በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አምባሳደር ነው !!
ሹሞቻቸውን በስልጣን ላይ የማያበረክቱት የብልጽግናው መሪ ዐቢይ አህመድ አሊ በ6 ዓመታት ውስጥ ሹመው የሻሯቸው ባለስጣናት ብዛት ካለፉት 60 ዓመታት ሹም ሽር ጋር አቻ ነው የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡
ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ስልጣናቸውን ስለማያምኑ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች “አንድ ባለስልጣን በአንድ መስሪያ ቤት ላይ ከሰነበተ ያሴርብኛል” የሚል ፍራቻ አላቸው ይላሉ፡፡
በዚህም የዐቢይን የሹም ሽረት ዜና መስማት ከችግኝ ተከላቸው ዜና የተለየ ክብደት እንደሌለው ይነገራል፡፡
ከዓመት በፊት ከውሃና መስኖ ሚኒስቴርነት አንስተው በፍጹም አረጋ ቦታ የሾሟቸውን ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡
ታዲያ በወቅቱ ሮሃም ምንጮቿን ዋቢ በማድረግ ዐቢይ ኢንጂነር ስለሺን በሌንጮ ባቲ ለመተካት ማቀዳቸውን ዘግባ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ አሁን ላይ የሮሃ የውስጥ ምንጮች ባደረሱን መረጃ መሰረት የአሜሪካ መንግስት በዐቢይ የተሾሙትን አቶ ሌንጮ ባቲን መቀበል አልፈቀደም፡፡
በዚህም አቶ ሌንጮ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
#Ethiopia #Washington D.C በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የ #ኢትዮጵያ ኤምባሲ “በኦሮሚያ ብልጽግና ስዎች የተሞላ፣ የኦሮሚያ ብልጽግና ጽ/ቤት እንጂ [“የኢትዮጵያ”] የሚባል ገጽታ የለውም” ። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ከህወሃት ዘመን ከነበረው… pic.twitter.com/CIegTvMDBI
— Neamin Zeleke (@NeaminZeleke) August 29, 2024
ይህም ሰውዬውን በኢትዮጵያ ታሪክ በተሾሙበት አገር መንግስት ተቀባይነት ያጡ የመጀመሪያው ሰው ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም ከንጉሱ ጊዜ ጀምሮ የታፈረና የተከበረ የነበረውን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዝቅ ያደረገ ሁነት ነው፡፡ በተጨማሪም አገዛዙ ምን ያህል የዘቀጠ የዲፕሎማሲ ቅርቃር ውስጥ አገሪቱን እንደከተታት አንዱ ማሳያ ሆኗል፡፡
ከቀጠናው እስከ አለም አቀፉ መድረክ የተናቀውና ፣ የተገፋው የብልጽግናው አገዛዝም ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከነበረበት ከፍታ አውርዶ በዳዴ እያስኬደው ነው፡፡
የሚገርመው ደግሞ ሮሃ ባደረገችው ማጣራት ሌንጮ ባቲ የጾታዊ ትንኮሳዎች እና ሌሎች ተያያዥ ክሶች የነበሩባቸው በመሆኑ ነው የአምባሳደርነት እውቅና ማግኘት ያልቻሉት፡፡
ይህም ስርዓቱ ለጾታዊ ጥቃት ያለውን ቦታ በግልጽ ያሳየ ሆኗል፡፡ ታዲያ በህጻን ፌቨን መደፈር የአዞ እንባ ያነቡት የስርዓቱ ቁንጮዎች እነ አዳነች አቤቤ ሌንጮን ከእነ ነውራቸው ለአምባሳደርነት ሲልኩ ግን አልኮሰኮሳቸውም፡፡
ስለተደፈሩ ሴቶች ሲጠየቁ “እነሱ እኮ የተደፈሩት በወንድ ልጅ ብልት ነው፣ አታካብዱ ” ያሉት አብይ አህመድ በጾታዊ ጥቃት የተወነጀሉትን ሌንጮ ባቲን ሾመው መላካቸው ምንም እንኳን የሚያስገርም ባይሆንም ሃገርን አንገት የሚያስደፋ ተግባር መሆኑ ግን የማይታበይ ሃቅ ነው፡፡
ዐቢይ ሌንጮን ከሳዑዲ አረቢያ አንስተው ወደ አሜሪካ መውሰድ የፈለጉት እንደ አሜሪካ ያሉ ወሳኝ አገሮች ላይ የስርዓቱን ታማኞችና ባለቤት የሚሏቸውን መሰግሰግ ስለፈለጉ ነው የሚሉ መረጃዎችም አሉ፡፡ ሮሃም በጉዳዩ ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡
#አይይይ_ሰላም….. pic.twitter.com/YH3imKVGOQ
— Son of Menelik (@Abebaw_Menelik_) August 28, 2024