የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

January 28, 2025

ይነጋል በላቸው

አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡ ሀገራችን ላይ የወደቀው አጋንንታዊ የአፍዝ አደንግዝ ጋግርት ከ130 ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን ሕዝባችንን ፀጥ ረጭ አድርጎ ለአንድ ንፍጡን ላልጠረገ ዕብድና ወፈፌ ልጅ አጋልጦት የሚሰማ ጠፋ እንጂ ጥቂት የማንባል ዜጎች እየሆነ ስላለውና ወደፊትም ሊሆን ስላለው ነገር መጮሃችንን አላቋረጥንም፡፡ ነገሩ “ወደሽ ከተደፋሽ” እንዲሉ ነውና ዝምታችንንና መለያየታችንን በተረዱ ጥቂት የሲዖል አምባሳደሮች ፍዳችንን እያየን ነው፡፡ ከተጻፈ ሁለት ዓመት ሊደፍን ጥቂት ጊዜ የቀረውን ያን መጣጥፍ ወቅቱ ይፈቅደዋልና ያላየነው ደግመን እንድናየው ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

የአማራን ችግር በሚመለከት ሁለቱ ብቸኛ አማራጮች የሚከተሉት ናቸው፦

  1. አማራየታወጀበትንዓለም አቀፍ የዘር ፍጂት አክሽፎ ለኦሮሞውም ሆነ ለሌላው ነገድ በእኩልነት  የምታኖረውን የጋራ ሀገር (ኢትዮጵያን)መፍጠር፡፡

ወይንም

  1. አማራበኦሮሙማተሸንፎ ከምድረ ገጽ መጥፋት (በጄኖሳይድም ይሁን ጎሣና ነገድን በማጽዳት)

በቃ፡፡ ከነዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ሰባተኛውን ንጉሥ አፄ ቦካሣ አቢይን ሥልጣን ላይ የማቆያና በባንዳውና ደንቆሮው ብአዴን ትብብር ታላቋን የኦሮምያ ቫምፓየር – ማናት – ኢምፓየር የመመሥረት ሂደትን ማረጋገጫ ነው፡፡ አህያና ጅብ፤ ሚዳቋና አንበሣ፤ ነብርና ፍየል፤ ዝንጀሮና ክምር ላለመደራረስ ሲደራደሩ ይታያችሁ፡፡ አይሆንም፡፡ ለድርድር የሚያስቀምጡ ችግሮች እንደኛው ዓይነት ሥር የሰደደ የዘር ጥላቻ ዓይነቱ ሳይሆን በሰውነት ተፈጥሮ በሚያምኑ ወገኖች መካከል የሚደረጉ ሰጥቶ የመቀበል ስምምነቶች ናቸው፡፡ እኛን የገጠሙን ገድለውን ካልጨረሱ እርካታ የማያገኙ ጉዶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ጋር ደግሞ ድርድር በፍጹም እውን ሊሆን አይችልም፡፡ ሊደራደር የሚፈልግ ወገን እኮ ቢያንስ ያሠራቸውን ንጹሓን ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታትና ቀናነቱን ማሳየት ነበረበት፡፡ አራት ኪሎ ላይ የተሰዬመው የሉሲፈር ልጅ እኮ የሰው ደም ካልጠጣና የሰው ሥጋ ካልበላ እንቅልፍ በዐይኑ የማይዞር የለዬለት ሰይጣን ነው፡፡ የኢሉሚናቲ አባልነቱን ለጌቶቹ ለማሳየት ሲል የቤት አሽከሮቹን ይዞ የሕዳሴ ግድብ ላይ ድራማ ሲሰራ ያደረገውን የተገለበጠ መስቀል ያለበት ቀይ ጫማ አላያችሁም?

ተመልከት! አማራ ለድርድር ተቀምጦ ከአቢይና ሽመልስ እንዲሁም እነሱ ካሠለጠኑት ቄሮ አእምሮ ውስጥ የተሰነቀረውን አማራን በጥርስም በጥፍርም ቦጫጭቆና አኝኮ በልቶ የመጨረስ የሃይማኖት ያህል የሚመለክ አስተሳሰብ ማውጣት ይቻላል ወይ??? ከዚህ ጥላቻቸው አኳያ አይደለም ወይ በዚች ቅጽበት እንኳን ነፍጥ ያልያዘ ንጹሕ አማራ ከየመንገዱና ከየሥራ ቦታው በገፍ እየታፈሰ በሥውር ማጎሪያዎች ያለምግብና ውኃ በድብደባና ጅምላ ርሸና፣ ህክምናም ተከልክሎ በወረርሽኝና በልዩ ልዩ በሽታ እያለቀ የሚገኘው? በሸገር ከተማ ተብዬው ምክንያት አማራ ላይ ምን ደረሰ? አዲስ አበባ እንዳይገባ በአምስቱም አቅጣጫ የታገደው አማራ ሎተሪ አዙሮ፣ ሱቅ በደረቴ ሆኖ፣ መኪና አጥቦ፣ ለማኝ ሆኖ፣ የመንግሥት ተቀጣሪ ሆኖ… የዕለት ጉርሱን እንዳያገኝ የተደረገው ለምን ዓይነት ድርድር ነው?

ከአማራ ወገን ለድርድር የሚቀመጥ ካለ በገንዘብ የተገዛ ነው ወይም በአማራ ስም ሠርጎ የገባ ኦነግ ነው ወይም የኦነግ ሸኔ ምንነት ያልገባው ቂላቂል ባንዳ ነው ወይም ኦነግ መሣሪያ እስኪያሟላ ወታደርም እስኪያሠለጥንና አማራን የመፍጃ አዲስና ሥኬታማ ሥልት እስኪነድፍ ድረስ ጊዜ ለመግዛት በውስጥ አርበኛነት ከኦነግሸኔ የተላከ ፀረ አማራ ነው፡፡ ይህንን የፈጠጠ እውነት የመታረጃ ቀኑን የሚጠብቅ በየትኛውም አካባቢ የሚኖር አማራ ይወቅ፡፡ በነገራችን ላይ ድሃም ሁን ሀብታም፣ ነጋዴም ሁን ፖለቲከኛ፣ ምሁርም ሁን ማይም፣ ሥልጡንም ሁን ባላገር፣ …. ምንም ሁን ምን አማራ ከሆንክ የኦሮሙማ ሠይፍ ሰለባ ነህ፤ ነገሩ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም አማራ በሂደት ከሚገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል፡፡ በሀብትህ ብዛት የምትድን መስሎህ ለኦነግ የምታሽቃብጥ ደንቆሮ የአማራ ባለሀብት ሁሉ ቀንህን ጠብቆ ኦነግ ባልተወለደ አንጀቱ በሜንጫው ይገነድስሃል፡፡ ከሁለት ያጣ ጎመን ሆነህ እንዳትቀር አስብበት፡፡ የገንዘብ ብዛት እንኳን ከኦሮሞ ሜንጫ ከሲዖል እሳትም አያድንህም – ከድሃ እየዘረፍክ ለድሃና ለቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ እያልክ ጥቂት ጥቂት እንደምትሰነዝር ስለማውቅ ነው እንዲህ የምልህ፡፡ ስለሆነም አሁን ገንዘብህ ነገ ሕይወትህ የኦነግ መሆኑን ካላወቅህ በርግጥም ኪስህ እንጂ ጭንቅላትህ ባዶ ነው፡፡

አዎ፣ አማራን የጎዳው ሚዛን በማያነሱ ነገሮች መለያየቱና ያንንም ተከትሎ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ መግባቱ ነው፡፡ አሁን ግን በግምት ከ20 እስከ ሠላሣ በመቶ የሚሆነው አማራ ምሥጢሩ የገባው ይመስላል፡፡ በዚያም ምክንያት ዕልቂት ያወጀበትን ዘረኛ ቡድን ሊያንበረክክና ኅልውናውን በነፍጡ ሊያስከብር ጉዞውን “ሀ” ብሎ በቅርቡ ጀምሯል፡፡ በድል እንደሚያጠናቅቅም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የታወጀበት የዘር ፍጂት የገባው አማራ ወደ ሰባና ሰማንያ በመቶ ቢጠጋ ኖሮ የኦሮሙማ ዕድሜ ከአንድ ጀምበርም ባላለፈ ነበር፡፡ ይሁን ግዴለም፡፡ ሁሉም ለበጎ ነው፡፡

ለማንኛውም በፈጣሪ የእጅ ሥራ የጥበብ መገለጫ የሰው ልጅ ላይ ሰማይና ምድር ሊሰሙት የሚሰቀጥጥ ግፍና በደል አዝንቦ በሠላም የኖረ የለምና አክራሪ ኦሮሞዎች የዘራችሁትን ለማጨድ  ተዘጋጁ፤ የአዝመራ ወቅት በደጃችሁ አለ፡፡ ዐውድማው ተለቅልቆ ውቂያው ሊጀመር ሰዓቱ ደርሷል:: “የእስካሁኑስ?” የሚለኝ መቼም አይጠፋም፡፡ የእስካሁኑማ የማሸነፍና የመሸነፍ ልምምዶች የመጨረሻው ትዕይንት ማማሟቂያ (warm up) ነበር ወይም ነው፡፡ ዋናው ገና ነው፡፡ አዲስ አበባም አይቀርላትም፡፡ ሸኔ ቀላል አይደለም፡፡

ግን ይህ ከፍ ሲል የተጠቀሰው መለኮታዊና ነባራዊ እውነት ለሰው እንጂ ወያኔንና ኦነግሸኔን ለመሰሉ ሰው መሠል እንስሳት አይገባቸውም፡፡ እነሱ ጥጋብ በወለደው ዕብሪት ስለታወሩ አጠገባቸው የሚገኝን ወጣት እስኪያስጨርሱና ብቻቸውን ቀርተው ባዶነታቸውን እስኪረዱ ድረስ ልበሥውራን ናቸው፡፡ መጥኔ ለቤተሰባቸው፡፡ ሁለመናቸው እንደታወረ ለሀገርና ለትውልድ የሚተርፍ ጠባሳ እያስቀመጡ ናቸው፡፡ የሚታይ ሁሉ እውነት እየመሰላቸው ምናባዊ ቅብዥር እያጥበረበራቸው ነው፡፡

ለአማራ ፋኖ ይህችን ማሳሰቢያ ቢጤ አድርሱልኝ፡፡ ጎንደር ተያዘ፣ ደሴ ተከበበ፣ ማርቆስ ግማሹ ተያዘ፣ ደብረ ታቦር ዙሪያው ተከበበ፣ ባሕር ዳር ከአምስቱ ወረዳ ስድስቱ በፋኖ ቁጥጥር ሥር ገባ… የሚለው አሁን አሁን ላይ ቀልብን መሳቡን የቀነሰው ወሬ ይብቃ፡፡ ይህ ዓይነቱ የዩቲዩብ መሸቀያ ከቀጠለ ሆዳችን በባዶ ተስፋ እየተቆዘረ ከ2015ዓ.ም እስከ 2055ዓ.ም መቆየታችን ነው፡፡ የኦሮሙማና ብአዴን ፍላጎትም ይሄው ነው፡፡ ደሴና ወልዲያ በፋኖ ተያዘ አልተያዘ ለኔ ምን ይፈይድልኛል? ቀልድ ይቁም፡፡ ቁማር ይብቃ፡፡ በፈረንጅኛው Let viable surgical operations be the fashion of the time to save Ethiopia and the poverini Amharas! ትግሉ በወለደው ፍራቻ ምክንያት ለቁጥር የሚያታክት የአማራ ወገናችን በነዚህ ጨካኝና ዐረመኔዎች በየእሥር ቤቱ እያለቀ ነውና ቶሎ እንድረስላቸው፡፡ እነዚህ ጉግማንጉጎች አንዲትም ቀን ባገኙ ቁጥር በሀገርና በዜጎች ላይ የሚያሣርፉት ግርፋት ቀላል አይደለም፡፡

እያንዳንዱን ወረዳና ቀበሌ ካልተቆጣጠርን ጭራቅ ግራኝ አቢይ አህመድን አላሸንፍም ብሎ “ሪሶርስ”ን በከንቱ ማባከን እውነቱን ለመናገር የዋህነት ነው፡  ጠላትህ አዲስ አበባ መሀል ተጎልቶ ላሊበላን ለመያዝ ቅርስን ማስወደም አይገባም፡፡ ጠላትህ ናዝሬትና ሻሸመኔ ተወዝፎ ደምበጫን ለመቆጣጠር ኃይልህን ማሟጠጥህ በፍጹም ሊገባኝ አይችልም – በትናንሽ የመንደር ድሎች በመደለል ሥነ ልቦናዊ እርካታን ለሚያገኝ ወገንህ ካልተጨነቅህ በስተቀር መርጦ ለማርያም ላይ ኦነግን የምትዋጋበት ምክንያት አይታየኝም፡፡ ይህን ሃሣቤን ለእውነተኛ የፋኖ አመራሮች አድርሱልኝ፡፡ ከተቀበሉት ተቀበሉት፡፡ ከኔ ግን ወጥቷልና ነገ የሚወቅሰኝ ኅሊና የለኝም፡፡ ትንሣኤያችን እሙን ነው፤ ጭንቀቴ መስዋዕትነትና የሀብት የንብረት ውድመት ከሚጠበቀው በላይ እንዳይሆን ነው፡፡ እንጂ ሦዶማውያን የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ/ብአዴን መንጋዎችን ሰው ቢሰንፍ ፈጣሪ መቀመቅ ይከታቸዋል፡፡

በመጨረሻም ኦሮሙማ በወረርሽኝ መከላከል ሰበብ አማራን በክትባት ሊዘምትበት መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ እንደኔ እምነት እስከዚህን እንኳን የሚዳፈሩ አይመስለኝም፤ ምክንያቱም ከአማራ ክልል ውጪ ያለውን አማራ በተለይ በየማሠሪያው እያጎረ ሆን ብሎ በሚፈጥረው ወረርሽኝ ስንቶችን በየቀኑ እየፈጀ ለአማራ ክልል ሕዝብ እቆረቆራለሁ ቢል የሚያምነው የለም፡፡ ለማንኛውም ይህ የተባለው ነገር እውነት ከሆነ እንደዘመነ ሕወሓት ዐይን ያወጣ አማራን በክትባት መልክ የማምከንና አሁን ደግሞ በልዩ መርዝ በክትባት የመፍጀት ዕቅድ ወደተግባር መግባቱን ልናይ ነው፡፡ የሚገርመው አማራ ብቻ ነው ለኮሌራውም ለትክትኩም ለአተት ገተቱም ክትባት ቀድሞ የሚታጨው፡፡ ሌላውስ ሕዝባቸው አይደለም እንዴ? ምነው ለአማራ ብቻ መጨነቃቸው?

የተባለው እውነት ከሆነ በሀኪም ስም ነጭ ገዋን ለብሶ አማራን በክትባት ሊፈጅ የሚመጣውን ኦህዲድሸኔ ዋጋውን መስጠት ተገቢ ነው፡፡ በሌላ ሲያቅታቸው በዚህ መጡ፡፡ ለየአካባቢው ፋኖ መረጃው ይዳረስ፡፡ የታወጀብን ጦርነት ዓይነትና ብዛት ግን ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ እግዜር ይሁንህ አማራዬ፡፡

2 Comments

  1. ይነጋል ይህን ሰው አካሄዱን ያወቁ ተው ሊባል ይገባል ብለው ሲነግሩን ተዘናግተን ቁመው የሰቀሉት ነገር ሁኖብናል ቀላል ሰው አይምሰልህ የከበቡት ጎበዝ ተገለባባጮችና ይሉኝታ ያልፈጠረባቸው ናቸው። ኤርምያስ ዋቅጅራና ሀብታሙ አያሌው ከፊት ተሰላፊ ናቸው የትግሬ ሚዲያዎችም ድጋፋቸው ለርሱ ነው እንግዲህ እኛው ባዋጣነው የእኛው ልጆች ተገዝተውበት ወደ ቤተመንግስት ሊገባ ነው። ያልሞተ ሰው አለ ያችን ፌስታል ይዞ አታለለን እስር ቤትም እንዴት እኔ አልጋ ላይ ተኝቼ ስብሀት ነጋ መሬት ይተኛል ብሎ ሀዘኔታውን የገለጸ ነበርን እስቲ ልብ ይስጠው ማንን እንመን?

  2. በአመዛኙ ሃስብህ ቅቡልነት አለው። በዚያው ልክም ገዳዳና አክራሪነት ይታይበታል። በወያኔ የ 27 ዓመት የአገዛዝ ዘመንና ዛሬ ደግሞ እሱን በተካው የብልጽግና መንግስት የአማራ ህዝብ መከራ ሰማይ ጠቀስ እንደሆነ ሰው ነኝ የሚል ሁሉ ሊረዳው የሚችል ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ ሃሳባችን ሁሌ ያዘው ጥለፈው ጣለው በለው የሚል ከሆነ የትም አንደርስም። ያለፉ ገዥዎቻችን ግትር አቋምና አመራር ዛሬ ሃገሪቱ ለገባችበት ውጥንቅጥ ዋንኛ ምክንያት ነው። ሃሳበ ግትርነት፤ እኔን ብቻ ስሙ ያኔም ዛሬም ያለ በመሆኑ እሱን ተፋልሞ መደማመጥን ማስፈን የተሻለ አማራጭ ነው። የግለሰብን እይታ፤ የመንግስትን አቋምና ክፋት ስንሟገት ተራ የሆኑ ስድቦችን መጠቀም የራስን ሃሳብ ዋጋ ማሳጣት ይሆናል። ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ሃገሩን የሚወድ፤ ከሁሉ ጋር አብሮ በልቶ የኖረና የሚኖር ለመሆኑ በመሃሉ የኖርን ጠንቅቀን እናውቃለን። በኦሮሞ የእድሜ ልክ የፓለቲካ ሰካራሞች እየተቀሰቀሰና እየተመራ በጣት የሚቆጠረው ፍርፋሪ ለቃሚናየኦነግ ታጣቂ በአማራ ላይ በሚያደርሰውና ባደረሰው በደል መላ የኦሮሞ ህዝብ ተወቃሽ ሊሆን አይችልም።
    ፋኖ ከተማ ያዘ ገጠር ለአማራ ህዝብ ተጨማሪ የመከራ ዝናብ እንጂ ምንም ከዚህ የፋኖ ድርጊት የሚያተርፈው ቅንጣት ታክል ነገር የለም። ሁለት ዝሆኖች ሲታገሉ የሚጎዳው ሳሩ እንዲሉ ነውና። ፋኖ የጠራ የጋራ የፓለቲካ አቋም በመያዝና ለመንግስት የፓለቲካ ጥያቄዎችን በማቅረብ ተቀብሎ በመስጠት መደራደሩ ምርጫ የማይገኝለት ጉዳይ ነው። ከበዙ ዘረባቸው መሃል የአማራ ፋኖ ታጋዪች አንድም ቀን በእስር ስለሚማቅቁት ድምጽ ሲያሰሙ ሰምቼ አላውቅም። ሁሌ ደመሰስን፤ ገደልን፤ አልፎ አልፎ ሞተብን ሲሉ እንጂ! ለመሆኑ የፋኖ ህብር የሆነ የፓለቲካ ጥያቂያቸው ምንድን ነው? በበረሃና በገደል እየተንከራተቱ የምንታገለው ለአማራ ህዝብ ነው ማለቱ ብቻውን ፍሬ አያስገኝም። የጠራ አላማ፤ መንግስትን የሚጠይቅ አጀንዳና ጥያቄ በግልጽ ሃገር ውስጥ ላለውም ሆነ በሩቅ ሆነው ለሚያዋጉት ይፋ ማድረግ ትግሉን የበለጠ ያጎላዋል።
    ሌላው የእርስ በእርስ የሃሳብም ሆነ የአፈሙዝ መፋለም ነው። ለአንድ ዓላማ የቆመ ስብስብ ከአመልካች ጣት አውራጣት ይበልጣል ብሎ አይቧቀስም። ግቡና ዓላማው አንድ የሆነ ሃይል በየወንዙ አይማማልም። አንድ አንድን አያጥላላም። ፈርቶ ነው፤ ከብልጽግና ጎን ቆሞ ነው፤ ጦርነት ሰልችቶት ነው ስለ ሰላም የሚያወራው ማለቱ በራስ ላይ ማሾፍ ነው። ሰው ይፈራል ጦርነትም ይሰለቻል። በጠረጴዛ ዙሪያ ተደራድሮ ተቀብሎና እንካችሁ ብሎ ወደ ሰላም መምጣትም ብልህነት ነው። ስለዚህ ፋኖ ሊደራደር ይገባዋል።
    ከላይ ጸሃፊው ወደሽ ከተደፋሽ የሚል ተረት በመጨመር አጋንንታዊ ያፍዝ ያደንግዝ ጋግርት እስከማለት ደርሰዋል። ሲጀመር አጋንት የእኛ የሰዎች ተግባር ነው። ወዳ ከተደፋችም ክብሯ ሊጠበቅላት ይገባል… እንዲህ አይነቱ ጎታች እይታ ሰውን ወደ ላቀ የህሳቤ ደረጃ እንዳያደርሰው እንቅፋት ሆኖበታል። የአማራ ህዝብ ወዶ አይደለም የሚሞተውና የሚሰደደው ተገዶ ነው። ኦሮሞም የአማራን ዝህብ ገድሎ አይጨርስም። ይህ ጭፍን የፓለቲካ ቱልቱላ ነው። ዛሬ መከራ የሚያየው እኮ የአማራ ህዝብ ብቻ አይደለም። የኦሮሞ ህዝብም እየተገደለ ነው። ለዚያውም ገዛ ልጆቹ። የትግራይ ህዝብ ለ 50 ዓመታት በስሙ የነገደው ወያኔ ዛሬም እያመሰው ይገኛል። ችግሩ በአማራ ክልል ይክፋ እንጂ በሁሉም አካባቢዎች ቋንቋን፤ ክልልና ብሄርን ተገን አርጎ በሚጫር ጸብ እልፎች ተገለዋል ዛሬም እየተገደሉ ይገኛሉ። ለገባው ዋናው ችግር ያለው ከሃገሪቱ ህገመንግስት ላይ ነው። አፓርታይዷ ኢትዮጵያ የክልል ፓለቲካን አክ እንትፍ እስካላለች ድረስ ሰው መፈናከቱን አይተውም።
    ኢትዮጵያዊያን የምናሳዝን ህዝቦች ሆነናል። በተወለድንበት ባደግንበት ሃገር ላይ በሰላም የመኖር መብታችን የተቀማ። በስደትና በሰቆቃ በየዓለማቱ የተረጨን፤ ያለፈ ታሪካችን ከሞላ ጎደል የዛሬውን የሚመስል ምንም ለውጥ የማታይ ሃገር መሆኗ ሟችን እያስለቀሰ መቃብር አውርዷል ያለነውንም ጧትና ማታ ያስቆዝመናል። ኦ አዲስ መንግስት መጣ እፎይ እነዚያ አረመኔዎች ተወገድ ሲንል ትሻልን ትቼ ትብስን እየሆነብን እንሆ ጊዜው ነጎደ። ይባስ ተብሎ የጋራ የመግባቢያ ቋንቋችን ሁሉ አረም በቀለበት። ይህን ያለፈና የአሁን ታሪክ ሳገናዝብ ነው የኢትዪጵያ ፓለቲካ ውሃ ወቀጣ የሚሆንብኝ። አይናችን ከፍተን፤ ልባችን አሳምነን በሰላም ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ሃገር ይኖረን ይሆን? አላውቅም። ጊዜ ሁሉን ለቋሚ ያሳያልና ጠብቆ ማየት ነው። በመጨረሻም በአንድ የግጥም ስንኝ ሃሳቤን አሳርጋለሁ።
    ሳልታይ ሳያውቁኝ እንዲህ ሁኜ ልኑር
    እንዲህ ሁኜም ልሙት መለቀሱ ይቅር!
    ሹልክ ልበልና ከዚህች አለም ልብረር
    የት እንደተጋደምኩ ድንጋይ አትናገር (ግጥም አለክሳንደር ፓፕ – ትርጉም ዳዊት ዘኪሮስ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

Go toTop

Don't Miss