“በሠይፍ የሚጥሉ በሠይፍ ይወድቃሉ” አምባቸው ዓለሙ (ከደሴ)

እነሆም፥ ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው። ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ። ማቴ. 26 ፣ 51-52

በሀገራችን እየሆነ ያለው ሁሉ ለንግግርም አልመች ብሎን ብዙዎቻችን ግራ ተጋብተናል፡፡ ከዚህም ከዚያም የሚሰማውና የሚደመጠው ዘመኑን ያልዋጀ የጭካኔና የዐረመኔነት ጥግ መፈጠርን እስከሚያስረግም ድረስ ያስደነግጣል፡፡ የሚታመን የዜና ምንጭ ማግኘት ደግሞ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡ ተጻራሪ ወገኖች በየሚዲያዎቻቸው የሚያወሩትን እንዳለ ከተቀበልን በኢትዮጵያ አንድም ጥፋተኛ የለም፡፡ ሁሉም በየፊናው ጻዲቅ መሆኑን ያውጃል፡፡ ሁሉም ተበዳይ መሆኑን ያትታል፡፡ ሁሉም ተከላካይ እንጂ አጥቂ አለመሆኑን ይናገራል፡፡ በመሀሉ ግን ንጹሓን ዜጎች ከነሀብት ንብረታቸው ጭዳ እየሆኑ ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡

በሃይማኖት ረገድ “ከማንኛውም የእምነት ተቋም የኛ ይበልጣል” የሚሉንና ሥርዎ መንግሥቱን ከላይ እስከታች የተቆጣጠሩት የኦሮሙማዎቹ ፕሮቴስታንቶች በርዕሴ ላይ ያስቀመጥኩትን የክርስቶስን ቃል በቅጡ የተረዱ አይመስሉም፡፡ ክርስቶስ በፍቅር ገዛ፡፡ ስለፍቅርም ሞተ፡፡ እነሱ ግን በሠይፍና በሤራ ፖለቲካ ኢትዮጵያን አይታው ወደማታውቀው የጨለማ ዘመን ለመክተት ቀን ከሌት እየማሰኑ ናቸው፡፡ የ“ኢየሱስ ጌታ ነው” (ጌትነቱን የሚክድ ያለ ይመስል!) አቀንቃኞች የኢየሱስን ቃል ካልተገበሩ አዛዣቸው ዲያብሎስ እንጂ ክርስቶስ ሊሆን አይችልም፡፡ ማልከስ የተባለው የቀያፋ አሽከር ሐዋርያው ጴጥሮስ በሰነዘረው ሠይፍ የቀኝ ጆሮው ቢቆረጥ ክርስቶስ ያቺን የተቆረጠች ጆሮ መልሶ ወደነበረችበት ቦታ በመትከል ከፍ ሲል በተቀመጠው ጥቅስ የተናገረውን ተናገረ፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለዶክተር አቢይ ማስታወስ ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ ማወቅና ያወቁትን በተግባር ማሳየት ግን ለየቅል ናቸው፡፡ የአቢይን አእምሮ ሰይጣን ወርሶ እየተጫወተበት መሆኑ በግልጽ ስለሚታወቅ እንጂ ከአንድ ክርስቲያን ነኝ ባይ የአቢይን የመሰለ በሤራ የተጠመደ ሥነ ተፈጥሮ ማየት እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ክርስቶስ ስለሰው ልጅ ተሰቃዬ፤ በመስቀል ላይም ተቸንክሮ ሞተ እንጂ ስለኦሮሞ ወይም ስለነጭና ጥቁር ብሎ መስዋዕትነትን አልተቀበለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮና ጩኸት እስከመቼ? (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

አቢይና መሰሎቹ የሰይጣን አገልጋይ እንደሆኑ በምን እናውቃለን?

