December 12, 2024
5 mins read

ከአህያ ውርንጭላ የበለጠ ለጅብ ልጅ ያዘነችው አህያ እጣ ፈንታ!

በላይነህ አባተ ([email protected])

ድሮ! ድሮ! ጥንት! ገና በጥኋት! እንግሊዝ፣ፈረንሳይና ጀርመን አገር ተመሆናቸው እጅግ እሩቅ ጊዜ በፊት! ነጋዴው ኮሎምበስም ወርቁን ሊያግበሰብስ ፓስፊክ ውቂያኖስን አቋርጦ “አሜሪካን አገኘሁ” ተማለቱ ረጅም ጊዜ በፊት በሰው መፈጠሪያዋ ኢትዮጵያ ሊቃውንት በሰምና ወርቅ በተዋበ ተረትና ምሳሌ እንዲህ እያሉ ትውልድን ያስተምሩ ነበር፡፡

6778u

ከእለታት አንድ ቀን አንድ የጅብ ልጅ ሞተና ሰማዩ ገና የአህያ ሆድ ሳይመስል አህያ መርዶውን ተረዳች፡፡ የራሷ ልጆች ሲሞቱ አፏን ተእንክርዳድ ተክላ ድምጥ የማታሰማዋ አህያ፤ ድፍን አህዮች ያለድብዳብ ቅርቀብ እየተጫኑ ጀርባቸው ምልጥልጥ ሲል “እኔ ተሞትኩ ሰርዶ አይብቀል”ን እየተረተች መስኳን “ቡርፍ ቡርፍ” እያደረገች ስትግጥ የኖረች አህያ፤ የራሷን ታፋ ጅብ እንደ ቡሄ ዳቦ እየከፈለ ሲገምጠው እንኳ ድምጥ የማታሰማ አህያ የጅብ ውርንጭላ ሞተ ስትባል ቀበሌው እስቲናጋና አገር ድብልቅልቁ እስቲወጣ “ኡ ኡ ኡኡ!” የሚል ጩኸቷን ለቀቀች፡፡ ይኸንን ጩኸት የሰሙ የሰፈሩ አህዮች “ምን ጉድ መጣ” እያሉ ተምትጮኽበት መስክ እንደደረሱ “ለቅሶ መድረስ የምትፈልጉ ተከተሉኝ!” ብላ ጋማዋን እንደ ነጠላ ዘቅዝቃና ፊቷን በወፍጥ ድንጋይ ነጭታ ልታስቀብር ወደ ጅቦች መንደር ነጎደች፡፡

አህዮ ተጅቦች መንደር ስትደርስና የጅብ ሐዘንተኞች የቆዳ በርኖሳቸውን ለብሰው ምድሩን አጣበውት ስታይ የሐዘን ሲቃ መንፈሷን በረዘውና ዛር እንደሚያስጎራው ተላይ ዘላ እየወደቀች መንከባለል ጀመረች፡፡ ይኸንን ያዩ ሐዘንተኛ ጅቦች ልቅሷቸውን አቋረጠው በአግራሞት ሲመለከቷት ጭራሽ ባሰባትና ጅቦችን ለመምሰል “አው እውውይ! አውውይይ!” እያለች ልቅሶዋን ለቀቀች፡፡

ስትመኘው የነበረውን ትኩረት ተጅቦች ያገኘችው አህያ፣ ለአህዮች ደንታ ሳይኖራት ለሌሎች እንሰሳት ወንፊት ልትጥድ የምትደርሰዋ አለማቀፋዊቱ አህያ የበለጠ የሐዘን ሲቃ ገፋፋትና እንዲህ ስትል የለቅሶ ሚሾዋን አወረደች፡፡

ምን እሩቅ ቢጮኹ ቅርብ ነው ድምጥዎ፣

ምን ጥቁር ቢበሉ ነጭ ነው ኩስዎ፣

አሁን የእርስዎን ልጅ ምን አገኘብዎ፡፡”

 

ይኸንን ሚሾዋን ስታወርድ ተከትለዋት የሄዱት አህዮችም እየዘለሉና እየነጠሩ አዳመቁ፡፡ የጅብ አዘንተኞች ግን አይናቸውን እንደ ጉርጥ ማጉረጥረጥ ጀመሩ፡፡ አይናቸውን አጉረጥርጠው ይመለከቱ ከነበሩት ጠብል ጅቦች አንዱ በምራቁ ላንቃውን ወለወለና “አሁን እንዲህ ብለሽ ይኸን የተረትሽ፤ የጅብ ሐዘንተኛ ምን ይብላ ብለሽ” ብሎ የመልስ ምቱን ሳይጨርስ የግድድሞሽ ንግግሩ ለአህያዋ ገባትና “አህያም ይሩጥ ጅብም ይዘርጥ!” ብላ የምታመልጠበትን መንገድ ማሰላሰል ጀመረች፡፡ ዳሩ ግን አህያዋ የምትወጣበትን መንገድ ስታሰላስልና ስታመነታ ከመቅጽበት በጅቦች የሰላ አቀንጣጤ ታርዳ ለጅብ ሐዘንተኛ ንፍሮ ተቀቀለች፡፡

ህሊና፣ ማተብና  ሃይማኖት ለሌለው ጅብ የሚያሸረግድ መጨረሻው የዚች አለሁ ባይ አህያ እጣ ፈንታ ነው፡፡ ከማይታወቅበት አገር ሄዶ “ቆርበት አንጥፉልኝ” ተሚል ጅብ፤ ሽምግልናን፣ ፍርድን፣ ኑዛዜን፣ ንስሀንና ሱባኤን ተማያውቅ ጅብ ስምምነንት፣ እርቅና ወዳጅነት ለማፍራት የሚንፈራገጥ መጨረሻው የዚች አህያ እጣ ፈንታ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሰባት ዓ..

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop