/

ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴሬሽን ምክር ቤት – በብርታኒያ እትዮጵያውያን

ቀን፡ ሚያዝያ  ቀን 213 ዓ ም    

      

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴሬሽን ምክር ቤት

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

:- በመተከልና አካባቢው ለረዥም ጊዜ ስለሚካሄደው የዘር ማጥፋት ዘመቻና የሃብት ውድመት እንዲቆም ሰለማሳሰብ፤

ለተከበችሁ የፌዴሬሽንና የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት አባላት

እኛ የመተከል እልቂት ያሳሰበን በታላቋ ብርታኒያ የምንገኝ እትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣

ማንኛውም መንግሥት ከዜጎቹ ጋር ባለው መስተጋብር ጥም ግዴታዎች አሉበት።  እነዚህም፣ አንደኛው አሉታዊ ግደውታው ሲሆን ማንንም ግለሰብ ከመግደል፣ አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ሰቆቃን  ከመፈጸም እና ሌሎች መብቶቹን ከመግፈፍ መቆጠብ ነው።  ሁለተኛው አዎንታዊ ግደታው ሲሆን ይህም ከላይ የተጠቀሱትን መብቶች ማንኛውም ቡድን ወይም ግለሰብ እንዳይገፈፍው በቂ ጥበቃ መስጠት ነው።  ይህም የመብት ገፈፋውና ጥቃቱ እንዳይፈጸም በቂ ጥበቃ ማድረግን፣ ሲፈጸም አጥፊውን በተገቢው መቅጣትንና ተጎጅውን በተመጣጣኝ መካስን ይጨምራል።በተልምዶ አባባል መንግሥት የዜጎቹን ደህንነትና  ሰላም መጠበቅ ዋነኛ መሰረታዊ ግዴታውእየተባለ የሚጠቀሰው ነው። 

ከዚህም አኩዋያ የኢትዮጵያ መንግሥት የመተክልን ሕዝብ ከፍጂትና ከአሰቃቂ የዘር ማጥፋት ድርጊት መጠብቅ መሰረታዊ ግዴታው ነው። እዚህም ላይ መንግሥት ማለት ከታችኛው ባለስልሥን ( ፖሊስ፣ የቀበሌ ሹም፣የወረዳ ሹም) ጀምሮ ሁሉንም  ባለስልጣኖች እስከ ጉልላቱ  ድረስ    ሲሆን፣  እነዚህ አካላቱ ሁሉ  በየፈርጃቸው ባለግደታና ተጠያቂዎች ናቸው  ማለት ነው። 

የዘር ፍጅት ወንጀል ዓለም አቀፋዊ ሕግ በመሆኑ በሀገራዊ ህግም በዓለም አቀፍ ሕግም ተጠያቂ የሚያደርግ ወንጀል ነው። የይርጋ  ጊዜ  ገደብም የለውም።በኢትዮጵያ ሀገራችን የዐማራ ሕዝብ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በርካታ በደሎች እንደሚደርስባቸው በየጊዜው የሚመዘግብ ሀቅ በመሆኑ ሁሉንም እዚህ ላይ መዘርዘር የዚህ ደብዳቤ ዋነኛ ትኩረት አይደለም።

የዚህ ደብዳቤ ትኩረት ባለፈው አንድ አመት ያህል እጂግ በጣም በተጠናቀረና በተደራጀ አኳዃን የመተክልን ዐማራና አገው ሕዝብ የጥቃት ዒልማ አድርጎ በሰፊው የሚንቀሳቀሰውን የዘር ማጽዳት  ዘመቻ ማስቆም ላይ የወጠነ ነው።

ይህ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በርካቶች የተገደሉበት፣ የቆሰሉበት፣ የዐካልና የሕሊና ሰቆቃ የተቀበሉበት፣ ንብረታቸውን በሰዓታት ውስጥ ያጡበት፣ በሕይወት የተረፉት ከሰፈርና ቀዬአቸው የተሰደዱበትና ለረሃብና ለዕርዛት የተጋለጡበት ነው።   የዘር ማጥፋት ጥቃቱ ራሱ ብቻ ሳይሆን፣ ድርጊቱ የተከናወነበት መንገድ በሰው ልጅ ሊፈጸም ይችላል ተብሎ የማይታዝሰብ በፍጹም ዘግናኝና ከመጠን ያለፈ ጭካኔ የተሞላበት መሆኑ ነው።  የሰቆቃውና የአሰቃቂ ግፉ  ጭካነያዊ ደረጃ እነዚህ ዘጎች ገና በሕይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ሰላባዎቹ ከተጨፈጨግፉ በሁዋል እንኳን አስከረናቸው ለግብዐተ መሬት የበቃበት የጅምላ አቀባበር፣ የግፉ መደምደሚያ በመደረጉ ከትውስታ ሊጠፋ የሚችል አይደለም።

የመተከል ዐማራና አገው ሕዝብም ሆነ ሌላው ዐማራ በሰላም ወቅት መረቱን አርሶ፣ ምርቱን አፍሶ ሌላውን ሕዝብ የሚቀልብ፣ በችግር ጊዜም የራሱን መሣሪያና ስንቅ ይዞ ያለ ደሞዝ ለዘመቻ ብቁ ሆኖ የሚቀርብ ነው። ለዚህም በቅርቡ ኅነግ  ሀገር ሊያጠፋ ዘመቻ ሲከፍት የዐማራ ሚሊሽያ በመባል ዘምቶ ከሌሎች ጋር ጥሩ ድል ያስገኘው  ገበሬ መልካም ምሳሌ ነው።ሀገራችን የምትከተለው ዘር ቶኮር ርዕዮት፣ ሕገ መንግሥቱና በዐማራ ላይ በሰፊው  ለሰላሣ ዐመታት ሲሰበክና  ሲስራጭ  የቆየው ትርክት ተጣምረው  ለዚህ ያበቁን በመሆኑ እኛ የምንቃወመው  ብቻ ሳይሆን  የሌሎች መንግሥታት መሪዎችንም  ነቀፌታ ያተርፈ መሆኑ በግልጽ  የሚታወቅ  ነው።   ከሁሉ ይበልጥ አሳዛኙና አሳሳቢው ነገር ደግሞ ድርጊቱ በመተከልም ሆነ በሌሎች ብዙ ቦታዎች ሁሉ ለበርካታ ዐመታት  መደጋገሙና አንድም ጊዜ የማስቆም በቂ እርምጃ አለመወሰዱ ነው።  ይህም መንግሥት ፈቅዶ የሚያደርገው ያስመስለዋል።

ከዚህም አስከትለን ስድስት ዋነኛ ነገሮች እንዲፈጸሙ በትህትና እንጠይቃለን።

፩። በመተከል ዐማራና አጐው ሕዝብ ላይ የሚደርገው የዘር ማጥፋት ዘመቻን መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያስቆም። ዘጎችን የመጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ፥

፪።  በዘር ማጥፋቱ ድርጊት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተሳታፊነት የሚጠረጠሩትን የበታችና የበላይ ሹሞችም ሆነ  ለሎችን ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ማቅረብ በዚህ ተሳትፎ ላቸውን የመንግሥት ሠራተኞችና ሾሞች ከፍርዳቸው ተጨማሪ በመገናኛ ብዙሃን ድርጊታቸወን በማስተማሪያነት ደጋግሞ ማቅረብ

፫። የዘር ማጥፋት ሰላባዎችንና  ተወላጆቻቸውን  ለደረሰባቸው ጉዳት በቂ ካሳ መክፈል፣ የጠፋብቸውን ንብረት መተካት፣ በነበሩባቸው ቀየዎች ተመልሰው መቋቋም የሚያስችሏቸውን ሁነታዎች ሁሉ ማሟላት  ::

እንደሚታወቀው አብዛኛው የቤንሻንጉል ክልል ህዝብ ዐማራና አገው ሆኖ እያለ፤ ሌሎች በዚህ ክልል የሚኖሩ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በበላይነት እንዲተዳደር መደረጉ ለዚህ ሁሉ በደል መንሳኤ ነው ብለን እናምናለን። ስለሆነም አስፈላጊና ህጋዊ መስተካከል እንዲደረግ እንጠይቃለን።

ለዚህ  ሁሉ የታሪክ ትልቅ ቁስል ሆኖ ለሚኖር ፍጅት መሰረት የጣ ዘር ኮር ርዕዮትና የትርክት ስብከት በመሆናቸው፣ በነዚህ ላይ በቂ ለውጥ በአስቸኳይ  ማስተካከያ እንዲደረግ እናሳስባለን 

በመጨረሻም የህዝቡ ፍላጎት በተገቢው  ተጠንቶ ዲሞክራሲያዊ ሕዝበ ውሳኔን  በማካሄድ የአማራና የአገው ማህበረሰብ ወደነበረበት ጎጃም መመለስ የእልቂቱን መነሻ ከማጥፋቱም በላይ  ህዝቡ ተገቢ ጥበቃና  ከዘር ፍጅት ሊድን የሚችልበትን መብት  ረጋግጥለታል።  

ግፍን ማስቆም የመንግሥት ግዴታ ነው።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 

ግልባጭ፤፡

ለክብርት ወ/ሪት ሳህለዎርቅ ዘውዴ የኢሕዲሪ ፕሬዝዳንት

ለክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢሕዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር

ለክብርት ሙፌሪያት ካሚል የኢሕዲሪ ሰላም ሚኒስተር

ለክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት

ለክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት

ለክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት

ለኢትዮጵያ ኢምባሲ ጽ/ቤት በእንግሊዝ

ለመተከል አስመላሽ ኮሚቴ

ለአማራ ሚዲያ ባህርዳር

ለአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)

ለዘሃበሻ ሚዲያ

ለአሻራ ሚዲያ

ለኢትዮ 360 ሚዲያ

ለአባይ ሚዲያ

 

 

 

2 Comments

  1. ለመዝገብ ቤት
    ግልባጭ ከተደረገላቸው ሶስቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች “ኢሕዲሪ” የሚል ተጠቅሷል። ኢሕዲሪ [የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ] ከሞተ 30 ዓመት ሆነው። ከላይ ደግሞ በትክክል ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ……… ተብሎ ተጽፏል። የተምታታ ነገር ስላለው “ደብዳቤው ተስተካክሎ እንደገና እንዲላክ” ከሚል ማሳሰቢያ ጋር ለላኪዎቹ ተመላሽ ይሁን።
    ቀንና ፊርማ አለው
    አፈ ጉባኤ

  2. አቢይ አህመድ ምንም ጫና ብታደርግበት የሚመለስ ሰው አይደለም። አረመኔው አቢይ የሚያደርገውን ጥፋት በደንብ የተረዳና ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው። አሁን ከሁሉም በላይ ትኪረት መሠጠት ያለበት አቢይን ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ማቅረብ ብቻ ነው። ለዚህ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ይተባበር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.