December 11, 2024
6 mins read

ከአማራ ፋኖ በወሎ የተላለፈ ጥብቅ አዋጅ!

468841004 1023072929834386 7940364238612457052 n

የአማራ ህዝብ ባለፉት ሀምሳ አመትና ከዛ በላይ የደረሰበትና አሁንም እየደረሰበት ያለው ሁለንተናዊ መዋቅራዊና መንግስት መር በደል የህልዉና አደጋ ላይ እንደጣለው የሚታወቅ ነው:: ይህንን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና እንደ ህዝብ ሕልው ለመሆን ፋኖ ከአብይ አህመዱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር ሁለንተናዊ ጦርነት እያካሄደ ይገኛል::

በዚህ የህልዉና ጦርነትም የአማራ ፋኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአውደ ውጊያዉም ሆነ በፖለቲካው ዘርፍ ጠላቱ ላይ ትልቅ የበላይነት በመዉሰድ በድል ዋዜማ ላይ ይገኛል::

ይህንን የተገነዘበዉና ሁለንተናዊ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው አገዛዙ በምድር ጦር፣ በሞርታር፣ ታንክ፣ መድፍ እና ቢ ኤም፤ በአየር ጦር ጀትና ድሮን አዝምቶ ህዝባችንን እየጨፈጨፈ ይገኛል::

➽አብይ አህመድ መሩ የብልጽግና አገዛዝ በአዋጅ ለህዝባችን የስኳርና ግፊት እንዲሁም የትቪና ኤች አይ ቪ በአጠቃላይ ምንም አይነት መድሃኒት እንዳይደርስ ያደረገው የሰራተኛ ደመወዝ መክፈል ያቃተዉና መክፈልም የማይፈልገው ያለዉንም ለጦርነት እያዋለው ያለው ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው አብይ አህመድና አገዛዙ ብልፅግና ከዛም አልፎ ብልፅግና መር የኑሮ ዉድነት በመፍጠር ህዝቡን በድህነትና በረሃብ እየጠበሰው ይገኛል::

➽ስለሆነም የተጀመረዉና ለአማራ ህዝብ ህልዉና ብቻ ሳይሆን ለአገራችን ኢትዮጵያ ትንሳኤም የሆነው በድል ዋዜማ የሚገኘው የፋኖ ትግል ከዳር ይደርስ ዘንድ ህዝባችን የህልዉና አደጋ የተጋረጠበት ህዝብ መሆኑን በመገንዘብና ለትግሉ ቅድሚያ በመስጠት ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታዉንም ጭምር ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ አገዛዙ በሕዝባችን ላይ የከባድ መሳሪያና የድሮን ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ጋር ተያይዞ በዚህ አመት ምንም አይነት ሰርግ እንዳያደርግ ቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን::

➽ሰርግና ሞት ለሰው ልጅ ተፈጥሮዊ የማይቀሩ ማህበራዊ መስተጋብሮች መሆናቸዉን በቅጡ የምንረዳና የምንገነዘብ ቢሆንም በኢኮኖሚ ለደቀቀው በምድርም ይሁን በአየር ጦር በገበያ በት/ቤት በጤና ተቋማት በቤተ-ክርስቲያንና መስጊድ እንዲሁም ክርስትና አስጠምቀው በሚመጡ ወገኖቻችን ላይ ሳይቀር ድሮን ጥቃት እየተፈፀመ በሚገኝበት ሁኔታ እና ይህንን ብልፅግና መር ዘር ማጥፋት ለመቀልበስ እንደ ህዝብ ተጋድሎ እያደረግን ባለንበት ሁኔታ ሰርግ ህዝባችን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ስለማይገልፅና ለፈፅሞ ጥፋት ስለሚዳርገን ክልከላዉን ልናዉጅ ችለናል::

➽ስለሆነም የተከበረው ህዝባችን የሃይማኖት አባቶች የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች አዋጁ ወቅቱን ጠብቆና ቀድሞ ለሰርግ የሚያስፈልጉ የምግብም ይሁን የመጠጥ ግብዓቶች ሳይዘጋጁና ሳይበላሹ እንዲሁም የተለያዩ ለሰርግ የሚያስፈልጉ ወጪዎች ሳይባክኑ የታወጀ መሆኑንም በመገንዘብ ለተግባራዊነቱና ለአዋጁ ተፈፃሚነት የበኩላቹህን እንድትወጡ ስንል በአማራ ፋኖ በወሎ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::

➽በመጨረሻም ለጋብቻ የተዘጋጃችሁ ወጣቶችም ሆነ ልጆቻችሁን ለመዳር ያሰባችሁ ወላጆች ሰርግ በህይወት ከመኖር አይቀድምምና የመኖር መብታችንና ህልዉናችንን ስናረጋግጥ ስለሚደርስ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጥሪያችንን እንድትቀበሉና አዋጁን ተፈፃሚ እንድታደርጉ ስንል በአክብሮት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን::

አዋጁ በገጠርም ይሁን በከተማ የፀና ሲሆን ይህንን አዋጅ ተላልፎ የተገኘ ማንኛዉም አካል ላይ ማንኛዉንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆኑንም እንገልፃለን!

➳➳➳➳➳➳➳
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

2 Comments

  1. አይ አዋጅ። ይገርማል። ዘመነ ካሴ መኪና እንዳይንቀሳቀስ ሲያግድ፤ የወሎው ደግሞ ጭራሽ ትዳር መመስረትም ወንጀል ነው እያለን ነው። ከዚህ የበለጠ እብደት የለም። ጦርነትና የሰላም ድርድር ጎን ለጎን የሚሄድ የፓለቲካ ስልቶች መሆን ነበረባቸው። በወል ስሙ ፋኖ እየተባለ ለሚጠራው ስብስብ የሰላም ድርድር የሚታሰብ ነገር አልሆነም። በሌለ ነገር ላይ ወደ ሰማይ የሚተኩስ የእብዶች ስብስብ የሰላምን ጥሪ እንደ ሥራ መፍታት ስለሚቆጥር እየገደለና እያስገደለ ጊዜ መቁጠርን እንደ ፓለቲካ ስልት ተቀብሎታል። ቀደም ብለው ትጥቅ አንስተው ከከሰሙ ወይም በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ ከነበሩ እና አሁንም ስልጣንን ሙጭጭ ብለው ከሚያላዝኑት የፓለቲካ ሙታኖች ሰው ትምህርት እንዴት አይወስድም። ለመሆኑ የፋኖ የፓለቲካ አጀንዳ ምንድን ነው? ለአማራ ህዝብ ነው የምንታገለው የሚለው ጥቅል አባባል የፓለቲካ ብስለትን አያሳይም። ወይስ በሰኔ አራት ኪሎ እንገባለን ተብለን እንደነበረው ቧልት ነው። ያ ሰኔ አልፎ ሌላ ተተክቶ! የአማራ ህዝብ ሰርቶ/አርሶ/ለፍቶ መኖር ነው የሚሻው። ግን በፋኖና በብልጽግና መካከል ባለው ፍልሚያ እንደ ገና ዳቦ በእሳት መሃል ሆኖ ይኸው እንሆ ሲሳደድና ሲገደል ይኖራል።
    መኪና እንዳይነቀሳቀስ መከልከል ምን ያህል ህዝቡን ለችግር እንደሚያጋልጠው ካለፈው እገዳና አፈና አይተናል። ያ ግን ለፋኖ መሪዎች ትምህርት አልሆናቸውም። ዛሬም እንደበፊቱ ያዘው ጥለፈው በለው የፓለቲካ መርህ! ባጭሩ የወሎውም ሆነ የጎጃሙ የአዋጅና መግለጫ ጋጋታ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው። እኛ እየሞትን ማንም ደስ አይበለው፤ ሰርቶና ነግዶም አያትርፍ። አብረን ድሃ እንሁን እንደ ማለት ነው። ሁለ አቀፍ የሆነ የጠራ የፓለቲካ ጥያቄ ለመንግስት አቅርቦ፤ ተቀብሎና ሰቶ፤ ያጠፋው ይቅር ተብሎ፤ የታሰረው ተፈትቶ ነገርን በሰላም ፈትቶ ምድሪቱን የሰላምና የጸጥታ እንደማድረግ ልክ እንደትላንቱ በዘርና በቋንቋ የተሰመረ የፓለቲካ መርህ ቆይቶ ቆይቶ ራሱን የሚበላና የሚጠፋ እሳት ለመሆኑ ታሪክ ይመሰክራል። የአማራ ህዝብ የሚፈልገው የአዋጅና የማስጠንቀቂያ ጋጋታ ሳይሆን ሰላም ነው። ፋኖ ለአማራ ህዝብ የሚያስብ ከሆነ የሰላም ድርድርን ከመግፋት ይልቅ ፈትሾና አስፈትሾ፤ በማይፈታ ቃልኪዳን ተደራድሮ ለሃገርና የመከራ ዶፍ ለሚዘንብበት የሃገራችን ህዝብ ሲባል ሰላምን መቀበሉ አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ ነው። እንኳን ፋኖ ይቅርና ወያኔ ከአንዴም ሶስት ጊዜ የሚኒሊክ ቤ/መንግስትን ተመኝቶ ከመንገድ ነው የቀረው። ሃገራችን ኢትዮጵያ ከረሃብና ጠኔ፤ ከሰዎች ፍልሰትና መከራ የምትድነው በመሳሪያ በሚመጣ ሰላም አይደለም። በዲሞክራሲና በምርጫ በሚደረጉ የሃሳብ ፍልሚያና ክንዋኔ እንጂ። ዝንተ ዓለም መሳሪያ ይዞ እንዘጥ እንዘጥ፤ የራስን እህትና ወንድም እየገደሉና እያስገደሉ ፉከራ በምንም ሚዛን ለወገን መቆምን አያሳይም። አፍራሽን አፍራሽ እየተካው መትመምን እንጂ! እልፈተ ቢስ የሃበሻ ፓለቲካ መቼ ይሆን አይኑን ከፍቶ ሰውን በሰውነቱ የሚመዝነው? ሰላምን ከመሳሪያ ይልቅ የሚያስቀድመው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አላውቅም። አዋጅም ሆነ መንገድ መዝጋቱ ለሃበሻ ህዝብ አናታማ እንጂ በረከት አይደለም! የፋኖ አመራሮች ልብ ግዙ። ደም መፋሰስ ይቁም። ብልጽግናም ተመከር። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop