በእውነቱ ኢትዮጵያ መንግሥት አላትን? አማራውስ አሁን ምን ማድረግ አለበት?

59390184 401

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በዚህች መጣጥፍ ሁለት ነገሮችን አጠር አድርጌ ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡

1. በቅድሚያ ስለመንግሥት ኅልውና?

በአንድ ሀገር ውስጥ መንግሥት መኖሩንና አለመኖሩን ወይም አለ የሚባለው መንግሥትም ቢሆን ለሕዝብና ለአገር የሚሠራ ወይ የማይሠራና እንዲያውም በተቃራኒው ሕዝብ-ፈጅ መሆን አለመሆኑን ለመረዳት በግድ የዘርፉ ምሁርና ተፈላሳፊ መሆንን የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡ በበኩሌ ከትምህርት ቤት ይልቅ ሕይወት ያስተማረችኝ እጅጉን ስለሚበልጥ በተለይ አቢይ ወደ ሥልጣን ከወጣበት ከመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም በአጠቃላይ ደግሞ ከ1983ዓ.ም ወዲህ ኢትዮጵያ ሀገራችን መንግሥት እንደሌላት በሚገባ እረዳለሁ፡፡ መንግሥት አለ ብሎ ለሚያምን የዋህ ወይም ለባለጊዜዎች የተገዛ የጥቅም ምርኮኛ ደግሞ አዝንለታለሁ፤ ያ ዓይነቱ ሰው አለመኛ ነው፡፡ ችግርን የማያውቅና በድሎት የሚኖርም መሆን አለበት፡፡ ከዚህ አኳያ ብዙ የማውቃቸው ሰዎች በነገዳቸው አማራ ነን እያሉ ሳይቀር በአቢይ አህመድ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ተማርከው በዚህ ትብታባም ሰውዬ ፍቅር ሲያብዱ ሳይ ይገርመኛል፤ ፍቅር በርግጥም ዕውር መሆኑን የምገነዘበውም በነዚህ ዓይነቶቹ ቂሎችና ምናልባትም ጥቅመኞች አማካይነት ነው፡፡ ይህ አቢይ እዚህና እዚያ፣ ትናንትና ዛሬ በየሄደበትና በየደረሰበት ከሚያሰማው ቱሪናፋና እርስ በርሱ የሚጋጭ ውል-የለሽ ንግግር ስለሰውዬው ጠባይ መረዳት የምንችለው አቢይ ማለት ምንም ዓይነት የፖለቲካም በሉት የሃይማኖት ብስለት የሌለውና የዜጎችን የማገናዘብና የማስታወስ ችሎታም የሚንቅ መሆኑን ነው፡፡ ሲዋሽ ደግሞ ለነገየ አይልም፡፡ የሚናገረውና የሚያደርገው ተስማማ ተቃረነ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ይህ ሰው ዘረመሉ መጠናት አለበት፡፡ የተለዬ ነው፡፡

በሀገራችን ያለው እውነት ቀጣዩን ይመስላል፡፡ ከመረጃ ቲቪ የዘመዴ “ነጭ ነጯን” የምትባል አነጋገር ልዋስና ነጭ ነጯን ላውጋችሁ፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት መንግሥት የላትም፡፡ መንግሥት አለ የሚባለው ለሁሉም ዜጎች በእኩል የሚጨነቅ፣ በዘር በሃይማኖት ዜጎቹን የማይከፋፍል፣ ዘረኝነትን የሚጠየፍ፣ በአካልና በመንፈስ እንዲሁም በአእምሮና በኅሊና በሳል በሆኑና ከተራው ዜጋ በተሻሉ ምርጥ ሰዎች የሚመራ፣ ከራስ ወዳድነትና ከሙስና የጸዱ አመራሮች የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎችን የሚይዙበት ግልጽ አሠራርን በመርኅ ደረጃም በተግባርም የሚከተል፣ በአንድ ሰው ዘፈቀዳዊ አመራር የማይነዳ፣ ዴሞክራሲንና ፍትህን እንዲሁም እኩልነትንና ነጻነትን የሚያሰፍን፣ የሀገሪቱንና የዜጎቿን ኅልውና የሚያረጋግጥ፣ የሀገርን ዳር ድንበር የማያስደፍር ብቻ ሣይሆን ሌት ተቀን ነቅቶ የሚጠብቅ፣ የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወት የሚያስከብር፣ የዜጎችን የዕለት ከለት በሰላም ወጥቶ መግባት የሚያረጋግጥ፣ ወዘተ. መንግሥት ሲኖር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን ይህን ዓይነት መንግሥት ለማግኘት አልታደለችም፤ ምናልባትም ክፉኛ የረገማት ኃይል አለ፡፡ እናም እዚህ የተጠቀሱትን የመልካም መንግሥት መገለጫዎች በሚጣረስ መልኩ የሚሠራ የነውረኛ ግለሰቦች ስብስብ እንጂ መንግሥት የሚባል ተቋም ሀገራችን ፈጽሞ የላትም፡፡

