December 9, 2024
1 min read

የማህበራዊ ሚዲያ አንቂው ሱሌማን አብደላ ወደ ኢትዮጵያ ተወሰደ

2 Comments

  1. የሚጠበቅ ነው ምን አደረግንለት? መስከረም አበራ፤አቶ ታድዮስ ታንቱ ሲከረቸሙ ምን አደረግንላቸው? ክርስቲያን ታደለ በተከፈተው ሜዳ ሲተጋተግ በአራጆች ተይዞ መከራ ሲያይ ምን አደረግን እንዚህ ሰዎች ትግሬ ቢሆኑ ኑሩ ምድረ ትግሬ ፍራሽ አንጥፎ አሜሪካና አውሮፓን ቀውጢ ያደርገው ነበር። እስራኤል ግን አይሞከርም ተንኮላቸውን ስለሚያውቅ። ወሬ ብቻ።

  2. የደላው ተቀምጦ ሙቅን እያኘከ
    ሌላው ተደላድሎ ውሃ እየጨለጠ
    ተናነቀውና ሲሻ ማዋረጃ
    ውስኪ አቀረቡለት ውሃው ተረሳና!
    የዚህ ወጣት መከራ ከሳውዲ ወደ አዲስ አበባ መሻገሩ ከምጣድ ወደ እሳቱ እንደሆነ የገባው ብቻ ይረዳዋል። ከእኛ ቀድመው ነቅተው ለህዝብና ለሃገር ዘርና ቋንቋን ተገን ሳያረጉ ድምጻቸውን ያሰሙ ጊዜ በሰጣቸው ዘብጥያ ሲወርድ ወይም አፈር ሲመለስባቸው፤ ቤተሰባቸው የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ወድቀው ሲቀሩ ያኔ በሉ አይዞአችሁ፤ ከጎናችሁ ነን እንዳላልን ሁሉ በያለንበት ተደብቀን መኖርን ናፍቀን እንደፋደፋለን። ግን እኮ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። ፍትህ በሌለበት ዓለም አይኑን ጨፍኖ በነጋ በጠባ ጮቤ የሚረግጥ የታመመ ሰው እንጂ ኑሮ የተሳካለት አይደለምና!
    የሃበሻ ፓለቲከኞችና መሪዎች መለካት ያለባቸው በቃላቸው ብዛት ቢሆን ኑሮ ዛሬ ደርግ በስልጣን ላይ በሆነ። ቁና ቁና እየተነፈሰ ህዝብ ያፋከሩና ራሳቸውም የፎከሩ ዛሬ ከስመዋል። በለስ ቀንቷቸው እነርሱን ገፍትረው ለ 27 ዓመት ህዝብን ያናኮሩ ጠባብ ብሄርተኞች ዛሬ ላይ ሌላ የሚነክሱት በማጣታቸው እርስ በእርስ በመናከስ ላይ ይገኛሉ። አሁን በብልጽግና ስም ህዝብን የሚያውኩት ሁሉ ልክ እንደ በፊተኞቹ የማብቂያ ጊዜ ይኖራቸዋል። ለዚህ ነው የሃበሻ ፓለቲካ በወረፋ የመጠላለፍ ፓለቲካ ነው የምንለው። ትርፍ የለሽ፤ እልፍን በዳይ! እንቁ ልጆቿን እየበላችን እያስበላች የምትፍገመገም ሃገር። መውለድ እንጂ ማሳደግ የተሳናት ምድር። ስንት ለሃገርና ለወገን በጎና መልካም ሥራ የሚሰሩት ላይ አፈር ተመለሰ? የዚህ ማብቂያው መቼ ነው? ሱሊማን አብደላ ለተገፉ ድምጽ በመሆኑ ብቻ ገመናውን ያያል። ግን እኮ ሁሉም ነገር በሰአቱ ያልፋል። ያኔ የምንወሳበት በጎ ሥራ ይኖር ይሆን? ለቀሪውስ ትውልድ ይበጃል? የሰው ልጅ መለኪያው ሰው መሆኑ ብቻ ነው። ሌላው የጠራሁ አማራ፤ የጠራሁ ትግራይ ወይም ኦሮሞ ወዘተ መባሉ ሁሉ ፈጠራ እንጂ እውነትነት የለበትም። ሃበሻ የተደባለቀ ህዝብ ነው። ቋንቋ ማንነትን አይወስንም። ሱሊማን አብደላም መከራን የሚቀበለው ሃገሩና ህዝቡን ስለሚወድ ነው። ልናደርገው የሚገባንን በህቡዕም ሆነ በግልጽ ለእርሱና በብልጽግና የሰቆቃ እስር ቤት ውስጥ ላሉ ሁሉ እጃችን እንዘርጋ። ግን ምን አይነት መንግስት ነው ህይወት ያለውን ሰው ከአስከሬን ጋር የሚያስር? ይህ እብደት አይደለም የሚል ራሱ ያበደ ነው። የግፈኛ ምድር! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop