ወገን ሆይ ክፉ ሞቶም ይገድላል …እንዳትታለል ! –  ማላጂ

በኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ላይ በጥላቻ እና ዕብሪት ተጠንሰሶ ተወልዶ ዛሬ ለአገራችን አንድነት እና ሉዓላዊነት ስጋት መሆኑን  በተደጋጋሚ  በተግባር  የሚያሳዩት  የጥፋት እና ሞት የዓመታት እና የዕለታት መርዶ በጠላት ብርታት ሳይሆን ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ሰሞነኝነት እና በዘላቂነት አለመደራጀት ነዉ ፡፡

እናት አገራችንን በሴራ ትርክት ፤ህዝባችንን በጥላቻ እና ፍርኃት ጭንብል  አንድን ህዝብ አባር  እና ገባር አድርጎ በመፈረጂ ለመፈረካከስ እና ለማርከስ ወደ ብሄራዊ  ቀዉስ እና ክስመት  የተደረገዉ የዘመናት የጥፋት ጉዞ ጠላት ሲጀምር ኢትዮጵያ ብሎ አገር ፤ ዓማራ ብሎ ህዝብ  የጥላቻ ማሟሻ  ሀ ሁ….ከሆነ ብዙ አስርተ ዓመታት አልፈዋል ፡፡

ት.ህ.ነ.ግ ኢህዴግ ወደ ማዕከላዊ መንግስት መንበረ ስልጣን ከመጣ በኋላ  በግለሰቦች ፣ በዓማራ ማህበረሰብ ፣ በህዝብ ሠባዊ መብት እና ነጻነት ጉዳይ ተነስተዉ የፖለቲካ አመራሮች ላይ የደረሰዉ ሰቆቃ እና መከራ በዓይነት እና ብዛት  ግዝፈት እና አድፎ አስከ ዛሬ ከተከፈለ የህይወት እና ሀብት ዋጋ በላይ አገሪቷን እና ህዝቧን ዛሬም እያስከፈላት ነዉ ፡፡

በመላዉ የአገሪቷ የሚገኙ ዜጎች በተለይም ዓማራ በጠላትነት ተለይቶ በማንነት ላይ ስደት፣ ፍጂት እና ጥፋት ሲደረግበት ዓመታት ተቆጥረዋል ፤ ይህም  ክፉዎች ከአስተሳሰባቸዉ እና ከድርጊታቸዉ ጋር ቢያልፉም ዛሬም የክፋት ዉርስ አራማጆች  የክፉዎችን መንፈስ አደራ እያስፈፀሙ ይገኛል  ፡፡

ከ1983 ዓ.ም. ማግስት ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጠል የበፖለቲካ ሴረኞች ወጥመድ ተጠልፈዉ   የሞቱት የመጀመሪያዉ የዓማራ ክልል  ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ሙሉዓለም አበበ፣ አንጋፋዉ የህክምና ምሁር እና የኢትዮጵያ ዕንቁ የሰባዊነት እና ነጻነት አባት ፕ/ር አስራት፣ አስማረ ዳኜ፣ ዶ/ር አምባቸዉ መኮንን ፣ ፣ጀ/ል አሳምነዉ ፅጌ …….የተሳደዱበት፣የተዋከቡበት እና የሞቱበት ምክነያት የግል ጥቅም እና ስም ፈልገዉ ሳይሆን የክፉዎች ስራ በህዝብ እና በአገር ላይ የሚያስከትለዉን መከራ ገና ከጥዋት  አስቀድመዉ በመረዳታቸዉ አምርረዉ በመጥላታቸዉ እና በመታገላቸዉ የደረሰባቸዉ አግላይ የፖለቲካ ሴራ  ዉጤት ነበር ፡፡

ኢትዮጵያዉያን እና ዓማራ ነን የሚሉት እና እንወክላለን የሚሉት የፖለቲካ ሊህቃን በተለይም ብአዴን…ትህነግን ከደደቢት ዋሻ ወጥቶ ፀሃይ እንዲሞቅ  በህዝብ እንዲታወቅ ካደረገበት 1982 የኢኃዴግ  ምስረታ በኋላ   ትህነግ ከፊት  በ.አ.ዴ.ን. ከኋላ ሆኖ የዓመራ ህዝብ ቤት ለንቦሳ ብሎ ከተቀበለ በኋላ    የአማራን ህዝብ ጠላት በማድረግ በ.አ.ዴ.ን.  ራሱም ሆነ  እወክለዋለሁ የሚለዉን ህዝብ በአገሩ ባዕዳ እና የበይ ተመልካች በማድረግ ዓመታትን አሳልፏል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዉያን በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በሚኖሩበት የፖለቲካ ዉክልና ሲያገኙ ፤ጥበቃ እና ከለላ ሲደረግላቸዉ ዓማራ ከዚያ አስካሁን እየሆነ ያለዉን ዓለም የሚያዉቀዉ ነዉ ፡፡

