ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
“ብዬ ነበር” እምብዛም አይጠቅምም እንጂ ስለሀገራችን ስንጮህ የነበርን ሰዎች ብዙ ነገር ብለናል፤ ካልነውም ውስጥ በተግባር የታዬው ብዙ ነው፡፡ ሆኖም ዘመኑ የስካርና የዕብደት ከመሆኑ የተነሣ መደማመጥ ጠፋና ሀገራችን የለዬላት የጨረባ ተዝካር እንደሚባለው ሆና ቀረች – ለጊዜው፡፡ በዘመነ ወያኔ ምን ብለን እንደነበር አንዷን ብቻ ላስታውስ – “ትግሬ ትግሬነቱን የሚጠላበትና ለፈጣሪው ‹ምን በድየህ ነው ትግሬ አድርገህ የፈጠርከኝ?› ብሎ የሚጸጸትበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ወያኔዎች እባካችሁን ጥጋባችሁን ልጓም አብጁለት….” ይህን ያሉ ጸሐፍት እኔን ጨምሮ በርካታ ናቸው፡፡ ያሉትም አልቀረም – ትግሬ በአሁኑ ወቅት የተመቸው ስላለመሆኑ ብዙ መናገር ይቻላል፤ አይጠቀመንም እንጂ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የሚነገር ሌላ ነገር ደግሞ ልጠቁምና ወደሌላ ጉዳይ ልለፍ፡፡ “ኦሮሞዎች እባካችሁን ልጆቻችሁን ገስጹ፡፡ ጥጋባቸውን እንዲቆጣጠሩ ምከሩ፡፡ ካልሆነ ‹አምላኬ ሆይ! ዋቀ ፈና ኢሬቻ! ምን አጥፍቼ ይሆን ኦሮሞ አድርገህ የፈጠርከኝ› የምትሉበት ዘመን በየደጃፋችሁ ቆሟል፡፡ እንዲያውም የእናንተን የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ስታዩ በትግሬዎች የደረሰውን ታመሰግናላችሁ፤ ምክንያቱም የእናንተዎቹ ጥጋብ ሰማየ ሰማያትን አልፎ የጽርሃ አርያምን ግቢ በዕንባና በደም አጨቅይቶታልና….፡፡” እውነት ነው፡፡ እውነትን የሚረዱ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ በጥጋብ የዘራኸው ምን ጊዜም አብቦና ጎምርቶ አፍርቶ ጎተራህን ሊሞላ ከች ይልልሃል፡፡ አዲስ ነገር አልተናገርኩም፡፡ ሁሉም በየደጁ የሚያየውንና የሚያገኘውንም ነው በግልጽ የምነግርህ፡፡ ዕድሜየ በመጫኛ አይገኝም፡፡ የብዙ ጥጋበኛ መጨረሻ አይቻለሁ፡፡ አምላኬ ስንቱን ፀረ-ኢትየጵያ በጥድፊያም በዝግታም እያፈራረሰና እያፈነዳ ሲወስድ አይቻለሁ፡፡ ምን አለፋህ – ሁሉም ዜሮ ዜሮ ነው፡፡ አንቺም ዜሮ ዜሮ፤ እኔም ዜሮ ዜሮ፡፡ ለዚህች ዕድሜ ነው እንግዲህ እንዲህ የምንጨካከነው፤ ከባዕዳን እንኳን በከፋ ሁኔታ በመስቀል ዕለት በሚሰግዱ ምዕመናን ላይ ድሮን ልከን ንጹሓንን የምንጨፈጭፈው ለዚች አጭር ዕድሜ ነው፡፡ ጽዮናውያን በፍልስጥኤሞች ይህን አያደርጉም!!
የአማራ ፋኖ አሁን ባለበት ሁኔታ በትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዘ አይደለም፡፡ ወሬንና ተግባርን ለይቶ ለመገንዘብ ሁለት ዓመታት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የኮንጎ አማፅያን በ11 ወራት ብቻ ከአንዱ የሀገሪቷ ጫፍ ተምዘግዝገው ኮንጎ-ኪንሻ የገቡት ቄጤማና ዘምባባ የሚጎዘጉዝ ተቀባይ ኖሯቸው ሣይሆን ልክ እንደነሱው ጥይት የሚያዘንብ መንግሥት ጋር ተጋፍጠው ነበር – ካቢላን አስታውስ፡፡ “የማያድግ ልጅ በአባቱ ምንትስ ይጫወታል” እንዲሉ ሆኖብን የኞች የምንላቸው ፋኖዎች ግን በሣምንታት ጊዜ ውስጥ ምራቅ የሚያስውጥ የተስፋ ዳቦ ሊያስገምጡን ሞከሩና ዐይን ገብቷቸው ወገቡን እንደተመታ እባብ እዛው ባሉበት ይጥመለመሉ ገቡ፡፡ መቋጫ በሌላቸው የተስፋ ቃላት የታጀበው የፋኖ ድል ለጥቂት ሶሻል ሚዲያዎች መሸቀያ ከመሆን አልፎ ሊታይ የሚችል ነገር እስካሁን የለም፡፡ እንዲያውም ከአንዳንድ ሁኔታዎች እንደምንረዳው “ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች” እንዲሉ ሆኖ ገበሬውና ንጹሑ ዜጋ በፋኖዎች በራሳቸውና በነሱም ሰበብ በአቢይ የዐውሬዎች መንጋ እየተበላ ፍዳውን ማየት ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡ እውነትን ብቻ ነው የምናገረው፡፡ አንድ ሰው ባሰበው ሳይሄድ ሲቀር ደግሞ ራሱም ተስፋ መቁረጡና ከፅድቅ ሥራዎች ይልቅ ዕኩይ ተግባራትን መለማመዱ ያለና የነበረ ነውና አሁን አሁን የምንሰማቸው ፋኖዎች ይፈፅሟቸዋል የሚባሉ በሰላይነት ስም የሚከናወኑ ግድያዎችና በዜጎች ላይ የሚደርሱ እንግልቶች “መቼ መጣሽ ሙሽራ፤ መቼ ቆረጠምሽ ሽምብራ”ን እንድንተርት እያደረጉን ነው፡፡ አዎ፣ ተስፋ መቁረጥና በትምህርት አለመግፋት ከሚያመጡብን ጠንቆች እንዲጠብቀን ፈጣሪን መለመን ትልቅ ጸሎት ነው፡፡ ሆደ ሰፊነት ከምግብ ጎተራነት ባለፈ ሊጠቅመን ካልቻለ የዞረ ድምር ውጤቱ ከባድ አደጋ ያስከትላል፡፡ በነፃነት ትግል ትግስት ወሳኝ ነው፡፡ አንዲት ጥይት ከተተኮሰች በኋላ ተመለሽ ቢሏት “ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ…” እያለች አንጀቷ እያረረ ትስቅብሃለች እንጂ አትመለስም፡፡
አንድ ነገር ሲጀመርና ሲካሄድ ብሎም ሲጠናቀቅ አንድ እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡ ነገር ግን መመካከርም ከሌሎች ተሞክሮ ትምህርት መውሰድም አንድን የነፃነት ትግል ጅማሮ ዳር ለማድረስ ያግዛል፤ መሣሪያ ደግሞ የኛ አሽከር እንጂ እኛ የነፍስ አልባውና የሕይወት የለሹ መሣሪያ ባርያዎች ልንሆን አይገባም፡፡ ሲጀመር ሰው ሲናደድ ከመሣሪያ መራቅ አለበት፡፡ ቃላት ለምን ተፈጠሩ? መማር ለምን አስፈለገ(ን)? አንዲት አረቂ ሻጭ ሴት አረቄ ሽጣ የነፍሷንና የሥጋዋን ኅብረት ከሰኞ ወደማክሰኞ በማሣደሯ ዋስ የምትጠራበትና የምትቀጣበት ሁኔታ – ለምሣሌ – በፍጹም ሊገባኝ አይችልም፡፡ ወጣት እንዳይጠጣ፣ ወጣት እንዳይቅም፣ ዜጎች የነፃነት ትግሉን እንዲቀላቀሉ በብልኃት ማስተማርና መምከር ያባት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በአእምሮና በአስተሳሰብ በልጦ መገኘትን እንጂ በአፈ-ሙዝ ማንበርከክን አይጠይቅም፡፡ ትግላችን ደግሞ ዓለማዊ እንጂ መንፈሣዊ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ መንፈሣዊስ ቢሆን ግደሉ ይላል እንዴ መጽሐፉ? ይህን መሰል አክራሪነት ፋኖዎቻችን ከየት አመጡት? ይህን መሰል ኢ-ሰብኣዊና ኢ-ሞራላዊ ድርጊት ከፋኖ መጠበቅ አልችልም – እንደተባለው ሆኖ ከሆነ፡፡ ወይም ፋኖ እኔ ባላወቅሁት መንገድ ተበርዞ ተከልሷል ማለት ነው፡፡ እኔ ዕንቅልፍ እያጣሁ ስለፋኖ ሃቀኝነትና ሃይማኖታዊነት የምጽፈው ዜጎችን የሚያንገላታና ከፍ ዝቅ አድርጎ የሚያዋርድ አርበኛ እንዲመጣልኝ ሳይሆን የሚያከብረኝንና ከታወጀብኝ የዘር ፍጂት የሚያተርፈኝን ነው፡፡ ለዚህ ለዚህማ አቢይ አህመድ ምን ሠርቶ ይብላ? የአጋንንቱ ዓለም ልዑካን እነዳንኤል ክብረትና አዳነች አበቤ፣ ምርኮኛ አሥር አለቃ ብርሃኑ ጁላና ሽመልስ አብዲሣ ምን ሠርተው ይብሉ? ኣሃ! የሰውን የሥራ ድርሻ መቀማትማ ነውር ነው፡፡
አለቃ ገ/ሃና ሚስታቸው የሠራችው ሽሮ ይሁን ጎመን ሰለቻቸው አሉ፡፡ ያኔ እጓደኛቸው ቤት ይሄዱና ማዕዱ ቢቀርብ እቤት ሰልችቷቸው ትተውት የመጡት ሽሮ ይሁን ጎመን ሆኖ ያገኙታል፡፡ ያኔ ምን አሉ መሰለህ – “በየት ዞረህ ቀደምከኝ”፡፡ ብዙ ነገር እየዞረ የሚገጥምብን ሊያውም እየከፋ እኛ ብቻ ነን፡፡
ይሄ የዞሮ ግጥም ታሪካችን አንዳችንን በአንዳችን እያጠፋፋ ምዕተ ዓመታትን መዝለቁ እጅግ ከሚገርሙኝ አሳዛኝ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ አንድ ቦታ ልናቆመው ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የጥይት ትጥቅ ሳይሆን የአእምሮ ስንቅን ማብዛት ነው፡፡ መነጋገር፤ መደማመጥና መግባባት፡፡ ወደዱላ በፍጹም ማምራት የለብንም፡፡ የእሥራኤልን ፓርላማ ታዘቡ፤ የእንግሊዝን ፓርላማ እዩ፤ የአሜሪካንን ፓርላማ ተመልከቱ፡፡ አሁን ብናገረው “ባለጌ” ትሉኛላችሁ እንጂ ስንትና ስንት የብልግና ቃላትን እየተወራወሩ ወደቦክስና ወደሽጉጥ መግባትን ግን በጭራሽ አያስቡትም፡፡ ሰዎች ናቸዋ! የሰውነት ደረጃ ላይ ደርሰዋላ! እኛ ግን ገና ዐውሬ ደረጃ ላይ ነን – በእውነት፡፡ ቀድሞ የሚመጣልን ጥይት ነው፤ ድሮን ነው፤ ባዙቃና ብሬን ነው፡፡ ያኔ ነው ዛራችን የሚሰክነው፤ አውሊያችን አደብ የሚገዛው፤ ሃጃችን የሚሞላውና በሰው ደም ሰክረን በሰው ሥጋ ጠግበን በዊስኪ የምንራጨው፡፡ መረገም ነው፡፡ እንደሰው ተፈጥሮ እንዐውሬ መኖር በርግጥም ትልቅ በደል ነው – የዚህ ዓይነት ማኅበረሰብ አባል መሆን በራሱ በጸጸት ሊገድል ይችላል፡፡ እናልህ ውድ ፋኖዬ – ይህን ሁሉ የምለው ባንተ ቦታ ሆኖ መታገል ያለውን ጣጣ አጥቼው ደግሞ እንዳይመስልህ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ንጋት ጨለማ አለውና ገብተሃል፣ ገብተሃል የነፃነት ትግሉን በድል መዘምዘም ብቻ ነው ካንተ የሚጠበቀውና ያለህም ብቸኛ አማራጭ፡፡ ማቄን ጨርቄን የለም፡፡ “ገጥመሃል፣ ገጥመሃል” ትል የለም እንዴ አንተ ራስህ? በጀመርከው ጨርስ፡፡ ተስፋህን በእግዚአብሔር ጣል፡፡ እውነትን ብቻ ያዝ፡፡
ብሶቴን ከተነፈስኩ ወደ ዋና ጉዳየ ልግባ፡፡ አንድ የልብ ወዳጄ ጋር ቅድም ስናወራ ነበር፡፡ አማራ ወደዘመነ መሣፍንት ዘመን መግባቱ ላይ ተስማማን፡፡ ወደመፍትሔው ስናመራ አንድ ቆንጆ ሃሳብ አመጣ፡፡ ሳልረሳው በሚል ወደኮምፒውተሬ ገሰገስኩ፡፡ እሱን ነው የምነግራችሁ፡፡
አራቱም ጠቅላይ ግዛት አንድ ሆኖ መታገል እንዳይችል የተለያዩ ተግዳሮቶች መግጠማቸው እሙን ነው፡፡ እንግዲህ ያ እውን መሆን ካልቻለ በየጠቅላይ ግዛቱ ያለው ፋኖ ራሱን አጥርቶና ከሠርጎ ገቦች አደጋ ራሱን ጠብቆ በየግዛቱ ያለውን የጠላት ጦር ማምሸክና ሁሉም አካባቢውን ሲያጸዳ ለመጨረሻው ሀገራዊ ዘመቻ ከሌሎች ተመሳሳይ ኢትዮጵያዊ ኃይሎች ጋር ስምምነትና ቅንጅት በመፍጠር ይሄን የኦሮሙማ ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ እንዲሁም ፀረ-ሰው የማይማን መንጋ በጋራ ተፋልሞ ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን መፍጠር፡፡ ይህ ደግሞ አማራጭ የሌለው የወቅቱ ጥሪ ነው፡፡ ይሄ ሥልጣን የሚሉት ደንቃራ መቼም እያመሰን መሆኑ አይካድም፡፡ ገና በሳይከካ ተቦካ አሣራችንን እያበላው የሚገኘው የሥልጣን ሱስና አራራ በየታጋዩና አታጋዩ ጭንቅላት ውስጥ ተሰንቅሮ እነሱንም ትግሉንም መከራ እያበላ ነው፡፡ አንዳንዱ የሰው ልጅ ደካማ ጎን ሲታይ ሰው መሆንን እንድንጠላ ያደርጋል፡፡ ለምሣሌ አርባ ጉጉና ገለምሶ፣ ሻሸመኔና ባሌ፣ ወለጋና አርሲ፣ አዲስ አበባና አማራ ክልል … በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማሮች በአማራነታቸው ብቻ እየታፈኑ አንገታቸው ሲቀላ፣ ቤት ንብረታቸው ሲቃጠልና ሲዘረፍ፣ ማሕፀን እየተቀደደ “አማራ እዚህ አይወለድም” በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ ሽል ሲታረድ፣ አማራነት ወንጀል ሆኖ ሊነገር የሚሰቀጥጥ ኢሞራላዊ ምግባር ሲፈጸምበት … ይህን ሁሉ ዘር ተኮር ውድመት ለማየት ባለመቻል ለሥልጣንና ለዝና ወይም ለወሲብና ለገንዘብ ብሎ ከጠላት ጋር ማበር ወይም በትግል ሜዳ ላይ ከሚገኙ ባንዳዎች ጋር መሞዳሞድ ታሪክም ትውልድም ፈጣሪም ይቅር የማይሉት የወንጀሎችና ኃጢኣቶች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ነገ ያልፋል፡፡ ያኔ የአገኘሁ ተሻገር ልጅ ወይ የልጅ ልጅ ነኝ ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ያኔ የማንትስ ነጋ ልጅ ወይ የልጅ ልጅ ነኝ ብሎ መናገር ምንኛ ያሣፍር? አእምሯችንን ማን ወይ ምን ቀማን? ከሦስት ቦታም ይወለዱ ከሠላሣ እሱ አያገባኝም ግን ያኔ የሙሓዘ-ከርስ ዳንኤል ክብረት ልጅ ወይ የልጅ ልጅ ነኝ ማለት እንዴቱን ያህል በሀፍረት ያሸማቅቅ፡፡ የኔ ልጆች አስቀኑኝ!! እንዴ፣ ድህነት ወርቅ አይደለም እንዴ? የድኅነት መሠረት ድህነት ሳይሆን ይቀር ብላችሁ? (ለጠቅላላ ዕውቀት ያህል – ድህነት – poverty – ድኅነት – spiritual salvation or Social wellbeing፡፡ ከዚህ በተገናኘ መድኃኔ ዓለም እና መድሓኒት ቀዳሚው በነፍስና ተከታዩ በሥጋ የሚገለጽ ዐውዳዊ የፍቺ ልዩነት እንዳላቸውም ልብ ይባል፡፡ የጨጓራ መድሓኒት ከፋርማሲ ገዛሁ፤ ጸሎት የነፍስ መድኃኒት ነው… ፡፡ አይ አማርኛ! ይቺን እኮ ነው እነ-ለአህያ ማር አይጥምሽ ያጠፉብን፡፡ግዴለም፤ እሷም ትንሣኤዋ ደርሷል፡፡ እንደጠፋች አትቀርም፡፡)
እንግዲህ የሰማህ ሰምተሃል፡፡ ከፈለግህ ትንቢት ልንገርህ ደግሞ፡፡ ትንቢቴ አንድም ዝንፍ ብሎ አያውቅም፡፡ አሁን ፋኖም ሆነ ሌላ ኃይል ተስፋ እንዳይኖረን ሊያደርግ ይችላል – እንደምድራዊ አስተሳሰብ፡፡ የአቢይ ድሮንና ጥይት ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችል ይሆናል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ተስፋ ሊያስቆርጠንና አንዳንዶቻችንንም ገመድ ይዘን ወደሚቀርበን ዛፍ እንድንሮጥ ሊገፋፋን ይችላል፡፡ ነገር ግን … አማራ የአቢይን ጥይት በማስጨረስ ጭምርም ቢሆን በቅርቡ ያሸንፋል – ተብሎ ተብሎ ያለቀ ጉዳይ ነው እንደምሥጢር ሹክ የምልህ – ኦሮሞን ያመጣብህ ከትግሬም የሚበልጥ ጨካኝ መኖሩን ሊያሳይህ ሽቶ እንጂ – በዚያም ላይ ትንሽ የምናወራርዳት የታሪክ ውዝፍ ዕዳ ኖራብን ይሆናል እንጂ እነዚህን ጭራቆች ፈጣሪ መቅጣት አቅቶት እንዳይመስልህ፡፡ ለዚያ ለሚጠበቅ የመጨረሻ ድል የሚያበቁን ሙሽሮች የት እንዳሉ ባላውቅም አንድ ቦታ ግን አሉ፡፡ አቢይና ቡድኑ ይህን ያውቃሉ፤ ለዚህም ነው በድንጋጤ ተውጠው ይሠሩትን በማጣት እየተራወጡ የሚገኙት፤ ደግሞም ገና ብዙ ጥፋት ያደርሳሉ – መች ተነካና፡፡ ዓለም አቀፉ ኃይል ኦርቶዶክስንና አማራን አጥፍቻለሁ ብሎ ልቡ ውልቅ ብሏል – አሁን፡፡ ግን አልጠፉም፤ አይጠፉምም፡፡ ቤተ ክህነቱንና ቤተ መንግሥቱን ሊቀ ሣጥናኤል ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ቢቆጣጠርም የዚህ ሁሉ አጋንንታዊ ደንቃራና ትብታብ መፍረሻው ጊዜ ደርሷል – የአሁኒቷ ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ በብዔል ዘቡል አገዛዝ ሥር እንዳለች ማመን አለብህ – ኢዩ ጩፋ የሚያማክረው ወፈፌ መሪ፣ እሥራኤል ዳንሣ የሚባርካት ቀዳሚ እመቤት፣ እህተ ማርያም የተባለች ዕብድ የምትቀድስበት ቤተ አምልኮ፣ አሥሩ ሴት ላይ የሚደቅል ጳጳስ … በሞሉባት ሀገር ኦርቶዶክስንና ኢትዮጵያን የማያጠፋ ኃይል ባይነሳና ባይገን ነበር የሚደንቀው፡፡ ቀደምት አባቶች ንግርታቸው መሬት ጠብ አይልም፡፡ ባለሰባት ዓመቱ ዕብድ ጭንጋፍም ጊዜው አልቋል፡፡ የጭማሪው ሰዓት 30 ደቂቃም አልፎ የሚቀረው የሪጎሪ መለያ ምቱ ብቻ ነው፡፡ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው፡፡ ፋኖ የዚህ ተዓምራዊ ሽግግር ተሣታፊ መሆን ከፈለግህ ራስህን በአፋጣኝ አጥራ፡፡ አራት ኪሎን እየተመኘህ መሣቂያ አትሁን፤ አራ ኪሎን እርሳው እንዲያውም፡፡ የት ይሄድብሃል? ቅዠትህን ወደህልም፣ ህልምህን ወደ እውን በአስቸኳይ ካልለወጥህ እዚያው ስትርመጠመጥ ትኖራለህ ወይም በሌላ ኃይል ትቀደምና እንደእናት ልጅ የምትሳሳላትን አራት ኪሎ ልታጣት ትችላለህ – መዳኘየ እሷ ናት ብለህ ችክ ካልክ ለማለት ነው እንዲህ የምዘባበትብህ፡፡ በበኩሌ ሕዝብ ከመረጠህ አራት ኪሎ ቀርቶ አሥር ኪሎም ግባ፡፡ ግን ወጡ ሳይወጠወጥ ትዝብት ውስጥ አትግባ፡፡ ይህን የምለው ምልባት የእግዚአብሔር ምርጫ – ሌላ ምርጫ ካጣ – እዚያ አካባቢ ከሆነ በሚል ነው፡፡ ጥሩ ጥሩ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ጥሩ የምላችሁ ፋኖዎች እባካችሁን በትርፍ ጊዜያችሁ ንባብን አዘውትሩ፤ ሌሎቻችሁም አንብቡ፡፡ ንባብ ሰውን ሰው ያደርጋልና ከንባብ አትራቁ፡፡ ግን በሌላ በኩል ደግሞ ይሄ ምድረ አሸንክታባም እያለ “እናቴ ነግራኛለች፣ አክስቴ ተንብያልኛለች” በሚል ሁሉም ትናንሽ የዘውድ አክሊል በየኪሱ ይዞ መዞሩ ነው አንደኛው ራስ ምታታችን፡፡ በዚህ አጋጣሚ የታጋዮችን ሆድ በባዶ የሹመት ተስፋ የምትቀበትቱ እባካችሁን እረፉ በሉልኝ፡፡ ወይ አክስት ማጣት! እናቴም በሕጻንነቴ አረፈችና ማን ይተንብይልኝ?
የአማራዊነት አሸናፊነት በቅርቡ ይረጋገጣል! አማራዊነት ሰው የመሆን ኢትዮጵያዊ ምልክቱ ነው! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ፡፡ ለሌሎቻችንም ልብ ይስጠን፡፡ ተዘጋጅተንም እንጠብቅ፡፡ በምለው የምትስቅ ሁላ ጥርስህን ተነቅሰህ ሣቅ፡፡ መብትህ ነው፡፡ እኔ ግን ያልኩትን ብያለሁ፡፡