንነት አመራር ሆኖ ይሰራ በነበረበት ወቅት ለኦነግ መረጃ አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር ራሱ በመናገሩ፣
  • ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸው ወገንተኛ የሆኑ ንግግሮቹ፤
  • በተለያዩ ተቋማት በተለይ ደግሞ ከፀጥታ ጋር በተያያዙት ላይ የሚያደርገው አድሏዊ የሚመስለው የሰው ሃይል ምደባው፤
  • በዋነኛነት ደግሞ የአቶ ሽመልስ ንግግር የፈለቀው ከዶ/ር አብይ ነው የሚለው አረዳድ ነው ብየ እገምታለሁ። ይህን ለማሳየት ዶ/ር አብይ እርካብና መንበር በሚለው መፅሃፉ ውስጥ ያካተታቸው ማኪያቬሊያዊ እሳቤዎቹ ጎላ ብለው ይጠቀሳሉ። መፅሃፉ ውስጥ በተለይ “”… ስውር ውጥመድ ማዘጋጀት ይበጃል። ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን ነገር እያሳየህ ወደምትፈልገው ቦታ ውሰዳቸውና ጣላቸው። ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ የሚለውን ተረት ተርትባቸው።”” የሚለው አንቀፅ ዋነኛው ነው።

በዚህ የዶ/ር አብይ እሳቤ መሰረት ፊት ለፊት የሚታየው ለበሬው ሳር መቅረቡ ነው። ድብቁ አላማ ግን በሬውን በሳር እያታለሉ  ገደል እንዲገባ ማድረግ ነው። ይህ መሰሪ የሆነ እሳቤ “ኦህዴድ” ውስጥ ድብቅ የተግባር መመሪያ መሆኑን የአቶ ሽመልስ ንግግር በሚገባ ያስረዳል። ምክንያቱም ስለ ብልፅግና ፓርቲ ፊት ለፊት የሚነገረው ፓርቲው ሁሉንም እኩል የሚያይ፣ የሁሉም፣ ለሁሉምና በሁሉም የሆነ ሃገራዊ ፓርቲ ነው የሚል ነው። ድብቁ አጀንዳ ግን የሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን መብቶች መጠቀሚያ በማድረግ አማራን አዳክሞ “የኦህዴድን”  የበላይነት ለመፍጠር የታለመ እንደሆነ የሚያስመስሉት በርካታ ሁኔታዎች አሉ። በዚያ ላይ በተለይ አቶ ሽመልስ ባደረገው ንግግር ዙሪያ “ኦህዴድም” ሆነ ዶ/ር አብይ ህዝቡን የጠየቁት ይቅርታ እና ያቀረቡት ማስተባበያ የለም። በዚህ ምክንያትም ቀላል ግምት የማይሰጠው የኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ የአማራ ህዝብ በዶ/ር አብይ ተከድቻለሁ የሚል ስሜት እንደተፈጠረበት ለመረዳት የሚከብድ አይመስለኝም። በዚህ መንገድ እየትጓዙ ደግሞ አገራዊና ህዝባዊ አንድነትን ማጠናከር ቀርቶ ማስቀጠል እንኳ የሚቻል አይሆንም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአሲድ የተደፋባት ትግስት ቀብሯ ተፈጸመ

የመፍትሄ ሃሳቦች፡

  • ኦህዴድ እንደ ድርጅትና ዶ/ር አብይ እንደ ሃገሪቱ ጠ/ሚ/ር መጠን እየፈፀሙት ላለው ክህደት ለኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ ለአማራ ህዝብ ልባዊ የሆነ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባቸዋል። ዶ/ር አብይ በተለይ አቶ ሽመልስ የተናገረውን የቁማር፣ የሴራ፣ የጥሎ ማለፍና የሸፍጥ ፖለቲካዊ እሳቤ አላመነጨሁም ቢል እንኳ ከሱ እውቅና ውጭ ስለማይሆን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ይህን መሰሪ ፖለቲካዊ እሳቤ በፍፁም አላውቀውም ቢል ደግሞ ኦህዴዶች በሱ እየተመሩ የዶለቱት ኋላ ቀርና ፍፁም ፀረ ደሞክራሲያዊ እቅድ ነውና ባወቀበት ሰዓት ከይቅርታው በተጨማሪ ሃሳቡን ባፈለቁትና ባስፋፉት አመራር አባላት ላይ የማስተካከያ እርምጃ ወስዶ ለህዝብ ማሳወቅ ይኖርበታል።
  • ኦህዴዶች በውስጣቸው ያለውን የጎራ መደበላለቅ ለማጥራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በተለይ በተሳሳተ ትርክት ላይ ተመስርተው አማራ ላይ ያሳደሩትን ስር የሰደደ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል በሚገባ ፈትሸው ሊያስተካክሉት ቆርጠው መነሳት አለባቸው። ካለበለዚያ በደርግ መንግስት ተገዶ ለሰፈራ የተወሰደው ምስኪኑ አማራ ሁሉ “ነፍጠኛ” እየተባለ መጨፍጨፉ የሚያቆም አይሆንም። ጭፍጨፋው ካላቆመ ደግሞ አብሮ ለመኖር አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩ የሚቀር አይሆንም።
  • “ኦህዴዶች” የተዘፈቁበት የቁማር፣ የሴራ፣ የጥሎ ማለፍ፣ የቡድነኝነት፣ ሌሎችን አስተባብሮ አንዱን የማጥቃት፣ የሸፍጥ፣ የሽንገላ ባጠቃላይም የመርህ አልባ ፖለቲካዊ እሳቢያቸውን በደንብ አብጠርጥረው አይተው ሊያስተካክሉት ይገባል።
  • የግለሰቦችን በተለይም የዶ/ር አብይን አምባገነንነት ከማበረታታት ይልቅ ተቋማዊ አሰራር እንዲኖር በፅናት መንቀሳቀስ አለባቸው። ዶ/ር አብይን እንኳን አምባገነን እንዲሆን አበረታትውት ጠንካራ ትግል ተደርጎም ወደ ተቁማዊ አሰራር ለመመለስ አስቸጋሪ እንደሚሆን እርካብና መንበርን ያነበበ ሰው ይስተዋል ብየ ልገምት አልሻም። ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማጎልበት ሲባል የግለስብን ተክለሰውነትና አምባገነንነት ሳይሆን ተቋማዊ አሰራርን ማዳበር እጅግ አስፈላጊ መሆን መገንዘብ ያስፈልጋል።
  • “ኦህዴዶች” በውስጣቸው ያሉትን ችግሮች ፈትሸው ካስተካከሉ በኋላ ተከታታይ ኮንፈረንሶች በማድረግ ህዝቡ ውስጥ የተሳሳቱ ታሪካዊና አሁናዊ ሁኔታዎች ላይ የግንዛቤ ማስተካከያ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።
  • ከዚያም ከሁሉም ክልሎች የብልፅግና አመራሮች ጋር ቁጭ ብለው መተክላዊና መርህን መሰረት ያደረጉ ውይይቶችንና ትግሎችን በማድረግ ነጥረው መውጣት ይጠበቅባቸዋል። ጥያቄዎችና ፍላጎቶች ካሏቸውም መጠየቅና መታገል ያለባቸው መርህን መሰረት በማድረግ እንጅ የሴራና የጥሎ ማለፍ ፖለቲካዊ መንገድን በመከተል ሊሆን በፍፁም አይባም። ይህ መንገድ ለጊዜው የተሳካ ቢመስልም እንደማያዛልቅ ግን መረዳት ይኖርባቸዋል የሚል ሃሳብ አለኝ።

በሚቀጥለው ፅሁፌ ደግሞ ስለ ብአዴን የምለው ይኖረኛል።

እስከዚያው ቸር እንሰንብት!!!

3 Comments

  1. እጅግ በጣም ግሩም ጽሑፍ ነው፤ ከፈለጉ የድንዙዛንን ዐይን ያበራል።
    መሠረት ከፈቀድክልኝ አንድ ማስተካከያ ልሥጥ – ካመንክበትም በቀሪህ ላይ አስተካክል።
    ኦህዲድ “መርህ አልባ” አይደለም። መርህ አልባ ግንኙነት የሚባል ነገር የለም። ንግግር ማሞቂያ ሐረግ ነው።
    ኦህዲድ መርህ (principle) አለው። እርሱም በጽሑፍህም እንደተገለጸው አማራን በማጥፋትና ሌላውን በኦሮሙማ የገዳ ሥርዓት በመዋጥ ታላቋን የምሥራቅ አፍሪካ ኃያል አገር ኦሮምያን በአጭር ጊዜ ውሥጥ መመሥረት ነው። ይህን ትልቅ አጀንዳ ይዞ አማራን በየቀኑ ከትራንስፓርት መኪኖች እያወረደ ጭምር በየመንገዱና በየበረሃው የሚረፈርፍ የአክራሪ ኦሮሞ ሥዩመ ዲያቢሎስ ወሲአይኤ መርኅ አልባ ማለት እነሱ ራሣቸው ፈገግ እንዲሉ መጋበዝ ነው። የምትለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ መሡ!

  2. የኦሮሞ ጎሳ አባላት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ብቻ በአዲስ አበባ መንግስታዊ ምርጫ እስከመረጥን ድረስ የአዲስ አበባ ባለቤት ኦሮሞም ባይሆን ችግር የለውም ፤ ስለዚህም ኦሮሞ የአዲስ አበባ ባለቤት እንዳይሆን የምትፈልጉ ከሆነ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመጪው ምርጫ ሆነም በሌሎችም መንግስታዊ ምርጫዎች ተሳትፋችሁ አትምረጡ ፤ ከመረጣችሁ ግን እኛ ኦሮሞዎች የአዲስ አበባ ባለቤትነታችንን በገሀድ እንደምናውጅ እና አዲስ አበባም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር እንደምትተዳደር አስቀድማችሁ እወቁት ፤ ምርጫው የእናንተ ነው። በምርጫ ብቻ!!

  3. What does he did to you sir ? Did he abandon you by killing Amhara while he was supposed to kill Oromo and Tigray ? You were cheering kill Tigray and arrest TPLF ? now, the war is expanding to your territory , beyond your expectation!!

    Repent ,you children of pythons !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share