እንደምን ሰነበታችሁ?አርበኛ ዘመነ ካሴ ነኝ።
ህዳር 27-2017 አም አርብ እለት ድርጅታችን የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላልተወሰ ጊዜ የሚቆይ የአገልግሎት ተቋማት እቀባ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ክልከላ መመሪያ ማስተላለፉ ይታወቃል።
ትዕዛዙ ከሰኞ ሕዳር ሰላሳ ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ጥሪው የስራ ማቆም አድማን የሚጨምር መሆኑን በድጋሜ ማሳወቅ እወዳለሁ። ይህን ትእዛዝ ተላልፎ የተገኜ ግለሰብ ወይንም ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዳለቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ የአውሮፕላን በረራንም ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የምናስቆም ይሆናል።
በዚህ አጋጣሚ ለመላው አማራ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪዎች አንድ አጭር ግን ታሪካዉ ጥሪ ማድረግ እንፈልጋለን።እንደሚታወቀው ገና ከፅንሰቱ የአማራን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ አስፈትቶ ዱላ እንኳን ከልክሎ ፥የህዝባችን ጉልበትና ወኔ መስለብ የሚችልበትን ጊዜና አጋጣሚ ሲጠብቅ የቆየው ጠላት በተለይ በዚህ ወር ውስጥ የአባውራ ቤት ሰብሮ እየገባ የአርሶ አደሩንና የከተማ ነዋሪውን መሳሪያ እየነጠቀ ይገኛል።
መሳሪያውን ከአማራው አርሶ አደርና ከተሜ እጅ ነጥቆ በስነልቦናም በጉልበትም ባዶ የሆነ አማራን ከመፍጠር ባለፈ የነጠቀውን መሳሪያ ጎዳና ላይ አፍሶ ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ተቋማት ላጋዛቸው ህፃናት ሊያስታጥቀው መዘጋጀቱን ድርጅታችን ደርሶበታል።ስለዚህ የአማራ ህዝብ ሆይ ለስነልቦናህ ጋሻ፥ለማንነትህ ዋሻ፥ለቤትህና ለበረትህ መከታ፥ለቤተሰብህ አለኝታ፥ለታሪክህና ነባር እሴትህ ዋልታ የሆነውን መሳሪያህን እንድትጠብቅ አደራ እንላለን።ሁለት አማራጮች እጅህ ላይ አሉ፥
1)መሳሪያህን ይዘህ ፋኖን በመቀላቀል ዘላለማዊ ጠላትህን ለዘለአለም ማሸነፍ እና ህልውናህን ማረጋገጥ
2)በየአካባቢህ ለሚገኝ የፋኖ መዋቅር በጊዚያዊነት በውሰት መስጠት።
የአማራን ህዝብ ከጥጃ ብረቶቹ እና ጥጆቹ ለይተህ ማሰብ አይቻልም። እስትንፋሶቹ፥ክብሩና ኩራቱ፥የማንነቱ አስኳሎች ናቸው።ጥጆቹ አለሙ የጥጃ ብረቱ ቅስሙ ናቸው።ስለዚህ ሁሉንም ዋጋ ከፍለን እንጠብቃቸዋለን።በዚህ ሂደት ውስጥ አርሶ አደሩና የከተማ ነዋሪው ተባባሪ እንዲሆን አደራ እንላለን።
(አንድ ህዝብ፥አንድ ትግል፥አንድ ድል!!)
(ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም)
(አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ)
ህዳር 29/2017 ዓ.ም
©️አሻራ ሚዲያ
አስቸኳይ ጥሪ ከአርበኛ ዘመነ ካሴ‼️
ለመላው የአማራ ህዝብ!እንደምን ሰነበታችሁ?አርበኛ ዘመነ ካሴ ነኝ።
ህዳር 27-2017 አም አርብ እለት ድርጅታችን የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላልተወሰ ጊዜ የሚቆይ የአገልግሎት ተቋማት እቀባ እና… pic.twitter.com/I9jP9phNNY— Demekech (@Etiozion) December 8, 2024