እናት ፤ ልክ እንደ ለም መሬት መሐፀኗ ፤ አብቃይ ነው ሰውነት ፡፡ ይኽ የዓለም ህዝብ ፤ ወንድ ና ሴት ከእናት መሐፀን የወጣ ነው በራቁትነት ፡፡ እናት … ወድና ሴትን አፈራች … በማሃፀን በደም ስሯ እያጠባች ፡፡ ዘጠኝ ወር በመሐፀኗ ተሸክማ በጭንቅ ዓምጣ የወለደች … ጡቷን አጥብታም ያሳደገች ፡፡ እናት … ፍቅር ናት ፡፡ ብሽቅ ፖለቲካ ፤ የማይነካካት … የዓለም ዜጋነት ። ዓለምን አቃፊነት ድንበር የማይገድባት