መንም እንኳን አስቀድመዉ የጠላት ሀሳብ እና ተግባር አስቀድመዉ የተረዱ ብዙ በድርጅቱ ዉስጥም ሆነ ዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን የነበሩ እና ያሉ ቢሆንም ብአዴን ካሉት ዉስጥ ጥቂቶች  ለዕዉነተኛ የህዝብ መብት እና ነጻነት  የቆሙ ቢኖሩም በተቃራኒዉ አስካሁን ከአስተሳሰብ በድንነት ያልተላቀቁ መኖራቸዉ ዛሬም ህዝቡን፣ ድርጅቱን እና አገሪቷን ዋጋ እያስከፈለ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራና ኢትዮጵያዊነት፤ በጠላትም በወገንም እስከ ሞት

በግዴለሾች እና ሠነፎች የብቃተ ህሊና ድክመት አገር እና ህዝብ አይከፍሉት አሳር እና መመዝበር ከግል እና ቡድን ጥቅም በላይ አገር እና ህዝብ ሊቀድም እንደሚገባ ካለማወቅ ሳይሆን በምንቸገረኝነት እና በማን አለብኝነት መንፈስ  አይቶ ባላየ ማለፍ ይህም አበዉ  “ጓደኛህ ሲታማ….” የሚሉትን አገራዊ የዕድሜ ልክ እና ዘመን ተሸጋሪ ብሂል እንደ ዋዛ የማየት በአገራችን የተጠያቂነት አሰራር አለመኖር እና አለመተግበር ነበር ፡፡

“ጅብ አስኪይዝ ያነክስ ” እንዲሉ አበዉ በአንድ ፖለተካ ጥላ ስር (ኢሃዴግ) የሚገኙ ብአዴን  እያለ እንደሌለ“ በድን ” መሆን እና ትህነግ ከኋላ መጥቶ ራሱን አድራጊ ፈጣሪ( አዉራ ፓርቲ) አድርጎ ያሻዉን ሲፈጽም  ሲያስፈፅም  የኖረ  “ኩት አትበሉኝ የሹም ዶሮ….”  አንድን አገር እና ህዝብ በመከፋፈል ፣በማታለል ፣ በማግለል ፣ መበደል እና መግደል  ብቸኛ ስልጣን አድርጎት መኖሩ ዛሬ የህዝብን ጥያቄ ለማስተናገድ ቢከብደዉ ችግር ላይሆንም ፤ላይገርምም ይችላል፡፡

የዓማራ ህዝብ እና ድርጅቶች ለጋራ እና ለአገር ህልዉና በህብረት አለመቆም እና አለመደራጀት ለዚህ ምቹ ነገር ሆኗል ፡፡

ለዘመናት እንደ ክፉ ቁስል በሚመረቅዝ ጥላቻ የተለወሰዉ ትህነግ የሚደርሰዉ ጥቃት በኢትዮጵያዊነት እና  ዓማራነት መደጋገም  “ ክፉ ሞቶም ይገድላል ” የሚለዉን የአበዉ ብሂል ማስታወስ ይገባል ፡፡

የየትኛዉም የፖለተካ ድርጅት አባል ፣አመራር ሆነ ደጋፊ እና ህዝብ የዓማራ ህዝብ ህልዉና ፣ነጻነት እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ምሶሶ አንድ እና የማይለይ መሆኑን ሳንዘነጋ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ደህንነት እንዲሁም ሉዓላዊ ክብር የምናስብ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ላለዉ እና ለነበረዉ አይረሴ ጥቃት ምክነያቱ የዓማራ ህዝብ ህብረት እና አንድነት አለመደራጀት እንደነበር መረዳት አለብን ፡፡

ስለዚህም የዓማራ ህዝብ በአንድነት እና ህብረት መደራጀት ፣ ማወቅ እና መታጠቅ እንዲሁም ከህዝቡ ለወጣ የህዝብ ቁርጥ ቀን ልጆች  ድጋፍ እና ሁለንተናዊ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡

ለአገር እና ወገን በችግር እና መከራ ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቀድሞ  ለሚደርስ  ህዝባዉ ሠራዊት ፋኖ፣ የዓማራ ልዩ ኃይል፣ ኢትዮጵያዊ ህዝባዊ ሠራዊት ባስፈላጊ ነገር ሁሉ መደገፍ ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡

እኛ እና ኢትዮጵያ ተከብረን እና ታፍረን የምንኖረዉ በሚነገረን ሳይሆን በምናየዉ እና በምንኖረዉ ልክ እና መልክ በተጨባጭ ለዕዉነተኛ ህዘባዊ እና አገራዊ ፍቅር ለሚዋደቁ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ፤ብሄራዊ ሠራዊት በወኔ፣ በሀብት፣ በዕዉቅና እና በማዕረግ ዕድገት ለሚገባዉ የሚገባዉን መቸር ያስፈልጋል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢቲቪ “ያልተገሩ ብዕሮች” ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ (ነቢዩ ሲራክ)

በዱር በገደል፤ በጋራ ሸንተረር ፤ በበረኃ እና በሜዳ …..በዕዉነተኛ ብሄራዊ ህዝባዊ ስሜት ለሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን (ጦር ሠራዊት፣ ዓማራ ህዝባዊ ሠራዊት/ ፋኖ፤ ልዩ ኃይል)  ዋጋ እንስጥ፣ አለን አንበል እንተባበር በህብረት እና በአንድነት እንኑር ፡፡

የሶስት አሰርተ ዓመታት የመከራ ገፈት ቀማሽ የሆኑት  ለኢትዮጵያ  እና ህዝቧ በተለይም ዓማራ ህዝብ ሞት ፣ባርነት እና ድህነት የታወጀበት  ዓማራ ህዝብ  ዘመናት ለደረሰበት ዘግናኝ ሁነቶች መንስዔም ሆነ ከነዚህ የዓመታት ስቃይ መቋጫ  እና መፃዒ ትንሳዔ የመጀመሪያዉ  ረድፍ ተጠያቂነትም ሆነ ባለቤት  የዓማራ ህዝብ እና የፖለቲካ አመራር ናቸዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በኢትዮጵያዉያን እጂ ሲሆን የዓማራ ህዝብ እና የፖለተካ ድርጅቶች ግን ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለባቸዉ ፡፡

ብ.አ.ዴ.ን.  ትህነግን ወደ ፊት አምጥቶ የስልጣን ባለቤት ያደረገዉ  በዓማራ ህዝብ ስም ሆኖ  ነገር ግን በዓማራ ህዝብ ላይ ለደረሰዉ የዘመናት ጭቆና እና መከራ ሲጫንበት ህይወት አልባነት (በድንነት) መመልከቱ ሙሉ ለሙሉ ሊቆም እና ሊደመደም ይገባል፡፡

ሁሉም ነገር ህዝብ እና የጋራ አገር ሲኖር እንደመሆኑ ከምንም ከማንም በላይ ለአገር እና ህዝብ ህልዉና ሲባል የግል ፣ቡድን እናፓለቲካ ጥቅም በይደር ሊታለፍ ይገባል፡፡

ስለዚህ ወገን ሆይ ከሞት በላይ ሞት የለም እና የኢትዮጵያ እና ዓማራ የህይወት እና ሞት ጉዳይ መሆኑን መረዳት እንደመሆኑ የኢትዮጵያ ህልዉና እና ሉዓላዊነት ያገባኛል ፤ይመለከተኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊል ይገባል፡፡

ማላጂ

“ድል ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን  !”


ባልተኖረ ህይወት ከንቱ ዉዳሴ..ይቅር !

በኢትዮጵያችን ታሪክ ሳይሰሩ ለታሪክ የሚሆን ትንሽ ዘር ፍሬ ሳያበረክቱ የጭንቅ እና መከራ ለሊት ሊነጋ ሲል አለን የሚሉ ከታሪክ ድረሳናት የምናዉቃቸዉ ብዙ እና ዕልፍ አዕላፍ ናቸዉ ፡፡

የሚገርመዉ እንደ ባህል ሆኖ ሲወርድ ሲዋረድ በትዉፊትነት መቀጠሉ ነዉ ፡፡

በዘመነ መሳፍንት አፄ ቴወድሮስ  ኢትዮጵያን ከአካባቢ ክፍልፍል ወደ አንድ እና ገናና ኢትዮጵያ ለማብቃት ከነበራቸዉ ብርቱ ህልም የተነሳ ላይ ታች ባሉበት ዘመን እርሳቸዉ እና ተከታዮቻቸዉ ወደ መኃል ኢትዮጵያ -ሸዋ ሲዘምቱ የጊዜዉ ባላባት ነን የሚሉት የዘመነ መሳፍንት ስርዓት ናፋቂዎች የንጉሱን ድል እና ተጋድሎ ታሪክ ለራሳቸዉ ለማድረግ ሞክረዋል ፤አምፀአልፎ በዘመን ሲለወጥ ትዉልድም በትዉልድ ሲተካ  በአገራችን ታሪክ ሰሪዎች ታሪክ  ሲነፈጋቸዉ የኋላ ረድፈኞች እና አዉርቶ አደሮች በቁማቸዉ ሀዉልት ለማሰራት ይሽቀዳደማሉ ፡፡

ይህ በ18ኛዉ ክ/ዘመን የነበረዉ የታሪክ ሽሚያ በዕምየ ሚኒሊክ ዘመን እንዲሁ በአድዋ ጦርነት ክተት ወደ ኋላ ያደፈጡ ታሪክ ለመሻማት በዕዉነት እና ስራ ቁርጠኝነት ያነሳቸዉ አድፍጠዋል    ፡፡

በኢጣሊያ የ ኛዉ ወረራ ጊዜ ለ ዓመት በተደረገዉ የሉዓላዊነት እና ነፃነት ተጋድሎ እና ትንቅንቅ  ከፍተኛዉን ዋጋ የከፈሉት የአገር ባለዉለታዎች ተረስተዉ እና ተገፍተዉ ፈርጣጭ እና አልማጭ ለታሪክ ሽሚያ እና ከንቱ ዉዳሴ መሽቀዳደም ዕዉነተኛ ታሪክ የሰሩትን  የታሪክ  ባለቤቶችን በታሪክ ቀበኞች አገሪቷ ብታጣም ታሪክ እና ህያዉ ስራቸዉ ለዘላለም በተዉልድ ቅብብል ሲያብብ እና ሲታሰብ ይኖራል፡፡

ከዘመነ ኢኃዴግ በፊት በነበር ህዝባዊ ንቅናቄ እና ማዕበል አይነኬ የተባለዉን የዘዉድ ስርዓት የህዝብን እና  አገርን ከነበረባቸዉ የመከራ እና ችግር ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመስበር በፊዉታራሪነት የመሩት ቁርጠኛ እና ሀቀኛ ኢትዮጵያዉያን በሴራ በፍርደ ገምድሎች እና ባልሰሩት ታሪክ ተሻሚዎች ታሪክ ሰሪዎችን በመግፋት ታረካዊ ስህተት ተፈፅሟል ፡፡

ይህ ሲወራረስ መጥቶ በዘመነ ኢኃዴግ በርዕዮተ ዓለም ልዩነት እና ከፖለቲካ ዓመለካከት ልዩነት ተርፎ በጎጥ እና በቋንቋ ወገንተኝነት ከስራ እና ተግባር ጋር የተጣላ የታሪክ ባለቤት ለመሆን የሚደረገዉ ሩጫ ቀጥሏል፡፡

በማንኛዉንም ነገር መጋራት እና መሳተፍ የባህላችን ገፅታ ቢሆንም የሰዎችን በጎ ተጋድሎ የስራ ዉጤት የሆነዉን አቋራጭ መንገድ በመከተል ባልዋሉበት የታሪክ ትሩፋት ባለቤት ለመሆን እና በተቃራኒዉ ታሪክ ለሰሩት ዕዉቅና እና ባለቤትነትን መጋፋት እና ንፍገት ለትዉልድ እና ላገር እንደማይበጂ ታዉቆ በዘመናችን   ለዕዉነተኞች የስራ እና የታሪክ ባለቤቶች ፍቅር እና ከብር ልንቸር ይገባል ፡፡

ለታሪክ ባለቤት ዕዉቅና እና ከበሬታ በመስጠት የታሪክ ተጋሪ የመሆን ሰጥቶ መቀበል ልምድ እና ወግ (መርህ) ጊዜዉ አሁን መሆኑን በመገንዘብ ለዕዉነት በመቆም ለትዉልድ የሚሸጋገር ታሪክ እንስራ ፡፡  ሳይኖሩ ታሪክ ለሚጋሩ ከሚነባበሩ እና ለሀሰተኛ ትርክት ከሚተባበሩ  ለዕዉነተኛ ባለቤቶች  የስራ ዉጤት ምስክርነት ፣ ዕዉቅና እና አክብሮት ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን እና ኃላፊነትን መወጣት ይጠበቃል፡፡

አበዉ ለም ባልዋለበት  ኩበት ….እንዲሉ  ከኋላ ሆኖ ደጀንነት እንጂ ፊዉታራሪነት ስለማይገኝ  ከአልቦ ስራ ታሪክ እና ከንቱ ዉዳሴ ልማድ ልንላቀቅ እና ነፃ ልንሆን ይገባል ፡፡

 ዛሬ እኛ የዘመናችን ባለታሪኮችን  ብንክድ መጪዉ ትዉልድ እና ታሪክ እኛን ዕጥፍ ስንካድ እና ስንረሳ  ታሪክ ሰሪ የታሪክ ባለቤቶችን ዝንተ ዓለም በክብር እና ፍቅር እንደሚዘክራቸዉ ለአፍታ መርሳት፤መዘናጋት  የለብንም ፡፡

“የምንጊዜም ምስጋና ፤ክብር ፣ፍቅር እና ድል ለብሄራዊ እና ህዝባዊ ሠራዊት !!   ”  

ድል ለባድል ፤ ታሪክ  ለሠሪ፤ ሞት ለመሰሪ   !!

 ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share