” አእምሮ  የጎደለው  ሰው  ድርጊት ፣  ልክ እንደ  እንስሳ  ነው  ፡፡ የወያኔም አመራሮች ድርጊት እንዲሁ ፡፡ ” መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

“The law of evolution is that the strongest survives!’ ‘Yes, and the strongest, in the existence of any social species, are those who are most social. In human terms, most ethical…There is no strength to be gained from hurting one another. Only weakness.”
Ursula K. Le Guin

ያቀን ናፈቀኝ ፡፡

እርግጥ ነው ፤ በዳርዊን የለውጥ ትወራ እና የተፈጥሮ ጥናት መሰረት  ፣ ብርቱዎች ፣ በህይወት ይኖራሉ ፡፡ አንዱን አንዱን እየበላ ማለት ነው ፡፡ በእንስሳት ዓለም ፡፡ ጉልበተኛው ፣ አሸናፊው  በጉልበቱ ተማምኖ ኑሮውን ይቀጥላል ፡፡ (Survival of the fittest ) ፡፡ ይኸ እውነት  ከሰው ልጅ ውጪ  በሁሉም ሕይወት ባላቸው ፍጥረታት ሁሉ ላይ ፣ በተናጥል የህይወት ግንኙነት ሁሉ የሚከሰት ነው ፡፡ ሰው የበለጠ ለሥነ – ምግባር ወይም ለሞራል የተገዛ ነውና ይህ ጉዳይ አይመለከተውም ፡፡ አንዳችም ጥንካሬ ወይም የኃይል እርምጃ  በእርስ በእርስ ግንኙነቱ ወቅት አንዱ አንዱን በመጉዳት ማትረፍ ስለማይችል ነው ፤ ይኽ ትወራ ለሰው የማይሰራው ፡፡ በመገዳደል የሚመጣ ትርፍ የለም ፡፡ ትርፉ መዳከም ነው ፡፡ትርፉ ቁልቁል መሄድ ነው ፡፡ …

ለዚህም ነው ፤ እውቁ ፣ ታላቁ ፤ ብርቁና ድንቁ ደራሲ ና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ ፤ ኦሮማይ በተሰኘ ድርሰቱ ፤ ” እኔ ውብ የምለው የሰውን ልብ  ነው ፡፡  በማለት ፣ ” የቁስ ሰቀቀን እና ስቁንቁናምነት በሰፈነበት ዓለም የሰዎች ኖሮ አርቴፊሻል እንጂ ተፈጥሯዊ አይደለም ፡፡ ” በማለት በግጥም ሃሰቡን የገለፀው ፡፡ መቼ ይሆን ? ፊደል የቆጠሩ ሆኖም አለማወቃቸውን  የማያውቁ ፖለቲከኞቻችን ፣ ቢያንስ  ነገ አፈር መሆናቸውን አውቅው ፤” ህይወት ለማጥፋት ምን አስቸኮለን ? ” ህይወት በራስዋ አጨር እኮ ናት  ! ” በማለት ግፍ መስራታቸውን የሚያቆሙት ? ያ ቀን ናፈቀኝ ፡፡

 ” አእምሮ የጎደለው ሰው ድርጊት ፤ ልክ እንደ እንስሳ ነው  ፡፡ “

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዓለም ማንኛውም ታሪክ ፤ የግለሰቦች ሚና ትልቅ ሥፍራ አለው - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

 የዚህ ጦርነት አስፈላጊነትና ፋይዳው ምድነው ? ተብሎ ቢጠየቅ የትግራይ ህዝብ ፣ ሚሰጠው አጥጋቢ መልስ የለም ፡፡ ለትግራይ ህዝብ የዚህ ጦርነት አስፈላጊነት ና ፋይዳ ምንም ነው ፡፡ የገዛ አገሩን የሚወርበት አንዳችም ምክንያት የለውም ፡፡ እንደፈለገው ተዘዋውሮ በመላው ኢትዮጵያ እየሰራ ሳለ ፣ ይኽቺን ምስኪን  እናቱን ለማደኸየት ፣በአፀያፊ መልኩ ደፍሮ ፣ መሶቧንም ገልብጦ  ለመብላት ብቻ ሲል ፤ በሆዱ እየተነዳ  የገዛ አገሩን የወረረው ተገዶ ነው ፡፡ ከኋለውም በሠለጠነው ልዩ ኃይለ ና ፖሊስ እንዲሁም ሚሊሻ ጠመንጃ ባይደገንበት ኖሮ በራሱ ተነሳሽነት ወገኑን ለማረድ ቢላዋ አያነሳም ነበር ፡፡ ወገኑንም  አይዘርፍም ነበር ፡፡ … ወገኑን አይገልም ነበር ፡፡ ይሄ ተገዶ የሚዋጋ ፣ መሄጃ ፣ መጠጊያና መሸሻ ያጣ ዜጋ ፤ የገዛ ወገኑን ፣  እየሰረቀ ፣ እየዘረፈ ፣ እያሰቃየ … እያለም ፤ ራሱን በመከላከል ላይ ባለው ፣ ወደጦርነት እንቢ ለአገሬ ብሎ ፣ በፍቃደኝነት ሆ ! ብሎ ፣ በወጣው ፣ በተባበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጦር ሃይል ፣ በድንገት ተመቶ ከንቱ ሞትን አይሞትም ነበር ፡፡ ያለመታደል ሆኖ በጥቂት የሴጣን አእምሮ ባላቸው  ፣ በትውልድና  በታሪክ በሚረገሙ አስገዳጅነት ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል ፡፡ ያሳዝናል ፡፡

ግን ፣ ግን ፣ ከዚህ አንጸር ፣  ዕውን የትግራይ ወጣት  ፣መሰዋቱ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃልን ? ጥቂት የማይባለው የትግራይ ህዝብስ ፣ ድብረ ፂዮንን እና ግብረ አበሮቹን የእግዜር ያህል የሚፈራቸው የመግደል መብትን በጉልበታቸው ስለተጎናፀፉ ና ርህራሄ የሚባል ቅንጣት ያህል ስላልፈጠረባቸው  አይደለምን ? ( ይህንን የእብደት ጠርነት የሚቃወመውን የነቃ እና ፈርሃ እግዚአብሄር ያለውን  ሰው ሁሉ ፣ አስረው እንዳሰቃዩት ፣ እንደገደሉት ና ሌሎች መሰል ተቃውሞ እንዳየሰሙ እንዳስፈራሩበት ፤ ነገ ግፋቸው ሲያበቃ በገሃድ መሰማቱ አይቀርም ፡፡ ) ግን እስከ መቼ ?

 ይኽ በእብድ የሚመራ እልቂት ማብቃት ይኖርበታል ፡፡ የትግራይ ህዝብ ፍርኸቱን ማሸነፍ አለበት ፡፡ እያንዳንዱ ትግራዋይምህረት አልባ እጅግ ጨካኝ የሆኑትን የእነ ደብረፂዮንን የሴጣን ሰራዊት ጭካኔ  ፈርቶ አይደለም  እንዴ ባላመነበት ጦርነት ፣ ከጎናቸው የተሰለፈው ? ጥቂት የማይባለው  በትግራይ ክልል የሚኖረው ህዝብ ከሰሜን ኮርያ ህዝብ የባሰ የታፈነ እና የራሱ ዓይን ና ጆሮ የሌለው አ እንደሆነስ ስንቶቻችን እንገነዘባለንን ? …

  ዛሬ ና አሁን ፤ ደብረፂዮን  እና  ግብራበሮቹ  የትግራይን  ህዝብ ፣ ምሽግ አድርገው ፣ ለመቀጠል ሲሉ ህዝቡን አስገድደው ባለአመነበት ጦርነት ውስጥ በግድ ገፍተው በማስገባት የለ አንዳች አዘኔታ እየማገዱት ነው ፡፡ በዚህ ጨካኝ ድርጊታቸውም  እጃቸው  በደም  ተጨማልቆ ይታያል ፡፡ ( ሲቀፍ ፡፡ ሲዘገንን ፡፡ ) እነሱ ትላንትም ቢሆን ፣ ያለሃሺሺ ውለው አያድሩም ና እጃቸው በደም ሳይሆን በማርና በወተት የተጨማለቀ ይመስላቸዋል  ¡¡ በዚህ ሃሺሽ ባሳበደው ህሊናቸውም ፣ሁሌም ፣ ያለውሸት ያለዘረፋ  ማለም  እንደማይችሉ ደጋግመው አረጋግጠዋል ፡፡  ለዘረፋ እንዲያመቻቸውም ፣ የትላንቱን 1983 ዓ/ም የአማራን ህዝብ የዋህነት ተጠቅመው ሥልጣን በያዙበት መንገድ ፣ ዛሬም ተጉዘው ፤ ሥልጣን መልሼ እይዛለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ  ፣ በተለመደው ውሸታቸው  ሲገፉበትና ህዝቡን እናታልላለን ብለው በከንቱ ሲደክሙም ይስተዋላሉ ፡፡

