January 13, 2025
15 mins read

ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ … ከቆሎነት እስከ ዳቦነት ብትሞክረው አልሆንልሽ ይላታል፡፡ ያኔ መደቡ ላይ ተጋድሞ የሚስቱን ጭንቀትና ጥበት ይታዘብ የነበረው ባል “ዕብድ እህል ገዝቼ ሚስቴን አሳበድኳት!” በማለት አዘነላት ይባላል፡፡ ለኛስ ማን ይዘንልን?

የኦሮሙማዎች ዕብደት ድንበር የለሽ ሆኗል፡፡ የኛ የሕዝቡ ዝምታና ፍርሀትም እንደዚሁ ቅጥ አጥቷል፡፡ ምን እስክንሆን እንደምንጠብቅም አላውቅም፡፡ እንደተለመደው ሁሉንም ለእግዚአብሔር እርግፍ አድርጎ መተውን የመረጥን መሆናችን ለዚህ ግፍና በደል አብቅቶናል – በጎሣና በሃይማኖት መከፋፈላችንም ጭምር፡፡ ራሳቸውን የሚሾሙብን ባለጊዜዎችም እግዚአብሔርንም ሆነ የሚገዙትን ሕዝብ አይፈሩም፡፡ የተሻለው ደንቆሮ እልም ባለው የባሰበት ደንቆሮ እየተተካ በተለይ ያለፉትን ሃምሣ ዓመታት አለመላው በከንቱ አሳለፍነው – ከአንድ ሰውና ከአንዲት ታሪካዊት ሀገር ግማሽ ምዕተ ዓመት በቃጠሎ መልክ እንዲህ ሲወድም በእጅጉ ያናድዳል ብቻ ሣይሆን ሰው ሆኖ መፈጠርን ያስረግማል፡፡ ያደላቸው የትና የት ሲደርሱ እኛ ግን ከአርሲ አቦምሣና ከበሻሻ እንዲሁም ከአምቦ ገጠሮች በመጡ በትምህርትም በዕውቀትም በሞራልም እዚህ ግቡ በማይባሉ የአጋንንት ባሪያዎች መቀመቅ ወረድን፡፡ ትምህርትን የሚገድሉ ትምህርት ጠል እንደመሆናቸው እነዚህ ኤቢሲዲን አስተካክለው የማይጽፉ ደናቁርት ቤተ መንግሥት ገብተው የትምህርት ተቋማትንና የተማረን ሰው በመግደል ኢትዮጵያን በዓለም ፊት ክፉኛ አዋረዷት፡፡ መነሳቷ ባይቀርም ለጊዜው ያናድዳል፡፡

እነዚህ “ሰዎች” – በሰውነት መጥራት ከተቻለ – ኢየሱስ ክርስቶስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል የጸለየላቸውን እርሱን የሰቀሉ ፈሪሣውያንን የሚያስንቅ አረመኔያዊ ተግባር በተለይ በአማራው ላይ እየፈጸሙ ነው – ከ50 ዓመታት በፊት ጀምሮ፡፡ አማራን በወያኔ ተሰፍሮ በተሰጠው ክልልም ሆነ አዲስ አበባን ጨምሮ በተገኘበት ቦታ ሁሉ የተቻላቸውን ሁሉ ግፍና በደል እየፈጸሙበት ነው፡፡ እሱም አሁንም ለጥ ብሎ ተኝቷል፡፡ ማን ምን ቢያዞርበት ይሆን ግን?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ አማራ በብዛት እንደሚኖርባት የምትታመነዋን አዲስ አበባን በልዩ ሁኔታ እያጠቁ ነው፡፡ በኮሪደር ልማት ስም – ሊያውም ቦታውን እያጠሩ ሊያስቀምጡት – ቤት ማፍረሱና ማፈናቀሉ፣ ሁለትና ሦስት ሆነው በተገኙበት ወጣቶችን አፍኖ ደብዛቸውን ማጥፋቱ፣ አማራ የተባለን የመንግሥት ሠራተኛ ባልንም ሚስትንም ከሥራ በማባረር ቤተሰብን በርሀብ መፍጀቱ፣ የኑሮ ውድነትን ከሰማየ ሰማያት በላይ መስቀሉ እንዳለ ሆኖ በየቀኑ በሚያወጡትና በሚተገብሩት ደምብና ዐዋጅ አዲስ አበቤ አብዶ ብቻውን እያወራ መሄድ ይዟል፡፡

