August 1, 2024
13 mins read

ሸህ መሃመድ አላሙዲን ጨክነው ይመለሱ ይሆን?  ሰመረ አለሙ

Mohammed Al Amoudiእኝህ በፎቶግራፉ የሚታዩት ከበርቴው አላሙዲ ከረጂም እገታ በኋላ ለመመለሳቸው በሶሻል ሚዲያና  በአርቲስት ተስፈኞች በስፋት ሲናፈስ ከርሞ አዲስ አበባ መምጫቸውን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። የእኝህ ከበርቴ እገታ እኛው አገር በኦነግ ሸኔና በመንግስት ከሚደረገው ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ካሁን በኋላ በሃገራችን የሚደረገውን እገታ ሸሁ አጥብቀው ይጠየፉታል ብለን እናምናለን።

ዶር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጡ አዲስ አበባ መቀመጥ በጣም ጠልተው ነበር መሄድ ነው መሄድ ነው ማውራት ነው ማውራት ነበር። የሃገር ቤቱ ሲሰለቻቸው ወደ ውጭ በመሄድ  በሳውዲ ባደረጉት ጉብኝት ቢንዛይድን አነጋግሬዋለሁ ዛሬ ወይም ነገ ሸህ አላሙዲ ወደ አገራቸው ይመጣሉ ብለው ነግረውን የሸሁን መምጣት ለሚጠብቁ ታላቅ ፈንጠዚያ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የ ጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄ  ይፈታልኝ ይሁን ትንሽ እሹልኝ  በቦታው ስላልነበርን እውነታውን  መመስከር አልቻልንም ያ ባይሆን በነጋታው ይመለሳሉ የተባሉት ሰው እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ? መቼም ብዙ ነገር ካየን በኋላ ዶር አብይን ማመን እጅግ ከብዶናል እንዳጋጣሚ ሁኖ አንዱም እውነትነት አልታየበትምና።

 

በእርግጥ የጀማል ካሾጊን የመሳሰሉ የሃገሩን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ  አምላክ የፈጠራትን ነብስና ስጋ ከታትፎ ገድሎ አላህ አኩበር ከሚለው አረመኔ መንግስት በኢትዮጵያ አምላክ እገዛ ተርፈው ወደ ተስፋይቱ ምድር ኢትዮጵያ ከተመለሱ እንኳን ደስ አሎት ሊባሉ ይገባቸዋል። ፡፡ የሸሁን መፈታት ተከትሎ ለአቀባበላቸው 600 000 ዶላር የሚፈጅ ሮልስ ሮይስ መኪና ወደ ጉምሩክ ደርሶ  የኦሮሙማ ባለ ስልጣኖች ይህ ለከፍተኛ የኦሮሙማ መስፍኖች ካልሆነ አንለቀም በማለት ትልቅ ውዝግብ ፈጥረው እንደነበረ በሚዲያ ተመልክተን ነበር።  እንግዲህ የኦሮሞ ከፍተኛ ባለስልጣን ማለት ወይ ሽመልስ አብዲሳ ወይ አብይ መሃመድ መሆኑ ነው። አረጋ ከበደን ሙስጠፌ መሃመድን አወል አርባን….. ማን ሰው ብሏቸው።

የአዲስ አበባን ነዋሪ ሲፈልጋቸው ሲቀሙ፤ ሲያንገላቱ፤ሲገድሉ  እንደከረሙ ሁሉ የሸሁን ንብረት መቀማት አሁን ላለባቸው ለዶላርና ተመሳሳይ ችግር ክፉ አደጋ ላይ የሚጥላቸው መሆኑን የኦሩሙማው ባለ ስልጣኖች ስለ ተረዱ እርምጃቸውን አዘግይተውታል። ሆኖም የአይን እማኞች እንደሚሉት መኪናውን በማይገባ አጠቃቀም እኛም እንሞክረው፤ መሪውን ይዘን ፎቶ እንነሳ በሚል ጅልነት አውቶሞቢሉ ውስጥ ተራ በተራ በመግባት አውቶሞቢሉን ስላጎሳቆሉት የመጀመሪያ ይዞታውን አለመያዙን በስፋት ይወራል፡፡ ይህ እንኳን ብዙ ቁም ነገር ያለው ባይሆንም የዘመኑ ባለስልጣኖች ነገር ስራቸው ሁሉ ለአቅመ አገር ለማስተዳደር እንደማይበቁ ለማሳየት በማዳበያነት የቀረበ ነው።

