ፍንክች አይሉም እኛም ፍንክች አንዳንል ያስፈልጋል – ሉሉ ከበደ

እነሱም ፍንክች አይሉም እኛም ፍንክች አንዳንል ያስፈልጋል። ሰሞኑን የኢሀደግ ስራ አስፈጻሚ ተብሎ  የህውሃትና የሎሌዎቹ ስብሰብ ከወር በላይ ሲመክር ቆይቶ የህውሃትን የተለመደ ግትር አቋም አብስሯል። ግልጽ የሆነ አደገኛ መልክትም አስተላልፏል። ይህም መልክት የጦሩን አዛዦች ለማመጣጠን በኦህዴድና በብአዴን በኩል ታስቦ ውሳኔ ያገኛል የተባለው አጀንዳ በህውሃታውያን ጦር አዛዦች ተቃውሞ መወገዱ ነው።  “ጣልቃ አትግቡብን በደማችንና በብቃታችን ያገኘነውን አዛዥነት ለማንም አሳልፈን አንሰጥም” ብለው የወያኔ ሰራዊት  አዛዦች በማስፈራራታቸው ስራ አስፈጻሚው ሳያነሳው አልፏል። ይህ ግልጽ መልክት ነው። የህውሃት የበላይነት ለድርድር አይቀርብም ማለት ነው። የምታመጡትን አምጡ እየገደልን እንቀጥላልን ማለት ነው። እናስ የኢትዮጵያ ህዝብ አየተገደለ ይቀጥላል ወይስ ከመቸውም በላይ አንድነቱን አጠናክሮ ደርምሶ ይጥላቸዋል? እርግጥ እነሱ የህውሃት  ጀነራሎች ይህን ሲሉ   ሁለት ዋናዋና ምክንያቶች አሏቸው። መላው የሃገሪቱ ሰራዊት በነሱ ትዛዝ ስር አንዲቀር ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ፤አንዱ በግል አያንዳንዱ የሰራዊቱ አዛዥ አቅሙ በሚፈቅደው ልክ የሃገሪቱን ሃብት ያለተቀናቃኝ እየዘረፈ በመበልጸጉ ያን ማጣት የማይታሰብ ነገር ነው።ሌላው የትግሬው ጎሳ የበላይነት እውን ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው በደህንነቱ በፖሊሡና በመከላከያው የበላይነታቸው እንደተጠበቀ ሲቆይ ነው። የሚያስቡት የተለየ ነገር እንደሌለ በመግለጫቸው  አረጋግጠዋል። ለምላሹ መዘጋጀት የኢትዮጵያ ህዝብ ፋንታ ነው።

የኦህዴድና የብአዴን መሪዎች የማፈንገጥ ሙከራ ህዝባዊ ድጋፍና ማበረታታት ያስፈልገዋል። ምክንያቱም ባሁኑ መግለጫቸው ህውሃቶች ዝተውባቸዋል ማለት ይቻላል። እራሳቸውን እንዲመረምሩና ማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ከህውሃት በስተቀር ለቀሩት የኢህ አደግ አባል ድርጅቶች ተነግሮአቸዋል። ይህ ማለት በተለይ ለአማራውና ለኦሮሞ ተወካዮች ይህን የጀመሩትን ህዝቡን ወደ አንድነት የማምጣት እንቅስቃሴ ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወስዱባቸው ነው የሚያመለክተው – ህውሃቶች። ለማ መገርሳ ዶክተር አቢይ እና ገዱ አንዳርጋቸውን ይመለከታል።ገዱ ፈራተባ ቢልም ሁለቱ ወጣቶች የለውጥ ሃዋርያ ሆነው ብቅ ያሉ ናቸው። በቆረጣ ይመታሉ ማለት ነው። “በመርህ ላይ ያልተመሰረተ መቧደን…” የሚለው ሃረግ የሁለቱን አንድ አቋም መያዝ እያጣጣሉ ለማመልከት ነው። ኦህዴድና ብአዴን ለህውሃት መጥፊያ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ባይቆሰቁሱ ይሻላቸዋል ባይነው ወያኔ። ምክንያቱም ኢትዮጵያን የመበታተኑ ፕሮጀችት ጫፍፍ ላይ አልደረሰም ገና ብዙ የሚቦጠቦጥ ሃብት ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቷልና!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀዳማይ ወያኔ፤ ዓድዋ እና የካቲት 11 በወያኔ ትግሬዎች ዕይታ - ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)

