የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ፓርቲ ዐሥር አባላቱን ማገዱን አስታወቀ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ29/08/2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በተመለከተ በጥልቀት ተወያይቶ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ የተለያዩ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡
ሀ. የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የንቅናቄያችን የስራ አስፈጻሚ አባል በተመለከተ
አቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ሆነው ሳለ ፣ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ፣ ከዚህ ቀደም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም በንቅናቄው ሥራ አስፈፃሚነታቸውም ሆነ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው በጋራ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመሆን እና ንቅናቄውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አንጃኞች ጋር ሕብረት በመፍጠርና ፣ ንቅናቄው የሃሳብና የተግባር አንድነት እንዳይኖረው በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ስተለገኙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል፡፡
ለ. ከድርጅት ማገድ
በፓርቲው መዋቅር ውስጥ በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ የንቅናቄው መካከለኛ አመራሮችና አባላት የሆኑት:-
1. አቶ አንተነህ ስለሺ መርዕድ ፣
2. አቶ እሱባለው ሙላት ዘለቀ ፣
3. አቶ ንጉሥ ይልቃል ያለው ፣
4. አቶ ዓለሙ ወልዴ አከለ ፣
5. ዶ/ር ጌታሁን ሣህሌ ወልዴ /የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል/ ፣
6. አቶ የማነ ብርሃን ሙጬ ፣
7. አቶ ጓዴ ካሴ ወልዴ ፣
8. አቶ ስንታየሁ ተስፋው ስዩም ፣
9. አቶ እስክንድር ለማ በቀለ ፣
10. አቶ ጌታነህ ወርቁ ይርዳው ፣
በድርጅት አመራርነት የተጣለባቸውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው በሚከተሉት ህገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ተሳታፊና መሪ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
• በፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅትን በሚመለከት የተሰጣቸው ውክልና ሳይኖር ፣ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ ነን በማለት ህገወጥ ቅስቀሳና አድማ መምራትና በንቅናቄው ውስጥ አንጃ መፍጠር ፤
• የጉባኤ አባላትን በተለያዩ አሉባልታዎች በማደናገር እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ፊርማ ማሰባሰብ ፣ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ ውክልና ይገባኛል መጠየቅና ድርጅታዊ ሥልጣን በእጅ አዙር ለመንጠቅ መሞከር ፤
• ከንቅናቄው እውቅና ውጭ የሆኑ የቴሌግራም ቡድኖችን በመክፈት አፍራሽ ቅስቀሳዎችን ማድረግ ፤
• የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት ምንም አይነት ስልጣን ሳይኖራቸው ፣ ጉባኤ ጠርተን ሪፎርም እናካሂዳለን በማለት ከድርጅቱ እውቅና ውጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ፤
• የድርጅትን ደንብ ተላልፎና ከሚመለከተው ክፍል ፈቃድ ሳይኖር በየሚዲያው መግለጫ መስጠት ፣ ድርጅታዊ ምሥጢር ማባከን ፤
• በንቅናቄው ላይ መሰረተ ቢስ ክሶች በመሰንዘር እና በከፍተኛ አመራሩ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት ፤
ከባድ ቅጣት የሚያስከትሉ የፓርቲውን የመተዳደሪያ ደንብ የተለያዩ ድንጋጌዎችን በመጣሳቸው ፣ የፓርቲውን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመገኝታቸው እና አሁንም ከጥፋት ድርጊታቸው ሊታረሙ ባለመቻላቸው ፤ በዚህም መሰረት ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ከድርጅት አባልነታቸው የታገዱ ሲሆን ፣ በቀጣይም የፈጸሟቸው ዝርዝር ጥሰቶችን የተመለከቱ ማስረጃዎችን መሰረት ተደርጎ የዲሲፕሊን ክስ እንዲመሰረትባቸውና ክሱም በአስቸኳይ በንቅናቄው የዲሲፕሊን ኮሚቴ በኩል እንዲታይ ተመርቷል፡፡
ሐ. ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት
1. አቶ ሀብታሙ በላይነህ መኮንን ፣
2. አቶ በቀለ ምንባለ አምሳሉ ፣
የንቅናቄው ቋሚ ኮሚቴዎች አባላትና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እያለ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አብረው ውሳኔ ያሳለፉበትን አጀንዳ በእጅ አዙር ለመቀልበስ አባላትን በማሳደም ፤ ለንቅናቄው የስብሰባና ሥነስርዓታዊ ህጎች ፣ እንዲሁም ለዴሞክራሲያዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ባለመገዛትና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎችን ረግጦ በመውጣት ተደጋጋሚ ጥሰቶችን በመፈፀማቸው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወቅታዊው ሁኔታ በሚጠይቀው መልክ ተጠናክሮ ለመገኘት ፣ ከግብታዊነት እና ስሜታዊነት ርቆ ፣ በበቂ ጥናት እና ዝግጅት ላይ ተመስርቶ ዘላቂ ድርጅታዊ ማሻሻያ /ሪፎርም/ ለማድረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ይገልፃል፡፡ ከዚህ አኳያ የፓርቲውን አመራር በአቋራጭ በመቆጣጠር ለህዝባችን በጎ ባልሆነ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ ለማስገባት የሚደረግ ማናቸውንም ጥረት ፓርቲያችን የማይታገስ መሆኑን እያስገነዘብን ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በመሰል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ የምታደርጉ አንዳንድ የፓርቲው አባላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ፓርቲው አበክሮ ያሳስባል፡፡
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የፋሲካ ዕርቅን ከሰሜን አየርላንድ ብንማርስ?

3 Comments

  1. Perfect timing!
    This looks like a ploy to distract the Amhara from the operation launched to annihilate Fanno ahead of TPLF’s impending full-scale re-invasion of the Amhara Region

  2. ይሄ የት እየሄደ እንደሆነ ለሚያሸተው፤ የአማራ የሆነ ማንኛውም ንቅናቄ እንዳያድግና ርስ በርሳችን እንድንነታረክ ወደታቀደ መንገድ ያዘነበለ ይመስላል። አሁን አጀንዳው አንድነትና አብሮነትን አራምዶ አማራውን ወደ አንድ ኃይል ማሰባሰብ ሆኖ ሳለ፤ ያሉን ድርጅቶችን ማዳከም አደጋው ከባድ ነው። ብልፅግና አማራውን እያዳከመ ባለበት ሰዓት፣ አማራው ችግሩን አውቆ ወደ መሰባሰብ ባዘነበለበት ወቅት፣ አማራ ወዳድ የሆኑ የብልፅግና አባላት እየተባረሩ ባለበት ሁኔታ፣ አብን ውስጥ ይህ መከሰቱ ያደናግራል። አንድም ለሥልጣን የጓጉ ወደሚፈልጉት ለመውሰድና የብልፅግና ተገዢ ለማድረግ የሚያደጉት ጥረት እንዳይሆን! አለያም ጨርሶ የአማራ ተቆርቋሪዎችን ከመድረክ ለማስወጣት የሚደረገው ትልቁ ጥረት አካል እንዳይሆን እፈራለሁ። በግል ሀብታሙ በላይነህን አውቀዋለሁ። የአማራ ተቆርቋሪ መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ለሁሉም ወደ ትልቁ አጀንዳችን እናተኩር፡፤ የአብን የውስጥ ችግር ከአማራው የሕልውና ጉዳይ በጣም አነስተኛ ቦታ ነው ያለው።

  3. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) is irrelevant organization because its program has not evolved since the country’s political, economic and military situation has evolved in the last few months. Unless አብን changes its program for confederation from “mama tobia” cry, it will be in disarrey in a shot order both in Amara region and in the country. Adios!

    .One Shegitu Dadi, a very forward looking Oromo woman has the following to say on confederation. I’m copying and pastion her write-up without her authorization hoping that she’ll not mind.

    “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer. ”

    GREAT!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share