August 9, 2024
19 mins read

ተስፋ የሰጠውና እመርታዊ የሆነው የአማራ ፋኖ እንቅስቃሴ ምን መሰናክል ገጠመው? እኛስ በጋራ ምን ማድረግ አለብን? 

አክሎግ ቢራራ (ዶር) 

የአማራ ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ህልውና እንቅስቃሴና ትግል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ይዟል። 

አዎንታዊ ክስተቶች ምንድን ናቸው?  

  1. የአማራውን ትግልና እምቢተኛነት የጀመረው የአማራው ሕዝብ ነው፤ ባለቤቱም ሕዝቡ ነው።
  2. አማራውን ለእምቢተኛነት የቀሰቀሰው ምክንያት በአማራው ሕዝብ ላይ በተከታታይ የተካሄደውና አሁንም የሚካሄደው ብሄር ተኮር፤ ጸረ-አማራ ጭፍጨፋ፤ ረሃብተኛነት፤ እስራት፤ በገፍ ከቀየው መፈናቀል፤ የጤናና የትምህርት አገልግሎት መነፈግ፤ የስነ ልቦና ጦርነት፤ የተቋማት መፈራረስ ፤ ወዘተ ነው።
  3. ግለሰቦች ለስልጣን፤ ለግል ዝና፤ ለጥቅም ሊጠቀሙበት እንደማይገባቸው ሕዝቡ በግልጽ እየተናገረ ነው። እንዲያውም ሕዝቡ አንድነታችሁን አጠናክራችሁ መከራችን በአስቸክይ ፍቱልን እያለ ነው። 

በአሁኑ ወቅት አማራው የተጋረጠበትን አደጋ ላስምርበት። በአማራው ስም የሚደረገው እርስ በእርስ መናከስ፤ አንዱን ከሌላው ለይቶ ማሞገስ ወይንም መኮነን፤ በጎጥና በመንደር ደረጃ ወገንተኛነት ማሳየት፤ ለዓላማ ብቻ ተገዢ አለመሆን፤ መከፋፈልና እርስ በእርስ መናከስ ከቀጠለ ለአማራው ሕዝብ የሚያስከትለው ዋጋ ከባድ ነው። አማራው በራሱ አገር የሚኖርባት ኢትዮጵያ አትኖርም። 

በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ለሌሎች ለተከፉ ወገኖቻችን ከፍተኛ ተምሳሌትና ሞዴል ሆኗል። የዓለም መንግሥታትም ያከብሩታል።

ይህ የማይገኝ እድል ሊያመልጠን መፍቀድ የለብንም። ንትርትኩ ግን ስጋቶችን እንደፈጠረ ልንክድ አንችልም። ይህንን ስጋት እንደ ቀላል ነገር አንየው። ክፍተቶችን ለይተን መፍትሄ መፈለግ ያለብን ለዚህ ነው።

    1. የአማራው የህልውና ትግል ያለፍትህ ሊቆም እንደማይችል በገሃድ እያየን ነው።
  • የአማራ ፋኖው ለፍትህ እንቅስቃሴ ለሌሎች በአገዛዙ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፈር ቀዳጂና ተስፋ ሰጭ ነው። ክፍፍሉ ግን ስጋት እየፈጠረ ነው። 

ለምሳሌ ለመላው የደቡብ ሕዝብ፤ ለጋሞው፤ ለወላይታው፤ ለአኟኩ፤ ተተኪነት አያዋጣም ለሚሉ ኦሮሞውች ወዘተ። አማራው ወዳጆች እንዳሉት እንቀበል። 

  • ሸክም ለሰለቸው፤ ትግሥተኛነትን መርህ አድርጎ ለተጎዳው የአማራ ሕዝብ አሁን ከተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ግልጽ ነው። 


