December 10, 2024
13 mins read

በትውልድ ግማሽ ትግሬ ግማሽ ኤርትራዊ ነው። ታሪኩ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነው

ከዚህ በታች ያለውን ጽሁፍ ጸሃፊው ቴክስት አድርጎልኝ ለብዙሃን አንባቢዎች እንዲዳረስ ፍቃዱን ጠየቅኩት:: እሱም ፈቃደኛ ሆኖ ኤዲት አድርጎ ላከልኝ:: በሰፊው መነበብ ያለበት ታሪክ ነው:: አንብቡት። አንባችሁም አሰራጩት።


ሰላም ውድ ዶ/ር ዮናስ፣ በቅርቡ ስለ ትግራይ ኤሊቶች ለመጻፍ እንዳሰቡ ሲያሳውቁ እኔስ እንደ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ምንድን ነው የሚሰማኝ የሚለውን ሳስብ ለምን ሃሳቤን ጽፌ አላጋራዎትም ብየ የሚከተለውን ጻፍኩልዎ።

እኔ ከኤርትራና ከትግራይ ከተገኙ ቤተሰቦች የተገኘሁና መሀል ሀገር የምኖር ተራ ዜጋ ነኝ። እዛ አካባቢ ካለፉት 30 ዓመታት (እኔ ልብ ብየ መከታተል ከጀመርኩበት ጊዜ) ጀምሮ እየሆነ ያለው ነገር፦ ጦርነቱ፣ ጥላቻው፣ እብሪቱ፣ ፍርሃቱ፣ ጭካኔው፣ ረሀቡ፣ ስደቱ . . . . በአጠቃላይ እብደቱ መጨረሻው ምንድነው? እንዴት ነው ይሄ ሁሉ አልፎ ሰላም የሚመጣው እያልኩ አስብ ነበር።

ይሁንና ትግራይ ላይ ከነበረው ጦርነት በኋላ መጀመሪያ ላይ ቤተሰቦቼን ለማየት በኋላ ደግሞ በስራ ምክንያት አብዛኛውን የትግራይ ከተሞችን ከጎበኘሁ በኋላ ያየሁትና የታዘብኩት ነገር በትግራይና በኤርትራ የወደፊት ሁኔታ ተስፋ እንድቆርጥ እንዲሁም በኢትዮዽያ የወደፊት እጣፈንታ አሁን እየሆነ ካለው ነገር ጋር ተደምሮ ከፍተኛ ፍርሃት እንዲያድርብኝ አድርጎኛል። ጦርነቱ የፈጠረውና ጥሎት የሄደው ጠባሳ እዛው ትግራይ ውስጥ ከነበረው ህዝብ በስተቀር ማንም የተረዳው አይመስለኝም።

ውድ ዶ/ር አሁን አምሳ ዓመት ሞልቶኛል። ከተወለድኩባት ዕለት ጀምሮ እዛ አካባቢ ጦርነት ተለይቶት አያውቅም። ትንሽ ሰላም እንኳ ሰፈነ ቢባል ከጦርነት ስጋት ጋር ነው የነበረው። የመጨረሻው ከአብይ መንግስት ጋር የነበረው ጦርነት ግን ለ17 ዓመታት ከወታደራዊው ደርግ እና በኋላ ላይ ከሻዕብያ ጋር ከተደረገው ጦርነት ጋር በፍጹም የሚወዳደር አልነበረም።

ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ኤሊት በህወሃት ላይ የነበራቸው ጭፍን ያለ መተማመን፣ ለአብይ መንግስት እና ለሻዕብያ ያሳዩት የነበረው ንቀት፣ ለራሳቸው የነበራቸው በጣም የተጋነነ ግምት እና ድንቁርና ላይ የተመሰረተው እብሪት ጦርነቱ በጣም የከፋ እንዲሁም የደረሰው አደጋ ማንም ሰው ከሚያስበው በላይ በጣም ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። ብቻ እዛ አካባቢ (በኤርትራም ሆነ በትግራይ) እንዴት፦

_ያ ሁሉ ጦርነት  ለምን ተካሄደ?

_ምን ዓላማ ለማሳካት ነበር?

_ጦርነቱስ ምን ውጤት አመጣ?

_ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ተጠያቂው ማነው?

የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቶ የሚጠይቅ ኤሊት ማየት አለመቻሌ፤ በተቃራኒው አህያውን ትቶ ዳውላውን እንደሚባለው የሁሉም ችግር  መንስኤ አንድ ብሄር ላይ ደፍድፈው ለበቀል በከፍተኛ ሁኔታ የተነሳሱና በጥላቻ ያበዱ ኤሊቶችን ማየቴ የወደፊቱ ሁኔታ ተስፋ እንድቆርጥ አድርጎኛል።

በተለይ ትግራይ ላይ 50 ዓመት ሙሉ ለየትኛውም የፖለቲካ ጥያቄዎች አፈሙዝ ብቻ ነው መፍትሄው ብሎ የሚያምንን የፖለቲካ ፓርቲ ለምን ብሎ የሚጠይቅ የተደራጀም ሆነ በግለሰብ ደረጃ አለመኖሩ ምን ያህል የትግራይ ህዝብንም ሆነ ኤሊቶቹን እንደጎዳቸው ገና በደንብ የተገለጠላቸው አልመሰለኝም።

ኤሊቶቹ በትግራይም ሆነ በኤርትራ ህዝብ መካከል በኢትዮዽያ ሀገረ መንግስት እና በቀድሞዎቹ መንግስታት ላይ የነበረውን የተለያየ አመለካከት ወደ አንድ ለማምጣት እና ህዝቡን ሞቢላይዝ ለማድረግ የተጠቀሙበት መንገድ ላለፉት ብዙ አስርት ዓመታት በሀገራችን የማያባራ ጦርነት እንዲነሳ፣ አንድ ብሄርን ታርጌት ያደረገ ጥላቻና ጥቃት እንዲኖር አድርጓል።

በዚህ አጋጣሚ ስሜቴን ስላነሳሱት ተራ ነገሮች የሚመስሉ ነገር ግን የዛን አካባቢ የእብደት ልክ የሚገልጹትንና ሁሌም ሳስባቸው የሚገርሙኝን ነገሮች ላካፍልዎት፡

የመጀመሪያው ደርግ መቀሌን ሲለቅ እዛው ስለነበርኩ የማይረሳኝ ነገር፤ ከእነርሱ በፊት የነበረው መንግስት እነሱንና ሻዕብያን ለማውገዝ በየአደባባዩ አቁሟቸው የነበሩት ቢልቦርዶች በቀለም ጠፍተው በምትኩ ደርግንና አንድን ብሄር ስሙን በመጥቀስ (ኢንተርቼንጄብሊ ሁለቱንም ይጠቀሙበት ነበር) የሚያወግዙ መፈክሮች ይጻፉ ነበር፣ በትግርኛ ቋንቋ በሬድዮ ጣቢያቸውም ሆነ በተለያዩ መድረኮች ብቻ በተገኘው አጋጣሚዎች ሁሉ ደርግን ጨምሮ የቀድሞ መንግስታትን በአንድ ብሄር ከረጢት ውስጥ ከተውና በጠላትነት ፈርጀው በህዝቡ ዘንድ ፍርሃትን ብቻ ሳይሆን ጥላቻንም ይዘሩ እንደነበር አስታውሳለሁ።

በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የአባቴ ቤተሰቦች በእብሪት ታውረው ጦርነት ሲጀምሩ በወቅቱ የነበረው ጠ/ሚያችን ”የአይናችሁ ቀለም  . . .” ብሎ እነሱን ሲያባርር እዚህ የሚኖሩ ቤተሰቦቼን ጨምሮ ገሚሱ ከዚህ በፊት ወደማያውቋት ኤርትራ ሲባረሩ፣ ገሚሱ ወደዛ ከምሄድ ብሎ ወደ ኬንያና ሱዳን ሸሸ። ቀሪው ግን በሚገርም ሁኔታ የመንግስትን እስር እና ማባረር ለመሸሽ እኔ ኤርትራዊ ሳልሆን የትግራይ ሰው ነኝ እያሉ ይከራከሩ ነበር።

የበለጠ የሚገርመው ኤርትራዊያን ላይ በደረሰው ያልተማሩት እነዚህኛዎቹ ከሃያ ዓመት በኋላ በአብይ መንግስት ላይ በእኔ እድሜ ከማውቃቸው ጦርነቶች ሁሉ የከፋውን ጦርነት አስነሱ። በተለይ ሁለተኛው ዙር ጦርነት ላይ ህወሃቶች ሸዋ ደርሰናል እጃችሁን ስጡ እያሉ ሲያስፈራሩ መንግስታችን ፓኒክ ሁኖ የእናቴን ወገኖች ሰብስቦ ማሰር ሲጀምር የተወሰኑት እንደኤርትራዊያን ወደ ኬንያና ወደ ሱዳን ሲሸሹ ቀሪዎቹ ግን የዛኔ የነበረውን ከፍተኛ የሆነ እስርና ማሳደድ ለመሸሽ እኛ ከትግራይ አይደለንም ኤርትራውያን ነን ይሉ ነበር።

ሶስተኛው የቅርብ ጊዜው ጦርነቱ ከመጀመሩ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ መቀሌ ሂጄ ነበርና ወንድሜ ተከራይቶ ወደሚኖርበት ቤት ለጥየቃ ስሄድ የዋናው መግቢያ የውጭ በር ላይ ቀለም የተቀባ ምልክት ስለነበር እንደዋዛ ይሄ ምልክት የምንድነው ብየ ብጠይቀው የሚገርም ነገር ነበር የነገረኝ። ለካ ወንድሜ ተከራይቶ በሚኖርበት ጊቢ ውስጥ የቤቱ ባለቤት ልጅ አሜሪካ ሲኖር አደጋ ደርሶበት የሚያስታምመው ሲያጡ መሰለኝ እዛ ያሉ ሰዎች ወደዚህ ልከውት እዚህ ከቤተሰቦቹ ጋር እየኖረ እያለ የአካባቢው የቀበሌና የደህንነት ሰዎች ትግራይ ላይ ስላለው አስተዳደርና ስለ ህወሓት ያለው አመለካከት እንደ አደገኛ ነገር ተቆጥሮ ለካ እነርሱ በሚያውቁት መንገድ እዚህ ጊቢ ውስጥ ለህወሓት ስጋት የሆነ ሰው አለ የሚል ምልክት ማድረጋቸው ነበር (ልክ ጀርመኖች በሒትለር ጊዜ የአይሁዳውያንን ቤት በቀላሉ ለመለየት እንዲቻል በር ላይ ያደርጉት እንደነበረው ምልክት ማለት ነው)።

በመጨረሻም ከ14 ወይም 15 ዓመታት በፊት ይመስለኛል ከወታደራዊው ደርግ መንግስት ጋር በነበረው ጦርነት የሻዕብያ ከፍተኛ የጦር መኮንን የነበረ በኋላም ምክንያቱን ባላውቅም በሂደት ሻዕብያን ትቶ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን የተቀላቀለ የአባቴ ቤተሰብ እና የእሱ የልጅነት ጓደኛውን እዚሁ አዲስ አበባ አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ አርፎ በአካል ሂጄ አግኝቸው ነበር።

በወቅቱ መለስ ዜናዊ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን አሰባስቦ አንድነት እንዲፈጥሩ የሚጥርበት ጊዜ ስለነበር አዲስ አበባ ይመላለስ ነበር። አንድ ጊዜ ምን አለኝ “እኛ ኤርትሪያውያን እና የትግራይ ብሄርተኞች በዛ ሁሉ መስዋዕትነት አመጣነው የምንለው መልካም ነገር እና ኪሳራው በፍጹም የሚመጣጠን አይደለም። በቀድሞ መንግስታት የተፈጸሙ እና ለትግላችን መንስኤ ናቸው ከምንላቸው ታሪካዊ በደሎች ጋር እንኳ የሚመጣጠኑ አይደሉም። ከአሁን በኋላ ግን ይሄንን እንቀይረዋለን።” ብሎኝ ነበር። ከዛ በኋላ የሆነውን ሁሉ ሲያይ ምን እንደተሰማው ባውቅ ደስ ይለኝ ነበር። ብቻ የእኛ ነገር በጣም ያሳዝናል!

የሚሰማኝን ነገር በዚህ መልኩ እንድገልጽ ስላነሳሱኝ አመሰግናለሁ

 

9 Comments

  1. ፒ ኤች ዲ ዮናንስ

    ደሞ ፍጹም ኢትዮጵያዊና ኢፍጹማዊ ኢትዮጵያ የሚል ነገረ ሰርቅ አመጣህ፡፡ አብይ አህመድንም እኮ ነቢይ ሙሴ መጣ ብለህ ነበር የለፈለፈውን ስምተህ፡፡ መቼ ይሆን ትምህርት የምትወስደው? እግዚኦ፡፡

  2. ዶር ዮናስ ይህ ትግሬ ብዙ ከሚያውቀው ቆጥቦ ይህንን ልኮሎታል ፡፡እርሶስ በምሁር እይታዎ የነዚህ ሁለት ትግሬዎች መጨረሻ ምን ይመስሎታል፡፡ አካባቢዬ የማየው ኤርትራዊ ትግሬ ሲያይ እንደ እብድ ያደርገዋል ትግሬዎቹ ደግሞ እንደ መሰልጠን ሲላቸው ኤርትራዊ ነኝ ይላሉ፡፡ በሁለቱ መሃል ያለው ነገር እንደ እኔ ከርቀት ነገርን ለሚመለከት አልገባኝ ብሏል፡፡ መለስ ዜናዊ በህይወት እያለ ኤርትራውያንን በአንድ በኩል ሲያብጠለጥል በሌላ በኩል እኔ እያለሁ ማን ይነካቸዋል ሲል ነበር፡፡ በቅርቡ ስብሃት ነጋም እንደማይሆን ሁኖ ተበለሻሽቶ የኢትዮጵያ መከላከያ ከጥልቅ ጉድጓድ በምቾት ቢያወጣውም እግሩን ቢያጥበውም አብይ ወደ አሜሪካ ለእረፍት ከላከው በኋላ በሰጠው ቃለ መጠይቅ የኢትዮጵያ ወታደር ፈሪ ነው የኤርትራ ወታደር ጎበዝ ነው ብሎ ቃለ መጠይቅ ሰጥቷል፡፡

    ትግሬ እንደ ዛሬው በነ መለስ ዜናዊ ኩልኩሎች እንደማይሆን ከመሆኑ በፊት ክብርና ታሪክ ነበረው ታሪኩን የሚያቆራኘው ከኢትዮጵያ ጋር ነበር ዛሬ ግን በአንድ በኩል አረብ ሰበከው በሌላ ወገን ደግሞ ሀገሪቱን መዝረፍ መጋጥ እንደ ህጋዊ የመኖር ዋስትና በመቁጠር በዘረፋ የኖሩበት ዘመን ዳግም ተመልሶ ይመጣ ይመስል በቅዠት ላይ ናቸው እንደ ማንኛውም ሰው መኖር ከበዳቸው ቁጥራቸውንም ከግምት መውሰድ ከበዳቸው፡፡ ዛሬ ወደ ኤርትራ የተወሰደው ባድሜ፤ይሮብ የነሱ ጉዳይ አይደለም ጉዳያቸው የአማራ ግዛትን ወስዶ ከእፍረት ለመገላገል ብር ብለው መገንጠልን ነው የፈለጉት እስቲ የሰውየውን ጽሁፍ መነሻ አድርገህ አደብ እንዲገዙ ምክር ቤጤ ብትለግሳቸው፡፡

  3. የትግራይ ኤሊቶች ለህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ተጎንብሰው ከትእምት (EEFORT) ጉርሻ ለማግኘት የወደቁ ለማኞች ናቸው። ከ 50 አመት በፊት የተሻሉ ነበሩ ለምሳሌ የኢህኣፓ፣ የህወሓት፣ የኢድዩ፣ ወዘተ ኤሊቶች ይከራከሩ ነበርና። በዚህ ኣስከፊ ጦርነት በተለይ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኤሊቶች ሁሉም (96%) ለማለት ይቻላል ህወሓት አሸንፎ የፈደራል ስልጣን ይቆጣጠራል ብለው ስልጣንና የትእምት (EFFORT) ሓብት ለመቀራመት ጦሩነቱን በመደገፍ፣ ቤታቸውን ሽጠው ገንዘብ ያዋጡ እንዳሉ ደረሰዋል፣ ተማርን የሚሉት እማ ለምሳሌ ለመተንተን ግዜ አገኘን ብለው ታሪካዊ እያደረጉ የህዝቡን ጭንቅላት ለጭካኔ አድርሰውታል። የዋሁ ገበሬ ለዚህ ሁሉ ርካሽ ፓለቲካ ጦርነት ከእህል እስከ ልጆቹ እንዲገብር ተደርጎ ኣሁን ውሃ የሚያቀርብለት ሰው አጥቶ ከቤቱ ተዘግቶ እየረገፈ ነው በአንጻሩ የህወሓት መሪዎችና ኤሊቶች ወርቅ እየሸጡ፣ ብረታ ብረት እየሸጡ፣ ማእድን አየሸጡ ኤሊትነታቸውን ለግዜው ተደራጅተዋል። የሚገርመው አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳለው ከወርቅ 17 ቢሉየን ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሁነዋል ሰዎስት (3) እጥፍ በኤርትራ ወደ አረብ አገሮች ተሽጠዋል፣ የትራንስፓርት ኤርትራ 35% ቀረጽ ወስዳለች ብለዋል። በውጭ ተረካቢው የመንጀሪኖ ወንድም አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲያልቅ ኤሊቶቹ መቸ ተቃውሞአቸውን ገለጹና?

  4. ፍሬ ፈርስኪ! ይህ ሃገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ነገር ግምሽ ኤርትራዊ ግማሽ ከትግራይ በሚል የፓለቲካ ውስልትና ተለብዶ መቅረቡ ለማጣፈጫ እንጂ እውነትነቱን የሃገራችን ህዝብ ከዘመናት ጀመሮ ያውቀዋል። አፍሪቃዊቱ ሰሜን ኮሪያ ኤርትራ ከ 30 ዓመት አፍራሽ ጦርነት በህዋላ ያተረፈችው ከዚህ ግባ የሚባል ቤሳ ቢስቲን ነገር የለም። ህዝቦቿ ለስደትና ለእስራት በየዓለማቱና በየስርቻው ተጥለው ነጻነት ነጻነት ቢሉት ነፋስ የበተነው ድቄት ነው። የሃበሻ ፓለቲካ ራሱን እያፈረሰና እየጠገነ፤ ጀግና ላልሆነው በስሙ ሃውልት እያቆመና እያወደሰ ያኔም አሁንም በፉቅቅም ሆነ በቁም እርምጃ በማዝገም ላይ ይገኛል። መሬት ላራሹ በማለት ደረታቸውን ለንጉሱ ጥይትና እስራት የሰጡት እነዚያ ብርቅዬ ልጆች በደርግ ተመንጥረው፤ ደርግም ሌላ መንጣሪ ለቆበት ተራፊዎችንና ለሃገር የሚያስቡ ምሁራንና እውቅ ሰዎች ወያኔ በመርዝ፤ በአፈና፤ በእስራት፤ በግድያ አፈር መልሰው አሁን በምድሪቱ ላይ የሚርመሰመሰው ለመኖር በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀስ ፍጡር ብቻ ነው።
    ይህ ድብልቅ ትውልድ አለኝ የሚለው የታሪኩ ጸሃፊ ማወቅና መረዳት ያለበት ወያኔና ሻቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸውን ነው። ከትግሬ ተወለድኩ፤ ከኤርትራ ተወለድክ መከራውን የጋራ የሚያደርገውም አንድ እንደነበርንና አሁንም አንድ እንደሆንን አስረግጦ ያሳያል። የብሄር ጥያቄ ያመጣው ውርጅብኝ በየሜዳው ሰውን እያስፎከረ እልፍ የትግራይን ልጆች አስጨረሰ፤ ሃገር ናደ፤ ህዝብ አበራዬ። አሁንም ያለፈው አልበቃ ብሎ ወያኔዎች እንደ ቄራ ውሻ እርስ በእርሳቸው ሲናከሱ መስማትና ማየት ምንኛ ያስጠላል? የሰው ልጅ እንዴት ባለቀ ሰአት ላለፈው ንስሃ ገብቶ ስልጣን በቃኝ ብሎ ለተተኪ ትውልድ አያስረክብም? ይህ በሻቢያና በወያኔ የፓለቲካ ስሌት ውስጥ ከቶ አይታሰብም። እኛ ብቻ ታጋይ፤ እኛ ብቻ ምጡቅ፤ በህዝብ ደም እየቀለድ መኖር!
    የሃበሻ ፓለቲከኞች ከሳዳም ውርደት፤ ከጋዳፊ ፍንገላ፤ ከደማስቆው የ 50 ዓመት መንግስት ድርመሳ የሚማሩት ምንም የለም። በራሳቸው ዓለም ስለሚኖሩ ዛሬም ጦርነትና ረሃብ ለእነርሱ ስልጣንና የመኖሪያ ብልሃት ዋና መንገዶች ናቸው። ልቤ የበለጠ የሚያዝነው የትግራይ ተወላጅ፤ የኤርትራ ተወላጅ የሆኑ የደም ሰዎችን ሲያሞካሹ ሳነብ ነው። አይን እያለው የማያይ፤ ጀሮ እያለው የማይሰማ፤ በእነዚህ አካባቢዎች የደረሰውንና የሚደርሰውን ግፍ የማይመዝን አንጎል ብልሹ ነው። የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ዝንተ ዓለም መከራ ሲያይ የኖረና የሚኖር ህዝብ ነው። እጃቸውን ለምርኮ ባነሱ ወታደሮች ላይ ታንክ የነዳ ትውልድ ለራሱም ሰላም የለውም ለሌላውም ሰላም አይሰጥም። የአረመኔ ስብስብ! ባጭሩ በእነዚህ ሰሜናዊ ክፍሎች ያለው የመከራ ዝናብ መሃል ሃገር ድረስ ዘልቆ እየገባ ዛሬ ላይ ሰው የማይነቀሳቀስባት በኦሮሞና በአማራ ብሄርተኞች የቡድንና የተናጠል ጠበንጃ አንጋቾች የምትታመስ ምድር አድርገዋታል። በዚህ ሁሉ አትራፊውም ማን ነው? ማንም! ጊዜው የእኛ ነው በማለት የብልጽግና የኦሮሞ ካድሬዎችንና ተለጣፊ ድርጅቶች ልክ እንዳለፈው ታሪካችን ሁሉ የቀረበላቸውን ሳያኝኩ በመሰልቀጥ ለከፋ መከራ ሃገራችን እየዳረጓት ይገኛሉ። በመጨረሻም በቅርቡ አንድ ሰው ደውሎ እንዲህ አለኝ። ዋው በሳምንት እኮ የደማስቆው መንግስት ተገለበጠ። ለእኛ ሃገር እንዲህ ያለ ጊዜ ይመጣ ይሆን አለኝ። እኔም ስማ ወዳጄ መንገዳቸውን ሳምንት ያደረገው ከህዋላ ያስከተሏቸው ሃይሎችና የዓለም የፓለቲካ ንፋስ ነው። በእነርሱ ጀግንነት የሆነ እንዳይመስልህ። ግራም ነፈሰ ቀኝ ኢራቅ፤ ሊቢያ፤ የመንና ሌሎችም የወሮበላ መፈንጫ እንደሆኑት ሁሉ የሶሪያም እድል ፈንታ ወደ ባሰ ባርነትና የመከራ ዝናብ እንዳይሆን እሰጋለሁ በማለት መለስኩለት። እሱም እንደ መቆጣት ብሎ የሚታየውን ትተህ የማይታይ ለምን ታወራለህ አለኝ። እውነት የቀረችው ከተደበቀው ጋር ስለሆነ ነው በማለት ቻው ቻው ተባብለን ነገራችን አበቃ። መሰንበት ለሚፈልግ (እድሜ ተችረን) የሃገራችን መዳረሻ ለማየት ያብቃን። ሌላው የዘርና የቋንቋ፤ የክልል ፓለቲካው ሁሉ ጊዜአዊ ውታፍ ነውና!

  5. ከትግሬና ከኤርትራ ቤተሰቦች የተወለደው ወንድማችን በደንብ የተገነዘበውንና ያጠናቀረውን ጽሁፍ በጥሞና አነበብኩት። ነገሩ የሚታወቅ ቢሆንም በቀጥታ ከሚመለከተው ሰው በዚህ መልክ ተጽፎ ሌላው እንዲያነበው ማቅረቡ በጣም ጥሩ ነው።
    አዎ ኢኤሌፍ፣ ቀጥሎ ደግሞ ሻቢያ ከኢትዮጵያ ነፃ መውጣት አለብን ብለው ትግል ሲጀምሩ የቱን ያህል የብዙ ሺሆችን ሰው ህይወት እንደሚቀጥፍ በደንብ የተገነዘቡ አልነበሩም። የመሰላቸው ካለብዙ ውጣ ውረድ ድል እንደሚያደርጉና የሚመኙትንም ነፃነት እንደሚቀዳጁ ነበር። በሁለተኛ ደረጃ የጦር ትግል ለመጀመር ሲያቅዱ ከተሳሳተ ትረካ በመነሳት ነው። ይኸውም የተለየ ታሪክ እንደነበራቸውና በኢትዮጵያ ግዛት ስር መጠቃለላቸው ወደ ኋላ እንዳስቀራቸው ነው። በተለይም የኤርትራ ኤሊቶች ያናፍሱ የነበረው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲወዳደሩ የቱን ያህል የሰለጠኑ እንደነበሩና ኋላ-ቀር ከሆነው ህዝብ ጋር በዝግታ ለመጓዝ እንደማይፈልጉ ነው። ስለሆነም የነበራቸው አማራጭ ነፃ መውጣት ነው። ትግላቸውን ለማቀነባበር ደግሞ ከተለያዩ የኢትዮጵያን አንድነት ከማይፈልጉ የውጭ ኃይሎች ዕርዳታ ማግኘት ነው። ይህም ተሳክቶላቸዋል። በሌላ ወገን ግን የኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅቶችም ሆኑ የኋላ ደግሞ ህወሃት ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተባብረው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የምትሆን አገር ለመገንባት ታጥቀው ቢነሱ ኖሮ ህዝባቸውን ከድንቁርናና ከድህነት በማላቀቅ ተከብረው መኖር በቻሉ ነበር። እንደዚህ ብሎ ለማሰብ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ምሁራዊ ብቃትነት ያስፈልጋል። ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድም ማሰብ ያስፈልጋል። ከኢኮኖሚና ከህብረተሰብ ዕድገት አንፃርም ትክክለኛው መንገድ የሀዝብ ብዛትና ይህ ዐይነቱ ህዝብ ኃይሉን ሲያጣምርና ሲሰራ ሰፋ ያለ ብሔራዊ ሀብት ሊፈጥር እንደሚችል ታሪክ ያረጋግጣል። ይህንን ዐይነቱን የተቀደሰ መንገድ ለመረዳት ያልቻሉት የኤርትራና የትግራይ ነፃ አውጭ ኃይሎች ትናንሽ አገር በመመስረት ዕድገትን ለመጎናፀፍ የሚችሉ መስሏቸው ነበር። እንደምናየው ህልማቸው የውሃ ሽታ ለመሆን በቃ። ለዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት ደግሞ ድንቁርና ነው። ጭንቅላት ከተዳፈነ ማሰብ ስለማይችል በጭፍን በመመራት የሰውን ህይወትና ሪሶርስን መጨረሽ ነው።
    ወደ ሌላው መሠረታዊ ጉዳይ ስንመጣ ሻቢያም ሆነ ወያኔ የህብረተሰብን ታሪክ የተረዱ አልነበሩም። ለመረዳትም የሚፈልጉ አይደሉም። ያሰቡት ከጭንቅላት ስራና ከምርምር ይልቅ በጉልበት በመመካት ነፃ መውጣት አለብን በሚለው ላይ ነው ያተኮሩት። ይህ በራሱ ደግሞ ራሳቸውንም ሆነ የተቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። አንደጠላትም እንዲተያዩ በመደረግ አለመተማመን ሊፈጠር ችሏል። አለመተማመን በሰፈነበት አገር ደግሞ አንድን አገር በጋራ መገንባት በፍጹም አይቻልም። የኤርትራም ሆነ የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅቶች ተበድለናል፣ ተጨቁነናልም ብለው ሲያወሩ በጊዜው የነበረው ኋላ-ቀር አስተዳደር ሁሉንም የበደለ እንደነበር የሚታወቅ ጉዳይ ነው። በሌላ ወገን ግን ያልተስተካከለ ዕድገት ቢኖርም በጊዜው በነበረው ስርዓት ይበልጥ ተጠቃሚዎች ኤርትራውያን ነበሩ። በኢኮኖሚም ሆነ በማህበራዊ ስታተስ የተሻለ ቦታ ነበራቸው። ትላልቅ ሹመትንም የተከናነቡ ነበሩ። ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ በአፄ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመን እንተ ከዚኸኛው ብሔረሰብ የወጣህ ስለሆንክ የመማር፣ በሙያ የመሰልጠንና በስራ የመቀጠርም መብት የለህም በመባል ወደ ኋላ የተገፈተረ ብሔረሰብ አልነበረም። ይሁንና በተሳሳተ የኢኮኖሚና የትምህርት ፖሊሲ አማካይነት ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማምጣት በዚያው መጠንም በሁሉም ክፍለ-ሀገር በእኩል ደረጃ ዕውቀትን ማስፋፋት አልተቻለም።

    ባጭሩ በአፄ ኃይለስላሴ የአገዛዝ ዘመን ካለማወቅ የተሰራው የፖለቲካ ስህተትና ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ ለማሰብ አለመቻል ለጦር ትግል አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር ችሏል። የጦርነት ትግል ሲጀመር ደግሞ አውሮፓ፣ አሜሪካና፣ በኋላ ላይ ደግሞ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ ቀድመውን ለመሄድ ችለዋል። በሌላ ወገን የኛን ኋላ-መቅረት በመገንዘብ የከፋፍለህ ግዛው ፖለቲካ ያካሄዱብን አሜሪካና የተቀሩት የአውሮፓ አገሮች ናቸው። ሻቢያ፣ ህወሃትና የኋላ ላይ ደግሞ ኦነግ በነፃነት ስም ጦርነት ያካሄዱት ለአሜሪካና ለአውሮፓውያን ነው። ወያኔም ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የጎሳ ፌዴራሊዚም ተግባራዊ ሲያደርግ የጠቀመው አሜሪካንና የተቀሩትን የኢምፔሪያሊስት ኃይሎችን ነው። የኢኮኖሚ ፖሊሲውም ዋሽንግተን ተረቆ የመጣና ለድህነትና ለጥገኝነት የዳረገን ነው። ዞሮ ዞሮ በአጉል ትረካና በድንቁርና መንፈስ የሚካሄድ ትግል ሁሉንም ነው ደሃ የሚያደርገው። በትግራይ፣ በኤርትራና በተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት የሚታየው ድህነትና መዝረክረክ የዚህ ዐይነቱ የድንቁርና ውጤት ነው። በተለይም የትግራይና የኤርትራ ኤሊቶች ጭንቅላት በተበላሽ መልክ የተቀረጸና በዚያው የደነደነ ስለሆነ መፍትሄ የሚገኝለት አይደለም። እየተፋጠጡና ጦርነት እያካሄዱ መኖር ነው። ወያኔም ሆነ ሻቢያ ካለጦርነት ለመኖር እንደማይችሉ አረጋግጠዋል። ባጭሩ የኢትዮጵያ ጉዳይ በቀላሉ መፍትሄ የሚገኝለት አይደለም።

  6. እንደ እውነቱ ከሆነ ኤርትራውያን ለኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ሊሰጡ ይገባል ዛሬ በየትኛውም ሃገር ባእድና ባይተዋር ናቸው እንደ ልባቸው ጸጉር አጎፍረው፤ስራ ሰርተው፤ሰው አግተው ጥላቻቸውንና ጥልፍልፋቸውን የሚከውኑባት አገር ኢትዮጵያ ነች፡፡ ዛሬ ታክሲ ነጅ፤ ቤት አከራይና ሻጭም ሁነው እየኖሩ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁሉ ድሎታቸው ጥላቻቸው አሁንም እንዳለ ነው፡፡ አልፈው ተርፈው ሃገሬውን መናቅ፤ማዋከብ በሳዋ የሰለጠኑበትን ጥላቻ ተግባራዊ የሚያደርጉበት ሃገር ኢትዮጵያ ሁናለች፡፡ ዛሬ በኤርትራ ክ70 አመት በላይ ያለው ዜጋ ብቻ ሲኖር ቀሪው ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ 30 አመት ደም አፈሰሱ ይህ አልበቃ ብሎ ዛሬም በጥልፍልፍ አገር ያምሳሉ፡፡ይህ ነገር መፍትሄ ቢፈለግለት መልካም ነው የጥልያንና የአረብ ተረትን ወደዛ ብለው ኢትዮጵያ አገራችን ብለው ከኖሩ መልካም ካልሆነ ግን ሁለት ወዶ መኖር አግባብ አይሆንም፡፡ ህዝቡም በነሱ በኩል ያለው ነገር እንዲገለጽለት ያስፈልጋል፡፡ መከራችንን ሲያበዛው ትግሬ የሚባል ጎሳ መሃል ላይ ተስንቅሯል፡፡

  7. አንድን ሰው ሰው የሚያሰኘው በሁለት እግሩ ቆሞ ስለሄደና ሙሉ አካልም ስላለው ብቻ አይደለም። አንድን ሰው ሰው የሚያሰኘው የማሰብ ኃይሉን የሚጠቀምና ሎጂካሊም የሚያስብ ከሆነ ብቻ ነው። እንደሚታወቀው ጤናማ ጭንቅላት ያለው ሰው የተለያዩ ባህርያት አሉት። ለሌላው ያስባል፣ ስህተት ከፈጸመም ይፀፀታል። ያዝናል፣ ይረዳል፣ ይናፍቃልም። ስለሆነም የሰው ልጅ ባህላዊም ነው። ራሱን የሚገልጸው ከዚህ ጎሳ የተወለድኩኝ ነኝ በማለትና ሌላውን በመናቅ ሳይሆን የአንድ ህብረተሰብ አካል መሆኑን የተረዳ እንደሆን ብቻ ነው።
    ከዚህ ሀቅ ስንነሳና ሌሎች መስተፍርቶችን ስንጨምርበት የኤርትራና የትግራይ ኤሊቶች እነዚህን ከላይ የሰፈሩትን መስተፍርቶች የሚያሟሉ አይደሉም። ውድ ወንድሜ ከላይ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩና የመስራት ዕድልም እያላቸው አሁንም የተቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ይንቃሉ፣ ይሳደባሉም። ለምሳሌ እኛ በየቦታው ተበታትነን በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካን የምንኖር ኢትዮጵያውያን በመጀመሪያ ደረጃ የየአገሩን ህገ-መንግስት ማክበር አለብን። የማናከብርና ከባድ ወንጀልም ስንሰራ ብንገኝ እንደየሁኔታው እንታሰራለን። በተደጋጋሚም የምንፈጽም ከሆነ ከአገር እንባረራለን። ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ የሚኖርበትን አገር ህዝብ ማክበርና፣ እንደየአስፈላጊነቱም በተለይም ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሽማግሌዎች፣ ጎረቤት ለሆኑ መለገስ አለበት። ይህንን የማናደርግ ከሆነ እንደ ሰው መቆጠር አንቸልም። በነገራችን ላይ ፈልገን ስለመጣንና አገራችንም የማናገኘውን ዕድል እዚህ ለማግኘት በመቻላችን እያመሰግን መኖር አለብን።
    ወደ ትግሬዎችና ኤርትራውያን ጋ ስመጣ ሁሉም ባይሆኑ በተለይም ሻቢያና ወያኔ መንፈሳቸውን መርዘው ያሳደጓቸው በጣም ብልሹና የስልጣኔ ጠንቅም የሀኑ ወጣቶች አሉ። እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን አገርቤት በነበርኩበት ዘመናት እንደ ወንድም የምንተያይ ኤርትራዊ ጓደኛ ነበረኝ። እዚህም ከመጣሁ በኋላ እናቴን ይረዳ ነበር። በይበልጥ ግኑኝነቱም ከተለያዩ ብሔረሰቦች ጋር ነበር። አዚህ ጀርመን አገር ከመጣሁም በኋላ ሶስት ኤርትራውያን ጓደኞች ነበሩኝ። በጠባይ ሁሉም ግሩሞች ነበሩ። ለማለት የምፈልገው ሁኔታው ስለተለወጠና በአገራችንም ያለው አገዛዝ የራሱን ህገ-መንግስት ስለማያከብርና ባህልም ስለሌለው ማንም እንደፈለገው ይፈነጫል። ህዝባችንንም ይንቃለ፣ ይሳደባልም።
    ስለሆነም ወደፊት በአገራችን ምድር ሌላ አገዛዝ ስልጣን ሲይዝ አዲስ ህገ-መንግስት በማርቀቅ ህግን የማያከብር ከአገር መባረር አለበት። የኤርትራ ዜጎችና የትግራይ ተወላጆች የሚያስቸግሩና ለስራም እንቅፋት የሚሆኑ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም። የኤርትራው ጉዳይ ግልጽ ነው። ነፃ ወጥተናል ብለዋል። የትግራይ ጉዳይ ያስቸግራል። ይህንንም ቢሆን መስመር ማሲያዝ ይቻላል። ትግራይ እንደ ነፃ መንግስት ሆኖ የሚንደላቀቅበት ምክንያት የለም። እንደማየው ከሆነ ወያኔዎችና የተቀረው የትግራይ ኤሊት እየረበሹና እየዘረፉ ለመኖር የሚፈልጉ ናቸው። ይህ ባህርያቸው ደግሞ ለዕድገትና ለስልጣኔ ጠንቅ ነው። ስለሆነም ያለው አማራጭ ትግራይ ነፃ እንዲወጣ በማድረግ ወደተቀረው ግዛት እንዳይገቡ በዲንጋይና በሽቦ ማጠር ነው። ሰዎቹ በባህርያቸው የተበላሹና ከሌላው በመጋባትና የሌላውን ባህል በማክበር አብረው ለመኖር የማይችሉ ስለሆነ እየተረባበሹ መኖር ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ዕድገት ጠንቅ ነው። የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም እንዲኖርና እንዲሻሻልም ከተፈለገ ያለው አማራጭ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ጋጠወጥነት የጤናማ ሰው ባህርይ ስላልሆነ ህዝባችን በጋጠወጤዎችና በዘራፊዎች መሰቃየት የለበትም።

    • ዶ/ር ትክክል አስቀምጠኸዋል እብሪታቸው ተንኮላቸው ሰማይ ነካ ሁለቱም ትግሬዎች ዋናው ስልታቸው የአንድነቱን ሃይል መፈልቀቅ፤አንዱን በኣንዱ ላይ ማስነሳት ነው፡፡ ህዝባችን ብሄራዊ አንድነቱን ስላጣ ነጋዴዉም ሹሙም እነሱ ይሆናሉ ባለፈው አንዱን ኢትዮጵያዊ “የድሃ ልጅ ብሎ ሲሰድበው” ሰምቼ እንዳልናገር ብዙ ነገር እንዳልሞክር የተለያየ ነገር ይዞኝ አንገቴን አቀርቅሬ ተመለስኩ፡፡ ጫማ ቤት ገብተው ለእንጀራው ያደረውን ሴልስ ማን ሲጨማለቁበት አይቼ “ስነ ስርአት እንዲህ ያለ ጫማ አስመራ አይታችሁ ታውቃላችሁ ወይ” ብዬ ብስጭቴን ገለጽኩ ይበዛል በጣም ይበዛል፡፡ አዲስ አበባ ያለ ህንጻ አምባዬ ህንጻ፤ገ/መድህንና ልጆቹ፤ ገስት ሃውስ ጠቅላላ የትግሬ ካፌ የኤርትራና የትግሬ ነው ይህ ሁሉ ሁኖ አሁንም ባለፈው ወንጀላቸው ተጸጽተው ህዝቡን እንደመካስ አጥንትህን ካልጋጥን ይላሉ፡፡ ከዚህ የሚወረወርላቸውን ስሙኒ በመጠቀም ምን ያህል ሲስተሙን ኮራፕት እንደሚያደርጉት ሳትሰማ አትቀርም፡፡ አባቶቻቸው በሰሩት ስህተት፤ከሻቢያና ከአረብ ከምእራቡ ጋር ሁነው በሰሩት ስራ አፍረው በማቀርቀራቸው ለነሱም ሆነ ለኛ የሚበጀው መገንጠላቸው ነው ስለዚህ የመገንጠል ጥያቄ ከነሱ ሳይሆን ከእኛ ቢቀነቀን መልካም ነው፡፡

  8. ዶር ዮናስ ብሩ ክስ ቀርቦብሃል https://ethiopiansemay.blogspot.com/ይህን ነገር አንብበህ ኦፊሴላዊ መልስ ስጥ፡፡ ግማሹ የአብይ አማካሪ ነበርክ ይልሃል፡፡ ሸኔ በአማራው ላይ የሚያደርሰውን ግፍ አደብዝዘህ ፋኖ አትግደሉኝ ብሎ እራሱን አባትና እናቱን ለማዳን ወደ በረሃ በመውጣቱ ከነ ፕሮፌሰር መሳይ ጋር ሁነህ በተዛባ ሚዛን አውርደህ ትጥለዋለህ፡፡ የአንትንም ሆነ የመሳይን ምክንያታዊነት ስናዳማጥ ዶር እና ፕሮፌሰር የሚል ቅድመ ስም ማእረግ ከማንጠልጠላችሁ በስተቀር የናንተ ልጆች ከሆኑት ወጣቶች አስተሳሰባችሁ፤ምክንያታዊነታችሁ፤የታሪክ እውቀታችሁ ብዙም አጥጋቢ ሁኖ አላገኘነውም፡፡

    በእርግጥ ስሙኒ መሰብሰቢያ ሞገስና ርእዮት በተባለች ሴት አማካይነት አዘጋጆቹ እናንትን በመጠቀም ስሙኒ ሲሰበስቡ እናንተ ደግሞ በምትሰጡት አስተያየት ከእናንተ ባነሱ ሰዎች በየጊዜው ሚዛናችሁ እየቀለለ ማየት ያሳስባል፡፡ አንተም ሆንክ መሳይ ከኦሮሞ ሼል ወጥታችሁ ለሃገር አንድነት ቁሙ፡፡ ከዚህ መስመር ከወጣችሁ ዛሬ ነበልባል የሆነ አገር ወዳድ ትውልድ ስለተፈጠረ ዋጋችሁ እየቀለለ ባነሳችሁት ሃሳብ እየተመከታችሁ አፍራችሁ ትኖራላችሁ፡፡

    ነጻ ሃሳብን ብናክብርም ከገዳይ ጋር ሁናችሁ ገዳይ የሆነ ርእዮተ አለም በገሃድም ሆነ በስውር እናራምዳለን ብትሉ ውርድ ከራስ ነው ከእውነተኛ ምሁራን ጋር ቀርባችሁ ላብ ላብ ሲላችሁ አይተናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop