የኢትዮጵያ ዲሽቃ የህዝቧ አንድነት ነው – ተነሣ ተራመድ!!! – ከአባዊርቱ

kejela
kejela

ይድረስ ለ አቶ ቀጄላ መርዳሳና ኢብሣ ነገዎ – መርጋን ሃርካፉኔራ!!

በቅርብ በአርትስ ቲቪ መስኮት ውይይታችሁን ተከታትዬ ነበር። ሁሌም ውስጤን ያቃጥለኝ የነበረው እንዴት ልጆቻችን ማሰቢያው ተሳናቸው እያልኩም እበግን ነበር። የአቶ ዳውድን ጉድ ይህን ሁሉ አመታት ተሸክማችሁ ምንም ሳተነፍሱ እስካሁን በመቆየታችሁ ከተጠያቂነት ባያስመልጣችሁም (በተለይም ለድርጅቱ ህልውና ብላችሁ በመሆኑ) የውይይታችሁን ጨብጥ ስረዳ ደግሞ አስደምሞኛል።
ወንድሞቼ!
ለመሆኑ ለኦሮሞ ሆነ ኢትዮጵያ ከአቢይ የተሻለ ማን ይምጣ? ይኸው ለ3 አመታት ሳላቋርጥ የምናገረውን ሀቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ስር ነቀል የሆነ ምርጫ አድርጎ አቢይን መርጧል:: ፅንፈኛ አማሮች አቢይን ሲያብጠለጥሉ አርቆ አሳቢው የአማራ ህዝብ ግን  አቢይን መርጧል:: ፅንፈኛ ኦሮሞዎች ኦሮሞነቱን በማሳነስ አሀዳዊ አቀንቃኝ አድርገው፣ እበት ቀባብተው  ከህዝብ ለመለየት ቢፈልጉም፣  ኦሮሞ አቢይ ይሻለኛል ብሎ መርጧል:: አሁን ውጤቱን አክብሮ ትግሉን ወደልማትና ሰላም መለወጥ ነው::በተለይ ያስደሰታችሁኝ የወያኔ ጭምብል ፌዴራሌ ሎሌ አንሆንም ብላችሁ ከነሱ ሴራ መራቃችሁ በዖሮሞነቴና ኢትዮጵያዊነቴ እጅግ አኩርቶኛል። ይበል አሁንም። አሁን እኔ እናንተን ብሆን በአስቸኳይ ይህን ለዖሮሞ ወገናችን የማይመጥነውን የነፃ አውጭ ስም ከ ኦቦ ዳውድ ጋር ወደ ሙዚየም ልካችሁ በሪጅናል ኦቶኖሚ የጠነከረ በሂደት ለምንመሰርታት እውነተኛው ፌዴራል የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት የበኩላችሁን ጥረት ለዖሮሞ መብትና ግዴታ እንዲሁም ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ታገሉ። የናንተ ጊዜም ስላበቃ አዲሱን ወጣት በዚህ ሃቀኛ የዴሞክራሲ መንገድ ለማጥመቅ በ ካውንስሊንግ እውቀታችሁንና ክህሎታችሁን ብታሳዩና ወደ አመራር ብታመጡ በትንሹም ቢሆን ስለ ባለፈው ስህተት ፈጣሪ ይቅር ይላችሁዋል። ሜ ሲሪቲ ኢቲያዳ ለሚዋን ቶ። ይብቃ ውርደቱ፣ ይብቃ ወያኔን ከመሰሉ የፅልመት ውላጆች አንጋች መሆኑ። የመረራና ዳውድ ወያኔ ላይ እንዲህ ጥብቅ ማለትን በሳቅ በፈገግታ ማለፍ እንዴት ይቻላል ወንድም ኢብሣ? እንዲህ ሲያዋርዱን የብዙሃኑ ዝምታ ያስቆጫል። የዖሮሞ ህዝብ ከትግል ጓድነት በላይ ነው። ጥልቅ ውግዘትና በሚዲያው እንዲህ እየተመላለሳችሁ አስተምሩ ወገኖቻችንን። በተለይ ሁለታችሁ  እንዲህ አይነት መልካም አንደበት ይዛችሁ ምነው ዘገያችሁ? መልካም ጅማሬ ስለሆነ ደጋግማችሁ አስረዱ እባካችሁ። ታሪካችን በከሀድያን በጣም ተዛብቷልና።
ይድረስ ለ 360 ቱልቱላ ተመልካቾች !
የዚህን ጣቢያ አቅራቢዎች ክብር ሰጥቼ በስም አልጠራም፣ ሆኖም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የነሱን ቱልቱላ የሚከታተሉትን ይመለከታል። መቼስ ሴራቸውን ካለመረዳት ካልሆነ በቀር ሳስበው ኢትዮጵያዊ የሆነ ሳይሆን ፣ የፅልመት ወዳጅ መሆን አለበት እነዚህን እርባናቢሶች አድማጭ ወገን። በተለይ መከላከያውና ኢትዮጵያ ላይ የሚያሳርፉትን የንቀትና ጥላቻ መልእክት ሳስበው ልቤ ይሰበራል። አንድ ነገር ግን ተገንዝቤአለሁ። የሀብታሙ አያሌውና ኤርምያስ ለገሰ አይነት ውታፎች እንዲህ ለይቶላቸው ለጁንታው እዬዬ ሲሉ በሸገርና በሌሎችም ከተሞች የተጀመረው የፅዳትና ማ ማንን እየወጋ ምንጠራ  ዘመቻ በጥልቀት እንዲስፋፋ ከልብ እማፀናለሁ። ዛሬ ሃርመኒ ሆቴልና ካሌብ ታሽገዋል፣ ነገ ደግሞ የነ ሀብታሙ አያሌው፣ ይባስና ያቺ ሴትዮ የፅልመት መስኮት የሚዘጋበትን እያንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መተባበር የግድ ይላል ። በምርጫና ድል ማግስት ዛሬም እንደ ትላንቱ የነዚህ ጉዶች ቲፎዞዎች እመሃላችን ሆነው ይዘፍኑብናል? ሞተን ካልሆነ በቀር። እያንዳንድሽ የወያኔ አሽቃባጭ የሆንሽ አማራ ሁን ዖሮሞ፣ ጋምቤላ ሁን ጉራጌ ቀናችሁን ጠብቁ። በዚህ አጋጣሚ የሳተናዋ አዳነች አቤቤ አጀማመር አስደምሞኛል። ወደሁዋላ የለም። በነካ እጃችሁ ሁሉም ቤት ግቡ። በሰማይ (አየር) መንገድም፣ በቴሌም፣ በመብራትም ብዙ ጉዳጉድ አለ ይባላል። ከዚህ ቀደም አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቀሷት ሸረሪት ገና አልተያዘችም። ምናልባት ድሯን በጣጥሰን ይሆናል እንጅ
ውድ ወገኖች!
የወያኔ እምባጠባቂ አማሮች፣ ዖሮሞዎች አሁንም በመሃላችን ብዙ አሉ። ለዚህም ነው አላማጣና ኮረምን ጁንታ ለብሪፍ ሲጎበኛት “አለቀልን፣ አቢይ አማራን ከዳ” እያሉ በወሬ ሊያሽመደምዱንና ዳግም ሊለያዩን ሌት ተቀን የሚዳክሩት። እምቢ በል ወገን! መከላከያችን በስንቱ ይከዳ? በጁንታም በራሱም ወገን? በ ሶስት ሳምንታት የነቡከደነፆርን የፅልመት ሰራዊት ድባቅ የመታ መከላከያ ፈረንጆች እንደሚሉት ሌላው ቢቀር benefit of the doubt ማንን ገደለ? በአንዲት ጀምበር እንደምን ጁንታ በቀደደልን ዋሻ እንገባለን?  እየተስተዋለ ለማለት ነው።
ኢትዮጵያ እትሸነፍም!
የአሜሪካና ምእራብያውያን አላማ ግልፅ ነው። አንበርክከውን ሎሌያቸው አድርገውን የነሱን ጥቅምና ጉዳይ አስፈፃሚ የማድረግ ዘመቻ ነው። አቢይ አህመድና ከሱጋ ያሉ የኢትዮጵያ ልጆች ግን አልተመቹም። በተለይ ፈጣሪውንና የቅድመአያቶቹን ወኔ ያነገበው አቢይ አልተመቻቸውም። ሊመቻቸውም አይቻለውም። ለምን? ውስጡና ውጭው በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ያጠነጠነ በመሆኑ። ጥቅም የማይገዛው ከጄልቱ ባለመሆኑ። ይህው ነው። ሌላ ምንም አይደለም። ያላወቁትና ምናልባትም ልባቸው እያወቀ በሀፍረት ሊቀበሉት ያልቻሉት በአቢይ ስር ኢትዮጵያ እንደማትንበረከክ ነው። እንዴት?
፩) አቢይ አህመድ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ገበታ ለመሰብሰብ ክህሎት ብቻ ሳይሆን የፈጣሪም ፀጋ አግኝቷል። ይህን የሚጠራጠር የጁንታ ጅብ መንጋና ኮልኮሌ ቀበሮዎችና ተኩላዎች ብቻ ናቸው።
፪) ሃያሏ አሜሪካም ሆነች ምእራብ አውሮፓ አፋቸውን የምናዘጋበት ትልቁ መሳርያችን አንድነታችን በመሆኑ ኢትዮጵያ አትንበረከክም። በጭራሽ!!  ተመልከቱ የዖሮምያ፣ ሱማሌና፣ ደቡብ ልዩ ሀይላት ዘመቻ ወደ አማራው ግዛት ። ይህ አይደለም የተኮላሸ ጁንታን ቀርቶ አለቆቹን እነ አሜሪካንን የሚያስደነግጥ ክስተት ነው። ይህ ነው መሳርያችንም። ወጥር ያገሬ ልጅ!!!!
፫) የኢትዮጵያ ልጆች መናገር ጀምረዋል። በውጭው የተወለዱት ልጆቻችን መቆጨትና መብገን ጀምረዋል። በዩቱብና ትዊተር ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ኢትዮጵያ የማትሸነፍ ፈጣሪዋን ያነገበች ሀያል አገር ናት። አትሸወዱ። ሀያልነቷ ከፈጣሪ ቁርኝቷ ነው። ዬት ፈረንጅ አገር አይታችሁዋል ሌትና ቀን ከፈጣሪው ሲነጋገር የሚውልና የሚያድር ክርስትያን ይሁን ሙስሊም ያለበት ሀገር? በምናብ አስቡና ሀያልነታችንን ትረዱታላችሁ።
እነዚህ ሶስቱ ብቻ አሜሪካንን የጠራ አቋም እንኳ እንዳታሳይ አድርጎ የቅሌት እብደት ውስጥ ናት። ፖሊሲ አይሉት በግልፅ የወያኔ አቡካቶ ሆና እየተወራጨች ያለው ይህው የኢትዮጵያ ሀገረ አንድነት በአቢቹ ስር አስፈርቷት ነው። በአፍጋኒስታን፣ ሶማልያና ሌሎችም እንደተዋረደችው በኛም ሀገር ውርደቷን ተከናንባ ዝም ትላለች። ግፋ ቢል እስከሃምሌና ነሀሴ መጨረሻ የመወራጨት መብቷን እናከብራለን። ከአባይ ሙሌት በሁዋላ ሁሉ ይሰክናል።
ማሳሰቢያ ለተቃዋሚዎች!
ምንድነው ዝምታው? በቃ ተሸነፋችሁ ማለት ኢትዮጵያን አባንደን ማድረግ ነው? ለምን በህብረት የመከላከያ ደጀንነታችሁን አታሰሙንም? ልወቅሳችሁ ሳይሆን ህብረታችንን ሁሉም ይጠብቃልና ነው። እነ አሜሪካንን አፍ የሚያዘጋም ነውና። ተቃዋሚ የምለው ጭምብል የትራንዚሺን መንግስት ተብዬ ፌዴራሌዎችን አይደለም። የለየላቸው ህዝብና መንግስት በፓርላማ ሽብርተኛ ብሎ ከፈረጃቸው ጉያ ሊሸጎጡ እያኮበኮቡ ያሉትን ማፈርያ ትክል ፌዴራሌዎችን አይመለከትም። እንደውም ለሀገር ደህንነት ሲባል መቀፍደድ አለባቸው ባይ ነኝ። ማንም ሀገር ይህን አይፈቅድም። በኛ ሁሉም መሞከሪያ መሆኑ ያሳዝናል።
ማጠቃለያ!
ወገኖች ያለን መሳርያ አንድነታችን ስለሆነ ይህን በጥብቅ እንግፋበት።  እናጠናክረውም። እንዴት?
፩) ኢትዮጵያዊ የሆነ የሚዲያ ሰው በየቀኑ የአንድነትና የተነሣ ተራመድ ጥሪ ያቅርብ። ውይይትም ይጧጧፍ በዚህ ጉዳይ
፪) መንግስት የባንዲራችንን ጉዳይ በአስቸኳይ ያስተካክል። ምንም ህዝብን ጥያቄም አያስፈልግም። የወያኔን ጨረቃ ከመሃል ቦድሶ አውጥቶ በልሙጧ የአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ይመልስልን በሁሉም ሀገር። አይምሰላችሁ፣ ወጣቱ ተወናብዶና ተሳክሮበት እንጅ ከግብፅ አይሉት አፍጋኒ ባንዲራ ፍቅር ኖሮት አይደለም። የአማራውም ክልል ቢሆን እንዴት የወያኔ ትክል ባንዲራ ይዞ ወያኔ ላይ ይዘምታል? ለውጡት በኢትዮጵያ አምላክ። ሰይጣናቸው እንዲህ በቀላሉ ያልተላቀቀንም አንዱ ምክንያት ይህም ይሆናል። አፈሯንና አመዳቸውን  በደንብ የሚልሱት ልሙጡ ባንዲራ በኢትዮጵያ ምድር በደንብ ሲናኝ ነው።
፫) ምሁራን፣ አገር ወዳዶች በግልፅና በዘመቻ መልክ ለመከላከያውና እናት አገር የማቴርያል ማሰባሰብ ዘመቻ ይጀመር። ታማኝን የመሰለ የኢትዮጵያ ልጅ ፣ ልምዱም ስላለህ በየኢትዮጵያ ሚዲያ እየቀረብክ አስተባብርልን። ብዙዎች የምንከተልህ አለን። አይዞህ ታማኝ። ብዙ ዋጋ ከፍለሀል ፣ ይረዳኛልም። ያሁኑ ወያኔን ከመቃብር እንዳያመልጡ አፈር የመመለሻ ዘመቻ ስለሆነ የሁሉም ተሳትፎ የግድ ነው።
፬) ጦርነቱ ከአገርና ባእዳን ጁንታዎች ጋር ነው። እነ አድሃኖም በአለም መድረክ ከለላ ሲወጉን እነ ሊንዳ ቶማስ ደግሞ በአምቻና ጋብቻ ከጁንታው የተቀላቀሉ ለመሆናቸው “ሀሜት” አለ። ሌላስ ምን ይሆናል ለነገሩ ሴትዮዋን በቅርበት የወያኔ አፈቀላጤነቷን  ለተከታተለ። ለዚህም ነው አንድነታችን ወሳኝ የሚሆነው!!
ፈጣሪ ስቃያችንን አይቶ እነዚህን የኢትዮጵያ ጠላቶችን ወደ አፈር ይመልስልን።
አንድነታችን ዋናው መሳርያችን ስለሆነ ወጥር በየአቅጣጫው ወገን!!!!
ተጨማሪ ያንብቡ:   የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽኝ መፍረስ የለበትም! - ገለታው ዘለቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share