ኢትዮጵያን በመበታተኑ ፕሮጀችት ውስጥ ተግባራዊ እየሆነ ካለው ድርጊት አንዱ የሶማሌ በተባለው ክልል ውስጥ አናም በራሳቸው የኦሮሞዎች በተባለው ክልል ውስጥ ህውሃቶች ያንቀሳቀሱት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ማፈናቀል ሰሞኑን እንዲህ በሚል ዜና ታጅቧል።….ወደ ነበሩበት ሳይሆን በሌላ የኦሮሚያ አካባቢዎች መኖሪያ ቤት ተገንብቶላቸው ከሰባት መቶሺህ በላይ ኦሮርሞዎች አዲስ ቦታ ይሰፍራሉ። ይህ ማለት ለኔ በሚገባኝ መንገድ ወደቀድሞ ቦታቸው አይመለሱም ማለት ነው። በየትም ሃገር ተደርጎ አይታወቅም። አንድ ህዝብ በገዛ ሃገሩ  ጦር ታዞ እንዲደበደብ ከተደረገ በኋላ በተሰደደበት ቦታ በዚያው እንዲቀር በዚያው መንግስት ድጋፍ ሲደረግለት። የርስበርስ ግጭት እንኳ ቢፈጠር የችግሩ መንስኤ ከመሰረቱ ተጣርቶ፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ፥ አስፈጻሚዎ ፥ ተባባሪዎች ፥ ሁሉ የሚገባቸውን ቅጣት አግኝተው ሰላም እንዲሰፍን ተደርጎ እዚያው በመሬታቸው በንብረታቸው ላይ እንዲቋቋሙ ይደረጋል እንጂ ፤ “በቃ ፥ ያ አገር የናንተ አይደለም”  ተብለው በማያውቁት ቦታ አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ አይደረግም። ይህ የህውሃት ሴራ ኦጋዴንን ሶማሌዎች ለብቻቸው  ተቆጣጠው እንዲይዙ የማመቻቸት ደባ ነው። ብሎም ወያኔ የሚበቃውን ያህል በመላ ሃገሪቱ ያለውን ሃብት ሰርቆ ሲበቃው ፥ ወይም ህዝባዊ ማእበሉ ከመሰረቱ ሲያናጋው ፤ ወደትግራይ አፈግፍጎ ነጻነቱን ሲያውጅ፤ ኦጋዴንንም ለማሰናበት ይቀለዋል ማለት ነው። አትገነጠሉም ብሎ መፋለም ስለማይቀር  የአንድነት ሃይሉ  ካለ ተዋጊው በያቅጣጫው ሊበተን ነው ማለት ነው። አብዲ ኢሌ  ኦሮሞዎች እኛን መግደል ካላቆሙ ከፌዴራሉ እንለያለን ፤እንገነጥላለን፤ የሚል አንድምታ ያለው ንግግር መናገሩ ተዘግቧል። ዝም ብሎ አይደለም ይህን የሚለው። ከጌቶቹ ጋር የሚለዋወጠው ሃሳብ ይኖራል።ልብ በሉ ቁጥሩ በአርባ ሺህ የሚገመት በልዩ ፖሊስ ስም የተደራጀ የሶማሌ ጦር ኦጋዴን ውስጥ አለ። በህውሃት የሚታዘዝ ነው። ኦሮሞንም ሆነ የራሳቸውን ዜጎች እየጨፈጨፈ ነው። ይህ ጦር ልዩ ልዩ ተልእኮ ነው ያለው ። የህውሃትን ጥቅም ማስጠበቅና በታዘዘ ጊዜ ኦጋዴንን ማስገንጠል። በታዘዘ ሰአት ህዝብን መጨፍጨፍ። ህውሀት ወታደራዊ ድጋፍ በሚያስፈልገው ጊዜና ቦታ ፈጥኖ ደራሽ የሚሆን ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እባብ ለእባብ፣ ይተያያል በካብ – በወንድሙ መኰንን፣ ለንደን

ይህ የድኩማን ቡድን ህውሃት ኢትዮጵያውያንን ከሚገባው በላይ እየተፈታተነ ይገኛል። ምንድነው ማድረግ ያለብን? ጦር ሰራዊቱስ ምንድነው የሚጠበቅበት? እንደህዝብ አብረን በዚች አገር ላይ ለመቀጠል አንድ ሆነን ይችን አገር ማዳን አለብን። ይህ የተጀመረው የአማራና የኦሮሞ ህብረት በምንም መልኩ እንዳይዳከም ነቅተን መቆምና መጠበቅ አለብን። ሰዎቹ አንለቃችሁም ነው የሚሉት። ንቀት ነው።

ኦሮሞዎች ወድሞቻችን አንዳንድ ግለሰቦች በፌስቡክ ላይ የጀመሩትን ወያኔያዊ ኦሮሞን የመነጠል ፕሮፓጋንዳ ባትሰሙ ጥሩ ይመስለኛል። አንድ ጅል ጊዜ ያለፈበት ወሬ ሲነዛ ሰምቻለሁ። “ማንም አይገዛንም ፤ ኦሮሚያ ነጻ ትወጣለች ፤ የራሳችንን መንግስት እናቆማለን ፤ ነፍጠኛ ስር የተለጠፋችሁ….” ምናምን እያለ ሲዘባርቅ የሰማሁት አሳዝኖኛል። ከንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ማን በማን ስር ያድራል ብሎ እንደፈራ አልገባኝም።

ወታደሩ ክፍል ጊዜ ሳያባክን የህውሃት ያልሆነው ሁሉ መናበብ እና ከህዝቡ ጎን ለመቆም መቁረጥ ይጠበቅበታል። አንድ ሰው ወታደር ሲሆን ለሞት ተዘጋጅቶ ነው ስልጠና የሚገባው። ወታደር ለህዝብና ለሃገር ደህንነት ይሞታል። የህውሃት ያልሆነው ሰራዊት አንድ ሆኖ አፈሙዙን ባዛዦቹና በደጋፊዎቻቸው ላይ ማዞር አለበት። ህዝቡም አንድ ሆኖ አብሮ ለመፋለም ይህን ሰው በላ ቡድን ለማውደም መነሳት አለበት። ድል የህዝብ ነው።

Share