  ትላንት የአማራን ህዝብ በውሸት ተርክት  ፈሪ አድረገው ሠለውታል ና በቀላሉ በእሱ እገዛ ወደ ሚኒልክ ቤተ መንግስት ሰተት ብለን እንገባለን ብለውም  ያስባሉ፡፡ ( የደብረፂዮን መግለጫም ከዚህ አንፃር ነው መታየት ያለበት… ) ተስፋዬ ገብረአብምበጋዜጠኛው ማስታወሻ ”  ( እውነተኛ ማስታወሻው ነው ፡፡ ) በዚህ መፀሐፉ ይህንኑ አማራን ፈሪ የማድረግ የሥነልቡና ውጊያ ተርኳል ፡፡ ምሥክሩም አቶ ተፈራ ዋልዋ ነው ፡፡ይተርክ እንጂ ፣ ትላንተና ና ዛሬ ለየቅል ናቸው ፡፡  ለመግደል ለመጨከን እኮ ትንሽ ጥቃት ፣ ትንሸ ክብር ማጣት በቂህ ነው ፡፡  ብሶት የወለደው ገለመሌ የምትለው ነገር ለወረርከው ፣ ለዘረፍከው ፣ ላሰቃየኸው  ለአማራ ህዝብ የማይሰራ እንዳይመስለህ ፡፡ በአማራ የዋህ ገበሬ ላይ በሰረፍከው የጭካኔ በትር ልክ አንተም ትወቃለህ  ፡፡

የሚገርመው ዛሬ ና አሁን ፤ በዘረፋ የናጠጡ ከበርቴዎቹ  ወያኔዎች  ግን በሚገርምና በሚደንቅ መልኩ    የሰሜን ኮርያን ዓይነት አስተዳደር  የለመደውን   በትግራይ ክልል የሚኖረውን  ህዝብ  “ብቻ ሳይሆን  መላውን  ኢትዮጵዊ   ለማቄል  በዓለም  ላይ  ተወዳዳሪ  የሌለውን  የሐሰት  ወሬያቸውን  በአደባበባይ  መናገራቸውን  መቀጠላቸው ነው ፡፡

  የኢትዮጵያን  ህዝብ  እየገደሉ   አገርን  እያስለቀሱ ፣ ኢትዮጵያን  በከባድ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እየዘፈቁልክ ቂቤ እንደቀቧት  ሁሉ  ፣ ለህዝቧ አዛኝ  ለመምሰል ሲጥሩ  ሰናስተውል ፣ የእነዚህ ሰዎች አእምሮ ጤነኛ እንዳልሆነ በተጨባጭ እናረጋግጣለን ፡፡   በህይወት  እስካሉ  ድረስ ህዝቡ  ለእነሱ ህይወት መቆየት ሲል  ከንቱ እና አላስፈላጊ መሰዋትነት እንዲከፍልም ይፈልጋሉ ፡፡  እነዚህ  ሰዎች  ኃይማኖተ  ቢስ   በሃሺሺ የጦዙ እብዶች  በመሆናቸውም አንዳችም  ረብ ለሌለው ፣ ትርጉመ  ቢስ  ለሆነ  ” የፈረንጅ መሳቅያ ና መሳለቅያ ” ለሆነ ጠርነት የትግራይ ህዝብ በሙሉ ቢያልቅ ከቶም ደንታ የላቸውም ፡፡  ሴጣኖች ስለሆንም አዘንና እንባን አያውቋትም ፡፡ 

  ያም ሆነ ይኽ ፤ የአማራ ክልልም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቢላዋ ቀልድ እንደሌለ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ፣ በትግራይ ህዝብ ሥም የሚነግዱት እነ ደብረፂዮን ፣ ቆም ብሎ በማሰብ ቢገነዘቡ መልካም ይመስለኛል ፡፡ … ወዳጄ የዳርዊንን ትወራ በቁንፅል የማትተረጉመው ቆም ብለህ ስታስብ  ነው ፡፡ ወደቀልብህ ስትመለስ ብቻ ነው ሰው መሆንህና ትብያነትህ በውል የሚገባህ ፡፡

ከፋሺስት የከፋ… ዘጋቢ ፊልም

ተጨማሪ ያንብቡ:   ማስጠንቀቂያና ወቅታዊ ማሳሰቢያ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share