የሻምቡ ጀግና የኦሮሞ ልጆች ፋሽስት ወያኔን በቃሪያ ጥፊ አጩለውታል!

ከአቻምየለህ ታምሩ

ወያኔ የኦሮሞና የአማራን ግንኙነት «መርህ አልባው ግንኙነት» በማለት ያወገዘበት የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ መግለጫ ቀለም ሳይደርቅ የሻንቡ ልጆች
«አንድ ነን! መቼም አንለያይም!
«የኦሮሞ ደም የአማራ ደም ነው!»
«የአማራ ደም የኦሮሞ ደም ነው!»
«የአማራ ጠላት የኦሮሞ ጠላት ነው!»
«የኦሮሞ ጠላት የአማራ ጠላት ነው!»
በማለት የተከዘ ማዶ ነውረኞችን ጨጓራ አቃጥሎ የሚያነድ መፈክር በአማርኛና በኦሮምኛ አሰምተዋል!
እኔም እንዲህ እላለሁ. . .
አንድ ወገኔ ወዲያ አንድ ወገኔ ወዲህ፣
ወለጋና ወሎ፣ ጎጃምና ሐረር፣ ጎንደርና ባሌ አጥር አንሳ እንግዲህ!
የሻምቡ ልጆችን መፈክርም እንደግመዋለሁ. . .
«የአማራ ጠላት የኦሮሞ ጠላት ነው!»
«የኦሮሞ ጠላት የአማራ ጠላት ነው!»
እነ ጌታቸው ረዳ «መርህ አልባ» ያሉትን ግንኙነት እንዲህ ሕዝባዊ ሆኖ ሲያዩት ጥንቢራቸው እስኪዞር ድረስ በጥላቻ ስክረው ጺማቸውን እየነጩ ጨጓራቸው እንደሚቃጠል አይጠረጠርም!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአራት ልጆች እናቷ ኢትዮጵያዊት አራስ ስንብት - በቨርጂኒያ መቃብር ቦታ

1 Comment

 1. “ይናዳል ገደሉ ይናዳል ገደሉ
  እየበሉ መጡ ይባላሉ ሲሉ !”

  * ከሰሞኑ የህወሓት/ኢህአዴጋዊ ማላገጫ “መርህ አልባው” የህወሓት፡ ብአዴን፡ ደህዴን፡ ኦህዴድ ግንኙነት ኢትዮጵያን አፍርሶ ክልልን(ጋጣ) ውስጥ ማጎር ሕዝብን በቋንቋና ነገድ መጠርነፍ አላዋጣም። ትውልድ የበይ ተመልካች ሆኖ ያለ ሀገር፡ የዜግነት ነጻነትና እኩልነት ፡እንዲመክንና እንዲባክን ፳፯ ዓመት ተፈርዶበት ነበር።
  * በአንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ የህወሓት/አድዋዊ የወሮበላ ቡድን ሥር ተጠርንፎ ነበር። ሌሎች የእንዱስትሪያል ኢኮኖሚ ግንባታ ራዕይ ሲቀረጽላቸው፡ልዩ የትምህርትና የደህንነታቸው ከለላ በርፓቲ አባልነትና ድገፊ/ተደጋፊነት ድጎማን ቅድሚያ መስተንግዶ ሲደረገላቸው፡ ሌላው እስታዲያም፡ ጭፈራ/አሺሽና የዝሙት ቤት በብዛት ይከፈትለታል። ወደፊት እንዳያይ አንገቱን ወደኋላ ጠምዝዘው ፻፴ ዓመት በማስርጃ አልባ ፈጠራ ታሪክ ተብትበው፡ መብቱን በጋራ እንዳይጠይቅ ለያይተው፡ ማንነትህን የማታወቅ እኛ በ፲፩፱፹፫ በሰራነው ሀገር ፡ልዩ ተጠቃሚ አድርገንሃል፡ ያለ እኛ ምንም ያልነበርክ/ያልነበረህ፡ በእኛ የተፈጠርክ ለእኛ ብቻ የምትኖር፡ ያለ እኛ የምትበታተንና የምትጠፋ ብርቅዬ ተናጋሪ እንስሳ ብለው ወይነውበታል።
  ኢትዮጵያዊነቱን አላግባብ አፍዘው አደንዝዘው ቀምተውታል!!

  ___እንግዲህ “ድንጋይን ማን ያናግረዋል ቢሉ ውሃ” አሉ። ጎርፍ እያላጋ ሲወስደው አይተው ማለት ነው።
  ኦሮሞን ማን አናገረው? ንቀት፡መገፋት፡ምሬት(መሬት) ትዝብት፡ቁጭት፡ቁጣ(የሀገር ባለቤትነት እጦት) ንቃት፡አንድነት፡(ይቅርባይነት)፡የአያት ቅድመ አያቱ አደራ ከጣና ከውሃ አልፎ ደምህ ኬኛ!፡ ከመንደር አልፎ ኢትዮጵያ ኬኛ! ለመሆኑ እንግዲህ ኢትዮጵያ የአንተ አደለም የሚለው ማን ይሆን?

  ***ግሎባላይዜሽን(ሙሉዓለም) ዓለም አንድ መንደር ሆነች እያሉ እርስ በርስ እየተባሉ፡ ጥሬ ሀብት፡ ወጣቱን ትወልድ፡ በመጤ እያስበሉ፡ ዙሪያውን ቆሞ ከማልቀስ፡ ዙሪያውን ከቦ ተማክረውና ተረዳድተው አብሮ እየሰሩ፡ የሚሰረስሩን እያቀነሱ ኢትዮጵያን አንድ መንደር አድርጎ (በሙሉ ነጻነት) እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው። ነን ሶቤ?
  ሁለተኛ ዜጋ የለም! ቶኮዳ ….ሲንገሌ///

Comments are closed.

Share