በጥቅል አነጋገር ከእግዚአብሔር መንገድ የወጣ ሁሉ ሰይጣናዊ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው፡፡ አትግደል እየተባለ የሚገድል፣ አትዋሽ እየተባለ የሚዋሽ፣ “ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ” እየተባለ የአንዲት ሀገር ዜጎችን በዘርና በጎሣ ከፋፍሎ ከአንዱ ጋር በፍቅር ከሌላው ጋር በጥላቻ የሚጠመድ፣ አትስረቅ እየተባለ የሚዘርፍና የሚሰርቅ፣ “በቀልን ለኔ ተዋት” እየተባለ በፈጠራ የጥላቻና የቂም በቀል ትርክት ከመሬት ተነስቶ በከንቱ የሚነድና የጠላውን መቆሚያ መቀመጫ የሚያሳጣ ዕቡይ ትውልድ … የሰይጣን ወገን እንጂ የእግዚአብሔር ወገን ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ ላይ እንደአቢይ ዓይነቶቹን የአጋንንት አሽከሮች ይበልጥ የምናውቃቸው በሚናገሯቸው የሀሰት ንግግሮችና በሚያደርጓቸው ዕኩይ ተግባራት ነው፡፡ እነዚህን ዓይነት ሰዎች ብዙውን ጊዜ ንግግሮቻቸውና ድርጊቶቻቸው እንደሚቃረኑም የታወቀ ነው፡፡ ለአፍ ዳገት የለውምና ቃል ሲገቡ የተስፋ ዳቦ ያሰገምጣሉ፡፡ በተግባር ግን ዜሮ ናቸው፡፡ የአቢይ ደግሞ ከሌሎች ለየት የሚለው እዚህና እዚያ የሚናገረው ርስ በርሱ የሚጋጭ ከመሆኑም ባሻገር አንዱን ለማስደሰት እንደመጣለት የሚዘላብደው ሌላውን ክፉኛ የሚያስከፋ መሆኑ ነው፡፡(የደሴውንና የባሌውን በምሣሌነት ማስታወስ ይቻላል)፡፡

ከሣጥናኤል ባለሟሉ ከዶክተር አቢይ ሰሞነኛ ንግግሮች አንዱን ብቻ ብንመለከት የዚህን ሰውዬ ባሕርይ በሚገባ እንረዳለን፡፡ ከመነሻው ጀምሮ የተናገራቸውን ታሪክ መዝግቦ ስለያዛቸው እነሱን ሁሉ አሁንና እዚህ አናነሳም፡፡

“በመቶ ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ዘመናዊ የጦር ኃይል እየገነባን ነው፡፡ (ከትህነግ ጋር) እያደረግን ያለነው ጦርነት መለማመጃችን ነው፡፡”

ለአንድ ሀገርና ለአንድ ሕዝብ የቆመ የሁሉም መሪ “መቀሌን በሻሻ አድርገናት ወጥተናል፤ በ30 ዓመታት ወደኋላ ጎትተናት ነው የለቀቅናትና ትግራይ ከአሁን በኋላ አታሰጋንም” ብሎ በዚያን ሰሞን ያስደመመን የሣጥናኤል እንደራሴ በኢትዮጵያ ዶክተር ኮሎኔል አቢይ አሁን ደግሞ ድፍረቱና አምባገነንነቱ ድምበር አጥቶ በሕዝብ ዕልቂትና በከተሞች መፍረስ እየተሣለቀ ነው፡፡ የእጁን ማግኘቱ የጊዜ ጉዳይ ቢሆንም ትዕቢቱና ዕብሪቱ ግን ለጊዜውም ቢሆን ያናድዳል፡፡ በነገራችን ላይ አምባገነኖችና ሕጻናት አንድ መሆናቸውን ከዚህ ሰውዬ ንግግር መረዳት ይቻላል፡፡ ሕጻናት አንድ ነገር ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ ብዙውን ጊዜ አያስቡም፡፡ አምባገነኖችም እንዲሁ ሁለመናቸውን ጥጋብና ዕብሪት ስለሚያሣውራቸው ስለምንም ነገር ለማሰብ ጊዜም ፍላጎትም አእምሮም የላቸውም፡፡ በሌላ አነጋገር ከዕብድ የሚሻሉት ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ነው – ከለየለት ዕብድ ማለቴ ነው፡፡ ዕብድ ይሉኝታና ሀፍረትን አያውቅም – አምባገነኖችም እንደዚሁ ናቸው፡፡ ስለዚህ አቢይን መሰል አምባገነኖች ዕብድም ሕጻናትም ናቸውና አእምሯቸውን የመጠቀሚያ ጊዜና አጋጣሚ አያገኙም፡፡ ለዚህም እኮ ነው አቢይ አህመድ አንዴ ታክሲ ነጂ፣ አንዴ አየር አብራሪ፣ አንዴ ትራፊክ ፖሊስ፣ አንዴ አትክልተኛ፣ አንዴ ሐኪም ወዘተ. እየሆነ ራሱ ታምሶ አጠገቡ ያሉትን ሁሉ የሚያምሰው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በገበያው እሣትነት ህዝብ እየተቃጠለ ነው። ማነው ገብያውን እሣት ያደረገው? - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ይህን ከፍ ሲል የተቀመጠውን ንግግሩን በተለያዬ አቅጣጫ ማየትና መተርጎም ይቻላል፡፡ መቶ ዓመት ሲል በዋናነት አባቱ ኦነግ ለኢትዮጵያ የሰጠውን ዕድሜ በተዛዋሪ ሣይሆን በቀጥታ መናገሩ ነው፡፡ ሌላው የአሁኑን ጦርነት መለማመጃችን ነው ሲል በሰፊው የአማራ ክልል በወያኔ እያለቁ የሚገኙት አማሮች እንደሰው የማይቆጠሩ ምሥኪን የኦሮሙማ ፍልስፍና ሰለባዎች መሆናቸውን እንድንገነዘብ ያደርጋል፡፡ አቢይ ሰው ሞተ ብሎ የሚያዝነው ምናልባት – ይህንንም እጠራጠራለሁ – ኦሮሞ ሲሞት ነው፡፡ ዜጎችን በዘርና በነገድ፣ በሃይማኖትና በፆታ እየከፋፈለ የሰው ግርድ እና አመሳሶ የሚያወጣ የሀገር መሪ ከሰይጣንነት ውጪ ሌላ መጠሪያ ሊሰጠው እንደማይችል በበኩሌ የማምነው ለዚህ ነው፡፡ ርኩስና ቅዱስ ያስታውቃል፡፡

ከተሞክሮ እንደተረዳሁት አቢይ – ለማጠቃለል ያህል – የሚደሰተው አማራ ሲሞት ነው፡፡ የአቢይ ቡድን በደስታ ጮቤ የሚረግጠው የአማራና የትግሬ ሕዝብ ሲጨፋጨፍለት ነው፡፡ እያንዳንዱን አክራሪ ኦሮሞ የሚያቃዠውን ያን ኦሮምያ የሚባል የምሥራቅ አፍሪካ ታላቅ ኢምፓየር ለመመሥረት እንደቅድመ ሁኔታ የወሰዱት የአማራና የትግሬ መጨራረስ መሆኑን ለመረዳት ብዙ መፈላሰፍ አያስፈልግም፡፡ ያለቀን ጦርነት ነፍስ ዘርተው በሁለንተናዊ የጦር መሣሪያና የስንቅ ድጋፍ አማራ ላይ ያመጡት ለዚህ ትልቅ ማሰረጃ ነው፡፡  እናም አንድ የአማራ ከተማ በወያኔ ሲያዝ የአቢይ ደስታ ወሰን የሌለው የመሆኑን ያህል አንድ ከተማ ከወያኔ ወረራ ነፃ ሲሆን የአቢይና ወንድሞቹ ሀዘን ልክ የሌለው መሆኑን መገንዘብ አይከብድም፡፡ ስለሆነም የተለቀቀን ከተማ መልሶ በወያኔ ለማስያዝ የአቢይ ቡድን የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ይህን ደግሞ የዋሁ አማራ የተረዳ አይመስልም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኦህዲድ ደንገጡር ብአዴን ስላለ የአማራውን ሸክም አብዝቶበታል፡፡ በአእምሮ ዘገምተኛው አገኘሁ ተሻገር የሚመራው ብአዴን አማራን ጉድ እየሠራው ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለሻለቃ ዳዊት - ሰለሞን ሥዩም ሲያትል፣ ዋሽንግተን