“አንተ ትግሬ፣ አንተ ኦሮሞ” እያለ የጋራ በሆነች ሀገር ዜጎችን የሚነጣጥልና ለአንዱ እሳት ለሌላው ወተት የሚያቀርብ መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ እውነት ነው ወርቅ መንግሥት አለን፡፡ “አንተ አማራ፣ አንተ ትግሬ” እያለ በማን አባት ገደል ገባ የልጆች ጨዋታ ጎሣና ነገዶችን የሚያጨራርስና በውጤቱም የራሱን ኦሮሙማ መንግሥት ለመመሥረት የፖለቲካ ሤራ ጠንስሶ ለአንዱ ወገን መሣሪያና ስንቅ በሥውርና በግልጽ እያቀበለ እውነተኛ የነጻነት ተዋጊዎችን ግን በሸፍጥ እያስመታ በማያቋርጥ የአፈግፍጉ የበላይ ትዕዛዝ ነጻ መሬቶችን በጠላትነት ለተፈረጀና ሕዝብን ለሚጨርስ ኃይል እያሰረከበ አገር ምድርን በእቶን የሚያቃጥል መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ ልክ ነው በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ልዩ የሆነ መንግሥት አለን፡፡ የሀገሪቱን ሀብት ለአንደኛው ነገድ በአድልዖ በብዛት እየበጀተ ወይም እየመደበ ለሌሎች ግን ጠበንጃና የጠብ ቁርሾ እያደለ እርስ በርስ የሚያፋጅ፣ አንዱ ክልል በትራክተርና በስንዴ ማሣ ሲምበሸበሽ ሌሎች ክልሎች በሰው ሬሣና በተቃጠለ ሀብት ንብረት እንዲጥለቀለቁ የሚያደርግ መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ እንደኛ የታደለ ባለመንግሥት በዓለም ላይ የለም፡፡ ኢትዮጵያን ለምታክል ታላቅ ታሪካዊት ሀገር ይቅርና ለአንድ መንደር መሪነት እንኳን የማይበቃ እልም ያለ ውሸታምና የበሻሻ አራዳ ጠ/ሚኒስትር በሚመራው የወንበዴዎች ቡድን ሕዝቡን የማያውቁና በሕዝብ ሊመረጡ ቀርቶ አንካሳ ይሁኑ አንጋሳ ስማቸውን እንኳን የማያውቃቸውን ሀገርና ሕዝብ ተሳዳቢ ሰዎች እንደሸቀጥ ከውጭ እያስመጣ ፓርላማ የሚጎልት መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ አሁንም እንደኛ ዕድለኛ የለም፡፡ ተሳዳቢዎችና ተረኛ ዘረኞች የፈለጉትን እያደረጉ (እየገደሉ፣ እየዘረፉ፣ አገር ምድሩን እያቃጠሉ….) ለሀገር የሚያስቡ ደጋጎች ግን ወደዘብጥያ እንዲወርዱ የሚያደርግ መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ እንደኢትዮጵያ የሚያስቀና ሀገር የለም፡፡ ምርቃና ላይ እንደሚገኝ መለስ ዜናዊን የመሰለ ሰው ሞቅ ባለው ቁጥር የይስሙላውን ፓርላማ እንኳን ሳይሰበስብ ሀገርን የሚያዋርድና ክፉኛ የሚጎዳ ውሳኔ የሚወስን አምባገነን ሰውዬ እንደመንግሥት የሚቆጠር ከሆነ ኢትዮጵያ በርግጥም በእጅጉ ታድላለች፡፡ “ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ” እንዲሉ የመንግሥት ልጓም ስለተጨበጠ ብቻ መቆጣጠር የማይችለውን የታኅታይና ላዕላይ መዋቅሮችን በስፋት ዘርግቶ የሀገርን አንጡራ ሀብትና ገንዘብ በሙሰኛ ቢሮክራሲ ማዘረፍ፣ በውጤቱም ልማትንና ዕድገትን ማቀጨጭ ወይም በእንደነገሩ የውሽልሽል ፕሮጀክቶች ንዋይን ለግል ጥቅም ማጋበስ በመንግሥትነት ማዕረግ ካስቀመጠ እንደኢትዮጵያ ያለ ውስጡን ለቄስ የሆነ መንግሥት በየትም የለም፡፡ በጣም ታድለናል አይደል?…

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች "እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል አደረሳችሁ!" ጌታቸው ወልዩ (ከሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

በብር አንድ መቶና ሁለት መቶ የሚገዛውን ዕቃ በሚሠራው አሻጥር ምክንያት ዕጥረት እንዲፈጠር እያደረገ በብር አምስትና አሥር ሽህ እንዲሸጥ የሚያደርግ አጭበርባሪና ኅሊና-ቢስ ነጋዴ ቢዝነሱን እንዲቆጣጠርና የመንግሥት ባለሥልጣናቱም የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ የሚሠራ መንግሥት፣ መንግሥት ከተባለ እውነት ነው ቆንጆ መንግሥት አለን፡፡ የፍትኅን ዐይን የሚደነቁልና ሕዝብ በፍትኅ ዕጦት እዬዬ እንዲል የሚያደርግ፣ በስልክ በሚሰጥ ማስጠንቀቂያና በብጫቂ ወረቀት ማስታወሻ የፍ/ቤት ውሳኔን የሚያዛባ ወይም የሚሽር፣ የፖሊስና የመከላከያ እንዲሁም የጸጥታ አካላት ሁሉ ወንበሩን ለመጠበቅ ሃያ አራት ሰዓት ዘብ እንዲቆሙለት የሚያስገድድ በዚያውም የሀገሪቱ አምራች ዜጎች ዘወትር ወንበር ጥበቃ ላይ በማሠማራት ምርት እንዲቀንስና በውጤቱም ርሀብ እንዲነግሥ የሚያደርግ፣ የሀገሪቱን ውሱን ሀብትና ዜጎች የሚከፍሉትን ግብር ለልማት ሳይሆን ለጦር መሣሪያ ግዢና ለሥልጣን ማስጠበቂያ የሚያውል፣ በዚያ አካባቢ የሚኖረውን ነገድ ዕረፍት ለማሳጣት በታቀደ የቀሽሞች ድራማ፣ ድንቁርናን መሠረት ያደረገ ድፍረት የተሞላበትን የፖለቲካ ሤራ እውን ለማድረግ ሲባል የሀገርን ድንበር ለጎረቤት መንግሥት በነፃ የሚያስረክብ፣ ሌላውን የጎረቤት መንግሥት ደግሞ “ወደ ድንበሬ ገብተህ ሀገሬን ውረርና ሀብትና ንብረትን ከቻልክ ዝረፍ ካልቻልክ አውድም” ብሎ የገዛ ሕዝቡን በጠላት ኃይል የሚያጠፋና ሀብት ንብረትን የሚያዘርፍ፣ እመራዋለሁ በሚለው የሀገር ግዛት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ሲፈናቀልና በርሀብ ሲሞት፣ ሲሰደድና በጥላቻ ባበዱ ወያኔዎች ሲገደል፣ ከብቶቹና ሰብሉ በጥይትና በእሳት ሲጋዩ፣ ከተሞች በኑሮ ውድነት የሰደድ እሳት ሲጠበሱ … አይቶ እንዳላዬ ሰምቶም እንዳልሰማ ራሱ በፈጠረው ምናባዊ የደስታ ዓለም የሚፈነጥዝ መሪ ያለን መሆናችን መንግሥት እንዳለን የሚያስቆጥር ከሆነ ከኖርዌይ ሕዝብ በበለጠ ተደስተን የምንኖር በመሆናችን ለዶክተር ኮሎኔል ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተለዬ ምሥጋናና ውዳሤ ማቅረብ አለብን፡፡ እርሱ ወደ ሥልጣን ባይመጣ ኖሮ ለዚህ ሁሉ ክብር አንበቃም ነበርና፡፡

ሌላው ሁሉ ይቅር – የብር 30 ኩንታል ማኛ ጤፍ ሰባት ሽህ ብርን ሲታከክ፣ የብር ዐርባ ሣንቲም አንድ ኪሎ ስኳር 60 ብርን ሲያልፍ፣ የአምስት ሳንቲም ፉርኖ ዳቦ በይዘታዊ ግመታ ከብር አሥር ሲበልጥ፣ የብር ሁለትና ሦስት አነስተኛው የቤት ኪራይ ባማካይ ብር ሦስት ሽህ ገደማ ሲሆን፣ የስሙኒ ዶሮ አንድ ሽህ ብር ሲገባ፣ በአንድ ብር መቶ ዕንቁላል እንዳልተገዛ ዛሬ የአንዱ ዕንቁላል ዋጋ ብር አሥርን ሊደፍን ሲታገል፣ የብር አምስት አዲስ አበባ ደሴ የተራ አውቶቡስ ትኬት ብር 200 ሲያልፍ፣ የስልሣ ሣንቲም አንድ ሊትር ቤንዚን በገጠር አካባቢ በተለይ ብር ሃምሣና ስልሳ ሲሆን፣ ብር 3000 አዲስ መኪና እንዳልገዛ ዛሬ የአንድ እግሩን ጎማ እንኳን መግዛት ሲያቅተው፣ የአምስት ብር የቮልሰ ዋገን ፑንቲና ባለመለዋወጫ ሱቁ ጌታ በኩራት ተጀንኖ “800 ብር” ሲልህ፣ የብር አምስትና አሥር የበግ/የፍየል ሙክት በአሥራዎቹ ሽዎች እየተሸጠና እየተገዛ፣ “ከዚህ ቁረጥልኝ!” የምትለው የሃምሣ ሣንቲም የበሬ ሥጋ አሁን በነአሹ ሉካንዳ ከሽህ ብር ሲያልፍ፣ የሦስት ብር ፍራቢ ጫማ መልኩን በማሻሻል በሽዎች እየተሸጠ፣ የአምስት ብር የእንጨት ከሰል ከብር 600 በላይ ሲሆን፣ የአሥራ አምስት ሣንቲም የከተማ አውቶቡስ ከአራት ብር ጀምሮ አሥር ብርን ጣጥሶ ሲሄድ፣ በአሥር ብር የሚታደስ መንጃ ፈቃድ ብር 620 ሲገባ፣ ምን አለፋህ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዘመን አንድ ብር አሁን በሚሊዮኖች ሲመነዘር “በእውነት መንግሥት አለ?” ብለህ ትደነግጣለህ – በብር 30 ተለምነህ የምትመራው 500ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አሁን በአንድ ካሬ እንደዬቦታው ደረጃ ከብር 100 ሽህ ጀምሮ ከአምስትና ስድስት መቶ ሽህ በላይ መሆኑን ድረስበትና የብሩን ምንዛሬ አስላው፤ በተረትም የማይታመን አምናና ዘንድሮ በኢትዮጵያችን ተከስቶ እየሆነ ያለውን ማመን ተቸግረናል፡፡ “ምነው አምና በሞትኩ እንዲያ እንዳማረብኝ፣ ሰው እንደበርበሬ ሳይለወጥብኝ…” የሚባልበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው፡፡ የሕዝብን ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ሆነ ብለው የሚያመሰቃቅሉት ይህችን አዲስ አበባ “ለኑሮ ተስማሚ እንዳትሆን እናደርጋለን” ብለው የዛቱትን በተግባር እያሳዩ እንደሆነ መረዳት አይከብድም፡፡ የሚገርሙ አቢዮችና ሽመልሶች!!… እውነቱ ይሄው ነው፡፡ የሲቪል ሰርቪስ የመንግሥት ደሞዝተኞች የወር ገቢ ወርን ከወር መግጠሙ ይቅርና ከልደታ እስከባታም የማይበቃቸው መሆኑ እየታወቀ … በዚህን የጨረባ ተዝካር ወቅት “ኢትዮጵያ መንግሥት አላት” የሚል ሰው ካለ የለዬለት ወፈፌና ዕብድ እንጂ ጤናማ ሰው ሊሆን አይችልም – ለዝርዝሩ ጊዜው ሲፈቅድ በአካል ተገናኝተን – ሊያውም ይህችን ጠባብ ዘመን ካለፍን – በግልጽ እናወራዋለን፡፡ ይህን ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት እየመራ የሚገኝ አካል ሀፍረትን የሚያስተናግድ የሰውነት ክፍል የለውም እንጂ በሀፍረት ተሸማቆ ወደሚቀርበው ዛፍ በመሄድ ራሱን በገመድ ያንቅ ነበር፡፡ ኦህዲዶች እጅግ የሚገርሙ ሰዎች ናቸው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለ ሚኒስትርና የፓርላማ አባል ተብዬዎች ሁሉ አሳፋሪ ናቸው፡፡ ለምን እዚያ እንደተጎለቱም የሚያውቁ አይመስሉም፡፡ አንጎል የሌለው አጋሰስ አገርን እንዲመራ የሆነ ኃይል ሲፈቅድ፣ ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለው ራስ ወዳድና ስግብግብ ሰው መሪ ሲሆን ምን ሀገራዊ ስዕል ሊታይ እንደሚችል እየታዘብን ነው፡፡ ለነገሩ አንድ ሕዝብ የሚገባውን መሪ ያገኛል ይባላልና ራሳችንን ብንፈትሽ ጥሩ ነው፡፡

  1. አማራው ምን ማድረግ አለበት?
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ የዕንቆቅልሽ ምድር - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አማራው ምን ማድረግ እንዳለበት መናገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ መቼና ምን እስከሚሆን ወይም ምን እስከሚደርስበት እንደሚጠብቅ መገመትም ሆነ ማወቅ ይቸግራል እንጂ አማራው ቆርጦ ሲነሳ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከግምት ባለፈ እናውቃለን፡፡ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ብዙ ስላልን ጠለቅ ብለን አንገባበትም፡፡ አሁን በአማራው አንገት ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ገመዶች የጠባበቁበት ይመስላል፡፡ እንደእስካሁኑ አንገቱን እያቀረቀረና በምን አገባኝ ስሜት ዳተኛ እንደሆነ መቀጠሉ እንደማያዋጣው ወያኔ ፈልጎት ሳይሆን ፈጣሪ ወዶና ፈቅዶ ይህን ዐረመኔ የባንዳ ውላጅ እቤቱ ድረስ ልኮለታል፡፡ ወያኔም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አሉ፡፡ እርግጥ ነው – የአማራ ጠላቶች ከጥንት ጀምሮ መናበብን በሚገባ ተክነውበታል፡፡ ይህ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ውጭ ምንም መመኪያና መኩሪያ የሌለው ሕዝብ አሁን ወደየትም ማምለጥ በማይችልበት ሁኔታ ጠላቶቹ በሁሉም አቅጣጫ ወጥረውታል፡፡ በበኩሌ እሰዬው እላለሁ፡፡ እንኳንም ወጠሩት፡፡ እሱም ገርነቱን አብዝቶት ነበር፡፡ አማራ የያዛቸው ካርዶች ሁሉ አንድ በአንድ ተቀዳደው ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ነው፡፡ “እከሌ ይምረኛል፤ እከሌ ያዝነልኛል፤ እከሌ ይዳኛል (“ረ” ትጥበቅ)፤ እነእገሌ ይረዱኛል (አሁን “ረ” ላልታ ትነበብ)፤ እገሌ ይደርስልኛል…” የሚል ሰበብ ከእንግዲህ ዋጋ እንደሌለው አማራው ውድ ዋጋ በመክፈል እየተማረ ነው፡፡ በውስጥም በውጭም ያሉ ጠላቶቹ ተባብረው – ሊተባበሩ የማይችሉ እንኳን አማራን ለማጥፋት ሲባል እየተባበሩ – የአማራውን ሥርዓተ ቀብር በማቀላጠፍ ላይ ናቸው፡፡ ሰይጣን አምላኪዎቹ አውሮፓውያንና አሜሪካውያን ከሕወሓትና ከኦነግ/ኦህዲድ ጋር በመቀናጀት ይህን ከየዋህነቱ በስተቀር ጠላት ሊኖረው የማይገባውን አማራ ስሊውን እያነቁት ነው፡፡ ለዘመናት እንቅልፉን ሲደቃ የከረመው አማራ ወለጋ ላይም፣ ጉራፈርዳ ላይም ሻሸመኔ ላይም፣ ዐርባ ጉጉም ላይ፣ አሰቦትና በደኖም ላይ፣ ወሎ ላይም፣ ጎጃምና ጎንደር ላይም፣ ሸዋ ውስጥም … በጥቅሉ ተሰፍሮ በተሰጠው ክልል ተብዬ ውስጥም ሆነ ከክልል ተብዬው ውጪ የትም ቦታ መኖር እንዳይችል የአማራ ጠላቶች ኅብረት ሊቀ መንበር አቢይ አህመድ ባዘዘው ቀጭን ት’ዛዝ መሠረት ከያለበት እየተለቀመ ወደሞት እየተጋዘ ነው – እርግጥ ነው በአንድ በኩል ሲታይ የገዳዮቹን የመግደል አራራ ለማርካት በሚመስል መልኩ አማራ ሞቶ የማያልቅ ሕዝብ ነው፤ ይህም ተፈጥሯዊ መለዮው ጠላቶቹን ይበልጥ ያናድዳቸዋል፤ በዚህ ጭርጭር ነው የሚሉት፡፡ አማራውን ፈረንጆች አይወዱትም፤ አማራውን ዐረቦች አይወዱትም፤ አማራውን በወያኔ የዘመናት ፕሮፓጋንዳ አእምሯቸውን የተሰለቡ በተለይ አሁን አሁን በርካታ ትግሬዎች አይወዱትም፡፡  በኦነግና ኦህዲድ የሀሰት አኖሌያዊ ትርክት የሰከሩ ብዙ አክራሪ ኦሮሞዎች አማራውን አይወዱትም፤  ምዕራባውያንና ምሥራቃውያን አማራውን አይወዱትም፡፡ ለምን እንደማይወዱት ምክንያት ስዘረዝር አልውልም፡፡ ግን ግልጽ ምክንያቶች አሏቸው፡፡ በአጭሩ አማራ ሞት የተፈረደበት ነጮችን ባዋረደው አፍሪካዊ የጥቁሮች የነፃነት ትግል የዚህ ሕዝብ ሚና ቀላል ካለመሆኑም በተጨማሪ ለሰይጣን አገዛዝ የኢሉሚናቲዎች  ዕቅድ ደንቃራ በመሆኑ ነው፡፡ አማራ ተመታ ማለት ኢትዮጵያ ተበታተነች ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ተበታተነች ማለት ፓን-አፍሪካኒዝም ለይቶለት ከሸፈ ማለት ነው፡፡ እናም ኢትዮጵያ ተበታተነች ማለት ሥውሩ የዓለም ገዢ በአፍሪካ ትልቅ ድል ቀናው ማለት ነው፡፡ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የመጥለቅለቁና ኦርቶዶክስም በራሷ ልጆች ሆዳምነትና ሰይጣናዊነት ጭምር የመፈረካከሷ ነገር አጋጣሚ ከመሰላችሁ ስህተት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ቅንብር ነው፤ በመቶዎች ዓመታት የተሰናዳ ልዩ ቅንብር፡፡ ግን ይህም ይፈርሳል፡፡ የመፍረሻውም አቡሻክር በጣም ተቃርቧል – በጣም፡፡ ብቻ እኛ ከክፋት እንታቀብ ወንድሜ፡፡

አማራ አስተዳደጉ ጠባብ አይደለም፡፡ የሚያስቀና ሥነ ልቦና የታጠቀ ግን ይህ ሥነ ልቦናው ወቅቱን ያልዋጀ በመሆኑ ክፉኛ እየጎዳው የሚገኝ በአፍሪካ ትልልቅ ከሚባሉት ሕዝቦች አንደኛው ነው – የትልቅነቱም መሥፈርያ ቁጥር ብቻ ሣይሆን አስተዋይነትና ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ናቸው፡፡ አንደኛው ጎጥ ከሌላኛው ጎጥ የመለያየቱ መንስኤም አንድነቱ ነው፡፡ የትም የሚገኝ አማራ ስለኢትዮጵያ ያለው አመለካከትና ፍቅር አንድ ነው፤ ስለሕይወት ያለው ፍልስፍና አንድ ነው፤ ስለዘረኝነት ብትጠይቀው መልሱ አንድ ነው፤ የቁርጥ ቀን ሲመጣም በመጨረሻው ሰዓት አንድ ነው፡፡ ብዙ ሆኖ አንድ መሆኑ ታዲያ ጎዳው፡፡ ይህ በብዙ ነገር አንድ የሆነ ሕዝብ የተምቦረቀቀ አንድነቱ ጎዳውና ለትናንሽ አስተሳሰቦች በሩን በርግዶ ለትልቅ ጉዳት ተዳረገ፡፡ በአንድ ጀምበር የሚያሸንፈውን ጦርነት 30 እና 40 ዓመታትን እየለገመ አሁን ላይ ለሚገኝበት የኅልውና ችግር ተጋለጠ፡፡ በዚያ ላይ በመሃሉ የበቀሉና በብአዴን የሚወከሉ የኔ ናቸው የሚላቸው ወይንም ያንተ ናቸው ተብሎ በወዳጅ መሳይ ጠላቶቹ የሠረጉበት ከሃዲና ሆዳም ዜጎች ያስከተሉበት ጉዳት ከግምት በላይ ነው፡፡ አማርኛን ደግሞ ሁሉም ስለሚናገረው ወዳጅን ከጠላት ለመለየት ተቸገረ፡፡ ኢትዮጵያውያን እንደሩዋንዳውያን በመልክና በቁመት አለመለያየታቸውም አማራን በብዙ ጎኑ ጎድቶታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዳያስፖራዎች ቤት ግብዣ | በእውቀቱ ስዩም

አሁን ካለፈ ስህተቱ ተምሮ አበጀ በለውን በመሰሉ የጎበዝ አለቆች ነፃነቱን መቀዳጀት አለበት፡፡ በዚያውም ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር እነዚህን የእፉኝት ልጆች ልክ አስገብቶ ኢትዮጵያን መታደግ ይኖርበታል፡፡ ጠላቶቹ የዘረጉበትን ወጥመድ በዘዴ በጣጥሶ ለድል የሚያበቃውን የጎበዝ አለቃ አሰላለፍ መከተል አለበት፡፡ በአቢይና በመከላከያ አማራ ይጠፋል እንጂ ኅልውናውን ሊያስጠብቅ አይችልም፡፡ ሸረኛው አቢይ አስፈላጊውን ስንቅና ትጥቅ በመደባቸው የኦሮሙማ የጦር አለቆቹ በኩል እያቀረበ ወያኔን ከመቀሌ እስከ ደሴ እንዴት አድርጎ እንዳደረሳት እናውቃለን – ሁኔታዎች ከፈቀዱለት ከደሴም አልፎ እስከ ደብረ ብርሃን እንደሚስባቸው ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱን ጅሎች ካላጨራረሰ የኦሮሙማ ዕቅዱን ለማሣካት ያስቸግረዋል፡፡ ይህን እውነት ብዙው ሰው ይክደዋል – በዚህ እኔም “ብው!” እላለሁ፡፡ “እንዴት ሰው የተዘረጋበትን ወጥመድ መረዳት ያቅተዋል?” በማለት በንዴት እንጨረጨራለሁ፡፡ ይሄ አማራ ድል ሲቀናው “አፈግፍግ” የሚሉት የበላይ ትዕዛዝ ደግሞ ስንትና ስንት ኪሣራ በአማራው ላይ እንዳስከተለ ሁሉም የሚያውቀው ገሃድ እውነት ነው፡፡ አማራው፣ አገኘሁ ተሻገርንና ማንም የማያውቀውን ይልቃል የተባለውን አዲሱን ድንዙዝ የአማራ ክልል ሹም ጨምሮ ሌሎች የብአዴን አባላት የወያኔና የኦህዲድ ቅምጦች መሆናቸውን ተረድቶ ለሚዲያ በማይጋለጥ አዲስ አደረጃጀት ይህን አስከፊ የጠላቶች ውርጅብኝ ማክሸፍ ይገባል፡፡ የአማራ ፋኖና ሚሊሻዎች ደግሞ ከወያኔ ተማሩና የግፍ ሥራ በማንም ላይ እንዳትሠሩ አደብ ግዙ – ተመልሶ የሚመጣው ወደ እናንተው ነውና በዚህ ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ዕብሪትና ጥጋብ የኋላ ኋላ ወደራስ ተመልሶ ያለአንዳች ርህራሄ የሚፋጅ እሳት ነው፡፡ ከወያኔ መማር አለባችሁ – ለተራው ዜጋ የደረሰው መከራ የተከሰተው በወያኔ ግፍና ዕብሪታዊ ተግባር ነው፡፡

አማራ ቆርጦ ከተነሳ የሚያስጨርሰውን መከላከያም ሆነ ወያኔን መዋጋት አያቅተውም፡፡ ወዳጅ መስሎ በውስጥ የሚያስጨርሰንን ባንዳና ቅጥረኛ ደግሞ አስቀድሞ ጥግ ማስያዝ ለነገ የሚተው አይደለም፡፡ በጎጥም ሆነ በአካባቢ መከፋፈል አማራን ያስጨርሰዋል እንጂ በፍጹም አይጠቅመውም፡፡ በአቢይ ቅቤ ምላስ መታለልም ይብቃ፡፡ አቢይ ገደሉን ሜዳ ነው ብሎ ማሳመን የሚያስችል ሰይጣናዊ ዕውቀት ከዲያቢሎስ ተችሮታልና ከአሁን በኋላ የሱን ንግግር ማመን አውቆ እንደመደንቆርና ወገንን በፈቃደኝነት እንደማስጨረስ የሚቆጠር ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በዚያ ላይ የቀን ጉዳይ እንጂ የትም የሚኖር አማራ ከጭዳነት አይተርፍም – ይህን ሃቅ ሁሉም አማራ ተገንዝቦ ኅልውናውን ማስጠበቅ ይችል ዘንድ ከማንም ጥሪ ሳይጠብቅ መዝመት ይኖርበታል – ወያኔዎች ደጁ እስኪደርሱና ኅልውናውን እስኪያሳጡት ድረስ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ አቢይ በመጨረሻ ሚስቱን ሳይቀር ገብር ቢባል ለቆሪጥ ወስዶ ከነልጆቿ የሚሰጥ ዐውሬ ነው፡፡ ይህን እውነት ደግሞ አማራው በየቦታው ሲጨፈጨፍ አዘኑን የገለጠበት አንድም ቀን ወይም አጋጣሚ አለመኖሩን በማስታወስ መረዳት ይቻላል፤ እጅግ ሲበዛ ፀረ-አማራ ዐረመኔ ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሰው የዕልቂት ድግስ ለመዳን አሁኑኑ መነሳት ተገቢና ወቅታዊም ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው – የሚገርመው – እወክለዋለሁ የሚለውም ሕዝብ ራሱ አይወደውም፡፡ ከሁለት ያጣ ጎመን እንደመሆኑ መጨረሻውም እንደማያምር በበኩሌ አልጠራጠርም፡፡

ጎጃም ያለው አማራ አሁን ምንም ስላልሆነ እስከወዲያኛው ምንም ሳይሆን ይቀራል ማለት አይደለም፡፡ አሁን ጎንደር ላይ ያለ አማራ ምንም ስላልሆነ ምንም ሳይሆን ዝንታለሙን ይኖራል ማለት አይደለም፡፡ የተነሳበት ጠላት ሞቶም እንኳን ዐፅሙን በሙቀጫ ወቅጦ ወይም በወፍጮ ፈጭቶ ዱቄቱን እስከመበተን ቢደርስም ጥላቻው የማይበርድለትና ቂም በቀሉ የማይወጣለት እጅግ ክፉ ነው፡፡ አማራን ተራ በተራ ግን ሁሉንም የሚፈጅ ጠላት ነው የመጣበት፡፡ በተረቱ “የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል” እንደሚባለው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም አማራ የኅልውና አደጋ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደቁንጫና እንደትኋን ማንም ሊገድለው የሚችልና ግድያውንም በመንግሥትነት ስም አራት ኪሎ የተቀመጠው ኦሮሙማ ስፖንሰር የሚያደርገው አማራው ነው፡፡ ለምሣሌ አንድ አማራ በመኪና ገጭተህ ፍርድ ቤት ብትቀርብ ዳኛው የታወቀ ነው ደቻሣ ነው – አቃቤ ህጉም የታወቀ ነው ሰርቤሣ ነው – የእሥር ቤቱ አዛዥም የታወቀ ነው ጉርሜሣ ነው – ፍርዱም የታወቀ ነው “በል እንዳይለመድህ፤ ሌላ ጊዜ ባይሆን ሰው እንዳትገጭ፤ ለዛሬ በገጨኸው ሰው ስም ምክንያት ምረንሃል” የሚል ነው – የገጨው ሰው መቼም “ስንሻው አበረ አዳሙ” መሆን አለበት፡፡ የትንሽ ሰዎችን ንግሥና ባለፉት 30 ዓመታት እስክንጠግብና እስኪያንገሸግሸን አየነው፡፡ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ደግሞ መንግሥትና መልካም አስተዳደር ምን እንደሆኑ የምናይበት የወርቃማው ዘመን መባቻ ይሆናል፡፡

ዝም ብለህ እመነኝ!

ከፋሺስት የከፋ… ዘጋቢ ፊልም

3 Comments

  1. ጒዱ ተጠማዝዞ ተጠማዝዞ ፍፃሜ ላይ የተነሳበትን እውነተኛ አሳቡን አስታውቆናል። “አንድ አማራ በመኪና ገጭተህ ፍርድ ቤት ብትቀርብ ዳኛው የታወቀ ነው ደቻሣ ነው – አቃቤ ህጉም የታወቀ ነው ሰርቤሣ ነው – የእሥር ቤቱ አዛዥም የታወቀ ነው ጉርሜሣ ነው – ፍርዱም የታወቀ ነው “በል እንዳይለመድህ፤ ሌላ ጊዜ ባይሆን ሰው እንዳትገጭ፤ ለዛሬ በገጨኸው ሰው ስም ምክንያት ምረንሃል” የሚል ነው – የገጨው ሰው መቼም “ስንሻው አበረ አዳሙ” መሆን አለበት።”

    ማሳሰቢያ፦ ጉዱና መሰሎቹ ከደነገጉሉት ውጭ ያሰበ ወዮለት! ዘሐበሻ አዘጋጆች በ “ነፃ አስተያየቶች” ዐምድ ሥር ይህን መፍቀዳቸው ምን ያህል የአሳብ ድህነት ውስጥ እንደ ገባን፣ ምን ያህል አንባቢው እንደ ተናቀ ያሳያል! “ነፃ” ጥላቻ ማራባት አይደለም! “ነፃ” መረጃ የሌለው ማለት አይደለም!

  2. አለም አይዞህ ኑረህም ሰለማትጠቅም ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ሁኖ ምርምር እንዲያካሂድብህ ሁኔታዉን በማመቻችት ላይ ነኝ። ለሀገሩ እንቅልፍ አጥቶ የኖረውን ሰው ሁሉ ብርሀኑ ነጋን፤አንዳርጋቸው፤ሌንጮ ለታ አብይ አህመድ አጠገብ አለፈ ብላችሁ ታጥረገርጉታላችሁ። እንደ ሰው አንድ አርቲክል ለመጻፍ አቅሙ የሌላችሁ አንተ፤ አምባው በቀለ፤ እውነቱ የምትባሉ ጉዶች ተከፍሏችሁ ምሁሩን ሁሉ ትጨረግዱታላችሁ። ይሄ እንደ ስራ ተቆጥሮ የምታግኙት ነገር ቢቀርባችሁስ? እስክንድር በቪ8 መኪና መጥቶ ትዛዝ ሰጥቶን ሄደ ያልከው አንተ ለመሆንህ ጥርጥር የለኝም።

  3. አይ (birega) ባይረጋ እንዲያው የጠመጅ እና የገብሱ እንክርዳድ ተደባልቆብህ፤ ለመጫር የምትሞክረው አስተያየትንም ከተሰጠው ዕርስ ጋር ማገናዘብ ተስኖህ የሰንበት ጽንስም በመሆንህ በደርስክበት ቦታ ሁሉ ትውኪያ እና ቅርሻትህ እንድ ዳግማዊ ጉድ ኮሣ ጠረናሕ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share