ልብ በል እንግዲህ፡፡ 86 መቶኛው የሀገራችን ሕዝብ ይቀምሰውንና ይልሰውን አጥቶ በድህነት አረንቋ እየተንከላወሰ ባለበት ሁኔታ ይህ ዕብድ ሕጻን ጠ/ሚኒስትር ተብዬ ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚሸጥ ዕቃ በእጁ አስገብቶ ሀብት ንብረቷን ለቤተ መንግሥት ግንባታና ለጦርነት እያዋለው ነው፡፡ ፓርላማ ለሰሙ እንኳን የሌላት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንቅልፋም አጨብጫቢ የፓርላማ አባል ከየጉራንጉሩ በራሱ በዕብዱ ማሙሽ ተመርጦ ቤተ መንግሥት ይገባና “10 ሚሊዮን ዜጋ ዛሬ በጥይት ይገደል” ተብሎ ድምጽ እንዲሰጥበት ቢቀርብ ከሚታወቁት ከነዚያ ሦስት የተማሩ የተቃውሞው ጎራ አባላት በስተቀር ሌላው አጨብጫቢ በሙሉ ድምጽ ያሳልፈዋል፡፡ እንደዚህ ያለ ፓርላማ ያላት ብቸኛ ሀገር የኛዋ ናት፡፡

ለማንኛውም የሚከተሉትን የሞት ዐዋጆች እንይ እስኪ – አሁን ትዝ ያሉኝ ብቻ ናቸው፡-

  • የመብራት፣ የውኃና የሥልክ ክፍያዎች እጅግ ከመጨመራቸው የተነሣ የጥንቱ ንዑስ ከበርቴ የአሁኑ የድሃ ድሃ ዜጋ እነዚህን ክፍያዎች መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ መታወቂያም ይሁን ሌላ ሰነድ ለማደስ፣ ለቦሎ፣ ለሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ፣ … የትም ሂድ የትም ግባ ክፍያው ጣሪያ ነክቷል፡፡ ደሞዝ ግን እንደተርኪስ ባቡር እዛው እንደተገተረ ነው፡፡ እነማሞ ቂሎ ታዲያ በአነስተኛው ከአንድ ሽህ ዶላር በላይ ደሞዝ የሚከፈልበትን ኬንያን በማጣቀስ የቤንዚን ዋጋ ከኬንያ ያንሳል ይሉሃል፡፡
  • ወያኔ ሲወጣ ብር 18 ገደማ የነበረ ሊትር ቤንዚን አሁን 101.45 ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ገበያውን ካለበት ዕብደት በብዙ የመቶኛ ሥሌት ያባብሰዋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ነገር ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ነውና፡፡ ባለፈው ሰሞን የነበረው የቀን 50 ብር ወጪ አሁን 80 ደርሷል – ከእኔ ሠፈር ወደ መሀል ከተማ ገብቶ ለመሥራትና ወደቤት ለመመለስ፡፡
  • ጤፍ ጥቁሯ እንደየቦታው ዋጋው የሚለያይ ሆኖ በኩንታል ከ14 ሽህ ብር በታች አትቀመስም፡፡ ቅቤ ከ900 በታች ከተገኘ መጠርጠር ነው – ለነገሩ ሙዝም ለካንስ ዋጋው 100ን እየታከከ ነው፡፡ ሥጋ ቁርጥም በለው ጥብስ ከ2000 በታች ከተገኘ እሰዬው ነው፡፡ እኔ አንድ ወቅት የነበሩኝን ሦስት ጠርሙስ ሬድ ሌብል ዊስኪዎች በድምሩ ብር 315 ሸጫቸዋለሁ – በ30 ዶላር የገዛኋቸው ነበሩ፡፡ ብሃጺሩ – ማለትም ባጭሩ እኛ ድሆች ሥጋን፣ አትክልትን፣ ልብስንና መዝናኛን ከመሳሰሉ መሠረታዊ የሕይወት ሰበዞች ከተፋታን ማለትም ከተለያየን ቆየን፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ለቤተ መንግሥትና ለመናፈሻ ግንባታ በሚል ሰበብ ከመኖሪያችን መፈናቀሉ ቢቀርልን ቀሪው ለአንድዬ የሚሰጥ የቤት ሥራ በሆነልን ነበር፡፡ ብዙ ስላየን እነዚህንም በቅርቡ እንደሚገላግለን ሥራቸው ራሱ ይመሰክራል፡፡ አለነገር እንዲህ አልተቅነዘነዙም፡፡ ለነገሩ መለስ ዜናዊም እኮ አስቀድሞ የታዬ ታይቶት ስለነዚህ ገዢዎች የተናገረው ነገር አለ አሉ – ረሳሁት ልበል?
  • የትራፊክ ቅጣት መብራትም ጣስ፣ በማይቆም ቦታም ቁም …. ክፍያው ከ1500 እስከ 3000 እና ከዚያም በላይ ሆኗል፡፡ በቂ መንገድና የትራፊክ ፍሰት አገልግሎት በሌላት ድሃ አገር እንዴት እንደሚቀናጡ ልብ እንበል፡፡ ይታይህ እንግዲህ – በመንገድ መጨናነቅ ምክንያት በቀን 500 ብር እንኳን ማግኘት ከባድ አእምሯዊ ሸክም የሚሆንበት አንድ ባለታክሲ 3000 ሲቀጣ እንዴት ሊኖር እንደሚችል ፈጣሪ ይወቅ፡፡ ነገሩ “ውጣ አትበለው እንዲወጣ ግን አድርገው” እንደሚባለው የትግርኛ ብሂል ነው – “ውፃዕ አይተበሎ ከምዝወፅዕ ግበሮ”፡፡ ሰዎቹ አዲስ አበባን irrelevant እናደርጋታለን ብለው እንደዛቱት ከዚያም በላይ እያደረጓት ነው፡፡ ከኛ ዘንድ ወንድ ጠፍቶ እንጂ ምን ያላሉንና ያላደረጉንስ ነገር አለ! ለነገሩ እነአቶ ይሁን ዶክተር ብትኔ ብትኔም ራሱ ተበትኖ አፈር ሆኗል አሉ፡፡ ይህን የሚከረፋ ዘረኝነት የሚባል የሰው ልጅ ጠላት የሚያራምዱ ሁሉ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡
  • አማራ ሞቶም ቢሆን ንብረት ማፍራት የለበትም በሚለው እሳቤያቸው ተመርኩዘው ላለፉት አሥር ዓመታት ለፍቶ ጥሮ ግሮ የተገኘን ሀብትና ንበረት ለመዝረፍ በእንቅልፋሙ ባርላማ ህግ አጽድቀዋል፡፡ ለአሥር ዓመት ማን ደረሰኝ ይዞ ይቀመጣል፡፡ አያያዛቸው ሌልኛ ነው፡፡ ሰውዬው ውጪ ሀገርም ይኑር ይሙትም ምንም ይሁን ምን በህግ ፊት ቀርቦ ማስረጃ ካላመጣ ንብረቱን ኦሮሙማ ኦሮምያን ጎጆ ያወጣበታል፡፡ በቃ፡፡
  • ዕብዱ ማሙሽ በዚያን ሰሞን ሲቀደድ 124 የመንገደኞች አውሮፕላን ለመግዛት ትዕዛዝ መሰጠቱን ነገረን፡፡ ቀጥሎም አሁን ካለው ቦሌ አየር መንገድ ጋር በባቡር የሚገናኝ አዲስ አየር መንገድ ሊሠራ ዕቅዱ ተነድፎ ማለቁን አበሰረን፡፡ ትንሽ ቀደም ብሎም በድምሩ ወደ መቶ ቢሊዮን የሚጠጋ ችግኝ በመላ ሀገሪቷ ማስተከሉን አስረድቶናል፡፡ ይህን በመሰለ ወንፊት ሰውዬ መመራት በርግጥም ትልቁ አለመታደል ወይም መረገም ነው፡፡ ቁጥርና ኦሮሙማ ሳይግባቡ የኦህዴዶች ሥርዎ መንግሥት ፍጻሜ ሊደርስ ነው፡፡
  • አሮጌ ሞዴል መኪኖች በአዲሱ የአቢይ መንገድ እንዳይነዱ ሊከለከል መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ 80 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ መኪና አሮጌ ሞዴል ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ባለዲኤክስና ባለቮልስ ሁሉ ጉዱ ፈላ፡፡ አቅም ያለው ከዚህ በምናቡ በፈጠራት ሀገር እንደዶንኪሾት ከሁሉም ጋር እየተላተመ ከሚኖር delusional and myopic ዕብድ ጋር መፋለምና ከመሰል ወገኖቹ ጋር ተባብሮ ማስወገድ ነው መፍትሔው፡፡ ዋይታና ልቅሶ አይጠቅምም፡፡ ወንድ ወንድ መሽተት ያስፈልጋል አንዳንዴ፡፡
  • ምን አለፋህ – እነዚህ ጉዶች አራት ኪሎ ላይ እስካሉ ድረስ ገና የማንሰማው ጉድ የለም፡፡ ምን ይታወቃል – “ከሚስቶቻችሁና ከባሎቻችሁ ጋር ስትተኙ ለምታገኙት ደስታ በአንድ ግንኙነት ብር 500 ትከፍላላችሁ፡፡ ለተግባራዊነቱም በየጭኖቻችሁ በህክምና ባለሙያ ባልቦላ ወይም ቆጣሪ ይገጠምላችኋል፡፡ በማን መሬት ላይ ተቀምጠሸ ትደሰቻለሽ!” ቢሉንም ይችላሉ፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት መቼም ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡  ፈጣሪ ሲጣላ ለካንስ በዐረመኔነታቸው ከሚታወቁ የዱር እንስሳትም በከፋ ሰው መሰል ፍጡር ይቀጠቅጣል፡፡ መጥኔ ለታሪክ ጸሐፊዎች፣እንዴት እንደሚከትቡት ይሄን ሁሉ ጉድ ታዬኝ፡፡ ቢበቃኝስ!… ኤዲያ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop

Don't Miss

59390184 401

በእውነቱ ኢትዮጵያ መንግሥት አላትን? አማራውስ አሁን ምን ማድረግ አለበት?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ በዚህች መጣጥፍ ሁለት ነገሮችን አጠር አድርጌ ማንሳት
gragn mohmed gvt

በአእምሮ ህሙማን የሚመራው የአቢይ ግራኝ አህመድ መንግሥት – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ሰላም ወገኖቼ፡፡ አለሁ ለማለት ያህል ብቅ አልኩ እንጂ የምናገረው አዲስ