ለማንኛውም ይህ ዓመት – 2014 – ወሳኝ ዓመት ነው፡፡ የመጥፊያ ወይንም የመልሚያ፡፡ የውድቀት ወይንም የትንሣኤ፡፡ እንደኔ ግምትና እምነት ደግሞ ሁሉም የሥራውን የሚያገኝበት ዓመት ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ፊቱን ወደኢትዮጵያ ይመልሳል፡፡ እንደኃጢኣታችን ሣይሆን እንደምሕረትና ቸርነቱ መጠን ያደርግልን ዘንድ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ በሁሉም ረገድ መልካም እረኞች የሉንም፡፡ ቤተ እምነቱም ሆነ ቤተ መንግሥቱ በአጋንንት ቁጥጥር ሥር ከገባ ቆዬ፡፡ ጳጳሡም ሼኪውም ለሰይጣን ባደረበትና ለሥጋው አድልቶ መቃወም የሚገባውን ላለመቃወም ፀጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ድኅነትን ከሰውና በሰው አማካይነት አናገኝም፡፡ ስለዚህ የምንመኘውን ሰላምና እውነተኛ ብልጽግና ከፈጣሪ ለማግኘት በጸሎት መትጋት ይኖርብናል፡፡

2 Comments

  1. ስማ/ሚ ወገኔ በአለም ላይ ለሚነሱ ግጭቶች መንስኤ ናቸው ከሚባሉት ቀዳሚው ሃይማኖትን ተገን ያደረገ ነው። ከዚያ ቀጥሎ ዘረኛነትና የሃብት ምንጭ ማግኛ ለምሳሌ የነዳጅ ዘይት ምንጭ እንዳይደርቅ በሃገሮች ላይ የሚደረግ የቀጥታና የእጅ አዙር ሽኩቻን ይጨመራሉ። በመሰረቱ አንድ ሃይማኖት ከአንድ ሃይማኖት አይበልጥም። ግን አንድ የሚያደርገንን ነገር አጎልቶ ከማሳየት ይልቅ ትንሿን ልዪነት ጣራ ላይ እየሰቀሉና ጸጉር እየሰነጠቁ ለራሳቸው ጥቅም የሚያላትሙን ሆዳሞችና ከፋፋዪች ናቸው። ለዚህም ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ በይፋ አማራንና የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ቀብረናቸዋል ብሎ የፎከረው። አሁን ላይ ለቆመ ማን የተቀበረው ማን እንደሆነ ማየት ይችላል። ጉራና ት እቢት ስለሆነም የፕሮቴስታንት አማኝ ጥርቅም ይህን አለ ያን አለ፤ አመራሩ ይህን አጠፋ፤ እከሌን ልከሰው ነው ምን የማይባል ነገር አለ እያሉ የህዝባችን የሰቆቃ ጊዜ ከማራዘም ብልህ የሚታለፈውን አልፎ የልብን በልብ ይዞ ለሃገር አንድነትና ልዕልና ይሰራል።
    ባጭሩ ማንም መንግስት ቢሆን ሙሉዕ አይደለም። በዲሞክራሲ ስም ምላ የምትገዘተው አሜሪካ እንኳን ዲሞክራሲያዊነቷ የውሸት ነው። ለዛ ነው በድንጋይ የተባረረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃገርን ለማፍረስ ከአሜሪካና ከሌሎች ሃገር አፍራሽ ሃይሎች ጋር የተጎዳኘው። የተላላኪዎች መንግስት መፍጠር የአሜሪካ የውጭ ፓሊሲ ዋንኛ ተግባር ነውና። ግን እኛ ትንኝን ልናጠራ ስንላፋ እነርሱ በለመድት ተንኮል ዛሬም ትላንት ያለቀሱ አይኖችን እያስለቀሱ ይገኛሉ። በመሆኑም ይህን ያን እያለን የቆመን ለማፍረስ ከመከጀል ይልቅ እኔ ምን ላርግ የቱ ላይ ልሰለፍ በማለት የምንችለውን በጎ ነገር ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖትን ተገን ሳናረግ አስተዋጾ ማድረጉ ከሁሉ የሚሻል ይመስለኛል። ለአሁኑ ሰይፍ ወጣ ሰይፍ ገባ ፍሬ የለውም። ሰው ሲጠቃ መከላከሉ ያለና የሚኖር ነው። አንድም ይሮጣል ያለዛም ቆሞ ይፋለማል። የምናየው ይህኑ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share