October 26, 2018
11 mins read

ለመሆኑ መስዋእትነት ከፈሎ ለውጡን ማን አመጣው ? ግቡስ ምን ነበር ?

ወደኋላ ብዙ ርቀት ሳልጓዝ ህወኃት በትረ ስልጣኑን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን መልስ ብለን ብንቃኝ ከሽግግር መንግሥት ምስረታው ፣ ህገመንግሥት አወጣጥና አጸዳደቅ ከዚያም እስከ ምርጫ 1997 (2005) በነበረው ጊዜ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰትና ሀገር የማፍረስ ተግባርን ሲቃወሙ የወደቁ የታሰሩና የተሰደዱ ጀግኖች አሁን ለምናየው ለውጥ ያበረከቱት ምንም አስተዋጽዖ አልነበረምን ???

ከምርጫ 1997 በኋላ ድምጻችንን አናሰርቅም ብለው ሰልፍ ወጥተው ያለቁት አዲስ አበቤዎች የከፈሉት ክቡር ህይወት ለፍትህ ፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት አልነበረምወይ ? ከሆነስ ሕዝባችን ከፍርሃት ቆፈን ተላቆ ለመብቱ እንዲቆም ፈር ቀዳጅነቱ እንዴትስ ይዘነጋል ? የቅንጅት አመራር አባላትና ደጋፊዎች ፤ የነጻው ፕሬስ አባላት ፣ የሌሎች የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አመራሮችና የወያኔን ስርአት የተቹ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችና ሕዝባችን አይቀጡ ቅጣት የተቀጡት ይህ ለውጥ እንዲመጣ ካልሆነ ለምን ነበር? ለሶስት ዓመት ያለማቋረጥ የተካሄደው የመብታችን ይከበር የሙስሊሙ ንቅናቄና የአመራሮቹ መሰቃየት ለዚህ ለውጥ ካልሆነ ለምን ሊሆን ይችላል ? እንዲህ እያሉ ብዙ ማተት ይቻላል ፡፡

ይህንን ሁሉ ለመዘርዘር የተገደድኩት ክብር ለሚገባው ሁሉ እኩል ክብር መስጠት ስለሚገባን ለማስገንዘብ ከመነጨ ፍላጎት ነው፡፡ መነሻ የሆነኝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ የብዙ አዛውንቶችን ፣ አረጋውያንና የህጻናትን ህይወት ጭምር ያልቀጠፈ ይመስል በትግሉ ውስጥ ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸውን ይባስ ብሎ በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ሲገሉና ሲያስገድሉ የነበሩትን ሁሉ አካቶ በወል መጠሪያ ወጣቱን በሙሉ ስርአተ አልበኛውን ጨምሮ የለውጥ ሃዋሪያ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለማስፈራሪያነት ጭምር ሲጠቀሙት በማየቴ ነው፡፡ ለለውጡ ወጣቱ የከፈለው ከፊተኛ መስዋእትነት ጠፍቶኝ ሳይሆን በኦሮሚያ ክልል የራሱ የታጠቅ ሰራዊት ያለው የክልሉ መንግሥት ያስታጠቃቸውን ሚሊሺያ ትጥቅ አስፈትቶ አካባቢውን የሚያተረማምስ ከሕዝብ ማንንም ሳያስፈቅድ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችል የኦቦ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ አባላትም ውስጥ ወጣቶች(ቄሮዎች) እንዳሉ ግልጽ ነው ፤ ሌላው ደግሞ በሀራሪ ክልል ሕዝቡን ውኃ እንዳያገኝ በማድረግና የቆሻሻ መጣያ በመከልከል ግብር ሰብስቦ ለወጣቱ የስራ መስክ ለመክፈትነው እያለ የሚያሾፍ የስርአተ አልበኞች ቡድንም ከዚህ በጅምላ በሚወደሰው የእድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም ጅምላ ፍረጃና ጅምላ ውደሳ ሁለቱም አግባብ አይደሉም ለማለት ነው፡፡

ሕወኃት የሚባለው ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቡድን አቅዶና አልሞ ለውጭ ጠላት አይበገሬ የሆነውን ጀግናውን ህዝባችንን በጎጥ ከፋፍለውና አዳክመው ለመግዛት በትረ ስልጣን ከመቅናጠጣቸው በፊትም ፣ ስልጣን እንደ ጨበጡና እስካሁንም ድረስ ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፍለ የሚታገላቸው ዜጋ ለምን ነበር ? በትግሉ ያለፉትም ሆነ አሁን በመታገል ላይ ያለው ሕዝብ ያመጣው ለውጥ ነገር ግን ከእህአዴግ በወጡ ተራማጅ ኃይሎች እየተመራ ያለው የስልጣን ጥም ያናወዛቸውን ግለሰቦችንም ሆነ ቡድኖችን ለማንግስ ወይንም ዜጎቻችንን በገዛ አገራቸው ባእድ በሚያደርግ የዘር ፖሌትካ እንዲለያዩ ሳይሆን ሕዝቡ የስልጣን ምንጭ ሆኖ ዲሞክራሲያዊ ስርአት የሰፈነባት አንዲት ኢትዮጵያን ለመገንባት ነው፡፡ ስለሆነም አሁን በተግባር እያየን ያለውን በወጣቱ ስም የሚካሄደውን ውብድና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአጠቃላይና በስሙ የሚነገድበት ወጣቱ ትውልድ ሊታገለውና ሊያስወግደው ይገባል፡፡

በአንድ አገር ውስጥ በአንድ ጊዜ የተለያዩ መንግሥታት ሊኖሩ አይችሉም ፡የጸጥታ አስከባሪ ሃይላትም ከሆኑ በፌደራል መንግሥት ወይንም በየክልሉ መንግሥት ቁጥጥር ስር ሆነው የዜጋውን ደህንነትና ንብረት የሚጠብቁ እንጂ ማንም ህገወጥ እያስታጠቀ ሕዝብን ማሸበሪያ አይደለም ፡፡መንግሥትም ቢሆን ህገመንግሥታዊ ሀላፍነቱን የመወጣት ጊዴታ ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ታጥቀው ሕዝብን የሚያሸብሩ የኦነግ ታጣቂዎች በአስቸኳይ ትጥቅ መፍታት አለባቸው የኦነግ አመራሮችም ከሆኑ በሰላም ለመታገል ፈቅደው ከገቡ በኋላ ፕሮግራማቸውን ለሕዝብ አቅርበው ተቀባይነት ካገኙ ወደ ስልጣን መጥተው ሀገር መምራትና ሕዝብ ማስተዳደር ሲችሉ ነባራዊ ሁኔታው ከፕሮግራማቸው ጋር የማይጣጣም በመሰላቸው ቁጥር ሁሉ ከእንቅልፍ እየባነኑ ሽፍታ ይመስል ጠብመንጃ ለመዳበስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ስልጡን አካሄድ አይደለምና ሕዝብ እንዲመርጣቸው ከፈለጉ ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን ቢዘጋጁ መልካም ነው፡፡

በሌላ በኩል ለውጡ ስር ነቀል ሳይሆን ከስርአቱ በወጡ ተራማጅ ሀይሎች የሚመራ አዝጋሚ በመሆኑ ለውጡን የማይፈልጉ ነገር ግን ስልጣን ላይ ያሉ የያዙት ቦታና ያካበቱት ገንዝብ የሚሰጣቸውን ጉልበት በመጠቀም ከኋላ ሆነው ወጣቱን በመጠቀም ነውጥ ፈጣሪዎች በየቦታው ችግር እየፈጠሩ ያሉበት ወቅት ነው ፡፡ ለዚህ ማሳያው የሐራሪ ክልል የመጠጥ ውኃ ነፋጊና ቆሻሻ መጣያ ከልካዮች ከክልሉ መንግሥት ቁጥጥር በላይ ሆነው አይመስለኝም ሊሆኑም አይችሉም
፡፡

የዶክተር አብይ መንግሥት ፈተናዎች ጥቂትና ቀላልም አይደሉም ፡፡ ኢትዮጵያን በጋራ ትግራይን በግሉ የሚያስተዳድር ከፌደራል መንግሥቱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ የወንጀለኞች ዋሻ የዶክተር ድርብረጽዮን መንግሥትም አለ ፡፡ ይህ ቡድን በሃያ ሰባት ዓአመት በአገራችን ለተከሰቱ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ ሆነው እያሉ ከለውጡ በኋላ የተሰጣቸውን እድል ተጠቅመው ይቅርታ በመጠየቅ የለውጡ አካል መሆን ሲገባቸው ይባስ ብለው ወንጀለኞችን በመደበቅና በመሾም ፣ በአጎራባች ክልሎች ሰላም እንዳይሰፍን ትንኮሳና አሻጥር በማድረግ በተንኮል ተግባር ላይ ተሰማርተው ለውጡን ለማሰናከል ሲባዝኑ ይታያሉ አልፎ ተርፎም በራያ የሚኖሩ ዜጎቻችንን በማን አለብኝንት በመግደልና በማፈናቀል ላይ ይግኛል፡፡ በሀገሪቱ ከዳር እስከ ዳር በነበራቸው መዋቅር ተጠቅመው ሰላም እያደፈረሱ ናቸው ፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት በአጭር ጊዜ ያስመዘገበውን
ለውጥ አድናቂና ደጋፊ ቢሆንም ለውጡ ለመቀጠሉ የሚተማመንበት ማረጋገጫ የለኝም ሹም ሽሩንም ቢሆን ጉልቻ ከመቀያየር በዘለለ ዘራፊዎችን ሙሰኛ እያላችሁ አታሽሞንሙኑ ሌባ ብላችሁ ጥሩ ከመባሉ በቀር ለፍርድ ሲቀርቡ አናይም፡

በጉባኤውም ወቅት ቀይ መስመር አስምረናል ካሉት ውጭ የቱ ጋ እንደተሰመረ እንኳን የምናውቀው ነገር የለም ፡፡ አልፎ አልፎ አይጡን ትተው ዳዋውን ሲደበድቡት እያየን ነው ፡፡ይህም ሆኖ በለውጥ ወቅት ይሚያጋጥም ነው እያልን ራሳችንን ለመሸንገል ብንሞክርም ማብቂያ የለለው ሆነብን ፡፡ ለውጥ የሚያካህድ መንግሥት ሕገመንግስቱ የሰጠውን ኃላፊነት በመጠቀም በመጀመሪያ ራሱን ከዚያም ህብረተሰቡን ከህገወጦች መከላከልና መጠበቅ ካልቻለ እርባና ቢስ መሆኑን ተገንዝቦ የዶክተር አብይ መንግሥት ቀይ መስመር ከማስመር በዘለለ መስራት አለብት፡፡

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop