September 16, 2021
15 mins read

 ከውሸታም  ሰው  ና  ቡድን  ጋር  መደራደር  አይቻልም – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

A man who lies to himself, and believes his own lies becomes unable to recognize truth, either in himself or in anyone else, and he ends up losing respect for himself and for others. When he has no respect for anyone, he can no longer love, and, in order to divert himself, having no love in him, he yields to his impulses, indulges in the lowest forms of pleasure, and behaves in the end like an animal. And it all comes from lying – lying to others and to yourself.

Fyodor Mikhailovich Dostoevsky   ( Military engineer novelist journalist )

” ሰው ራሱን መዋሸት ከጀመረ እና ውሸቱ በራሱ ህሊና እና በሌሎች የሚታመን ከመሰለው  ለሌሎች ሰዎች እና ለራሱ ክብር መሥጠቱን ያቆማል ። ውሸቱንም በነጋ ጠባ በመቀጠል ፣ መዘባረቁን ይገፋበታል ።  የራሱን ውሸት አምላኪም ይሆናል ።  በሥተመጨረሻም ውሸቱ በሌሎች የማይታወቅ ይመሥለውና  ራሱን በውሸት ማዋረድና ቂላቂል ተግባራትን ማከናወን የዘወትር ተግባሩ ይሆናል  ።

ሰውን ሁሉ እየዋሸ ኗሪ  ማንንም የማያከብር ከሆነ    ደግሞ ከሰዎች ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያተርፍም ። ሰዎች በቀጣፊነቱ ፊት ሲነሱት ፣  ራሱን በጅላጅል ተግባራትም ማቃቄልን ሥራዬ ብሎ  ይያያዘዋል ።  በመጨረሻም   ሞራል አልባ ይሆንና የእንሰሳትን ባህሪ ይጎናፀፋል ።   ይህ ሁሉ የሆነው እንደ ቀልድ በጀመረው ውሸት ምክንያት ነው ። ውሸታም ሰው ፤ ራሱን እና ሌሎች ሰዎችን በመዋሸት ” ሀ ” ብሎ ጀምሮ በመጨረሻ እንሥሣ ሆኖ ያርፈዋል ።    ”

ፎይዶር  ሚካኤሎቪች ዶሥቶቭሥኪ  ( የጦር መሐንዲስ ፤ ደራሲ ና ጋዜጠኛ … “ ዶሥቶቭሥኪ “ እንደብዕር ሥም እየተጠቀመ ነበር የሚፅፈው ። )

በውሸት ትርክት ነው ፤ በኦሮምኛ እና በትግሪኛ ተናጋሪዎች  ሥም ፤ ከ46 ( TPLF ) እና ከ48 ( OLF ) ዓመት በፊት የተመሰረቱት ? ያውም በጥቂት  ( በጣት በሚቆጠሩ ) ሰዎች   ፡፡

የኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅትን ከ1941 ጀምሮ ኮትኩቶ በይፋ ደግሞ ፤ በ1951 ማነው ያቋቋመው ? በውሸት ፈጠራ የተካኑ ፣  የኢትዮጵያውያንን ብልጽግና የሚጠሉ እስትራቴጂካዊ ጠላቶቻችን እና ብዝበዛቸው እንደይነጥፍ የማይፈልጉ አውሮፓና አሜሪካ አይደሉምን ? ተርታው የኢትዮጵያ ህዝብ በሆዳሞቹ የፖለቲካ ኢሌቶቻችን የማያባራ ውሸት አይደለም እንዴ  አገርን አውዳሚ ከሆኑ ገጣዮች ና አሥገጣዮች  ጋር  ፖለቲካዊ ሴራውን ባለማወቁ   በጭፍን ተባባሪ የሆነው ? ጭፍን የጥፋት   ተባባሪነት የሚከሰተው  አማራጭ ሲታጣ እንደሆነሥ ሥንቶቻችን እናውቃለን ? ለመሆኑ በቃላት ለመግለፅ በሚያዳግት ድህነት ውሥጥ የሚኖር ደሃ ወሥፋቱን ለማሥታገሥ ሲል  ደቦ ካከማቸው በውሸት ከተካነ ተላላኪ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ጋር ቢተባበር ማነው የሚፈርድበት  ? …

በበኩሌ ድህነት ያኮራመተው ሰው ወሥፋቱን ለማሥታገሥ በብርቱ በሚሻበት የችግሩ  ወቅት ፣ ዳቦ የሰጠውን ህሊና ቢስ   ሰው ወይም ለጥፋት ዓላማ የተቋቋመ ቡድንን አማራጭ በማጣት በውሸቱ ተታሎ ቢከተለው ትዕዛዙንም ፈፃሚ ቢሆን አይገርመኝም ። ዛሬ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በትግራይ የምናስተውለው የህንኑ ተገባር ነው ፡፡ በህዝብ ደረጃ ሰው ተርቦ  ዳቢሎሱ ወያኔ እጅግ የበዛ የእርዳታ ምግብን አከማችቶ በገዳይ ጦሮቹ  እያሥጠበቀ ፣ ወንድምና እህታቸውን ለመግደል ወደ ጦርነት ካልሄዱ ለቤተሰቦቻቸው ቀለብ እንደማይሰፍርላቸው  እየሰፈራራና እነሱም ምግብ የሚያገኙት ፣ በግዳቸው ሸፍታ ሆነው ወገናቸው የሆነውን የኢትዮጵያን ዜጋ በመግደል ንብረቱን ሲዘርፉ ብቻ እንደሆነ በተራበ አንጀታቸው እንዲያምኑ በማስገደድ ይኸው የጥይት እራት እያደረጋቸው እንደሆነ ይታወቃል ፡፡

ዛሬ የትህነግ አመራሮች  በውሸታቸው ሰበብ ልክ እንደ እንሥሣ ሆነዋል ። ዶሥቶቭሥኪ ያለውም ይህንኑ ነው ። እንደ እንሥሣ ሆነውም በዛሬው እጅግ ዘመነኛ ዘመን  ዘራያዕቆብ ጥንት በደቂቀ እሥጢፋኖስ ተከታዮች ላይ የፈፀመውን ዓይነት  የግፍ ተግባር ፣ ለታሪክ ደንታ ቢስ በመሆን     በኢትዮጵያውያኑ ወድሞቻቸው  ላይ እየፈፀሙ ነው ፡፡ ታሪክ ግን ይቅር አይላቸውም ፡፡

የሚቀምሰው ቀርቶ የሚልሰው በጎጀው የሌለው አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ሳይወድ በግዱ ባላመነበት ጦርነት ውሥጥ የገባው ታሪክ ይቅርታ በማያደርግላቸው ፣ በወያኔ ጪራቆች ዘግናኝ ተግባራት አስገዳጅነት ነው ፡፡ ደብረ ፅዮን እና ግብረ አበሮቹ  እንደ ደቂቀ እስጢፋኖስ ተከታዮች አገዳደል ፣ የራሴ ነው የሚሉትን ወገን  ወድሞቹ ፊት አንገቱን እየቀሉ ፣ ” ይህንን ምስጢር ብታወጣ ወይ ብትሸሽ እጣፈንተህ ይሄው ነው  ፡፡ ” በማለት የእናቱን እንጎቻ በልቶ ያልጠገበውን እያስደነገጡትና እያስፈራሩት የጥይት  ቁርስ ምሳና ራት እያደረጉት ነው ፡፡ በሚዲያቸው በሚነዙት ውሸትም የትግራይን ህዝብና ተወላጁን እያወናበዱት ነው  ፡፡

ጌታቸው ረዳ ፤ ደብረ ፅዮን ፣ እና መሰሎቻቸው ” የሰረቃችሁትን ቁጭ ብላችው ብሉ ፡፡ ”  ሲባሉ  “ እንቢ ገና አልበቃንም ፡፡ የትግራይ ህዝብ ለመግደል የተፈጠረ እንጂ ሞት የማይነካው ጀግና ነው ፡፡ “ በማለት በከንቱ ውዳሴ ሸንግለው ፡፡ ነገ ወርቅ እንደሚነጠፍለት ሰብከው ና ሀሽሽ አጉርሰው እያደነዘዙት የራሱን አገር እንዲወጋ በአማራና በአፋር የአገራችን ግዛቶች  አሰማርተውታል  ፡፡ እነዚህ ጭራቆች ፤ የማንነታቸው መገለጫ ውሸት በመሆኑ  የተነሳ ከሰው ተርታ የወጡ እንስሶች ናቸው ፡፡  ምንም ትርጉም ለሌለው ዓላማ ቢስ ጦርነት  ድፍን የትግራይ ህዝብ ቢያልቅ ደንታ የላቸውም ። ዛሬ

ውሸታሞቹ የትህነግ መሪዎች  ፣ ድሮ ና ጥንት የጠፋባቸው ህሊና ቢስ እብዶች ሆነዋል  ። ሰው ሁሉ ባለችው አጭር ዕድሜ ከሰው ሁሉ ጋር ተሥማምቶ ና ተዋዶ እንዲኖር አይፈልጉም ። ዛሬም በድንቁርና ዘመን ውሥጥ የሚኖሩ በመሆናቸው “ ሰው  እንደ አውሬ እና እንሥሣ ተገልሎ በየቋንቋው እያወራ መኖር አለበት ። “ ባዮች ሆነው የተገኙትም ለመብላት ብቻ የሚኖር የእንስሳ አስተሳሰብ አእምሮቸውን ስለተቆጣጠረው  ነው  ።

እነዚህ ከልጅነት እሥከ አዋቂነት ውሸትን በአእምሯቸው ያነገሡ ፣ የነፃነት ትርጉም የማይገባቸው እብዶች ፤  ተፈጥሯዊው ሰው በተፈጥሮ የተቸረውን ሁሉ በሥርዓት እየፈፀመ  ኑሮውን  በተገቢው መንገድ እየመራ ፤ የህይወት ሥቃይዎን በመቀነሥ ደሥታዎን በማብዛት እሥከጊዜው በዚች ምድር  መሰንበት ሲገባው ዘላለም ዓለሙን በርሃብ ከለንጋ እንዲገረፍ ፈርደውበታል ። ( ከ46 ዓመት በፊት ያው ነበሩ ፡፡ ያውና ያው ፡፡ የወጣቱ ዘፋኝ የከስማስር ዘፈንን ያዳምጧል ፡፡   … )

ከ48 እና ከ46 ዓመት በፊት  ጥቂት ውሸታም ሥግብግቦች  ነገ ሲሞቱ ይዘውት ለማይሄዱት ቁሥ ፣ ዝና እና ሀብት ሲሉ ህሊናቸውን ሽጠው ፤ በሐሰት  በተሞላ ፕሮፖጋንዳ ፣ በቋንቋና በዘውግ ህዝብን በማቧደን የጀመሩት በገዳይ መሣሪዬ የሚታገዝ  አሥቀያሚ ” የጥላቻ ፖለቲካ ጫወታቸው ” ፤ ይኸው ዛሬ በሰቅጣጭ ሁኔታ ለመተላለቅ አብቅቶናል ።

እውነት እንነጋገር ከተባለ ፤ ከቢጤው ጋር   በየትኛውም ክልል የእኔ አንዱ መለያዬ ኦሮሞነቴ ነው በማለት የሚኖር ህዝብ አማራ ጠል ፣ ትግሬ ጠለ ፤ ወዘተ  ጠል ነውን ?  እንደ ጨው ዘር የትም የሚገኘው ና በየትኛውም ክልል ጎጆ ቀልሶ    አንዱ የእኔ መለያ ወይም የማንነቴ መገለጫ ትግሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ  ዜጋ ፣ ኦሮሞ ጠል ፤ አማራ ጠላ ፤ ወዘተ   ጠል ፤ ነውን ? አንዱ የእኔ መለያ ወይም የማንነቴ መገለጫ አማራ ነው የሚል ኢትዮጵያዋ ዜጋ ትግሬ ጠል ፤ ኦሮሞ ጠል ፤ ወዘተ ጠል ፤ ነውን ?  ሌላውም ቋንቋ ተናጋሪ ወይም ነገድ አልያም ዘውግ በያለበት በጉርብትናው በፍቅር ያለውን ተካፍሎ አዳሪ እንጂ ተጠላልቶ ለመጠፋፋት እያደባ የሚኖር ዜጋ  አይደለም ። ኢትዮጵያዊ  ዜጋ ለወገኑ  ጠላት ሆኖ ከቶም አያውቅም ።

ባለፉት ሦሥት ዓመታትት በገሃድ እንደታየው ህዝብን ከሞቀ ጎጀው የሚያፈናቅሉት ኢትዮጵያውያንን በነገድ ና በቋንቋ ከፋፍሎ  መግዛት ይቻላል የሚሉ ከሰው ተፈጥሮ ውጪ የሚያሥቡ ፣ የለየላቸው የውሸት አባቶች ናቸው   ። አንዱን ነገድ አቅርቦ ሌለኛውን በማግለል ፣  በማጋጨትና ደም በማቃባት ፣ ሁሉም ነገድ በዜግነቱ ለአንድ አገሩ ሳይሆን ለእናቱ ቋንቋ እንዲወግን በማደረግ ፤ በወንድማማቾች መካከል ያልተቋረጠ ጠብ ትላንትና በሐሰት ትርክት በመታገዝ በአገራችን ውስጥ የፈጠሩት ና የሌለ ርዮት የጫኑብን ህሊና ቢሶቹ በውጪ ፀረ ኢትዮጵያ  ስግብግብ ኃይላት ከ46 እና ከ48 ዓመት በፊት   የተቋቋሙ ባንዳዎች ናቸው ። በአላዋቂነት ና በደናቁረት ግለሰቦች  የተተረተ ተረትን ሁሉ ቁም ነገር በማድረግ እያስፋፈን  ፤ አንዱ ቋንቋ ተናጋሪ በሌላኛው ላይ   ጥላቻ እንዲያድርበት  በማድረግ ፣ ኢትዮጵያውያን በማይረባ ተረት እርስ በእርስ ተባልተው እንዲልቁ ና ኢትዮጵያ የምትባል አገር   እንዳትኖር ማድረግ ይቻላል ብለው ነበር ቀደም ሲል በሴራ ፖለቲካቸው የተነሱት ። ዛሬ ደግሞ አሻንጉሊታችን የሆነው ህውሓት ለምን ከሚኒልክ ቤተ መንግስት ዙፋኑ ተወገደ  በማለት ፤ ትግራይ ሆነው የውክልና ጦርነት ከፍተውብናል ፡፡ በሚዲያዎቻቸውም የሐሰት ፕሮፖጋንዳቸው ይነዛሉ ፡፡ የትኛውንም የጥፋት መንገድ ቢከተሉ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ለፋሺስቶች እጁን አይሰጥም ፡፡ ዳግም ፋሺዝም ሚኒልክ ቤተመንግስት እንዲገባም አይፈቅድም ፡፡ አሜሪካ በኒኩለር ቦንብ ኢትዮጵያዊያንን አውድማ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያውያን ለዘረኞች ባርነት እጃቸውን አይሰጡም ፡፡ የኢትዮጵያውያን እጅ በክብራቸው ለመጡ ጠላቶቻቸው የእሳት ሰደድ መሆኑን ዓለም ካላወቀ ዛሬ ያውቃል ፡፡ ከውሸታሞች ጋር አንድ ድርድር የለም ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop

Don't Miss