(ይህ ከትናንት በስቲያ በመሠረት ሚድያ የቀረበ መረጃ በብዙ አንባቢዎች ጥያቄ መሰረት ለሁሉም አንባቢዎች ክፍት ተደርጎ በድጋሜ ቀርቧል)
ከጥቂት ወራት በፊት የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ “ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው” ቢባልም ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሊቀነሱ እንደሚችሉ መሠረት ሚድያ ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
አሁን የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ከሀምሌ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ ታውቋል።
በዚህም ሁሉም የመንግስት ተቋማት ‘ሪፎርም’ በሚል አሰራር ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ሰራተኞችን ጨምሮ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ውላቸው እንዲቋረጥ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን መሠረት ሚድያ ከመንግስት ምንጮች አረጋግጧል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ከፓርላማ ፅህፈት ቤት እስከ ዩኒቨርስቲዎች፣ ከክፍለ ከተማዎች እስከ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ወዘተ ይተገብሩታል በተባለው በዚህ የሰራተኛ ቅነሳ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከስራቸው ይሰናበታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ከወራት በፊት ማብራሪያ ሰጥተው በነበሩበት ወቅት በቀጥታ ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ነገር ባይኖርም በመንግስት አቅጣጫ ከተያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ “ከሚያስፈልገው በላይ የመንግስት ሰራተኛ አለ” የሚለው ዋናው መሆኑን ጠቅሰው ነበር።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌም ሂደቱ የግለሰቦችን መብት ያለአግባብ እንዳይጎዳ ሚዛኑን አስጠብቆ በመሄድ ረገድ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል ቢሉም በርካቶች ከስራቸው መቀነሳቸው እንደማይቀር ታውቋል።
የረቂቅ አዋጁን ይዘት በአግባቡ ባለመረዳት በአንዳንድ የሚዲያ ተቋማት የተዛቡ መረጃዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ነገሪ በበኩላቸው ግልፀኝነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ረቂቅ አዋጁን የበለጠ ለማዳበር እና ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ ይደረጋል ብለዋል።
አዋጁ እንደ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ህግ፣ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ ተቋማት ውስጥ የብሄር ስብጥር ለማድረግም ያለመ መሆኑን የጠቁሙት ምንጮቻችን አዋጁ “የብሔር ብሔረሰቦች ብዙሃነት እና አካታችነት ስርዓትን ይገነባል” በሚል በመንግስት እንደታሰበ አስረድተዋል።
የዚህን የመንግስት ሰራተኞች ቅነሳ የሚጠቁም ነገር ግን ብዙ ሰው ልብ ያላለው አንድ መረጃ በአንድ የመንግስት ሚድያም ተለቆ ነበር።
“ሲቪል ሰርቪሱ ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑ ተጠቆመ” የሚል መረጃ በቅርቡ በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው የሲቪል ሰርቪሱ ቁጥር ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑን ዶ/ር ነገሪ መናገራቸውን ዘግቦ ነበር።
ዶ/ር ነገሪ በዚህ ንግግራቸው እንደጠቀሱት “በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያለው የሠራተኛ ቁጥር በጣም በርካታ ነው። ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ ነው። ከአደረጃጀት አንጻር ሲታይም በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ መዋቅሩ የሚሸከመው ብዙ የሰው ኃይልን ነው፤ በተሸከመ ቁጥር ደግሞ የሚያገኘው ጥቅም አናሳ ነው” ብለው ነበር።
ሀላፊው አክለውም “የመንግሥት ሠራተኞች የብዛታቸውን ያህል የ