ሼህ አላሙዲ የሚዲያና የውይይት ቀልብ ይስባሉ ስለ ልግስናቸው የሚወራው መቼም አይጣል ነው። አቶ እከሌን መጨበጣቸውን የተመለከት ወሬ አናፋሽ ባይኔ በብረቱ አየሁ እድለኛውን ኬሻ ሙሉ ብር አሸክመው ላኩት ይላል፡፡ በመንገድ ሲያልፉ የወጣቱ ጥረት ስለሳባቸው ወደ ባህር ማዶ ልከው አስተምረውት የአንዱ ድርጅታቸው ስራ አስኪያጅ አድርገውታል ይልሃል ሌላው ምናባዊ ወሬኛ ፤አርቲስቶች ለተባሉትማ ሰጡ የሚባለው ሲሰማ ጆሮ ጭው ያሰኛል ሰውየው ከተራው ህዝብ ጋር አብረው ለመሆን ችግር እንደሌለባቸው ግን እኛም በርቀት ታዝበናል።

ዛሬ ስለ ሼህ አላሙዲ ልናነሳ የተገደድነው ዋናው ፍሬ ነገር ሸሁ ቀደም ሲል የኢትዮጵያን ህዝብ አጥንትና ሃብቱን የጋጠውን የብዙ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈውን የትግሬን ነጻ አውጭ ሽፍታ በጎደለው ክፍተት እየሞሉ ምርኩዝ ሁነው ሃገርና ወገን ላይ የደረሰውን በደል  ዛሬ ላይ ዜጎች እንዳልረሳነው ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ በአንድ ወቅት በግላጭ ዝንብ ይሁን ንብ የህወአትን መገለጫ መለያ ቲ ሸርት ለብሰው ህዝብን በመናቅ የሰጡትን አስተያየት ዛሬም ከዜጎች አእምሮ አልተፋቀም። ከአጋዚ አለቆች ከነስብሃት ነጋ ጋር በአንድ አስርሽ ምችው ፓርቲ ላይ ንፋስ እንዳይገባቸው ተገጣጥመው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲያላግጡም አይተን ታዝበናል። ሸሁ ከአረመኔዎቹ ከነ ስብሃት ነጋ፤መለስ ዘራዊ፤አርከበ እቁባይና መሰል የትግሬ ፋሽስቶች ጋር በፌሽታ ላይ  ፍቅር በፍቅር ሁነው ሲፍነቀነቁ በተለያዩ ምስሎች ተቀርጾ ተለቋል፡፡ ዛሬ እነዛ ለሰማይና ለምድር የከበዱ አረመኔ የትግሬ ገዥዎች ከተደበቁበት ተበለሻሽተው ከጎሬያቸው በመከላከያ ሃይሉ ተጎትተው ሲወጡ ነገሮች ባሉበት እንደማይቀሩ ለሸሁ ትምህርት ይሰጣል ብለን እንገምታለን። ምድሪቱ የምታስተምረን ግፈኞች የሃጢያታቸው ስበት ሲያመዝን እንደዚህ ተዋርደው በህዝብ አይን መበላታቸው የታሪክና የተፈጥሮ ሀቅ ይሆናል በነሱም ምክንያት ወዳጆቻቸው ልጆቻቸው አብረዋቸው የሰሩ ሁሉ እንዳቀረቀሩ ይቀራሉ። እንግዲህ ካለፈው በመማር ዛሬም እንዲህ ዜጋን ልብ የሚያደማ ነገር በድጋሚ ከኦሮሙማ ግፈኛ ሹሞች ተዳብለው አገርን የሚጎዳ ነገር ይሰራሉ ብለን አንገምትም። ነገር ግን የተፈጥሮን ህግ ንቀው የኢትዮጵያን አምላክ ተጋፍተውና ታብየው በፍቃዳቸው ከሄዱ የህዝብ ሃዘን ያደረሰውን ለመታዘብ በቂ እድል የተሰጣቸው ይመስላል

አላሙዲ ኢትዮጵያን ይወዳል የሚሉ አሉ እውነት ከሆነ እናመሰግናለን ነገር ግን አፋኝ ስርአቶችን የጎደላቸውን እየሞሉላቸው ግፍና ጭቆናን ምድሪቱ ላይ የሚያሰፍኑ ከሆነ አጥብቀን እንቃወማለን። በቀጥታና በተዘዋዋሪ የራሳቸውንና እስላማዊ የአረብ አጀንዳ ይዘው ያንን ለማስፈጸም የተለያዩ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ወንጀለኞች ጋር  በገሃድም ሆነ በስውር  የሚሰሩ ከሆን አንድ አይናችንን ጨፍነን እንመለከታለን። በመጨረሻ ግን ህዝብ አሸናፊ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ዛሬ ከትግሬዎች የቀጠለው የኦሮሙማ መንግስት ከሃገርም ከውጭም ውግዝ ካሪዮስ ሁኖ ባለበት ሁኔታ ህዝቡ ሃይል አስተባብሮ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊንደው በመንደርደር ላይ እያለ አላሙዲ ይህን ሃይል ለማቆም ያላቸውን ሃብት፤እውቅና ፤የውጭ ትስስር በመጠቀም ትግሉ ላይ ውሃ ሊቸልሱ ከሞከሩ ሁል ጊዜ የተገፋ ሃይል አሸናፊ በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ይህንን ስርአት ደግፈው ዳግም ስህተት እንዳይሰሩ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

አላሙዲ ባለሃብትና መዋእለ ንዋይ አፍሳሽ ናቸው አንድ ባለሃብት ከሚያደርገው ህጋዊ አሰራር ውጭ ከቆሸሹ በደም ከታጠቡ ነብስ ካጠፉ መሪዎች ጋር በመሆን የህዝብን ሰቆቃ ማብዛት ለክብራቸው አይመጥንም ብለን እናምናለን፡፡ እሳቸው  ሲደግፉት የነበረው የህወአት አገዛዝ ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን በደል ዛሬ ከዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በላይ ስለሚያውቁት ወደኋላ ሂዶ ማስታወስ አያስፈልግም። አዲሶቹ ገዥዎቹም ቢሆኑ ለሸሁ ቀና ልብ እንደሌላቸው ማስገንዘብ እንወዳለን። በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎች በአይሁድ ያልደረሰው ስቃይ ወርዶባቸዋል የአላሙዲም እናት ዛሬ ከወሎ ተጉዘው ወለጋ ቢሰፍሩ  የዛሬን ተውኝ ሁለተኛ አማራ አልሆንም ቢሉም መገደላቸው አይቀሬ ነበር ስለሆነም ከዚህ ስርአት ርቀታቸውን ጠብቀው ቢጓዙ መልካም ነው እንላለን።

ባጠቃላይ ሸሁ ከባለ ስልጣኖች ጋር የሚኖራችው ግንኙነት ላይ ገደብ መጣል ይኖርባቸዋል ግንኙነታቸው ፖለቲካዊ ሳይሆን ኢኮኖምያዊ መሆን ስለሚገባው እነሱ የሚያዙትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከመፈጸም መቆጠብ ያስፈልጋል። ዛሬ የአማራ ባለሃብቶች የተባረሩት፤የተቀሙት ፤ተገፍተው ዳር የደረሱት አብይ መሃመድ አበባ ውሃ የማጠጣበት   ይሄን ያህል ሚሊዮን አምጡ፤የአዳነች አቤቤን የሽመልስ አብዲሳን የልደት ቀን ለማከበር ይሄን ያህል ሚሊዮን አምጡ እየተባሉ ፍዳቸውን በሚያዩበት አገር ለሸሁ ከመንግስት የሚደረገው እንክብካቤ ጤናማ ባለመሆኑ ነቃ ብለው ምክንያቱን ሊመረምሩ ይገባቸዋል። ዶር አብይ በመጻፋቸው እንደገለጹት የሚፈልገውን ስጠው ከዛ ወደ ገደል ጨምረው እንዳሉት ሁሉ ሸሁ ቅድመ ጥንቃቄ ካላደረጉ መጨረሻው የጤና አይመስልም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሰመረ አለሙ

semere.alemu@yahoo.com

3 Comments

  1. I am sorry to say but I have to say that this man who hade made the billboard of the the TPLF/ EPRDF election symbol ( Bee) and who had made very clear that he had/has no any interest other than getting richer and richer by any means will return and will allow himself to be the billboard of Abyi ( Prosperity) for the coming so called election if it is lucky enough to survive.
    I sincerely believe that we must watch closely and seriously in order not become the victims of people who are mischievous and not trustworthy like this guy! We got so many other things to be done instead of just talking l

  2. ለምን ስለ አላሙዲን መጻፍ እንዳስፈለገ አልገባኝም።አንድ ሰው ስሌላ ሰው የሚጽፈው የሚጻፍለት ሰው ለህብረተሰብ ዕድገትና ስልጣኔ የቆመ ከሆነና ያበረከተውም አስተዋፅዖ ካለ ነው። በተጨማሪም ጥሩ የስነ-ጽሁፍ ስራዎችን ያበረከቱና ስለሳይንስ የጻፉና የተመራመሩ እንደዚሁ በመወደስ ሊጻፍላቸው ይችላል።
    ከዚህ ሁኔታ ስንነሳ አላሙዲን ለአገር ውድቀት እንጂ ለአገር ዕድገት ያበረከተው ነገር የለም ።ሼራተን ሲሰራ በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቦታቸው ተፈናቅለዋል። የሼራተንም መሠራት ለኢትዮጵያ ህዝብ የጠቀመው ምንም ነገር የለም። ሆቴሉ ብልግና የሚካሂድበት ብቻ ሳይሆን ሲአይኤና ሌላ የስለላ ድርጅቶች ከኢትዮጵያውያኖች ጋር እየተገናኙ አገር እንዴት እንደምትፈራርስ ሴራ የሚሸርቡበት ነው። አላሙዲን ከወያኔዎች ጋር የነበረውን የጠበቀ ግኑኝነት በመጠቀም በብዙ ሺህ ኪሎ የሚገመት ወርቅ እየዘረፈ ወደ ውጭ አገር የሚያወጣ ነበር። ቁጥጥር በሌለበት አገር ለአቅመአዳም ያልደረሱ ሴቶችን የሚያባልግ ነበር። የሱ ሳውድ አረቢያ መታሠሩ የኢትዮጵያ አምላክ ያዘዘው ነው።አገር ቤት ሲመለስም መታሰር ያለበት ነው። ታዲያ ለዚህ ወንጀለኛ ሰው ትልቅ ነገር እንደሰራ ለምን እንደሚጻፍለት አልገባኝም። የሚጻፍ ነገር ከጠፋ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ይቻላል። ዘሃበሻም ትምህርታዊ ጽሆፎች የሚወጡበት መድረክ መሆን አለበት። እንደዚህ ዐይነት ጽሁፍ የሰውን መንፈስ ስለሚረብሽ ባይወጣ ጥሩ ነው።

    ፈቃዱ በቀለ

  3. ዶር በፍቃዱ
    እናመሰግናለን በተረዳኸው ልክ ለሰጠኸው አስተያየት፡፡ ሲጀመር የጽሁፉ አላማ አላሙዲ ቀደም ካለው ስርአት ጋር ተጣምሮ ለወያኔ ምርኩዝ ሁኖ ያገለገለ ነው ያልነው እንጅ ያላሙዲን ገድል የሚዘክር ጽሁፍ አልነበረም፡፡ ሲቀጥልም አሁን ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ ያለፈውን ስህተቱን እንዳይደግም ማሳሰቢያ የሚሰጥ እንጅ በጀመርከው ቀጥል የሚልም አልነበረም፡፡ አላሙዲን ግለሰብ አይደለም እንደ ቢልጌት ወይም ሌሎች ቱጃሮች ከሱ ጀርባ የሚሳቡ ብዙ ነገሮች አሉ ስለ አንድ ክስተት ስናወራ ከጀርባቸው ሰዎች አሉ ፡፡ስለ ሰዎቹ ስናወራ ስለ ፖለቲካቸው፤ስኬታቸው፤ውድቀታቸው፤ወንጀላቸውን የመሳሰለውን ያካትታል ስለ አላሙዲም ስናወራ እንዲሁ፡፡

    በሆቴል ቤቱ ስለሚሰራው ስራ እንዳንተ የቀረበ መረጃና ማስረጃ ካለማግኘቴም በላይ የጽሁፌ አላማ እሱ ስላልሆነ ስለሱ መጻፍ አላሻኝም በአባዱላም ሆቴል ሆነ በሌሎች ዘራፊዎች ሆቴል ቤቶችም የሚሰራው ስራ ከሸራተን የተለይ ነው ብዬ አላማንም፡፡
    ዘሃበሻም በገጹ የሚያወጣው አካዳሚክ ጽሁፎችን ብቻ ሳይሆን ከላይ በግልጽ እንዳስቀመጠው ዜናን፤ነጻ አስተያየትን፤ጥናታዊ ጦማሮችን፤ግጥሞችን፤ጋዜጣዊ መግለጫዎችን፤ሰብአዊ መብትን ፤ከታሪክ ማህደርን፤ኢኮኖሚን፤ጤናን፤ስፖርትን የመሳሰሉ ጽሁፎች የሚወጡበት ገጽ ነው የኔም ጽሁፍ ከእነዚህ ውስጥ በአንዱ ወይም በሌላው የተካተተ በመሆኑ ሳንሱር ሊደረግበት አይገባም፡፡ እንዳንተ ሚዛኑ ያልደፋለትና ትምህርት የማያገኝበት ሊተወዉ ሲችል ሌላው ደግሞ በግንዛቤው መልካም ነው ብሎ የሚያነበውም አለ፡፡ ለማንኛውም ጽሁፉ አንተ ከተቸህበት ሃሳብ ብዙ ያልራቀ መሆኑን እያመለከትኩ ስለሚወጡት ጽሁፎች ዝርዝር ለዘሃብሻ ኤዲቶሪያል ቦርድ ብንተወው መልካም መሰለኝ ባሁኑ ጊዜ የረጅም ጊዜ ልምድ አላቸውና፡፡ የትኛው የጽሁፉ ክፍል እንደረበሸህ ግን ሊገባኝ አልቻለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

192717
Previous Story

እስክንድር ድርድር ከመንግስት ጋር/አስደንጋጩ የዶላር ከአዲስ አበባ መጥፋት

192735
Next Story

ፊ/ማ ብርሃኑ ጁላ ለአብይ ቁርጡን ነገሩ | የሰራዊቱ አዛዥ በጄ/ል ተፈራ እጅ ወደቀ | ፋኖ ባልታሰበ ሁኔታ ወልድያ እና ደሴ ገባ | 4ተኛ ቀን ያስቆጠረው ከባዱ የጎንደር ትንቅንቅ

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

Fekadu ethiopian Point

አረንጓዴ ልብ፣ ጥቁር ልብ፣ ሰይጣናዊ መንፈስ!

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) (መስከረም 21፣ 2017) October1,  2024) በጀርመን፣ በፍራንክፈርት አማይን በሚባል የታወቀ የፋይናንስና