birr
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 136.6286 ብር መሆኑን አስታወቀ።
50 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበት በዚህ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ 11 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል አግኝተዋል።
ዛሬ ይፋ የተደረገው የምንዛሪ ተመን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው 7ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ከተመዘገበው 134.95 ብር የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር፣ የብር የመግዛት አቅም በ1.6786 ብር መቀነሱን አመላካች ነው፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas