መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም
ከ 48 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት
ንጉሰ ነገስቱ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ የተቋቋመው የደርግ አባላት በቀረበው ትዕዛዝ በሻለቃ ደበላ ዲንሳ የተነበበላቸው ደብዳቤ
ሻለቃ ደበላ ዲንሳ ለንጉሱ ሰላምታ ካቀረቡ በኃላ ንግግራቸው ጀመሩ
ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኖረው ዘውድ ህዝቡ በቅን ልቦና የአንድነት ምልክት ነው ብሎ የሚያንበት ቢሆንም ከ ሃምሣ አመታት በላይ ከአልጋ ወራሽነት ጀምረው ሃገሪቷን ሲመሩ ከህዝብ የተሰጦዎን ክብር ስልጣን አልአግባብ በልዩ ልዩ ጊዜ ለራስዎና በአካባቢዎ ለሚገኙት ቤተሰቦችዎና ለግል አሽከሮችዎ ጥቅም ላይ በማዋል ሃገሪቷን አሁን ላለችበት ችግር ላይ እንድትወድቅ ከማድረጎም በላይ እድሜ ሰማንያ ዓመት በመሆኑ በአካልም ሆነ በአዕምሮ በመድከመዎ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን ሃላፊነት ሊሸከሙ አይችሉም።
ንጉሠ ነገሥቱ:
ያላችሁትን በጥሞና አዳምጠናቹኃል። ለሀገር በጎ አስባችሁ ከተነሳችሁ የአገር ጥቅም ከራስ ጥቅም ማስቀደም አይቻልም። እኔ እስከ ዛሬ አገራችንና ህዝባችንን አቅማችን በፈቀደውና በምንችለው ሁሉ አገልግለናል። አሁን ተራው የኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ
ሻለቃ ደበላ ዲንሳ:
ለግርማዊነትዎ ሲባል ሌላ ቦታ የተዘጋጀ ስለሆነ ወደ ተዘጋጀልዎ ስፍራ እንዲሄዱ እጠይቃለሁ ።
ከዚያም ከቤተመንግስት በቮልስ ዋገን መኪና ኮሎኔል ዳንኤል አስፋው በመሾፈር ወደ ተዘጋጀላቸው ስፍራ ማለትም ወደ አራተኛ ክ/ጦር ተወሰዱ።