
ነፃነት ዘገዬ
እንቅልፊን ኢንጅሩ ወንድሜ፡፡ ዓለም በጭንቀት፣ ኢትዮጵያ በፓርላሜንታዊ ቀልድ እየታመሱ የምን መተኛት ነው፡፡ በደረቅ ሌሊት የተሰማኝን ትንሽ ላውጋችሁማ፡፡
በማንኛው ልጀምር? የአቢይ አባት ሊቀ ሣጥናኤል ግራ አጋባን እኮ፡፡
አሻንጉሊቱ ፓርላማችን፣ አቢይ በጣት ጥቆማ ከየጉራንገሩ በባጃጅና በፒካፕ አስጭኖ አስመጥቶ አዲስ አበባ ላይ የጎለታቸው ማይማን አጨብጫቢዎች በትናንትናው ዕለት አሣለፉት የተባለው የፌስታል ላስቲክ ዐዋጅ በአዝናኝነቱ ወደር አላገኘሁለትም (ሰው አይጥላህ አንተዬ! አቢይ ቪ8 መኪና አጥቶ በባጃጅና በፒኮክ ማለቴ በፒካፕ አስመጣቸው ልበል?)፡፡ አንድ ትልቅ የትልቅ ሀገር ፓርላማ የላስቲክ ፌስታል ይዘው የተገኙ ዜጎቹን ከ2 ሽህ ብር እስከ አምስት ሺህ ብር ሊቀጣ፣ ፌስታል አምራቾችን ደግሞ ከ50 ሽህ ብር እስከ 200 ሺህ ብር እና/ወይም እስከ 5 ዓመት ፅኑ እሥራት ሊፈርድባቸው በአብላጫ ድምፅ ሲወስን እንደማየት ያለ አስገራሚና አስደንጋጭ ክስተት የለም፤ ምን ሥራ ቢፈቱ በዚህ አስጨናቂ ወቅትና ዘመን ይህን መሰል ተራ ነገር ፓርላማ ውስጥ ማንሳት ራሱ ወራዳነት ነው – የመለስን አባባል ልዋስና – እደግመዋለሁ ወራዳነት ነው፤ በድሃ አገር ፌስታልን አንዴ ብቻ ተጠቅማችሁ ጣሉ ማለት ገደብ ያለፈ ዕብደት ነው – ለምን ሺህ ጊዜ አልጠቀምበትም? ማንስ ሊያገባው ይችላል በራሴ ፌስታል? እነሱ ይገዙልኛል? እንደቀልድ እየመሰሉ የሚጣሉብን አሣሪ ግዴታዎች አሁን አሁን በቀን ስንቴ መተንፈስ፣ ስንቴ መሽናት፣ ስንቴ መሣቅና ማልቀስ እንደሚገባን ሳይቀር የሚደነግጉ ደምቦች እንዳይወጡ በከፍተኛ ሥጋት ላይ ነን፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ባለጌ አትበሉኝና ባለትዳሮች ከትዳር አጋሮቻችን የምናገኛትን ያቺን ብቸኛ አንጻራዊ ደስታ በግብር መልክ አስልተው በወር 10 ሺህም ይሁን 20 ሺህ እንዳያስከፍሉን የምንፈራ ብዙዎች ነን – “በማን ግዛት ውስጥ ተኝተህ ማነው ተቀምጠህ ልትደሰት ያምርሃል?” ሊሉ ይችላሉ፡፡ ኦሮሙማዎች እኮ አስቂኝም፣ አስገራሚም፣ አሳቃቂም ፍጡራን ናቸው፡፡ መጠቆሜ እንዳይሆንብኝ ግን፡፡ እነሱ ጫት በቃሙና የዊስኪ ብርጭቆ በጨበጡ ቁጥር ትዝ የማይላቸው የደምብና የሥርዓት ዓይነት የለም፡፡ የሚጥሉት ቅጣት ደግሞ ከሕዝብ ኑሮ ጋር ሲተያይ ሰማይና ምድር ነው፡፡ ከነሱ ውጪ ደግሞ ሰው ያለ አይመስላቸውም፡፡ እኛን እንደዝምብም አይቆጥሩንም፡፡ እዚህ ላይ ያቺ በአፄው ዘመን “የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ነው?” ተብላ ስትጠየቅ “500 እንሆናለን” ብላ የመለሰችውን ልዕልት ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ የቆጠረችው የንጉሣውያኑንና