  • ውጭ ያለነው ትግሉን የምንደግፍ ሁሉ ትግሥትንና ብልህነትን መርህ አድርገን ለመደማመጥና አብረን ለመስራት ብንችል ሸክሙን ልንቀንሰው እንችላለን። ጦረነቱን ለማሳጠር የምንችልበት እድል አለ። 
  •  ቢያን ቢያንስ ከእሳቱ ላይ ቤንዚን አንጨምርበት። የሚጎዳው አማራውን ነው።
  • የአማራ ፋኖ ፍኖተ ካርታ እንደሚያስፈልገው በተከታታይ አንስተናል። ይህንን ወሳኝ ሰነድ የሚያቀነባብር ቡድን መቋቋሙ ትልቅ ሂደት መሆኑን ልገልጽ እፈልጋለሁ። 

10 በሜድያም በኩል ያለውን ልዩነት ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። 

  1. የፋኖ መሪዎችን ለማነጋገር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። 

ከላይ እንደ ገለጽኩት፤ በሁሉም ዘርፍ የተጀመረው የምክክር ሂደት ያስፈልጋል የሚለው ሃሳብ ደጋፊዎችን እያገኘ መሆኑ ተስፋ የሰጣል።  

  • በኔም ሆነ ሌሎች ተቆርቋሪዎች እምነት የተለያዩ ልምዶች፤ ሟያዎች፤  ባህሪዎችና ዝንባሌዎች ቢኖሩንም በአማራ ፋኖ የህልውና ትግል ያለን አቋም ተመሳሳይ ነው። በጋራ የምንጋራቸው፤ ሁላችንም የሚያስተሳስሩን መሰረታዊ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል የአማራው ህልውና ካልተከበረ የኢትዮጵያም ሊከበር አይችልም የሚለው ዋናው ነው። 
  • ሁላችንንም በጋራ አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ እንረባረብ።
  • የችግሩን ጥልቀትና ስፋት መጋራት ግድ ይላል። የአማራ ሕዝብ ዘመን ባላፈ ቁጥር እየከፋ የሄደ ዘርፈ-ብዙ የህልወና አደጋ ውስጥ እየወደቀ መሆኑን ማለቴ ነው።

 

  • በተለይ ባላፉት 6 አመታት ብቻ የአብይ አህመድ አረሚናዊ አገዛዝ በሃገሪቱ ላይ የበላይነት ከተቀዳጀበት ወቅት ጀመሮ ይህ የህልወና አደጋ እየከፋ መጥቷል። ማስረጃውን ሁላችሁም ስለምታውቁት መዘርዘር አያስፈልግም።
  • ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ብቻ የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራውን ህዝብ የበለጠ አደጋ ውስጥ የሚጨምር፤ ለከፋ የህልውና አደጋ የሚዳርገው ትጥቁን የማስፈታት እርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ አስተላላፎ ከተንቀሳቀሰበት ወቅት ጀመሮ የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት እርምጃ የታወጀበት ሕዝብ ሆኗል።
  • የአማራን ህዝብ በጠላትነት የሚያዩ አካላት እስከጥርሳቸው ታጥቀው በሚገኙበት ወቅት አማራን ብቻ ለይቶ ትጥቅ ለማሰፈታት የተደረገው ሙከራ የአገዛዙን የአንድ የዘውግ ልሂቃን የበላይነት  አላማ ለመላው የአማራ ህዝብ ገሃድ ያደረገው ሆኗል። ይህ አደጋ ሌላውንም ሕዝብ፤ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ይመለከታል። 
  • የአማራው ህዝብ፣ ይህ የአብይ አህመድ አገዛዝ ሴራና ተንኮል ስለገባው፣ ትጥቄን አልፈታም በማለት ህልውናውን በክንዱ ለማስከበር ተንቀስቃሷል። 
  • ሕዝቡ ችግሩ ስርአታዊና መዋቅራዊ መሆኑ ገብቶታል ማለት ነው። ይህንን ሁላችንም የመጋራት ግዴታ አለብን። 

 ይህ ህዝባዊ አመጽ ነው ዛሬ ፋኖ የሚባለውን እንቅስቃሴ የፈጠረው። እንቅስቃሴው ሕዝባዊ መሆኑን ያሳያል። 

  • ይህ ኣመጽ ድንበር የለውም፤ ግለሰባዊ አይደለም። ከየአንዳንዱ አማራ ህልወና ጋር የተያያዘ ምክንያት ስላለው ህዝቡ ቀስቃሸ፣ አደራጅ ሳይፈልግ ሁሉም በየሰፈሩ ጎበዝ አለቃ ተጠራርቶ የጀመረው አመጽ ነው።
  • በአንድ ጊዜ የአማራን ክልል አጥለቅሎቆ የአብይን አገዛዝ ያመከነ፤ ግዙፍ እንቅስቅሴ ለመሆን በቅቷል። እመርታዊ እንቅስቃሴ መሆኑን የዓለም ሕዝብ ተቀብሎታል። 
  • የዛሬ አመት በዚህ መልኩ የጀመረውን ህዝባዊ አመጽ ባህሪ እንደያዘ ቢቅጥል ኖሮ ዛሬ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ምድርም ቢሆን የአብይ አገዛዝ አይኖርም ነበር። አሁንም ይቻላል። 
  • ይህ ወደ ዋናው ጥያቄየ ይወስደኛል። 

 

ይህ የህዝብ አመጽ እንደጀመረው እያደገና እየጎለበተ ሄዶ የአማራውን ምድር ነጻ አውጥቶ አብይን ከአራት ኪሎ ያላባረረው ለምንድን ነው?

 

የአማራን ህዝብ ሰቆቃ ባጭር እንዲቀጭ ያላደረገው ለሚለው ጥያቄ በርካታ መልሶች መቅረብ የሚቻል ቢሆንም ተቆርቋሪዎችን፤ የአማራ ፋኖ ደጋፊዎችንና ወዳጆችን የሚያስማማን አንድ ጉዳይ አለ። ይኼውም ከታች ወደላይ የሆነ፤ ሁሉን አማራ አቀፍ ተቋምና አመራር አለመመስረቱ ነው የሚል ግንዛቤ አለን።  

 

በሌላ አነጋገር ሕዝባዊ እንቅስቃሴው በሚገባ አቅሙን አስተባብሮና አቅዶ ለትልልቅ ድሎች ሊያበቃው የሚችል አማራውን ሁሉ የሚወክል፤ አሰባሳቢ ተቋም፤ ድርጅት እና አመራር በማጣቱ ነው የሚል ክፍተት አለ። ይህ ክፍተት ባስቸኳይ መፍትሄ ማግኘት አለበት። ነው። 

 

  • በአማራው ክልል በተለያዩ ደረጃዎች ተበጣጥሶ የተደራጀውን ወታደራዊ ሃይል የሚያስተባብር ሃይሉን አቀናጅቶ ጠላቶቹን መደምሰስ የሚችል የጋራ ወታደራዊ ኮማንድ መፍጠር አለመቻሉ ክፍተት ሆኗል። ይህ ነው የአገዛዙን እድሜ ያራዘመው፤ የአማራውን ግፍ፤ በደልና ሰቆቃ ያባባሰው።
  • ይህ ክፍተት በአስቸኳይ መፍትሄ መግኘት አለበት። 

ይህ የጋራ ወታደራዊ ኮማንድ ቢመሰረት ኖሮ ትግሉ የሚመራባቸው የተለያዩ እሳቤዎችን መልክ የሚያስይዝ የፖለቲካ አካል አስፈላጊነት ውሎ ሳያድር መከሰቱ የማይቀር ይሆን ነበር። 

 

ችግሩ አማራጭ ሞዴሎች አለመኖራቸው አይደለም። አሉ። ችግሩ የፖለቲካ ፈቃደኛነት አለመኖሩና ከየአቅጣጫው የሚመጣው ጫና ግፊት ከፍተኛ መሆኑ ነው። 

 

ይህንን የጋራ ወታደራዊ አመራር አስፈላጊነት ሁሉም በየፊናው ተረድቶ ጋንታዎች ወደ መቶ፣ መቶዎች ወደ ሻለቃ፣ ሻለቆች ወደ ክፍለጦሮች ክፍለጦሮች፤ ክፈለጦሮች ወደ እዞች ያደጉበት ተስፋ የሚሰጥ ሁኔታ ተፈጠሯል። ይህንን የጀመሩትን አመሰግናለሁ፤ ሌሎቹም ይህን ሂደት እንዲያስተናግዱ ወንድማዊ ምክር እለግሳለሁ። 

 

በአራቱ የአማራ ቀጠናዎች ውስጥ የተደረገ ጥረት መልካም ነው ቢባልም፣ አሁንም ቢሆን በአንድ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ የታጠቁ አካላትን በሙሉ በአንድ የቀጠና እዝ ስራ ያለምንም እንከን ሙሉ በሙሉ ያሰባሰበ ቀጠና ማግኘት መቻል አለበት፤ እስካሁን አልተቻለም። ይህ ክፍተት ትግሉን ጎድቶናል። 

የአማራው ሕዝብም ተስፋ እንዳይቆርጥ ስጋት አለኝ። 

 

አንዳንዶቹ ቀጠናዎች ከሞላ ጎደል አብዛኛውን ተዋጊ ያቀፈ የቀጠና እዝ የመሰረቱ ሲሆን፣ በሌሎች ቀጠናዎች በሁለት እዝ ተከፋፍለው መደራጀት ብቻ ሳይሆን፣ እዞቹ ፍጥጫ ውስጥ የገቡበት ወደ ግጭትም ያመሩበት ሁኔታ እየታየ ነው። 

 

ይህ የአማራውን ትግል በክሎታል። አማራው በአማራው ላይ የሚያካሂደው ጫና፤ አፈናና ዘለፋ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ እየፈጠረ ነው። ባስቸኳይ መታረም አለበት የሚል እምነት አለኝ፤ አለን።

 

  • ምን ይደረግ ብለን ስንጠይቅ፤ የአማራን ህዝብ ወደ ድል የሚወስደው አንድ አማራ አቀፍ ተቋማዊ፤  ወታደራዊና ዲፕሎማሳዊና ፖለቲካዊ አደረጃጀት መቀየስና አደረጃጀት መመስረት ወሳኝ መሆኑ የአማራ ህዝብ መርህ፤ ፍላጎትና አላማ መሆኑ ግልጽ ነው። 

 

  • የአማራ ፋኖ ትግል ግን ይህንን ሂደት  በሚያስችል ቁመና ላይ አለመድረሱ አሳሳቢ ነው። 
  • የታወቁት ሳይንቲስት አልበርት አይንስታይን ያሉትን ልጥቀስ። 

 “አንድን ችግር ለመፍታት የሚቻለው መጀመሪያ ችግሩ ምን እንደሆነ በማያሻማ ደረጃ ማስቀመጥ ነው” ያሉት ትክክል ነው።  ችግሩን በሚገባ ሁላችንም መጋራትና ማስተጋባት አለብን የሚል ምክር አቀርባለሁ። 

 

  • መቀበል ያለብን፤ የቀጠናዎችም ሆኑ የአማራ አጠቃላይ የአመራር ፈጠራ ሂደት ትልቅ ችግር ተጣናውቶታል። 
  • ይህ ችግር ባፋጣኝ ካልተቃለለ የሚፈጠረው ውስጣዊ ቅራኔ የአማራን ህዝብ ቅስም የሚሰብር እና ጠላቶቹን የሚያስፈነድቅ እንደሆነ ግልጽ ነው። በሰሞኑ ቀውስ እያየነው ያለው ሃቅ ይህንን ነው።
  • ሁላችንም በየፊናቸን ይህንን አይነት የጋራ አመራር እንዲፈጠር ሰንድ ስናቀርብ፣ በሰልክ መሪዎችን ስናነጋግር፣ በምንችለው መንገድ በገንዘብ በቁሳቁስ ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል። 
  • በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአማራ ፋኖ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገናል፤ አድርጋችኋል። አሁንም፤ ወደፊትም እንቀጥል፤ አናመናታ የሚል ምክር አቀርባለሁ። 

4

  • በኔ እምነት ለእልቂት የተዳረገው የአማራ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ ከመታገል፤ የራሱን ህልውና ከመታደግና ዘግናኙን ስርአት ከመገርሰስ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።  

 

  • በመጨረሻ፤ ከችግሩ ከፍተኛነት አንጻር ስገመግመው የምንጽፈው፤ የምንነናገረው፤ የምንወያየውና  የምንመካከረው መፍትሄ ለመፈለግ ብቻ መሆን አለበት። ትችቱን፤ መወቃቀሱን ወዘተ ባስቸኳይ እናቁም። እስካሁን ጥረታችን በየግላችን፤  በምንቀርባቸው የፋኖ ቡድኖች አማካይነት፤ ሳንናነብ ያደረግናቸው መሆኑና የፋኖ ቡድኖችም መሬት ላይ በቡድን አኳያ የሚፈልጉተን ብቻ ፈጻሚ እንድንሆንላቸው ሲያሳድሩብን በነበረው ተጸእኖ የተነሳ ሁላችንም ተሰባስበን ይህ የአማራ የአመራር ፈጠራና ምስረታ ሂደት ችግሮቹ ምንድን ናቸው? እንዴት ሊቃለሉ ይችላሉ የሚሉትን ህሳቤ በማድረግ መፍትሄዎችን እንለግስ።  

 

የአማራ ፋኖ ፍትሃዊ ትግል ስኬታማ ይሆናል!!

August 8, 2024 

192994
Previous Story

በጎጃም ተሽከርካሪዎች ታገዱ | የባህርዳር ኦፕሬሽን – “ስልጣኑን ውሰዱ” ስልጣን ለመልቀቅ የጠየቁ 4 ባለስልጣናት| ሃላፊው ተሸኘ | ጄ/ሉ መርዶ ላኩ “ዋና ዋና መስመሮች በፋኖ ተይዘዋል”|

193026
Next Story

የመጨረሻው ዘመቻ ታወጀ ጎጃም ወሎ ትዕዛዝ ተሰጠ አሁን የደረሱን መረጃዎች Vዘመነ በመላው ጎጃም አወጀ – የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ተመረዙ |ኮ/ር አሰግድ እና ኮ/ል ጌታሁን አሳዛኝ ነገር ተሰማ|

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

193911

”በቅርቡ ትልቅ የድል ዜና ይኖረናል።” አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

Anchor Media ”በቅርቡ ትልቅ የድል ዜና ይኖረናል።” አርበኛ አስረስ
aklog birara 1

ሁሉም ነገር ወደ አፋር ግንባር!! ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ ህወሓትን መደምሰስ ያስፈልጋል – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

አክሎግ ቢራራ (ዶር) “ኢትዮጵያን ማንም አይረዳትም። ብቻዋን ናት። ሞሰለኒን ሃሳቡን እንደገና እንዲያይ የሩሲያ የማስፈራሪያ ቃል እንኳ አላቆመውም። ምን ያድርግ? ፈረንሳዮችና እንግሊዞች አይዞህ፤ ከእግዚአብሄር የተሰጠህ ቅዱስ መብትህ ነው ብለውታል። አሜሪካ እንኳ ሳትቀር በተዘዋዋሪ ደግፋዋለች። አርፈሽ ተቀመጭ፤ ይኼ ነጻነት፤ ነጻነት የምትይው ትግልና መፈራገጥ ለመላላጥ ነው ብላታለች።