December 6, 2021
7 mins read

ህውሃት እያዘናጋን አንዳይሆን! ለህወሃት መዘናጋት በትውልድ ላይ መፍረድ ነው፤ – ገብረ አማኑእል፤

Tigray leader 800x450 1አገራችን ኢትዮጵያ በ1960ዎቹ የወጣቶች አንቅስቃሴ  ምክንያትነት በመጣው ለውጥ የተነሳ በችግርና መከራ ስትናጥ ይኽው ግማሽ ምዕተ ዓመታት ሊቆጠር የቀረን ጥቂት ጊዜ ነው። በዚህ ሁሉ ነውጥ ውስጥ ‘ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሄር ተዘረጋለች!’ ነውና ከየዘመናቱ ሃይለኛ ማዕበላት ተርፋ እንደገና ለመቆም እየተውተረተርች ትገኛለች። በነዚህ ዓመታት የደረሱ ጥፋቶች የትየለሌ ናቸው። በእነዚህ ዘመናት ከሁሉ በከፋ ላገር ዕድገት መሠረት የሆነው ወጣት ውሃ በማያቋጥሩ ምክንያቶች እንደቅጠል ረግፏል። በርካታ አገር የመምራት አቅም የነበራቸው ወጣቶች ፊደል በቆጠሩም ሆነ ባልቆጠሩ ፖለቲከኞች የትርምስምስ ፖለቲካ ረግፈውል። ከነዚህ ሁሉ ጊዚያት ወድቀቶች ግን ያለፉት ሠላስ አመታትን የሚስተካከል ውድቀት በአገራችን የታየ ያለ አይመስለኝም።

ውለታ-በላውና ዓይናውጣው ህውሃት ሥልጣን ለመያዝ በ1983 ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ወዳጅ መስሎ ገብቶ፤ከቤቱ እያሳደረ እየመገበ፤ ከመንግስት ሃይል እየደበቀ፤ ከቤቱ እያኖረ ያሳለፈውንና ለሥልጣን ያበቃውን ባላገር ዛሬ አባውራውን ገድሎ፣ ሚስቱንና ልጁን ደፍሮ፣ ከብቱን አርዶ በልቶ የተረፈውም ገድሎ፣ ጎተራውን መዝብሮና ዘርፎ፣ ለነገ አንዳይተርፈው የቀረውን ቤቱንና ንብረቱን አቃጥሎ ለዘመናት ችግር ዳርጎታል። ይህ ህወሃት የተሰኝው የዲያቢሎስ መልክተኛ ለተገኘበት ህዝብም ሆነ ለሌላው የሚያዝን ልብ የለውም። በሰው ቁመና ውስጥ የሚንቀሳቀስ እኩይ አንሰሳ ነው ብሎ መደምደም የሚቻል ይመስለኛል። ይህንን ተግባሩን ለአያሌ ዘመናት አሳይቶናልና ነው።

በአሁኑ ሰዓት ይህ እኩይ የጥፋት ሰራዊት ከብዙ ትዕግስት በኋላ በአምላክ ፈቃድ ወደአንድነት በመምጣት ላይ ባለ ህዝብ እየተቀጣና ወማይቀረው መቃብሩ እየወረደ ይገኛል። ሆኖም ከዚህ ሁሉ የህውሃት የክህደት፣ የውሸት፣ የጭካኔ፤ የበቀል፤ ከሰው ተፈጥሮ ውጭ የሆነ ባህርይና ምግባር ሳንማር ቀርቶ ለዳግም ጥቃትና መከራ፣ ውድመትና ዕልቂት ህዝባችን አንዳይዳረግ፤ የማጭበርበሪያ ስልቶቹን ተረድተን ልንከላከለው ይገባል።

በቅርቡ፣ በርካታ የወያኔ ምላምሎች እጃቸውን በመስጠት ላይ አንደሚገኙ ተመልክተናል። ዕርግጥ ነው እነዚህ ወጣቶች በቅርቡ በግዳጅም ጭምር የተመለመሉ ሊሆኑ ይችላሉ። በመጀመሪያ እነዚህ ወጣቶች በህውሃታዊ ርዕዮተ ዓለም ተጠምቀው ያደጉ በመሆናቸው የአገርና የወገንነት ስሜት አንዲኖራቸው ለማድረግ ጊዜ የሚፈጅ ስልታዊ ጥረትን ይጠይቃል። ህውሃት ወደሥልጣኑ ለመመለስ ይሆነኛል ያለውን መንገድ ሁሉ እንደሚጠቀም መዘንጋት ጅልነት ይመስለኛል። በመሆኑም እነዚህን ምርኮኞች በመልካም ሁኔታ አንዲያዙ ማድረጉ መልካም ሆኖ፤ በተለይም ብዙዎቹ በወያኔ ስርዓት ውስጥ የተወለዱና ያደጉ እንደመሆናቸው የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲያመጡ ማስተማር ጊዜና ትዕግስት የሚጠይቅ መሆኑን ተረድቶ በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝና ተመልሰው በተለየ የህውሃት ስልት መሣሪያ አንዳይሆኑና በህዝብ ላይ ጥቃት አንዳያደርሱ ባግባቡ መያዝ ይገባል። በጥንቃቄ የሚመራ የተሃድሶ ስልትና የጊዜ መርሃግብር መንደፍ ተገቢ ነው።

አገራችን ኢትዮጵያ ከደረሰባት ጉዳት ለማገገምና የህወሃት አወቃቀር ከተበተበባት ችግር ለመላቀቅና አንደአገር ቆማ፣ የህዝብን ሰባዓዊ መብትና ባገሩ በነጻነት የመኖር መብት ለማስከበርና ደህንነቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ሥርዓትን ለማምጣት ገና ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ መረዳት ይገባል። ለዚህ ያለውን ሥርዓት የምጠይቀው ብዙ ጥያቄ አለኝ። ሆኖም ለአሁኑ ዘለቄታዊ ሰላም፣ ነፃነት ዲሞክራሲ የሚገነባው የሰዎች አስተሳሰብና አመለካከት ሲለወጥ ስለሆነ ሁሉም ዜጋ አንደያቅሙ በተለይ በህውሃታዊ አስተሳሰብ ተቀርጾ ያደገን ወጣት ሥርዓታዊ በሆነ መንገድ ትክክለኛ አስተሳሰብና የሰውን ክቡርነትና እኩልነት አውቆ አብዲያከብር ለማድረግና፤ ይህም ተቋማዊ መሰረት ይዞ ዘላቂና ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ቋሚ የዲምክራሲ ስርዓት መገንባቱ እስኪረጋገጥ ለአፍታም ሳንዘናጋ ልንታገል፤ ልንማር፤ ለናስተምር፤ ሥርዓትን ልንገነባና የጸና መሠረትን ልንጥል ይገባናል።

ኢትዮጵያ በአዲሱ ትውልድ፤ በአውቀትና ብቃት ላይ የተመሠረተ ዕውነተኛ ሥርዓት ትገነባለች፤

ፍትህና ርትዕ በኢትዮጵያ ይሰፍናል፤

አገርችን መግባ፤ አልብሳና አስተምራ ያሳደገቻቸው ከሃዲያን ካደረሱባት ስቃይ ታገግማለች!

በፈጣሪዋ ሃይል፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ታፍራና ተከብራ ለህዝቧ የደስታና የተድላ የምስጋና ምድር ትሆናለች!

 

ገብረ አማኑእል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop