ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን፤ ኤርትራውያን፣ሱማሌያውያን እንዲሁም ሌሎች ለእውነት የቆሙ ወዳጆች በየአገሩ የታየው በአንድ ተሰልፎ የምዕራባውያንን ሴራ ማውገዝ እጅግ ካስደሰቱኝ ነገር ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ዓለም ይፈራሀል፣ ያከብርሀል፡፡ ብዙዎች በተበታተነ ሐሳብ በመቆማቸው ተበልተዋል ጠፍተዋል፡፡ ለሊቢያ መውደም ዋነኛ ምክነያቶች ሊቢያውያን ናቸው፡፡ ለኢራቀም ለሶሪያ ለሌሎችም የራሳቸው ዜጎች አለማስተዋል ነው፡፡ ሊያውም ከ30 ዓመት የዘር ተኮር የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ መረጨት በኋላ ይሄ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዳይሆን እግዚአብሔር እየሰራ ያለውን ድንቅ ነገር ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ እንኳንስ ኢትዮጵያውያን ሌሎችን ሁሉ ስለኢትዮጵያውያንና ብሎም ስለአፈሪካ ቀንድ ሕዝቦች ሁሉ እያሰባሰበ በአንድነት ያቆመን የእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ በዚህ ወቅት ግን በተቃራኒው የተሰለፉ ከዚህ እድል የተገለሉ እንደሆኑ አስባለሁ፡፡
ብዙዎች ኢትዮጵያዊ ሆነው ከኢትዮጵያ ይልቅ የአብይ አህመድ ነገር እንቅልፍ ነስቷቸዋል፡፡ በቀጥታ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብለው ከተነሱት እነዚህ የተለዩ አደሉም፡፡ ይሄ እየሆነ ያለው የዓለም እውነትን ናፋቂዎች ሁሉ በአንድነት ስለኢትዮጵያ በቆሙበት በዚህ ወቅት መሆኑ ደግሞ የሚገርም ነው፡፡
በትላንትናው እለት አብይ አህመድ መግለጫ ሰጠ ተብሎ የብልጽግና ልሳኖች ሁሉ ቀኑን ሙሉ ስለዚሁ ሲያወሩልን ውለዋል፡፡ ዛሬም በሰፊው ቅትለሏል፡፡አዝናለሁ፡፡ አብይ አህመድም በመናፈሻ ፎቶ ሲያደርገው የነበረውን ድራማ በአዲስ መልክ የጀመረ ይመስላል፡፡ መግለጫው እንደመግለጫነቱ ባልከፋ፡፡ ሲጀምር ሰውዬው በአፉ ተናገረ እንጂ በተግባር ሲሰራ የታየው አንዳች ነገር የለም፡፡ እንግዲህ ከሶስት ዓመት ተኩል በላይ በሆነው በዚህ ቦታ የተቀመጠበት ጊዜ አንስቶ በተግባር ሲያደርግ ያየነው ከሚናገረው ተቃራኒውን ነው፡፡
አብይ አህመድ አስጠንቁሎ ይሁን ምን እንደሆነ ባይገባኝም ከስንሞት ኢትዮጵያ ከስንኖር ኢትዮጵያዊ አደንዛዥ ንገግሩ በኋላ የመጀመሪያ ያደረገው ተግባሩ የኢትዮጵያዊነት ምሳሌ በሆነው አንበሳ ምትክ በኢትዮጵያ ምድር እንኳን በሌለች ወፍ ፒኮክ የቤተመንግስቱን ምልክት መቀየር ነው፡፡ ይሄን እንደዋዛ ሊያሳዩን የሚፈልጉ አሉ፡፡ ምን አለበት ይሉናልም፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ ማንሳትም አያስፈልግም ይሉናል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት እንደም ጊዜ መሠረታዊ ነገር ላይ እንዳናሰብ በየቀኑ አጀንዳ እየሰጠና በገዛቸው ሚዲያዎቹ ሕዝብን እያደነዘዘ ዛሬ ያለንበት ደርሰናል፡፡ የአንበሳው በፒኮክ መቀየሩ ዋና የሴራው ምልክት ነበር፡፡ ለብዙዎች አይገባቸውም፡፡
ኢትዮጵያዊነት ተመልሶ ይገንባል ብለን ተስፋ ያደረግንውን ሁሉ ከትግሬ ወያኔ በቀዳው አካሄድ ከዛም በከፋ ዛሬ በምናየው የኦሮሞ ኦነጋውያን ተረኝነት ተክቶት አይናችን እያየ ሕሊናችን እያወቀ ይሄን በመካድ ነው ዛሬ ብዙዎች በኢትዮጵያዊነት ሥም የአብይ አህመድ አምልኮታዊ አስተሳሰብ ውስጥ እንድንኖር የሚፈልጉት፡፡
በመጀመሪያ ለአገሩና ሕዝቡ ቅን የሆነን መሪ እግዚአብሔር በግልጽ ይረዳዋል፡፡ በሚመራው ምድር ሁሉ ሰላም ይሆንለታል፡፡ የሚሰራውና የሚናገረውም ሁሉ ይከናወንለታ፡፡ በአለፉት ሶሰትና ተኩል በላይ በሆኑ ዓመታት ያየናቸው አረመኔያዊና ለጆሮም ለአይንም የሚሰቀጥጡ ድርጊቶች በአብይ አህመድ ዘመን መሆኑን ማንም ሊክደው አይችልም፡፡ ሲጀምር ከወያኔ ትግሬነት ወደ ኦነግ ኦሮሞዋዊነት ከመቀየሩ በቀር አንድም የተቀየረ ነገር ባልኖረበት ለውጥ እያልን አብረን ስንዘፍን ከረምን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አስተውሉ፡፡ እግዚአብሔር የገዛ ሕዝቡንና አገሩን በቅንነት የሚመራ መሪ እግዚአብሔርን ባያምን እንኳን ለሚመራው ሕዝብ ባለው ቅንነት ይረዳዋል፡፡ አሁን እያየንው ያለው እውነት ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የአብይ አህመድን የትላንት መግለጫ በተግባር ምን እንደሚመስል እናያለን፡፡ ዛሬም ቢሆን ነገሮች ጸጽተውት ከልቡ ከሆነ እድል አለው፡፡ ዛሬም ለኮንቪንስና ኮነፊውዝ ቁማር ከሆነ ግን እየመጣበት ያለውን እንዳያስተውል ስለሆነ እየሆነ ያለው ይሆናል፡፡ በመናፈሻ ያጣውን የፎቶ ሾውና ደራማ ቁማር አሁን በአዲስ መልክ ለመጀመር ከሆነም እናያለን፡፡ አስመሳዮችና መሠሪዎች ጨርሰው እስኪጠፉ ድረስ እየሆነ ያለው ይቀጥላል፡፡ ሁሉንም በፍጥነት እናየዋለን፡፡
ቁማርተኞቹና ሟርተኞቹ የራሳቸውን ሕልውና በአገር እየመሰሉ የሕልውና አደጋ መጥቶብናል ብለው ከጅምሩ በሕዝብ ላይ የስነልቦና ሽብር የፈጠሩ እለት አንድም አካል እንዴት እንዲህ ይባላል ሊል የደፈረ የለም፡፡ ወያኔ ለኢትዮጵያ የሕልውና አደጋ የሆነችው አገር ወያኔ ባሳደገቻቸው በወያኔ ማደጎዎች መመራቷ እንጂ ከትግራይ የመጣችው ወያኔ አልነበረችም፡፡ የሕልውና አደጋ እያለ ለወያኔ መንገድ እየለቀቀና እየጠረገ ሸዋ ሮቢት ድረስ አምጥቶ እውንም የሕልውና አደጋ አስመሰለው፡፡ ሲጀምር እንዲህ ያለ የወራዳነት ቃል መጠቀም ወያኔን ለማጀገንና የወያኔን አይበገሬነት በሕዝብ ጆሮ በማሰራጨት ተሸናፊ ማድረግ እንጂ እውን በየትኛው መለኪያ ነው ወያኔ የኢትዮጵያ የሕልውና አደጋ መሆን የምትችለው ነበር፡፡ ገና እኮ ከትግራይ ሳትወጣ ነበር የሕልውና አደጋ እያሉ እነአገኘሁ ተሻገር ሲያሸብሩ የነበሩት፡፡ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተባለው ሌላው የአብይ አህመድ የብልጽግና ልሳን ሕዝቡን ቆራጥ በሆነ አስተሳሰብ ከማነጽ ይልቅ በሚገርም ሁኔታ ሲያፌዝብን ከርሟል፡፡ ቀኑን ሙሉ ስለወያኔ ጭካኔ አስፈሪነትና ተራ ሌብነት ነው ሲደሰኩር የሚውለው፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ አረመኔ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ሕዝቡን ስነልቦናውን ለመግደል ሆን ተብለው በተቀረጹ ፕሮግራሞች ስለደረሰው ውድማትና የወያኔን ሌብነት ሊጥና ማንኪየ አይቀራቸውም እያለ ሲደሰኩር ይውላል፡፡ ወያኔ ያደረገቸው ግን ተራ ሌብነት አደለም፡፡ ፋብሪካ ነቅላ ከኮምቦልቻ መቀሌ ስትገባ ምንም አልተደረገም፡፡ ሰሞኑን ድግሞ የአማራ ኢኮኖሚን መልሶ ለማቋቋም 30 ዓመት ይፈጃ
የሚለው ሌላ የስነልቦና መግደያው ፕሮፓጋንዳ ተጀምሯል፡፡ ጦርነቱ ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የኮመቦልቻ ፋብሪካዎች ሲወድሙ የአማራ ንብረት ወደመ እያለ ጮቤ የሚረግጥ ብዙ ነው፡፡ ወድመቱ ለአማራ ብቻም ከሆነ ይውደም፡፡ አሁን የምናወራው አልነበረም፡፡ አሁንም እየወደመ ነው እኮ፡፡
ቅንነቱ፣ ቆራጥነቱና ለሕዝብና አገር መቆሙማ ቢኖር ከጅምሩ ወያኔ አመድ ዶቄት ከተባለች በኋላ አትነሳም፣ ብትነሳም ከትግራይ ወጥታ ይሄን ሁሉ ውድመት አታደርስም፡፡ እስካሁንም ከመቀሌ እስከ ሸዋሮቢት መሥመር ተለቆላት እየዘረፈችና እያወደመች ነው፡፡ ብዙ ሕዝባዊ ሠራዊት ወያኔን ለመደምሰስ ቢሰለፍም በእዝ ሰንሰለት ተጠርንፎ ይሄው ምንም እነዳይሰራ ሽባ ተደርጎ እናያለን፡፡ አሊያማ ወያኔን አንድ ቦታ አደልም ከአላማጣ ጅምሮ አስር ቦታ በመቆራረጥ እንደተባለውም በገባችበት መቅበር አይቻልም ነበር? እስኪ ይሄን ጥያቄ መልሱልኝ፡፡ በስልታዊ ማፈግፈግ ዛሬ ሰሜን ሸዋ ድረስ ስቦና እስከመቀሌ ለወያኔ መመላላሻ ሆን ተብሎ መንገድ ሰጥቶ እያየን አሁንም ስልታዊ ሲል ልክ ነው የምንል እኮ አለን፡፡
ለማንኛውም ዛሬ በወያኔ ሰንደቅ ዓላማ፣ በወያኔ ሕገ–መንግስት፣ በወያኔ አሰራርና አስተሳሰብ እየመራ ያለው አብይ አህመድ እንጂ መለስ ዜናዊ እንዳልሆነ ሁሉም ግልጽ ሊሆንለት ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን በዘር መሸንሸኑም ቀጥሏል፡፡ በሶስት ዓመት ውስጥ ሁለት ተጨማሪ የዘር ክልል ተፈጥረዋል፣ ወላይታ ሶስተኛ ሊፈጠር ነው፡፡ ይሄው 11ኛው ክልል በዚህ አገር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅትና አስቸኳ ጊዜ በሚል በሚቆመረበት ጊዜ በዋና ከተማ አለመስማማት ገና ከጅምሩ እየተናጩ ነው፡፡ ወደፊት ደግሞ ክልል ሆነው ከአጎራባች ክልል ጋር ይፋዊ ጦርነት ይጅምራ፡፡ ወላይታም መንግስት ሲሆነ ከጋሞ ጋር ጦርነት ይገባል፡፡ ይሄ ቀበሌ የኔነው ያንተ አይደለም በሚል ገና ብዙ ጦርነቶች እናያለን፡፡ አብይ አህመድ በተግባር እየሰራ ያለው ይሄን ነው፡፡ ሲዳማ ለጊዜው ወያኔ ኦሮሞን እንደተጠቀመችበት እይነት ስልት ነው ኦነግ ብልጽግና ሲዳማን ክልል ያደረገው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሆይ አስተውሉ፡፡ እየሆነ ያለው ሁሉ መሆን ስላለበት ነው፡፡ እኛ እስከሚገባን መቀጠል ስላለበት፡፡ በፍጥነት ቢገባን ግን መከራዎች ያጥራሉ፡፡በወያኔ ሕገመንግስት፣ በወያኔ ሴራና ስልት በወያኔ ሰንደቅ ዓላማ እየቀጠሉ አይናችን እያየ ራሳችንን አናታል፡፡ የወያኔ የሆነ ምልክት ሁሉ ከኢትዮጵያ መነቀል ለኢትዮጵያም ሆነ አካባቢው ሠላም ወሳኝ ነው፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ፣ ይጠብቅ!
አሜን