የመኳንንት የመሣፍንት ቤተሰቦችን ብቻ ነው፤ ሌላው ለእሷ እንደሰው የማይቆጠር ትንኝ ነበር፡፡ ኦሮሙማዎችም ልክ እንደዚያች ከንቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቁብም አልቆጠሩት፡፡ ለዚህ ነው በስቃያችን እስከጥግ የሚደሰቱት፤ ለዚህ ነው በልቅሷችን ሃሤት የሚያደርጉት፡፡ ለዚህ ነው በተለይ አማራን መግደልና በሬሣው መጫወት የመጨረሻውን እርካታ የሚሰጣቸው፡፡ ለዚህ ነው በኮሪደር ልማት ስም አማራን ከአዲስ አበባ አፈናቅለው በማስወጣት ከተማዋን ባዶ ያስቀሯትና ለጥቂት ሺዎች የብልጽግና ደጋፊ ባለሀብቶች መኖሪያነት ያመቻቿት፡፡ እጅግ ብዙ “ለዚህ ነው”-ኦችን መደርደር ይቻላል፤ ማለቂያ የለውም፡፡ ትንንሾች መያዝ የማይገባቸውን የሥልጣንና የሀብት ቦታ ሲቆጣጠሩ የሚፈጠረው አስቀያሚ ትዕይንት ይህን ይመስላል፡፡ አዳሜና ሔዋኔ ከዚህ ተማር፡፡ ሞኝ አትሁን፡፡ አስተዋይና ብልኆች፣ ምሁራንና ዐዋቂዎች … እየፈሩም በይሉኝታና በፍርሀትም ገለል እያሉ ራሳቸውን ሲደብቁ ደንቆሮው ደፋር አራት ኪሎን እየተጠቆጣጠረ የሚያደርስብን ኢዮባዊ ቁስል መቆም አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ጨርሳ ሳትጠፋ የተደበቃችሁ ውጡና ቢያንስ ለልጆቻችን የምትሆን የጋራ ሀገር ፍጠሩ፡፡ የተወሰነ መስዋዕትነት ቢያስከፍልም ይቻላል፡፡
ሳልጠቅሰው ማለፍ የሌለብኝ አንድ ሰሞነኛ ጉዳይም አለ፡፡ በኦሮሙማ የማይታይ ጉድ መቼም የለም፡፡ የታክሲ ተራ አስከባሪነት እንደጉድ እየተቸበቸበ ነው፡፡ የፊተኞቹ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች እንደተባረሩ ሰምታችኋል፡፡ በምትካቸው ታዲያ ለአንድ አዲስ ተመዝጋቢ ከ40 ሺህ ብር ጀምሮ ጉቦ እየተከፈለ በውክልና ሳይቀር ቤት ቁጭ ተብሎ ወይንም ሌላ ሥራ እየሠሩ ተራ የማስከበር ጥገት ላም ማለብ እንደሚቻል ሲወራ ሰማሁ፡፡ ከሁነኛ ሰው ነው የሰማሁት፡፡ “ብር ካለህ ላስመዝግብህ”ም ተብያለሁ፡፡ በቃ – ሙስና ከራስጌ እስከግርጌ እግር አውጥቶ እየተራመደ ነው፡፡ እግዚዖ እንበል፡፡ የምፅዓት ቀን ሆነ፡፡
ይታያችሁ ወገኖቼ፡፡ ትናንት አንድ የሥራ ማስታወቂያ ስመለከት “ለባንክ ቤት ጽዳትና ተላላኪ” በሚል ርዕስ ለወጣ ክፍት የሥራ ቦታ የተመደበው ደመወዝ ብር 3000 ነው፡፡ ሌሎችም አሉ እንደዬርዕሣቸው፡፡ አማካዩ ደሞዝ ብር 5000 ነው፡፡ የ3000 ተቀጣሪ ተቆራርጦ የሚደርሰው ብር 2600 አካባቢ ነው፡፡ ቤቱ ጉለሌ ቢሆን ሥራው ፒያሣ ቢሆን ትራንስፖርትን አስቡት፡፡ ትራንስፖርቱ ብቻ ከዚህ ገንዘብ ከግማሽ በላይ ይፈጃል፡፡ ይህ ዜጋ ነው እንግዲህ ፌስታል ይዞ ቢገኝ ብር 5000 እንዲቀጣ የተወሰነበት፡፡ ደግሞስ ምሣውን በምን ይያዝ? ምን ዓይነት ድራማ ነው ግን?! ሌላ አማራጭ ሳይኖር?
ቅጣቱን የወሰኑት ሰዎች እርግጥ ነው ብር 5000 የጫማ ማስጠረጊያቸው ነው፡፡ “አምስት ሺህ የወሰንነው ከሕዝቡ የመክፈል አቅም አኳያ ተነስተን አሳንሰነው እንጂ ይህ ገንዘብ በጣም ትንሽ መሆኑን እናውቃለን” ብሎ የተናገረ ትልቅ የኦሮሙማ ባለሥልጣን እንደነበርም ሰምተናል፡፡ ይሄው ይሁን ሌላ ባለሥልጣን ደግሞ “ሕዝቡ የሁለት ብር ዳቦና የአሥር ብር ስኳር ቋጥሮ የሚይዝበት ላስቲክ…” ብሏል አሉ፡፡ ለመሆኑ የሁለት ብር ዳቦ አለ እንዴ አሁን? አንድ ጉርሻ የማትሆን ዳቦ አሥር ብር እንደሆነች ለዚያ ሰውዬ ንገሩት፡፡ የአሥር ብር ስኳርም ዱሮ ቀረ በሉት፡፡ ወገኛ ነው፡፡
ኦሮሙማዎች ገንዘብ ችግራቸው አይደለም፡፡ አዱኛ እንደጎርፍ ያጥለቀለቃቸው ኦሮሙማዎች የሚጥሏቸው ገንዘብ ነክ ቅጣቶች – ለምሣሌ የትራፊክ ቅጣትን የመሳሰሉ – እጅግ ከፍተኛ የመሆናቸው ምክንያት የሰዎቹ የገንዘብ ዕውቀትና የእኛ የዜጎች የኑሮ አቅም በነሱ በኩል ግንዛቤ ማጣት ነው፡፡ አንድ ባለሥልጣን ሲታመም ዱባይና ቤጂንግ ሄዶ ከታከመ፣ ሲርበው ባንኮክ ሄዶ ቁርሱንና ምሣውን ከጓደኞቹ ጋር በልቶና በእግረ መንገድም ከፈለጋት ጋር ተሸራሙጦና ተዝናንቶ ከተመለሰ፣ ለታዳጊ ልጆቹ ሳይቀር ውድ መኪና እየገዛ ካደለ፣ የወር ገቢው በብዙ ሚሊዮኖች ከሆነ … ባዶ እግሩን በርሀብ እየተንጠራወዘ በሚሄድ ድሃ ላይ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍል መወሰን ለዚህ ዓይነቱ ሰው በርግጥም ኢምንት ነው፡፡ የደናቁርት ሰዎች መጥፎነት ዋና መለኪያ ሁሉም ሰው እንደነሱ የጠገበ የሚመስላቸው መሆኑ ነው፡፡ ባለጌ ሲጠግብ ኅሊናው ይታወራል፤ ጭንቅላቱ ወደሆዱ ወርዶ ይሸጎጣል፡፡ ስለዚህም ከዕውቀትና ከጥበብ ጋር ይቆራረጣል፡፡
የኛ ኑሮ ያው ብዙ ጊዜ የተነገረና የሚታወቅም ስለሆነ እኔ አሁን ይህን ጉግማንግ መንግሥት “ይህን ተው፣ ያን ተው” በማለት ወደኅሊናው እንዲመለስ ማድረግ አይቻለኝምና በነጻነት ትግል ዙሪያ ያላችሁ ወገኖች የእርስ በርስ ፍትጊያውን ወደጎን ትታችሁ በዚህን መሰሉ የኑሮ ጣጣ እንኳን የምንሰቃየውን ዜጎች በአፋጣኝ ከዚህ ስቃይ ለማዳን በቶሎ ድረሱልን፡፡ ለሥልጣን ሽሚያው ኋላ ትደርሱበታላችሁ፡፡ በቅድሚያ ከሲዖል አውጡን፡፡ መጀመሪያ ሀገር ትኑረን፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ነው ነገሩ፡፡ በያላችሁበት ብትራኮቱ ለእናንተም ለእኛም አይጠቅምም፡፡ ወደየኅሊናችሁ ተመለሱና እኛን አስቡ፡፡
እንደአካሄድ የኢትዮጵያ ፍጻሜ እየተገባደደ ይመስላል፡፡ አቢይም ሊሰናበት፣ ኢትዮጵያም ከዚህ ብዔል ዘቡል ሰውዬ ነፃ ልትወጣ ዳር ዳር እያለች ነው፡፡ ከቀሪው ዓለምና ከኢትዮጵያ ማን ቀድሞ ነፃ እንደሚወጣ አናውቅም፡፡ ሁለቱም ከተያዙበት የሰይጣን (666) አገዛዝ መገላገላቸው ግና አይቀርም፡፡ ቀድሞ የተባለ ነገር ይዘገያል እንጂ መፈጸሙ ግድ ነው – ባይፈጸም ቀድሞውኑ አይባልም ነበራ!
በሌላው ዓለም እየተስተዋለ ያለው ሁኔታ እየተባባሰና ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ለመሆኑ የሰሞኑ የኡክሬንና የራሽያ ድንገተኛ ክስተት ጠቋሚ ነው፡፡ የምታውቁትን ነው የማስታውሳችሁ፡፡ ኡክሬን ሰሞኑን በራሽያ ላይ ያደረሰችው በሰባት ቢሊዮን ዶላር የተገመተ ቁሣዊ ውድመት ቀላል አይደለም፡፡ በጌታዋ ያልተማመነች በግ ላቷን ውጭ ብታሳድር የሚደርስባትን ታውቃለችና ይህን ታላቅ ታሪካዊ ውድመት ኡክሬን ብቻ(ዋን) ትሠራዋለች ብሎ መገመቱ ደግሞ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰኔና ሰኞ የገጠመባት የመሰለችው ራሽያ ያን ያልታሰበና ያልተገመተ ጥፋት ዝም ብላ ታልፋለች ተብሎም አይታሰብም፡፡ ይህ ግምታችን ነው እንግዲህ በከፍተኛ “ጉጉት” ስንጠብቀው የነበረውንና በግልጽ አይሁን እንጂ በአገም ጠቀም ደረጃ ከበርካታ ዓመታት በፊት እንደተጀመረ የሚታመነውን 3ኛውን የዓለም ጦርነት ያስጀምረዋል የሚባለው፡፡ ራሽያ በዚህ መልክ እስከ 40 መቶኛ የሚደርስ ነው የተባለ የመከላከል አቅሟን ያዳከመ ድብደባ ተፈጽሞባት ዝም ልትል እንደማትችልና ኒኩሌርን ጨምሮ ማንኛውንም ቤት ያፈራውን ዕልቂት አዋላጅ ክኒንና መርፌ ብትጠቀም ህጋዊ መብት እንዳላት እየተነገረ ነው፡፡ በዚህ ላይ ዓለማችን በርዕዮተ ዓለምም እንበለው በሃይማኖትና በሌላ ሌላ ልዩነት እንደመወጠሯ ራሽያን ደግፈው የቆሙ ኢራንንና ቻይናን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያን የመሰሉ ሀገራት ከራሽያ ጋር ይሠለፋሉ እየተባለ ነው፡፡ በመሆኑም አንዲት ዓሣማ እሰው ጓሮ ገብታ የአንደኛው ዓለም ጦርነት መንስኤ ልትሆን መቻሏ እንደሚነገረው ሁሉ 400 ምናምን ድሮን ተሠማርቶ ያነደደው የሰባት ቢሊዮን ዶላር ውድመትና ከዚያም በተያያዘ ተከሰተ በተባለው የሰዎች መገደል ምክንያት 3ኛው የዓለም ጦርነት በጣም በቅርቡ እንደሚጀምር ከፍተኛ ግምት ተጥሏል፡፡ እኔም እላለሁ – “ከሁልጊዜ ፈስ የአንድ ቀን ምንትስ፡፡” አሁን እኮ እኛም ኖርን ተብለን ይታዘንልን ይሆናል፡፡ “ድንቄም መኖር”፡፡ አቢይ ዕቶን ባደረጋት ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም መኖር ዕርም ሆኗል፡፡ የሚኖሩ ጥቂቶች – የሚያኗኑሩ ብዙዎች በሆኑባት ሀገር 3ኛው ቀርቶ 10ኛው የዓለም ጦርነት ቢፈነዳ ከ100 ሚሊዮን የምንበልጠው ዜጎች “ኬሬዳሽ” ሆነናል፡፡ እየቀለድኩ አይደለም፡፡ የምሬን ነው፡፡
ለማንኛውም ወንድም ዲያቢሎስ ይመቸው፡፡ ሥራውን እያገባደደ ነው፡፡ የትኛውንም ሀገር ስትመለከት አገዛዙ በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ ከጥልሚያኮሱ ባሕር የሚመነጭ ነው – ከ666፡፡ እዚህ ላይ መብላት መጠጣት፣ መደኽየት መክበር፣ ማጣት ማግኘት፣ መጥቆር መንጣት፣ ማጠር መርዘም … የአጋንንቱ ዓለም ሎሌ ከመሆን አንጻር ስሌት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ ከድሃው ወገን ብቻ ሣይሆን አብዛኛው ቁንጮ ባለሥልጣን የኢሉሚናቲዎች አባል ነው፡፡ መታወቂያቸው ግልጽ ነው፡፡
ለአብነት ያህል የጥልቁ አባል የሆኑና በየትኛውም ሀገር ትልልቅ ሥልጣንን የተቆጣጠሩ መሪዎች የሚያሳዩዋቸውን የፊት ላይና የአለባበስ የቃል ኪዳን ምልክቶች ተመልከት፡፡ በቅርቡ ሞተ የተባለውን የቫቲካን ሊቀ ጳጳስ ጨምረህ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የዓለም መሪዎች የሰላምታ አሰጣጥና የግንኙነት ሥርዓት ስታጤን ዓለማችን ምን ያህል ለሰይጣን እንደተንበረከከች ትረዳለህ፡፡ በዚህ ረገድ ቄስ የለ መነኩሴ፣ ጳጳስ የለ ኤጲስ ቆጶስ … ሁሏም በኢሉሚናዎች ኅቡኣን ድርጅቶች ግልጥና ሥውር ትዕዛዝ እየተነዳች ትገኛለች፡፡ ከትዕዛዙ ደግሞ ውልፊት የለም፤ ቅጣቱ ከባድ ነው፡፡ ለሥጋው ያደረ ደግሞ እንኳንስ እንደአቢይ አህመድ በማይምነት ጃኖ የተጀቦነ ደንቆሮ ይቅርና በየልና ካምብሪጅ፣ በግላስኮውና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲዎች ከሚያስተምሩ ፕሮፌሰሮች ጥቂት የማይባሉት የጥልቁ ተገዢና ገዢው የሚያዝዘውን ሁሉ ያላንዳች ማንገራገር የሚፈጽሙ ሆድ አደር ባሪያ ናቸው፡፡ ሌላውን ሁሉ እንተወውና በቅርቡ የሞቱት ፖፕ ፍራንሲስ “ሦዶማዊነት የግል መብት ነው፤ ሦዶማዊነትን ኃጢኣት ነው ብዬ ለመፈረጅ እኔ ማን ነኝ?” ያሉትን ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው የአጅሬን እጅ እርዝማኔና ድፍረት ለማወቅ፡፡ መዳን በራስ ነው፤ መዳን ከራስ ነው፡፡ መዳን ለራስ ነው እህቴ፡፡
በጸሎት ብንለያይስ?
አቤቱ አምላከ ሰማይ ወምድር ኅያው እግዚአብሔር ሆይ! ለሚያልፍ ዓለም ብዬ የማያልፈውን ያንተን መንግሥት የሚያሳጣ ወንጀልና ኃጢኣት እንዳልሠራ ጠብቀኝ፡፡ ሆዴ ቢራብ፣ ሥጋየ ቢራቆት ግድ እንዳይሰጠኝ ይልቁንም ነፍሴ አንተን ከመራብና መንግሥትህን ከመሻት እንዳትጎድል ታደርግልኝ ዘንድ በቅድስት እናትህና በቅዱሣንና ቅዱሣት ሰማዕታት ልጆችህ እለምንሃለሁ፡፡ በዓለም ፍጻሜ ላይ እንደመገኘቴ በመንፈስ አጠንክረኸኝ ከመንግሥትህ ወራሾች እንደ አንዱ እንድታደርገኝ ዘወትር እጸልያለሁና ጸሎቴን ቅቡል አድርግልኝ፤ አሜን፡፡