አልፎ አልፎ እንደነ ሔርሜላ የመሳሰሉ ከትግራይ ቤተሰብ የተወለዱትን ሳይ እጽናናለሁ እንጂ በአብዛኛው የትግራይ የማያቸው ተወላጆች የወያኔ ደጋፊነት እጅግ ያሳዝነኛል፡፡ እኔ ትግራይን ቀበሌዎቹንና ጉራንጉሩን ሁሉ ሳይቀር አውቀዋለሁ፡፡ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ የ27 ዓመት ዘመን ለብዙዎች እንደሚመስላቸው የተለየ ምቾት የነበረውና የደላው እንዳልነበር አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ብዙዎች እንደሚያስቡት በትግራይ ልዩ የሆነ የትግራይን ሕዝብ መሠረት ያደረገ ልማት ይቅርና በትግራይ ከወያኔ የገንዘብ አውታር ከሆኑት የኤፈርት ድርጅቶች በቀር ይህ ነው የሚባል የግል ድርጅት እንኳን አላውቅም፡፡ በተቃራኒው ሕዝቡን ለአገዛዝ እንዲመቻቸው በሴፍቲ ኔት እርዳታ እንዳኖሩትና ራሱን እንኳን ችሎ እንዳይኖር እንዳደረጉት አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በከፋ ደግሞ ለዘመናት በባህልም በሐይማኖትም በእርግጥም በደሙ ራሱ ወንድሙ የሆነውን የአማራ ሕዝብ እንደ ልዩ ጠላት እንዲያይ ከታች ከትመህርት ቤት ጀምሮ ወጣቶችን በከፋ የጥላቻ አስተሳሰብ ሲሞሉት ኖረዋል፡፡ ዛሬ የምናየውን አረመኔያዊነት አውርሰውታል፡፡ በትግራይ ትምህርት ቤቶች ሕጻናት እንዲዘምሩ የሚደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ሳይሆን እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የሕጻናትን አእምሮ በአረመኔነት የሚያሳድግ መዝሙር ነው፡፡ ምን አልባት ይሄን መዝሙር የምታውቁና ቋንቋውን በደንብ የምትረዱ ተርጉማችሁ ለቀሪውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ብታደርጉት የወያኔን አረመኔነት ላልገባቸውም እንዲረዱት ብታደርጉ ጥሩ ነው፡፡ ቢቻልስ ወደ ዓለም ዓቀፍ ቋንቋዎች ሁሉ በመቀየር ለተባበሩት መንግስታት የሕጻናት ድርጅት ዩኒሴፍ ጭምር ቢሰጥ እላለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ ደግሞ ወያኔ ሕዝቡ ከነበረው እምነት (የክርስትናም እስልምናም) አውጥቶ የወያኔ አምላኪ ያደረገው ቁጥሩ ቀላል አደለም፡፡
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ 27 ዓመት ከዛም በፊት 17 ዓመት በአጠቃላይ ዛሬ ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት እየሆነው ባለው ዘመን የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥሉለትና ለእኩይ ሴራው ግብር እንዲሆን የሚያስችሉትን ሁሉ አድርጎ ይሄው ዛሬ እንደምናያው በጦርነት እያስጨረሰው እናያለን፡፡ አዝናለሁ፡፡ በ17 ዓመቱ የቀደመ የውንብድናው ዘመን ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ስም በእርዳታ ያገኘውን ገንዘብ ለጦር መሳሪያግዥና ለራሱ ማደራጃ አውሎ ምን ዓልባትም በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖችን በረሐብ እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ ይሄን ወንጀል በቅርብ ማለትም ወያኔ በሥልጣን ላይ እያለ ለማጋለጥ የሞከሩ ሚዲያዎች ከኢትዮጵያ በዘረፈው የገንዘብ ኃይል ዝም አስኝቷል:: በወቅቱ ብዙ ሚዲያዎች ርዕሳቸው የነበረ ሲሆን የሚከተሉት ጥቂቶቹ እስካሁንም ይህን እውነት በድረገጻቸው እናነባለን፡፡ የሚከተሉትን እንብቡ፡፡ http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/8535189.stm ፣ https://www.dw.com/en/aid-millions-for-ethiopia-may-have-been-used-for-arms-purchases/a-5341167 ፣ https://www.theguardian.com/media/2010/mar/07/bbc-holds-firm-ethiopia-famine-funds
በዛን የረሀብ ወቅት የ ዊ አር ዘ ዎርልድ ቡድን የነበረውና በኋላም የሟቹ መለስ ወዳጅ የሆነው እንገሊዛዊው አቀንቃኝ ቦብ ጊልዶፍ ይህ ዜና በወጣ ወቅት እንጅ ተበሳጭቶ እንደነበረና በእርዳታ ሥም ከፍተኛ የሆነ ወንጀል እንደሰራ ተሰምቶት ነበር፡፡ ምክነያቱም ነብስ ለማዳን ሰጥተናል ብሎ የሚያስበው እርዳታ በረሐብ ላለቁት አለመድረሱ ሳያንስ ጭራሽ ለሌላ ነብስ ማጥፋት እኩይ ሴራ መዋሉ ነበር፡፡ በዛም ወቅት ቢሆን ገንዘቡን በእርዳታ ለጋሽነት ለወያኔ ያስረከቡ ድረጅቶች የሰሩትን አረመኔያዊ ተግባር ሊታወስ ይገባል፡፡ ዛሬም በእርዳታ ሥም ለሕዝብ ሳይሆን ወያኔን በምግብና በተለያዩ ቁሳቁስ እየረዱት እንዳለው ማለት ነው፡፡
እንግዲህ እንኳንስ ገና ከጅምሩ በጠላትነት ፈርጆ አማራን ማጥፋት መሪ ዓላማው አድርጎ በማኒፌስቶው ሳይቀር የጻፈውን ይቅርና እስከዛሬም በስሙ የሚጠቀምበትንና ነጻ አውጭህ ነኝ የሚለውን ሕዝብ ሳይቀር እንዴት ባለ አረመኔነት ይጨርስና ያስጨርስ እንደነበር ታዘቡ፡፡ ብዙ በተለይም ደግሞ ለእኩይ አላማው የማይተባበሩትንና ኢትዮጵያዊ ሥሜት ያላቸውን ትግሬዎች ባዶ ስድስት በተባለው የማጥፋት እቅዱ ጨርሷል፡፡ ሐውዜንን ለእኩይ አላማው በአየር አስደብድቧል፡፡ ሌላም ሌላም፡፡
ዛሬ ብዙዎች በየአደባባዩ እየተንከባለሉ የሚጩሁለት ለዚሁ ቡድን እንጂ ለትግራይ ሕዝብ እንዳልሆነ ግልጽ የሆነ መሰለኝ፡፡ ምክነያቱ ደግሞ በአንድም ይሁን በሌላ ከትግራይ ውጭ አብዛኛው በሌላ ቦታ የሚኖረው ትግሬ ከወያኔ ሥርዓት ተጠቃሚ ነበርና ነው፡፡ ሕዝብን ለመርዳት በሚል የሰበሰቡትን ገንዘብም ለዚሁ የወያኔ እኩይ ዓላማ አውለውታል፡፡ ጥቂቶችም ቢሆኑ ግን ባልገባቸው የዚህ እኩይ ዓላማ ተሳታፊ የሆኑ ይመስለኛል፡፡ እንግዲህ ምክሬ ለእናንተ ነው፡፡ ዓላማችሁ ምንድነው? ብዬም እጠይቃለሁ፡፡ ከዚህ ጦርነት በኋላ ትግራይ ከጥቂት እደለኛ ወጣቶች በቀር የአዛውነቶች ምድር ልትሆን እንደምትችል ማስተዋል ከቻላችሁ እውነቱ ይሄ ነው፡፡ እስካሁንም በጣም ብዙ ወጣት ረግፏል፡፡ እየረገፈ ያለው በአንድ ግንባር ብቻ በብዙ ሺዎች ጭምር ነው፡፡ የተረፈ እንኳን ቢኖር ከዚህ ጦርነት በኋላ ምን ያህል የስነልቦና ቀውስ እንደሚፈጠር አስተውሉ፡፡ በወገናችሁ ላይ የዚህን ያህል ጨካኝ አትሁኑ፡፡ የትግራይ ወጣት አሁንም እያለቀ ነው፡፡ እንደድሮው ጄኖሳይድ እያላችሁ ለመነከባለል እንኳን ዛሬ እያለቀ ያለው ትግራይ ውስጥ ሳይሆን የወያኔን አረመኔያዊ እቅድ ለማስፈጸም በአማራና አፋር የሰላማዊ ሕዝብ ነዋሪዎች መንደሮች ውስጥ ገብቶ የተሰጠውን የአረመኔያዊ ተግባር እየፈጸመ ባለበት ነው፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች በተለይም ከሕዝብ ብሶት በወጡ የአከባቢ ወጣቶች ለምርኮ እንኳን እጅ መስጥ በማይችልበት ሁኔታ ነው እያለቀ ያለው፡፡ በጥላቻና አረመኔያዊነት ያበዱ መሪዎቹ ከጅምሩ ይሄን ጦርነት እንዴት እንዳሰቡት ሳስብ ይገርመኛል፡፡ ይሄ ሁሉ እየሆነ ያለው ዓለም ሁሉ የወያኔን አረመኔያዊነት እስከሚያምን ድረስ ነው፡፡ ከወያኔ ጋር የቆሙ ሁሉ ያፍራሉ፡፡ ወያኔም ታሪክ ትሆናለች፡፡ ወገናችን ብላችሁ የምታስቡ ካላችሁ እንግዲህ የቀሩትን እንኳን ለማትረፍ ሞክሩ፡፡ በእኔ እምነት የአማራ የሆነ ልዩ ኃይል ሆነ ፋኖ ትግራይ ምድር ገብቶ ወያኔን ማሳደድ አይጠበቅበትም፡፡ በመንደሩ የመጣውን ሙሉ በሙ ሊጨርስ ግን ያለውዴታው የሆነበት አማራጩ ነው፡፡ ቢሳካለትና ቢያሸንፍ ወያኔ ምን ሊያደርግ እንደነበር ለዓለም ሁሉ በተግባር አሳይቷል፡፡ በዓለም ላይ የትኛውም አሸባሪ ኃይል እንደወያኔ አረመኔ እንደሌለ አስመስክሯል፡፡
ለሌሎች በተለይም ደግሞ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያዊ ከእኛ በላይ እያላችሁ በሕዝብ መከራ የምትነግዱ አሁንም ከድርጊታችሁ ብትታቀቡ እላለሁ፡፡ ኢሳት የተባለው ሚዲያና መሳይ የተባለው ጋዜጠኛው ከዚህ ጋዜጠኛ ጋርም በአላስፈላጊ መልኩ እየተገናኙ ያሉ የመከላከያ ባለስልጣናት ሕጋዊ የሆነ ምርመራ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ በቀደም የታማጆር ሹም የሆኑትን ማናገሩ ሲገርመኝ እንደገና ጀንራለ ባጫ ደበሌን በተመሳሳይ በስልክ ማናገር ብቻም ሳይሆን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሚፈቅድለት አካል ውጭ መነገር የሌለባቸውን መረጃዎች ሲያስተላለፉ ሰምቻለሁ፡፡ ጀነራል ባጫ ደበሌ የዛሬ ዓመት ሲሰጡ የነበረው አላስፈላጊ የሆነ ድንፋታዊ መረጃ ሳያንስ ሰሞኑን በተከታታይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሚፈቅደው ውጭ በየሚዲያው ያልተገቡ መረጃዎችን ሲሰጡ እያየን ነው፡፡ የእኚህ ግለሰብ ዓላማ ምንድነው? ለመሆኑ ግን አንድ ከፍተኛ የጦር መሪ ይቅርና በመከላከያው አነስተኛ ማዕረግ ያለው ሰው እንኳን በዚህ መልኩ በሞባል ስልክ ሳይቀር እየተደወለ መረጃ የሚሰጥበት አገር አለ? ሲጀምር በእንዲህ አይነት መልኩ በስልክ ቃለ መጠየቅ መደረግ በሕግ ጭምር እንዴት እንደሚታይ አላውቅም፡፡ በብዙ አገሮች ግን አይቻልም፡፡ ቃለመ ጠይቅም ካስፈለገ በአካል ቀርቦ እንጂ፡፡ ለማኛውም ኢሳት የተባለው ሚዲያና በተለይም መሳይ የተባለው ጋዜጠኛው እንዲሁም ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ጀንራሎች ሊመረመሩ ይገባል እላለሁ፡፡ ማን ይነካኛል አይነትም ይመስላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኢሳት ሚዲያ የተዛባ ወሬ በመንዛት ለወያኔ ከፍተኛ የሆነ እገዛ ካደረጉት ነው፡፡ ከጅምሩ እውነታውን ለሕዝብ ይፋ ያደረገውን የሚዲያው ተቀጣሪ ሲሳይ ጎበዜን ለምን እውነትን ተናገርክ በሚል ከሥራ በማሰናበትና እየሆነ ያለውን እውነት በመደበቅ በሕዝብ ላይ ወንጀል ሲሰራ የቆየ እንደሆነ አይናችን አይቷል፡፡ ሆኖም ዘመኑ በጅምላ የሚታሰብበት ስለሆነ ጠያቂ ላይኖር ይችላል፡፡ አንድ ቀን ግን መጠየቅ ግድ የሚልበት የመጣል፡፡ የደረሰው ጉዳት እጅግ አሳቃቂ ነውና ሁሉም ከመጠየቅ አይቀርም፡፡
ሰሞኑን ከአስገረሙኝ ነገሮች አንዱ የብልጽግና የሐይማኖት ክንፍ ካድሬዎች አንድ ደረጄ ከበደ የተባለ ሰው አማራ እየተገደለ ነው ለምን ትላልህ ተከትሎ በዘመቻ በተናጋሪው ላይ የተነሱበት ሁኔታ ነው፡፡ እውነት ነው ብልጽግና በዋናነት የፕሮቲስታነት እምነት ተከታዮችን ወደ ስልጣን በማምጣት የበላይ ለመሆን የሚጥር የአገርና ሕዝብ ራዕይ የሌለው በተቃራኒው ከወያኔ በተወረሱ ሴራዎች ገና ከጅምሩ በተበላበት ሴራ የሚንደፋደፍ የጥፋት ቡድን እንደሆነ እያየን ነው፡፡ አሁንም በካቤኖው ከ60 በመቶ በላይ በተለይም ደግሞ ጸረ-ኦርቶዶክስ የሆኑ ግለሰቦችን በማካተት መንግስት ነኝ እያለ ያለ አንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ አስገራሚው ነገር ግን በስልጣን ላይ የታሰበሰቡት የጴንጤ ስብስቦች ሳይሆኑ የፕሮቲስታንት አማኝ ነን የሚሉና በተለይም በእምነቱ አገልጋይ ነን የሚሉ ናቸው፡፡ ሰሞኑን ያየነው ጉድ ታዲያ አብይ አህመድ እንዴት ይነካብናል በሚል እብድ የሆኑበትን ትዕየንት ነው፡፡ እንደ እውነቱ ደረጄ ከበደ ምን እንደተናገረ አልሰማሁትም፡፡ በየቦታው የምሰማው ደረጀ ከበደ እንዴት አማራ ተጎዳ ይላል በሚልና አብይን እንዴት ይናገራል የሚል ነው፡፡ ደረጄ አማራው በልዩ ሁኔታ እየተጠቃ ነው ብሎ ከሆነ በእርግጥም እውነትን መካድ ስለማይችል ለህሊናው ይህን ተናግሯል፡፡ በላፉት ሶስትና ተኩል ዓመት የፕሮቲስታንቲኒዝም ዘመቻ በመንግስታዊ ተቋሙ ላይ ብቻ ሳይሆን በአገኛችሁን የአብይ አህመድ አዞህ ባይነት ማህበራዊ ስርቶችንም ስታወድሙ እንደነበር እናያለን፡፡ እነድነ ኢዩ ጮፌ፣ ዳንኤል ዳንሳና ስንት ተቆጥረው የማያልቁ ሕዝብን ወደለየለት ሥርዓተ ዓልበኝነት የሚከቱ ወንበዴዎች በየቦታው ሲፈነጩ ነበር፡፡ አሁንም የቆመ አይመስለኝም፡፡ ኮረና መጥቶ ትንሽ ቆም ብሎ ከሆነ እንጂ፡፡ ተው እንጂ፡፡ ይመስላችኋል? ማንም ቢሆን አይቀርለትም፡፡ እየሆነ ያለው ሁሉ ሁሉንም አጥርተን እንድናውቀው ነው፡፡ አንዱን በየኛ ቲቪ ቀርቦ አብይ ለኦርቶዶክስ ትልቅ ውለታ ውሏል ሲል ምን እልባትም መስሎት ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ያቀደውን እደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ ብዙዎች እንደሚያስብት ኦርቶዶክስ ሁለት ተከፈለች ከዛ አብይ አንድ አደረገን እንዳሉት አደለም የማስበው፡፡ እግዚአብሔር የራሱ እቅድ ነበረው፡፡ የጊዜው ጊዜ የሆነው ሁሉ ሆነ፡፡ ይልቁንስ አብይን ለሌላ ትዝብት ወደስልጣን አምጥቶት ነበር፡፡ ሆኖም በብልጽግና ማኒፌስቶው ሳይቀር ጽፎ አሁን በተግባር እያደረገው ያለው የጸረ-ኦርቶዶክስ ዓላማውን ሁሉም በደንብ እስኪገባው ነው፡፡ ወያኔ ዘር ብቻ ነበር፡፡ ብልጽግና ከወያኔ የወረሰውን ዘረኝነት ከፍ በማድረግ የሐይማኖት መስፈርትን እየተጠቀመ ነው፡፡ ኧረ ተው ብለን ነበር፡፡ በግድ እስከሚሆን በፍቃደኝነት እንዳያስተውሉ ታውረዋልና ጊዜው ሩቅ አልመሰለኝም፡፡
ሌላው ሰሞኑን ታማኝ በየነ በሰሜን ሸዋ ሕዝብ ሰብስቦ አማራ እንዴት ወያኔ እዚህ እስክትደርስ ምን ሲሰራ ነበር በሚል በከፍተኛ ድንፋታ በሚመስል ሲናገር ነበር፡፡ ሆኖም በስተመጨረሻ እንድ ትልቅ አባት በፊቱ ነገሩት፡፡ እንዲሁ ያለ ነገር አንድ ደረጄ የተባለ ሌላው የብልጽግና አፈቀላጤ ሲናገር ነበር፡፡ ታማኝ በወስንት አጅብ ታጅቦ ሰሜን ሸዋ ስለተገኘ ትልቅ ገድል የፈጸመ መስሎታል፡፡ ደሀ ገበሬ በእጁ በያዛት ግፋ ቢል ክላሽና ጥቂት ጥይቶች መድፍና ታንክ ታጥቆ በመከላከያው ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል እየተከዳ ብቻውን ምንስ ሊያድርግ ኖሯል፡፡ ያም ሆኖ ይመጣብኛል ብሎ ሳይዘጋጅ በታክና መድፍ ተዘጋጅቶ የመጣን እንዴት ሊቋቋም ይችላል ብሎ ይሆን ታማኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን የማንም ቀላማጅ አፍ ማሟሻ አይሆንም፡፡ ተደራጅቶ ሲመክትማ አይንህ አይቷል ወይም ሰምተሀል፡፡ ምን አልባት አንተ ያለህበት መከላከያው ስላለ ነው፡፡ በአንዳንድ መከላያው ዝር ባላለበት ቦታዎች እኮ አሁንም ቢሆን ብዙ ቦታዎችን እየያዘ ያለው ገበሬው ነው፡፡ ሊያውም የወያኔን ወራሬ አረመኔ ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳያስቀር፡፡ ምነው አቅለበለባችሁ ግን? በዚህች አጭር የሶስት ዓመት ጊዜ ለእናንተ ከአሜሪካ አዲስ አበባ መንሸራሸር ስለሆነላችሁ ሕዝብን ሳይሆን ለዚህ ያበቃን እያላችሁ ለምታመልኩት ከወያኔም በከፋ ሕዝብን እያስጨረሰና እየጨረሰ ላለ የኦነጋውያን ብልጽግናን ገመና ለመሸፈን የሄዳችሁበት ርቀት ወጋ ሳያስከፍላችሁ አይቀርም፡፡ ማንም የሚያልጥ አይመስለኝም፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ፣ ሠላም ይስጥ!
አሜን
ሰርፀ ደስታ
http://amharic.zehabesha.com/ethiopia-famine-aid-spent-on-weapons/
http://amharic.zehabesha.com/bbc-holds-firm-over-ethiopia-famine-funds-report/