December 9, 2024
10 mins read

የአገር አፍራሹ ወቅት አልፎ፤ የአገር አጨራራሹ ዘመን ነገሠ

GeMaa50XwAAsUvRአንዱ ዓለም ተፈራ

ታህሣሥ  ቀን፣     ዓ. ም.

አዲስ አበባ በተኩስ ተናወጠች።

አዲስ አበባ በተኩስ ተናወጠች። ተኩሱ ባንድ ጎኑ፣ ሕጋዊ ነበር። በሌላ ጎኑ፣ ሕገወጥ ነበር። ይሄ እንዴት ሊሆን እንደቻለ አስከትላለሁ። እስካሁን የአገራችን የአስተዳደር መመሪያ የተመሠረተበት፤ ወደ የምትፈራርስ ጎዳና የነዳት፤ “አንድ ሕዝብ አይደለንም!” “የተለያየን ሕዝቦች ነን!” “እናም ተለያይተን፣ ራሳችንን ችለን እና ለትንሽ ጥቅም ብቻ ነው በፌዴሬሺን የምንሰባሰበው!” በሚል የፖለቲካ ፍልስፍና ነው። በ “የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር” ይሄው መመሪያ ተቀንቅኖ፣ ይሄው ድርጅት ይሄን መርኅ የሚያራምድ ሕገ-መንግሥት አስጸድቆ፣ የተለያዩ ክልሎችን ፈጥሮ፤ ያራመደው የአገራችን ፖለቲካ፤ አገር እየፈረሰች የምትሄድበት መንገድ ውስጥ አስገብቷት ነበር። ይህ እስካሁን የሄድንበት መንገድ፤ ዛሬ ወደምንጨራረስበት መንገድ አሸጋግሮናል። በአዲስ አበባ የተካሄደው፤ ለዚህ ደረጃ መብቃታችንን አብሳሪ ነው። እንዴት ለዚህ በቃን?

በአገራችን ያለው የፖለቲካ ቅኝት መንገድ የሳተው፤ የአስተዳደር በደልን፣ ከበዳዮችና ከተበዳዮች፣ ከገዢዎችና ከተገዢዎች አውጥቶ፤ በገዢ ብሄርና በተገዢ ብሔር መካከል ሆኖ የተቀመጠ ጊዜ ነው። ይህ፣ ትልቅ መታለፍ ያልነበረበት ቀይ መስመር ነበር። የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ይህን በቦታው ያሳቀመጠበትን ምክንያት፤ ያሳለፍነው ሰላሳ ሶስት ዓመታት በግልጥ አሳይቶናል። ስንት ሰው እንዳለቀ፣ ስንት ንብረት እንደወደመ፣ አገራችን በእድገት ምን ያህል ወደኋላ እንደተጎተተች፤ እያንዳንዳችን የምናውቀው ነው። ያ የፖለቲካ እውነታ፤ እስከዛሬ ገዝቶናል። የዋሆች፤ ይሄ ስርዓት ራሱ ያልፋል! አገራችን ምንም ቢሆን እንዲህ ሆና አትቀጥልም! የሚል ምኞትን እና ተስፋን ይዘው፣ በቀጥታ በትግሉ ከመሰማራት ይልቅ፣ ሁሉን ነገር ለነገ ሠጥተው፤ ለዚህ በቃን። አሁን ወደባሰ አዘቅት ገብተናል።

በአንድ በኩል፤ ይሄ የዘር ክፍፍል አስተዳደር ሄዶ፣ ሄዶ፣ ሊቀጥል የማይችልበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ፤ የግድ ለውጥ አይቀሬነቱ ገሃድ ሆነ። የብዙዎቻችን ፍላጎት፤ ይስተካከላል ነበር። ክፍፍሉ ይቀርና፤ አንድ እንሆናለን ነበር። የተገነዘብነው ግን ወደባሰ መሄዳችንን ነው። በሌላ በኩል፤ መቆየት የማይችለው፣ አናሳ ብድን ብዙኀኑን መግዛት የማይችልበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ፤ የግድ ማብቃት ነበረበት። ይሄ ግን፤ ወደተስተካከለ መንገድ መመለስ የሚችለው፤ በተፈጥሮ ሂደት ሳይሆን፤ በጉዳዩ ባለቤቶች ጥረት ነው። ዋናው ተጫዋች በቦታው የሚያደርገው ክንውን፤ ወሳኝ ነው። በሥልጣን ላይ ያለው የአክራሪ ኦሮሞዎች ገዢ ቡድን፤ እብሪቱ እያየለ ሲሄድ፤ ከዚህ የገዢ ቡድን የበለጠ አክራሪ የሆነው ሌላው ቡድን፤ ጉልበት ማብጀቱ ግልጥ ነበር። ሲጀመርም፤ የኦነግ ዓላማ፤ ኢትዮጵያን መቀየር እንጂ በደልን ማስቆም አልነበረም። እናም ያ እንዲሆን፤ የሚያራምደው የበለጠ አክራሪዎች ቡድን፤ ራሱን ከገዢው ቡድን የበለጠ አድርጎ አደራጀ። በመካከል የተረዳነው፤ በቦታው የተቀመጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ወሳኝ እንዳልሆነ ነው። በጎን ሌሎች በኦሮሞ አክራሪዎችና ፍጹም አጽናፍ የረገጡት አክራሪዎች መካከል ስምምነት እንዲፈጠር አደረጉ። ይሄም ስምምነት በሥልጣን ላይ ባለው ገዢ ቡድን መሪነት ሳይሆን፤ በፍጹም አጽናፍ በሄዱት መሪነት እየተነዳ ነው። ለዚህ ነው፤ አዲስ አበባ በተኩስ የተናወጠችው። በስምምነታቸው መሠረት ሕጋዊ ሊሆን ይችላል! የስምምነቱን ይዘት ብናውቀው። አዲስ አበባን በምንም መንገድ በተኩስ ማናወጥ ሕጋዊ አይደለም።

ለመሆኑ፤ በአንድ አገር፣ መንግሥታዊ መዋቅር ባለበትና መንግሥታዊ የጦር ሠራዊት ባለበት፤ ከመደበኛ ሠራዊቱ ውጪ የሆነ አካል፤ እንዴት ብሎ ነው ታጥቆ ከተማ በመግባት፣ እንደልቡ ተኩስ በተኩስ የሚፏልለው! ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የትኛው ሕገ-መንግሥት ነው ይሄን የሚፈቅደው? በስምምነታቸው ላይ ምን ሰፍሯል? ይሄ ተቀምጧል ወይ? ለነገሩ የደቡብ አፍሪካዉን የገዢው አክራሪ ኦሮሞ ቡድን እና የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ስምምነት ዝርዝር መቼ እናውቅና! እንኳንስ የርስ በርሳቸው ስምምነት!

ወደ ዛሬው እውነታ ስንመለስ፤ ለዚህ ያበቃንን ሂደት እንቃኝ። ስምምነቶች!

ሕዝባዊ መሠረት የሌለው ገዢ ክፍል፤ ለአገር ዘለቄታ ሰላምና ትክክለኛ አካሄድ ሳይሆን፤ ዛሬን እንዴት ውሎ እንደሚያድር ስለሆነ የሚጨነቀው፤ አንድም፤ ከማንም ጋር ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ነው። ሌላው ስምምነቱ ከሥልጣን እስካላወረደው ጊዜ ድረስ፤ ምንም ነገር ላይ ለመፈረም ወደኋላ አይልም። ለዚህ ነው፤ የአክራሪ ኦሮሞዎች ገዢ ቡድን፤ በጣም አገር አሳፋሪ ድርድሮችን ያደረገው። በደቡብ አፍሪካ ከትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ጋር፤ ቀጥሎ ከኦነግ ሸኔ ጋር ስምምነቶችን አካሂዷል። በኒህ ስምምነቶች ውስጥ፤ ምን ያህል የአገሪቱን ጥቅም አስጠባቂ ጉዳዮች ተካተዋል? በኒህ ስምምነቶች ውስጥ፤ ምን ያህል ያፈጠጡ ችግሮችን ቀራፊ መፍትሔዎች ቀርበዋል? ግባቸው እውነት ዘለቄታ ሰላም ነው ወይንስ ጊዜያዊ መተንፈሻ መግዣ? ሌሎችን ጥያቄዎችን ማከል ይቻላል። በዚህ ላቁም።

ምናልባት፤ አሁን ገዢው ኦነግ ሆኖ ሳለ፤ ምን ፈልገው ነው ይሄን የሚያደርጉት? ብሎ ጠያቂ አይጠፋም። ጉዳዩ ግን ወዲህ ነው። ቆርጦ የተነሳ አፍራሽ ቡድን፤ ምንም ዓይነት ድጎማ ቢደረግለት፤ ከተነሳበት ዓላማ ንቅንቅ አይልም። ኦነግ ሸኔ፤ ከሽመልስ አብዲስ ምንም ነገር ቢቀርብለት፤ በቃኝ አይልም። ይሄን በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል። በአንድ በኩል የአክራሪ ባህሪ ነው። አክራሪ ምክንያትና ሠጥቶ መቀበል አያውቅም። በሌላ በኩል፤ ሺመልስ አብዲሳ ራሱ የሚደራደራቸውን ፍላጎት የያዘ ስለሆነ፤ ድርድሩ የወግ ነው። ድርድሩ በማር የተለወሰ የስም መገለጫ ነው።

በማጠቃለሊያ፤ የተያዘው መንገድ፤ አገራችንን ለረሃብ፣ ለድርቅ፣ ለምስቅልቅሉ የወጣ አገር አስተዳደር የሚዳርግ፤ የቂም በቀልና እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድድር የሚዳርግ ሂደት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ መለስ ዜናዊን አንበርክኮ እንደሸኘው፤ ዛሬም ያንኑ ለአብይ አሕመድ ሊለግሰው ይገባል።

2 Comments

  1. “”…እናም የሆነ ቀን፣ የሆነ ሰዓት እንደ ሶሪያው አላሳድ ሠራዊት የኢትዮጵያም ጨፍጫፊ፣ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት ቅስሙም፣ ጅስሙም ተሰብሮ መበተኑ አይቀርም። ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር ይሄ አረመኔ አራጅ ሠራዊት ይሠበራል። ይበተናል። ያነዜ ነው እኔን የሚያስፈራኝ፣ የምሰጋውም ክስተት ይፈጠራል ብዬ የማስበው። መለኮታዊ ጣልቃገብነት ካልተፈጠረ በቀር ዓለም ዓይቶት የማያውቀው ጥፋትና እልቂት ይፈጠራል ብዬ ነው የምሰጋው። በቀል፣ በቀል፣ በቀል፣ በቀል በበቀል ምድሪቷ የምትዘፈቅ ነው የሚመሰለኝ። አዎ ከወዲሁ ለዚህ ጊዜ ተዘጋጅተን ካልመከርንበት፣ ይሄ ግማታም፣ ጥንባታም፣ ሸታታ ሥርዓት መገርሰሱ እንደማይቀር ዐውቀን ተረድተንም ከሥርዓቱ መውደቅ በኋላ እንደ ሕዝብ ከመጠፋፋታችን በፊት ከወዲሁ ምክክር ካልተደረገ እጅግ ሰቅጣጭ ነገር ነው የሚከሰተው። ከወዲሁም ዘገዛዙ ራሱ ምልክቱን እያሳየ ነው። በኦሮሚያ ሰው ሲያሳርድብት የነበረውን የሰው ቄራ ሠራተኞቹን በታላቅ ክብር ተቀብሎ መሃል ሃገር ለሌላ ጭፍጨፋና ዕልቂት እያዘጋጀ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይሄን ዓለም ሁሉ እያየ፣ እየተመለከተም ነው። ሩዋንዳ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲፈጸም እነ ፈረንሳይ በዚያ ነበሩ። ዛሬም አቢይ አሕመድ ከተመረጠ ወዲህ ፈረንሳይና ጣልያን እንደ ውኃ ቀጂ ሴት ነው የተመላለሰው። ጣልያን የገንዘብ እርዳታ ሁላ ነው ስታደርግለት የሚታየው። እናም በመንግሥታቱ ዕውቅና በቀጣይ ዕልቂት እንደሚኖር መጠርጠርና መስጋት ሟርተኛ አያሰኝም።”

    From Zemedkun Bekele’s telegram page

    I would like to highlight, “እናም በመንግሥታቱ ዕውቅና በቀጣይ ዕልቂት እንደሚኖር መጠርጠርና መስጋት ሟርተኛ አያሰኝም።”

    All of us have to realize that the grandest genocide in human history is about to unfold and that this premeditated genocide has been designed, planned, financed and produced for staging by the western powers.

  2. ከላይ በምስሉ ያስቀመጣችሁልን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው ወይስ አቶ አዳነ አቤቤ? አረ ግራ አታጋቡን? ይሄኛው ደግሞ ጃል ማን እንበለው? ጄነራል አበባው በጃል ሰኝ ሲታዘዝ ድሮም ወታደር አልነበርክም አሁንም ምንም አይመስልህም ምርኮኛና ሃገር አፍራሽ እየመጣ አናትህ ላይ ሲቀመጥ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop