የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025

Eskinderከቴዎድሮስ ሐይሌ

ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል:: የእያንዳንዱ ዘርፍ አፈጻጸም ትግሉን በድል ለውጤት የማብቃት ወይም ለውድቀት የመዳረግ ተጽዕኖ ይኖረዋል:: ሕዝባዊ ትግል ምንም ያህል በሕዝብ ቢደገፍ በርካታ ታጋዮችንን ቢያሰልፍም በተገቢው መንገድ እስካልተጏዘ ድረስ ከግቡ አይደርስም :: ይህን ለማስረዳት ከሃገራችን ሆነ ከአለም የፖለቲካና የትጥቅ ትግሎች ታሪክ በርካታ ምሳሌዎች መጥቀስ ይቻላል:: ሕዝባዊ ትግል ከግቡ ለማድረስ ድርጅት ሊኖረው ይገባል::

የድርጅት መኖር ያልተዛባ መዋቅር የእዝ ሰንሰለቱ የጠበቀና የተማከለ አሰራርን ለማሳለጥ ተቋማዊ መሆን የግድ የሚል ነው:: በተደራጀ ሁኔታ የሚመራ ትግል ማንኛውንም ተጽዕኖ የመቋቋም አቅም ብቃትና የማሸነፍ ወኔው የተሟላ ይሆናል::

በአንጻሩ መዐከላዊ አመራር የሌለው የተበታተነና በተለያየ ቅራኔ የተተበተበ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ተገን አድርጎ የሚንቀሳቀስ ስብስብ በዲፕሎማሲው አለም ያለው ተቀባይት ቅራኔን ለመፍታት ያለው አቅም እና ትግሉን መርቶ ከዳር ለማድረስ ያለው እድል አነስተኛ ነው:: ሰፊ ሕዝባዊ መሰረት ያለው ትግል መጠነ ሰፊ ውስጣዊና ውጫዊ ቅራኔዎች ሊገጥመው እንደሚችል የሚጠበቅ ነው:: የድርጅት መኖርና ተቋማዊ አደረጃጀቱ የሚፈተነው ይህንን ቅራኔ መቆጣጠርና ድንበሩ እንዳያልፍ አድርጎ ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ መቻል ነው:;

አንድ ወጥ የሆነ ሁሉንም ሃይሎች ያካተተ የፉኖ አደረጃጀትን ለመፍጠር በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል:: የፉኖ አፈጣጠር ከታች ወደ እላይ እየሰፉ የመጣ መደበኛ አደረጃጀት የሌለው ተቋም ነው::ይህ አይነት አደረጃጀት በጣም በጥንቃቄና በማስተዋል ሊያዝ ይገባል:: ፉኖ ከተነሳበት አሃድ ተነስቶ ታላቅ መዐበል ወደሚሆንበት ወታደራዊ መዋቅር ለማሸጋገር የተደረጉት ጥረቶች በከፊል ተሳክቶ በክፍለ ሃገር በዕዝ ደረጃ ማዋቀር ተችሏል:: ከትግሉ ሁኔታ : ከፖለቲካ ግብ : ከወታደራዊ ስምሪት እና ከሎጀስቲክ ማሳለጥ አኳያ ይሄ አደረጃጅት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ ወደ አንድ ወጥ የአማራ ፋኖ ኮማንድ ለማምጣት የተደረገው ጥረት ያልተጠበቀ ቀውስ ፈጥሯል::

ይህንን ቀውስ ለመፍታት ከመነሻው የታየው አክራሪና አንጀኛ አሰላለፍ ሁኔታውን እንደገና ከልሶ ለመመልከት ያለውን እድል አጨንግፎት ቆይቷል:: የጋራ ድርጅት ምስረታው ባይሰምርም የተወሰኑ ሃይሎች የአማራ ሕዝባዊ ድርጅትን መስርተናል የሚል አቋም ወስደው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል:: በድርጅቱ በተካተቱት እና በተለዩት የአንድ እናት ልጆች መካከል የልዩነቱን አድማስ ለማስፉት የደም ነጋዴዎች ተረፈ ብዐዴኖች ምንደኛ ሚድያዎች እና የብልጽግና ቅጥረኞች ታላላቅ ሽብልቆች አኑረዋል:: መሪዎቹ ሃላፊነት የጎደለው ሚና ተጫውተዋል:: የፉኖ ሃይል መሪዎች ጎራ ለይተው በእርስ በእርስ ሽኩቻ ሲቆራቆሱ ሰራዊቱና ሕዝቡ ግን በመስዋዕትነት የታጀበ ፍልሚያውን ለአፍታም አላቆመም:: ዛሬም ፉኖ ጠላቱን በገፍ እየረፈረፈ እየማረከና እየታጠቀ ነው:: በአንጻሩ በመሪዎቹ እንካሰላምታ ደጀኑ ሕዝብ ሞራሉ እየወደቀ መጥቷል:: በዲያስፖራ ያለው ድጋፍ ቆሟል:: በተቃራኒው ከዲያስፖራው የክፍፍል የልዩነትና የክፉት አጀንዳና አሉባልታ በመጠንም በይዘትም ጨምሮ ሕዝባዊ ትግሉን ለአደጋ እያጋለጠ መጥቷል:: በዚህ ሁኔታ ላይ ሌላ ቤንዚን የሚርከከፍበት ትኩስና ጮማ የልዩነት ጦርነት ተከፍቷል::

በአርበኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ከአለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ውይይት ማድረጉ ከባድ አቧራ አስነስቷል::የውይይቱ አላማ ከተገለጸበት መንገድና  ውድ ውጪ ይሄን ያህል ጎራ የለየ የልዩነት ምክንያት ሆኖ መቅረቡ የአማራ ሕዝብ ትግል የመደራጀት ፈተናው ገና አለመጠናቀቁን ይጠቁማል::

አለም ዓቀፍ ድርጅቶች የፉኖን ሁኔታ ተረድተው ለማነጋገር መቻላቸው በእራሱ የትግሉን እድገት የሚያንጸባርቅ ተደርጎ በበጎ ጎኑ በታየ ነበር:: ከዲፕሎማቶቹ የተገናኙት የፉኖ መሪዎች ያደረጉት ውይይት በቀጠናቸው ባሉ ሰብዓዊ ጉዳዬች እና የፉኖ ትግል መንስዔ ምክንያቶችን ከማብራራት የዘለለ ሌላ ጉዳይ በውይይታቸው አለመካተቱን ተናግረዋል:: ይህን ቃል ይዘን ትችትም ተቃውሞም ካለ ማቅረብ ሲገባ የድርጅቱ መሪዎች ያደረጉት ድርድር ነው የፉኖን ትግል አሳልፈው ሊሰጡ ነው ወዘተርፈ አያሌ የልዩነት ምክንያቶችና የሴራ ትንተና ሲሰጥ እያየን ነው::

ድርድር እና ውይይት የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ነው:: በመርሕ ደረጃ በየትኛውም ቀጠና ያለ የፉኖ አደረጃጀት ከአለም ዓቀፍ ተቋማት ይሁን ሚድያዎች ጋር ስለ ትግሉ አላማ ስለሰብዓዊ መብት እና እርዳታን በተመለከተ የመወያየት መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ጭምር ነው:: እንኳን ሜዳው ድረስ ሄደው ሊያናግሩት የፈቀዱ ዲፕሎማቶች ኖረው አይደለም ሲሆን የራሱን የዲፕሎማሲ መዋቅር ሊያሰማራበት የሚገባ አንዱ የትግሉ አካል ነው::

ከዚህም በላይ የፉኖን በአንድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ መምሪያ ስር አዋቅሮ በጋራ ለመቆም ያልቻለ ስብስብ እኔ ከሌለሁ ምንም አይደረግ የማለት ሞራል ሊኖረው አይችልም:; ከነጉድለቱም ቢሆን ድርጅት ፈጥረናል መሰባሰቡን አምነንበታል በሚል በአማራ ፉኖ ሕዝባዊ ድርጅት ውስጥ የታቀፉ ፉኖዎች የአለም አቀፍ ሃይሎችን ትኩረት መሳቡ ሊገርመን ባልተገባ ነበር:: የምዕራቡም ሆነ አህጉራዊ ተቋማት ሚሊዮን ጭፍራ ካስከተለ ሚናውን ካለየ ስብስብ ይልቅ ድርጅታዊ ቅርጽና መዐከላዊ አመራር ካለው ተቋም ጋር መነጋገርን ያስቀድማሉ:: ድርጅት ተቋም ነው:: ተቋም ደግሞ ይነስም ይብዛ መዋቅር አለው:: ለስራም ሆነ ለንግግር የሚመረጥ ነው::

በአንድ የጋራ መዐከላዊ ተቋም መሰባሰብ ያልቻሉ በአራቱም ቀጠና ያሉ የፉኖ አደረጃጀቶች በየምክንያቱ የተጣደፈ እና በአላስፈላጊ ቃላት የተሞላ ሃላፊነት የጎደለው መግለጫ ለማውጣት ከመጣደፍ ይልቅ ግዜ ወስደው በአንድ የጋራ ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ ቢጠቃለሉ ሕዝባዊ ድርጅቱ ትኩረት ባገኘው ልክ ተቀባይነት ይኖራቸዋል:: ይህን ማድረግ ለምን ተሳናቸው? አሁን ባሉበት ክፍለ ሃገራዊ አቋምስ የት ድረስ ይሄዳሉ? በዚህ ሁኔታስ አለማቀፉ ተቋማት ከእነርሱ ጋር በተናጥል ለመገናኘት ፍላጎት ይኖራቸዋል ወይ? ይሄን መመለስ የአደረጃጀቶቹ ድርሻ ነው::

ለብልጽግና ሰርጎ ገቦች ለተረፈ በአዴኖች በፖለቲካ ቅልውጥ ለተሰማሩ አድርባዮች ለጨልምተኛ የሶሻል ሚድያ መንጋዎች ሁኔታው ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸው በሴራ ትንተናና በክፉት ፕሮፓጋንዳ ተጠምደዋል:: የነዚህ ሃይሎች አፍራሽ ሚና የሚጠበቅና ተልዕኳቸውም በመሆኑ አይደንቅም:: የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ይመለከተኛል የሚል ማንኛውም ሃላፊነት የሚሰማው አማራ : የሁኔታውን አካሄድ በስክነትና በጥንቃቄ ሊመለከተው ይገባል:: በፉኖ መሪዎች ላይ የሚሰጠው አስተያየት የፋኖን የአሁን ብቻ ሳይሆን የወደፊት አብሮነቱን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መታየት ይኖርበታል::

በአርበኛ እስክንድር የሚመራው ድርጅት አንዳንድ ቡድኖችና ግለሰቦች በሚያወርዱት ልክ ዝቅ ያለ ሳይሆን በአማራ ትግል ውስጥ ደማቅ አሻራ ያኖሩ የገዘፈ የፖለቲካ ስብዕና አካዳማዊ እና ወታደራዊ እውቀት ያላቸው ታጋዮች ያካተተ ተቋም ነው:: ለታጋዮቹ አክብሮት ባለው መልኩ ወቀሳም ትችትም ካለ ማቅረብ ሲገባ መሪዎቹ ባልተገራ ቋንቋ መናገር እራስን መስደብና ማዋረድ ይሆናል:: በየትኛውም አደርጃጀት ያለን ወገን በመዘርጠጥ የሚከብር ማንም የለም:: አማራ በታሪኩ ጨዋነት እና የአደባባይ ቋንቋው የተገራ ለራሱ ክብር ያለው ማህበረሰብ ነው:: ይህ የአባቶች ወግና በሃል ማክበሩ እንደ ሕዝብ እንደሚያስከብረን ልናውቀው ይገባል::

አበው ሽልም ከሆነ ይገፉል ቦርጭም ከሆነ ይጠፉል እንዲሉ ብዙ ውዝግብ የተነሳበት የሕዝባዊ ድርጅቱ ከዲፕሎማቶች ጋር የተደረገ ውይይት ተቃዋሚዎቹ ድርድር ያሉት ፍረጃ መዳረሻው ምን እንደሚሆን በቅርቡ የምናየው ይሆናል:: በእኔ እምነት ምንም ሕዝባዊ ድርጅቱ ሁሉንም አካቶ ባለመመስረቱ ቅሬታ ቢኖረኝም የአማራን ሕዝብ ጥቅም ሊጎዳ በሚችል ደረጃ ይሰማራል ብዬ ፈጽሞም አልገምትም:: በክህደት ሊታማ የሚችል የስብዕና ጉድለት ከመሪዎቹ ይኖራል ብዬም አላስብም::

የጉዳዩ ተቃዋሚዎች ያሉትን ወስደን ሕዝባዊ ድርጅቱ ከመንግስት ጋር ተደራድሮ የትኛውን አላማ ሊያሳካ ይችላል? የብልጽግና ጦር ከአማራ ምድር ወጥቶ ክልሉን ከጦርነት ቀጠና ውጪ በማድረግ ሊያስተዳድሩ ነው? ይህንን የማድረግ አቅምና ተቃባይነት ይኖራቸዋል? የሕዝባዊ ድርጅቱ መሪዎች ከመንግስት ተደራድረው ስልጣን ገንዘብና ሹመትን ሊቀበሉ ተዘጋጅተዋል? በእርግጥ በዚህ ደረጃ ሊገመቱስ ይችላሉ? ሊወድቅ አንድ ሃሙስ ከቀረው አገዛዝ ጋር እንኳን የተከበሩ የፉኖ መሪዎች አንድ ማሰብ የሚችል ቦዘኔ በዚህ ደረጃ ይዘቅጣል ብሎ መገመት ይከብዳል: እነዚህ ታጋዮችን በዚህ ደረጃ ማሰብም በእራሱ ሰቅጣጭ ነው:: ቢሆንም ሕዝብ የማወቅ መብት ስላለው በሕዝባዊ ድርጅቱ ላይ ለሚቀርበው ወቀሳና ትችት መሪዎች በተከታታይ ማብራሪያ መስጠትና ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅባቸዋል:; ድርድርን በተመለከተ ግልጽ ያለ አቋማቸውን ለሕዝብ ሊያሳውቁም ይገባል:: ለወደፊቱም ድርድር ያስፈልጋል ከተባለም የአንድ ወይም የጥቂቶች ብቻ ተሳትፎ ሳይሆን የመላው ፉኖ አደረጃጀቶችን ይሁንታና ያካተተ መሆን እንዳለበት መተማመንም ያስፈልጋል::

በሕልውና አደጋ ውስጥ እንዳለ አማራ አስምረን ልንሄድበት የሚገባው መስመር በቅጡ ለይተን ማድመቅ ይኖርብናል:: የፉኖ አሁናዊ የተበታተነ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ለከፉ አደጋ ሕዝባችንን ያጋልጣል:: ይሄ ክፍፍል መሰርታዊ ምክንያቱ በጥንቃቄ ተፈትሾ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል:: እስከዛው ጎራ ለይቶ እንዲጠፉፉ ጠላቶቻችን የቀየሱት ስልት ለማምከን ከስሜታዊነትና ከወገንተኝነት የጸዳ መከባበርን ያስቀደመ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ መከተል አዋቂነት ነው::

ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን!

 

1 Comment

  1. እስክንድር ከጓደኞቹ የተለየው ከአማራ ሕልውና ይልቅ ለሥልጣን ቅድሚያ በመስጠቱ ነው። ችግሩ ይህ ካልሆነ ከጓደኞቹ ተለይቶ ድርድርም ሆነ ውይይት ማድረጉን ምን አመጣው ? ቅድሚያ ለሆዱና ለሥልጣን ከሰጠ፣ ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ከመለስ ዜናዊ፣ ከሌንጮ ለታ፣ ከአቢይ አሕመድ ምን ይለየዋል ? ጠመንጃ ማንሳቱ ለሆድ ከሆነ ምን ፋይዳ አለው ? የኔልሰን ማንዴላን አርዓያነት መከተሉ ለማንኛውም መሪ ነኝ ባይ ያዋጣል። የአውሬ አመራር በቃን።

    የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አመራር በገዛንለት መሣሪያ እኛኑ ገዳይና ረግጦ ገዢ ሳይሆን ፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚኖሩበትንና የሚሠሩትን ራሳቸው እንዲመርጡ፣ በሕብረት የሚተዳደሩበትን ሕገ መንግሥት እንዲያረቅቁና እንዲያጸድቁ መድረኩን አመቻችቶ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ሃይማኖት፣ መንደር፣ ጾታ፣ ዕድሜ ወይም በሌላ ዘዴ ሳይለይ፣ ለተወሰነ ጊዜ የምንሰጠውን የሕዝብ የሥልጣን አደራ ባጸደቅነው ሕግ አግባብ ጠብቆ የሚመራ አስተዳደር ነው ። በመንደርና በዘር እየመነዘረና እየከፋፈለ ራሱ ወደ አውሬ ደረጃ የወረደ አመራር እኛንም ጭምር አውሬ እንዳያደርገን ሥልጣንና ሀብት አምላኪዎችን በሕብረት በሕግ አግደን እንደ ሌሎች የለሙ አገሮች ዜጎች መኖር አለብን።

    በዘር የሚለይ አስተዳደር ከዱር አራዊት አካሄድ በምን ይለያል ? የአንበሳ፣ የነብር፣ የዝንጀሮ፣ የሌሎችም አራዊት ኑሮ መሠረቱ ዘር ነው። ኢትዮጵያውያን ግን አራዊት አይደለንም። መሪ እንሁን ብለው ብቅ ለሚሉ ሁሉ ይህን ተባብረን ማስተማርና ማስረገጥ አለብን። በመሪ ሴራ መከፋፈሉ ለሆዳም፣ ለሥልጣን እሥረኞች፣ ለሀብትና ዝርፊያ አምላኪዎች እንጂ ዛሬ ለሚራበው ለትግሬም ሆነ መድረሻ ላጣውና ለተራበው ለኦሮሞ ሰፊ ሕዝብም አልበጀም። ከሕወሐት መሪዎችም ሆነ ከኦነግ መሪዎች መካከል ረሀብም ሆነ ችጋር ወይም ሞት የለም፣ ያለቀውና የተራበው መሪዎች ተጠቅመው የወረወሩት ድሀው ነው። ስለሆነም፣ ከፋፋዮችን ረድተን ከማንገሣችን በፊት ለዘመናት እንዳደረግነው፣ ሰላማችንን ጠብቀን፣ በጋራ ቆመን፣ የጋር መተዳደሪያችንን ሕገ መንግሥት ማዘጋጀት አለብን። ቢበዛ በዘጠኝ ጎሣ ሥር መገዛቱም መቆም አለበት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop