የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ከ108 ሚሊዮን በላይ ደረሠ

(ዘ-ሐበሻ) በአለም ባንክና መሠል አለም አቀፍ ተቋማት በዚህ ሳምንት ይፋ የሆነው መረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ ብዛት ከ108 ሚሊዮን በላይ አድርሶታል። በዚህ መሠረት ኦክቶበር 22 ቀን የህዝቡ ብዛት 108,354,282 መሆኑ ተገልፇል። ይኸው መረጃ በብሄሮችም ደረጃ ያለውን የህዝብ ስብጥር ዘርዝሯል። በመሆኑም የኦሮሚያ ህዝብ 34.4 ሚሊዮን በመሆኑ በቀዳሚነት የተቀመጠ ሲሆን ቀጣዩ የአማራ ህዝብ ደግሞ 27 ሚሊዮን መሆኑን መረጃው አስረድቷል። ከኢትዮጵያ ህዝብ በቁጥር ሶስተኛ እንደሆነ የተገለፀው ደግሞ 6.2 ሚሊዮን ነው የተባለው ሡማሌ ነው፡፡ መረጃው ትግራይን በ6.1 ሚሊዮን አራተኛ፣ ሲዳማን በ4 ሚሊዮን አምስተኛ፣ ጉራጌን በ2.5 ስድስተኛ፣ ወላይታን በ2.3 ሠባተኛ፣ ሐዲያን በ1.7 ስምንተኛ፣ አፋርን በ1.7 ዘጠነኛ እንዲሁም ጋሞን በ1.5 አስረኛ አድርጏቸዋል።

በከተሞች ያለውን የህዝብ ቁጥር ካየን በግንባር ቀደምነት አዲስ አበባ ሲመራ፡ ጎንደርና መቀሌ ተከታዩን ደረጃ መያዛቸውን መረጃው ጠቁሟል። በዚህ መሠረት የአዲስ አበባ ህዝብ 3,434,000 እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የጎንደር ህዝብ ደግሞ 360,600 መሆኑን አስረድቷል። በቀጣይነት የመቀሌን ህዝብ 358,529 ያደረሠው መረጃው፣ የአዳማን 355,475 እንዲሁም የሀዋሳን 335,508 በማድረግ ደረጃ ሠጥቷቸዋል። በስድስተኛነት 313,997 ህዝብ ያላት ባህር ዳር፣ በሠባተኛነት 293,000 ህዝብ ያላት ድሬዳዋ፣ በስምንተኝነት 209,226 ህዝብ ያላት ደሴ፣ በዘጠነኛነት 195,228 ህዝብ ያላት ጅማን እንዲሁም በአስረኛ ደረጃ ጅግጅጋን 169,390 ህዝብ በመያዝ ዘርዝሯቸዋል።

እንደዚሁ መረጃ ባለፈው የፈረንጆች አመት የኢትዮጵያ ህዝብ 104 ሚሊዮን 957 ሺህ 438 የነበረ ሲሆን፣ ካቻምና ደግሞ 102 ሚሊዮን 403 ሺህ 196 ነበር፡፡ መንግስት በ10 አመቱ የህዝብ ቆጠራ ማድረግ የነበረበት ቢሆንም በአገሪቱ በተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  25,000 housemaids from Ethiopia has been delayed

1 Comment

  1. ትግሬና ኦሮሞ ልጅ መፈልፈል ቢታቀቡ ይመከራል::
    ጤናማ ዜጋ ለማፍራት ለህብረተባችን እናስብ:: በተለይ ትኩረት መስጠት ያለበት ከዘመድ ከቤተስብ በባህል ተጽእኖ መጋባት የሚያመጣውን ጉዳት ማስተማር አለብን:: በቅርቡ ከሜኒሶታ “ጠፍታ ” የመጣች አግኝቼ ስትነረኝ ወንድሜ ካላገባሁሽ እያለ ስላስቸገረኝ እለች::

    በእርግጥ ለእገሩ ገና እዲስ ናት መግባባት በደንብ እልቻልንም እና ወንድም ማለት በባህላ የቤተስብ አባል ነው የሚስለው:: ነገሩ ገርምኝ በተለይ በምዕራብ አገር ያለ ስው እንዲህ ማድረጉን ስጠይቅ የተለመደ ነው አሉኝ:: :በተለይ በኦሮም ህብረተስብ:: :

    በማፈር በአደባባይ መወያየት ይማያስችሉ ህብረተቡን ጤናም የማያደርጉ ጉዳዬችን ማስቆም እልብን::

Comments are closed.

Share