August 28, 2024
3 mins read

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮን በምክትል ስራ አስፈፃሚነት የሚመራው የብልፅግናው ሹም በቁጥጥር ስር ዋሉ

Amhara Media Amicoየፋኖ ብርቱ እንቅስቃሴ ደግሞ በአማራ ህዝብ ገንዘብ ተቋቁሞ የብልፅግናውን መንግስት የጥፋት አዋጅ እያራገበና የጥፋ አዋጁን እያስፈፀመ ያለውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮን በምክትል ስራ አስፈፃሚነት የሚመራው የብልፅግናው ሹም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል ዝርዝሩን ይዘነዋል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከስሙ በስተቀር ለአማራ ህዝብ የሰራውና የፈየደው አንድም ነገር እንደሌለ ግልፅ ነው፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአማራ ህዝብ ገንዘብና በአማራ ህዝብ ስም የተቋቋመ ቢሆንም እያደረገ ያለው ተግባር ግን ለጠላት ተግባር ማስፈፀሚያና የአማራን ህዝብ የጥፋት አዋጅ ማስተግበር ሆኖ ቀጥሏል።

ይህን ተግባሩን እንዲያቆምና ከብልፅግናው ቡድን በላይ የኦሮሙማው ሙቭመንት አስተግባሪና አስፈፃሚ ካልሆንን የሚሉ የራሱ የአማራው ተወላጅ የአሚኬ ብአዴኖችን በአማራ ፋኖ ተደጋጋሚ መልዕክት ቢሰጣቸውም በእንቢታ ቆይተዋል።

በዚህ የጥፋት ተግባራቸውም በርካታ ንፁሀን በብልፅግናው ቡድን ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲረሸኑ በዝምታ እያለፉ በአማራ ህዝብ እንባና ደም ለብልፅግናው ቡድን እስክስታ ሲወርዱ የነበሩ ብአዴናውያን በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።

ከነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው አሁን የተያዘው የአሚኮ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አንተነህ መንግስቴና የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ደምሳቸው ፈንታ ተይዘዋል።

ተደጋጋሚ ተቋማዊ ማሻሻያ እንዲደረግና በፋኖ ሀየረሎች ላይ በተቋሙ በኩል ያለው ፋኖን የማጥላላት ዘመቻ እንዲቀንስ ተደጋጋሚ መልዕክት የደረሰው አቶ አንተነህ መንግስቴ አሁን ላይ በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

በህዝብ ንብረት የተቋቋመው ድርጅቱ ለአማራ ህዝብ ክብርና ጥቅም የቆሙ ሰራተኞቹን በደመወዝና በአገዛዙ ወታደሮች ከማስፈራራትና ከማሳደድ ሳይቆጠብ አሁንም የአማራን የህልውና ትግለወ እንዳራከሰ ቀጥሏል ያሉት የትግሉ ሰዎች አሁንም የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop