
የአማራ ህዝብ ባለፉት ሀምሳ አመትና ከዛ በላይ የደረሰበትና አሁንም እየደረሰበት ያለው ሁለንተናዊ መዋቅራዊና መንግስት መር በደል የህልዉና አደጋ ላይ እንደጣለው የሚታወቅ ነው:: ይህንን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና እንደ ህዝብ ሕልው ለመሆን ፋኖ ከአብይ አህመዱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር ሁለንተናዊ ጦርነት እያካሄደ ይገኛል::
በዚህ የህልዉና ጦርነትም የአማራ ፋኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአውደ ውጊያዉም ሆነ በፖለቲካው ዘርፍ ጠላቱ ላይ ትልቅ የበላይነት በመዉሰድ በድል ዋዜማ ላይ ይገኛል::
ይህንን የተገነዘበዉና ሁለንተናዊ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው አገዛዙ በምድር ጦር፣ በሞርታር፣ ታንክ፣ መድፍ እና ቢ ኤም፤ በአየር ጦር ጀትና ድሮን አዝምቶ ህዝባችንን እየጨፈጨፈ ይገኛል::
➽አብይ አህመድ መሩ የብልጽግና አገዛዝ በአዋጅ ለህዝባችን የስኳርና ግፊት እንዲሁም የትቪና ኤች አይ ቪ በአጠቃላይ ምንም አይነት መድሃኒት እንዳይደርስ ያደረገው የሰራተኛ ደመወዝ መክፈል ያቃተዉና መክፈልም የማይፈልገው ያለዉንም ለጦርነት እያዋለው ያለው ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው አብይ አህመድና አገዛዙ ብልፅግና ከዛም አልፎ ብልፅግና መር የኑሮ ዉድነት በመፍጠር ህዝቡን በድህነትና በረሃብ እየጠበሰው ይገኛል::
➽ስለሆነም የተጀመረዉና ለአማራ ህዝብ ህልዉና ብቻ ሳይሆን ለአገራችን ኢትዮጵያ ትንሳኤም የሆነው በድል ዋዜማ የሚገኘው የፋኖ ትግል ከዳር ይደርስ ዘንድ ህዝባችን የህልዉና አደጋ የተጋረጠበት ህዝብ መሆኑን በመገንዘብና ለትግሉ ቅድሚያ በመስጠት ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታዉንም ጭምር ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ አገዛዙ በሕዝባችን ላይ የከባድ መሳሪያና የድሮን ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ጋር ተያይዞ በዚህ አመት ምንም አይነት ሰርግ እንዳያደርግ ቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን::
➽ሰርግና ሞት ለሰው ልጅ ተፈጥሮዊ የማይቀሩ ማህበራዊ መስተጋብሮች መሆናቸዉን በቅጡ የምንረዳና የምንገነዘብ ቢሆንም በኢኮኖሚ ለደቀቀው በምድርም ይሁን በአየር ጦር በገበያ በት/ቤት በጤና ተቋማት በቤተ-ክርስቲያንና መስጊድ እንዲሁም ክርስትና አስጠምቀው በሚመጡ ወገኖቻችን ላይ ሳይቀር ድሮን ጥቃት እየተፈፀመ በሚገኝበት ሁኔታ እና ይህንን ብልፅግና መር ዘር ማጥፋት ለመቀልበስ እንደ ህዝብ ተጋድሎ እያደረግን ባለንበት ሁኔታ ሰርግ ህዝባችን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ስለማይገልፅና ለፈፅሞ ጥፋት ስለሚዳርገን ክልከላዉን ልናዉጅ ችለናል::
➽ስለሆነም የተከበረው ህዝባችን የሃይማኖት አባቶች የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች አዋጁ ወቅቱን ጠብቆና ቀድሞ ለሰርግ የሚያስፈልጉ የምግብም ይሁን የመጠጥ ግብዓቶች ሳይዘጋጁና ሳይበላሹ እንዲሁም የተለያዩ ለሰርግ የሚያስፈልጉ ወጪዎች ሳይባክኑ የታወጀ መሆኑንም በመገንዘብ ለተግባራዊነቱና ለአዋጁ ተፈፃሚነት የበኩላቹህን እንድትወጡ ስንል በአማራ ፋኖ በወሎ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
➽በመጨረሻም ለጋብቻ የተዘጋጃችሁ ወጣቶችም ሆነ ልጆቻችሁን ለመዳር ያሰባችሁ ወላጆች ሰርግ በህይወት ከመኖር አይቀድምምና የመኖር መብታችንና ህልዉናችንን ስናረጋግጥ ስለሚደርስ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጥሪያችንን እንድትቀበሉና አዋጁን ተፈፃሚ እንድታደርጉ ስንል በአክብሮት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን::
አዋጁ በገጠርም ይሁን በከተማ የፀና ሲሆን ይህንን አዋጅ ተላልፎ የተገኘ ማንኛዉም አካል ላይ ማንኛዉንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆኑንም እንገልፃለን!
➳➳➳➳➳➳➳
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም